cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ጊዜ ቤት

በግጥም ለመርካት፣በወግ ለመፍታታት ቤተሰብ ይሁኑ!ያላችሁን አስተያየት በማንኛውም ጊዜ በውስጥ መስመር @gize_yayeh ላይ አስቀምጡልኝ።ሸሎም ለአቢሲኒያ!

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
234
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
ቡና ትዳር ................ ትዳሯ ቡና ነው፣ ጭሳጭስ ማድበቅበቅ፣ ለመጣ ለሄደው፣ ጀበና መዘቅዘቅ። ከጥቁሩ ቡና ጋር፣ ፈገግታ ስታድል፣ ያያታል... ግን አያወራትም፣ ቡናዋንም ቀምሶ፣ "ግሩም ነው" አይላትም። በጥርሷ መገለጥ፣ ልቧን እንዳገኙት፣ እንደሚሰማቸው፣ የቆረፈደ ቀልድ፣ የማያልቅባቸው፣ ስር ስሯ እንደሚሉት፣ ገላ እንደተራቡት፣ አይጎነትላትም፣ ብቻ ከሩቅ ሆኖ፣ ከሰል ያጠቆረው፣ እጇ ላይ ያፈጣል። ወዲያው... አንድ ድምፅ ይመጣል። "እማዬ..."  የሚል ቃል፣ ባልደረሱ እጆቹ፣ አቅፏት እስከ ነፍሱ፣ "ራበኝ" ይላታል፣ በዛለ እስትንፋሱ። ራበኝን ስትሰማ፣ ቀልድ አያስቃትም፣ ትሄዳለች የትም፣ ቁራሽ ልታመጣ፣ ይህንን ከሩቅ ሲያይ፣ ብዕሩን አወጣ። እንዲህ ከተበላት... "ለስላሳ ጣቶቿ፣ እንሾሽላ አልሞቁም፣ ወይ በዘመን ቅባት፣ አያብረቀርቁም። ብቻ ግን አያርፉም፣ እሳት የሚበላው ፒያኖ ሲመቱ፣ ጥቁር ቅኝት ያለው ፣ የሚያሰክር ምቱ። ፒያኖው ድምፅ አለው፣ ትርታ 'ሚጨምር፣ በእሳት ካልታጀበ፣ ዜማው የማይሰምር።" ማዕዶት ያየህ
Show all...
10👍 5
Photo unavailableShow in Telegram
ምናል ብትተነፍስ ቃል አፏን ባይጨንቀው ገዷ በኔ እንደሆን ከመሸ ልታውቀው ከመሸማ ወዲያ... የእግዜር በረከቷን ዝሟ ከነጠቃት አለማወቅ በሏት... ለቀትር ላይ መና በእኩለ ሌት መንቃት ምናል ብትነግረኝ አንዴ ብትረታ የፃፈ ሊቅ ላይኖር ፍቅር የሴትን ትጥቅ ቀድሞ እንደማይፈታ ከሰው እንዳልሰራት አለት ልብ እንዳላት "አልወደድኩም"ብላ ስትፋጭ ከነፍሷ ንገሯት በማርያም... ኩነኔ እንደሌለው ቀድማኝ መተንፈሷ እኔ... አንድ ብኩን አዳም... አልጣለችኝ ብዬ ኩራት ባልዛመድ አልነግራት 'ሚለጉም ባያስሩብኝ ገመድ የ"አልተረታሁም" ቃል በሽቆኝ ምፅድቋ ካልጠፋ የፍቅር ቃል 'ሚቸግረኝ ቋንቋ ምናል ብትሸነፍ... 'ወደድኩ' ላይቀስፋት... ሲሳይ መግፋት እንጂ ወዶ መንበርከኩ የለውም ግርፋት ታሳዝነኛለች...ንገሯት... ማዕዶት ያየህ(ዘማርቆስ) @gize_yayeh 19/10/15 ዓ.ም.
Show all...
🥰 6
Photo unavailableShow in Telegram
6
ገጣሚ: ሚኪያስ ፈይሳ አንባቢ:ማዕዶት ያየህ ድምፅ ጥይት ሆኖ ቢገድል አዳሜ አልቆልሽ ነበር😁
Show all...
👏 4 1🔥 1😁 1
ፀሀፊና አንባቢ : ማዕዶት ያየህ (ዘማርቆስ) @gize_yayeh
Show all...
👏 3
ወገን...የሀሳብ ድርቅ ታውቁ የለ?የዝህችን ወግ ቀጣይ ክፍል እንዳልጥፍ የሀሳብ ድርቅ ግምኛ መቶኛል!ብዕር-ደፈር የሆናችሁ እስቲ በሞቃችሁ መንገድ ፈጣጥሟትና የድርቅ ማዕቀቡን አንድየ ሲያነሳልኝ እኔ የምቋጫት ይሆናል።እስኪ ለመቋጨት ሞክሩ ... የሞከራችሁትን @gize_yayeh ላይ አስቀምጡልኝ።የተሻለ የሚባለውን እዚህ ቻናል ላይ የማጋራችሁ ይሆናል። እግዚአብሔር ይስጥልኝ! አላህ ይባርካችሁ! ማዕዶት ያየህ(ዘማርቆስ) @gize_yayeh 03/10/2015 ዓ.ም.
Show all...
👍 2
"እንዴት አደሩ እትዬ?ማታ...ኮ አምሽቼ የምጨርሰው ስራ ኖሮኝ ሰዓት ስለሄደብኝ እንዳልረብሻችሁ ብዬ እዛው አድሬ ነው" "ኧሯሯሯሯሯ!እና ስልኩ ቢከፈት ምን ይላል አደራሽ?...በዚህ በከፋ ዘመን እንደው ሰውስ ያስባል አይባልም?ጅብ በመውጫው አንችን ፍለጋ እንጉለሌ ልህድ?" "ይቅርታ በጣም" "የሆነው ሁኖ...ምን ልትገዥ ነው?" ብለው እጅ ከፉ እንደተያዘ ሌባ ያፋጥጡሻል። "እ...እንቅልፉ ነው መሰል ትንሽ ራሴን አሞኛል ማስታገሻ ልግዛ ብዬ" "እህህህህም ነው?በይ...ደህና ዋይ"ብለውሽ ከፋርማሲው ሲወጡ የዘመናት ሀጥያትሽ የተፋቀልሽ ያህል ይቀልሽና "እፎፎፎፎፎፎይ!"ትያለሽ በሆድሽ።የምትገዥውን ገዝተሽ ስትወጪ አከራይሽ ፋርማሲው በር ላይ ቆመዋል።ስታያቸው ስቅቅ ብለሽ ታልፊያቸዋለሽ።ከማለፍሽ ወደ ፋርማሲው ድጋሚ ሲገቡ ታይና ጠጋ ብለሽ ለማየት ትሞክሪያለሽ። "የኔ ዓለም...እንደው አሁን የወጣችቱ ልጅ የገዛችው ክኒና የምንድነው?" ይሉታል መድሀኒት ሻጩን። "ምነው ማዘር ችግር አለ?" "ኧረ የለም ዓለሜነህ!...አምና ቁርጥማት ያመኝ የነበር ግዜ ይኸን መሳይ ክኒና ነበር እምውጥ እንደው ሲያገረሽብኝ ግዜ ድጋምኛ ልዋጠው ይሆን ብየ ነው ...ሌላም አይደል" "ኧረ...ተመሳስሎብዎት ነው 'ሚሆን ማዘር ይሄኮ post pill ነው" "ምን pill?" "postpill....postpill ማለት..."ብሎ ማብራሪያ ሲጀምርላቸው አንቺ እቃሽን እንዲያሻክፉሽ ወደ ጓደኞችሽ እየደወልሽ ነው። ማዕዶት ያየህ(ዘማርቆስ) (@gize_yayeh) 25/09/2015 ዓ.ም.
Show all...
👍 7 1
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ዘርሽ ቢቆጠር ጉድፍ የለበትም።የጀግና ዘር ነሽ!በአባትሽ በኩል ቢኬድ ቅድመ አያትሽ የሚኒሊክ ዘብ ጠባቂ የቅርብ ወዳጅ ነበሩ።በእናትሽም በኩል ቢኬድ ምንጅላትሽ የሽምብራ ቆሬ ጦርነት ላይ የግራኝ አህመድን አሽከር በቀይ ጥይት ግራ ቂጡን ነድለውት ሲቅመደመድ ኖሮ መሞቱን አዲስ ዘመን ጋዜጣ የሆነ ጊዜ ላይ አስነብቧል። በማን እንደወጣሽ ባይታወቅም፣ዕድልሽ ይሁን ተፈጥሮሽ ግልጽ ባይሆንም፣ከአንድ ወንድ አትረጊም።ተረግመሽ ነው መሰል ከሚያጋጥሙሽ ወንዶች 25 % የሚሆኑት የጥሪ ማሳመሪያ ተጠቃሚዎች ናቸው። ልክ ስትደውይ "ወይ ሞልቶ ላይሞላ ለዚች ዓለም ኑሮ እኔ አልጨነቅም ከዛሬ ጀምሮ" የሚል መፈክር ይሁን ዘፈን ያልለየለት ብሶት ትሰሚያለሽ።(ሳትረገሚማ አትቀሪም!) ሌሎቹ 25 % የሚሆኑት ደግሞ የትንሽ ጣታቸውን ጥፍር የሚያሳድጉ ናቸው።ደህና መትረየስ እንዳነገበ ጀግና በጥፍራቸው አይን አ*ቸውን እየመነገሉ፣የከናፍራቸው ጫፍ ላይ የወጣችን ቡግር እየፈነቀሉ ቀንሽን ለሰማይ ለምድር የከበደ 'ትራጀዲ'ያደርጉብሻል።(በእርግጠኝነት ምንጅላትሽ የመቱት አሽከር ነው የረገመሽ!) 'እፎፎፎይ'ብለሽ ወደ ሌላኛው 25% ስትሮጪ መፈናፈኛ እስኪያጣ ሱሪውን የሚያስጠብብ፣ቀሪው 25% ደግሞ የሞተ ፍየል በብብቱ የያዘ እስኪመስል ድረስ አስጨናቂ ጠረን ያለው፣ላቡ ከብብቱ ስር እንደቀበና የሚወርድ ክልል-ዘለል የሆነ ፌደራላዊ ግማት ላይ ትወድቂያለሽ ። "እና እንዴት ነው ኑሮው?"ይልሻል አፉ እንደተቀየደ ፈረስ ድዱን እያሰጣ። "ደህና ነው መቸም" ትያለሽ ሰው ያገኘሽ መስሎሽ። "እናስ ተማሪ ነሽ ሰራተኛ?"ይልሻል እንዳገጠጠ አንዴ ከላይ ወደታች፣አንዴ ደግሞ ከታች ወደ ላይ scan እያደረገሽ። አንድ ቀን አልፎልሽ በፀሃፊነት ወደምትሰሪበት ድርጅት ለጉዳይ የመጣ ነጋዴ ነኝ ባይ ትተዋወቂያለሽ...ቀጠሮ ትይዣለሽ።ደሞዝሽ በፈቀደው መጠን ለመዘነጥ ትሞክሪያለሽ።ከታች እናትሽ መሰረተ-ትምህርት ሲማሩ ለብሰውት ይሄዱ የነበረውን ቀሚስ ከወገቡ አስቆርጠሽ በሰውነትሽ ልክ አሰፍተሽ ለብሰሻል።ከላይ ከሰልቫጅ ተራ በ80 ብር የገዛሻትን ቲሸርት ጣል አድርገሻል።ባለፈው ወር እቁብ ሲደርስሽ የገዛሻትን የ 200 ብር ሽቶ "ምናባቱ!ሺህ ዓመት አይኖር!"ብለሽ የግራ ብብትሽ ስር አንዴ ረጭተሻታል። የቀኙንም'ኮ ልትረጭው ነበር ግን አሰብ አረግሽና "መቸስ ከጎኑ ስሄድ አንድ ጎኔ ነው በሱ በኩል የሚሆን"ብለሽ ተውሽው።ኤታባቱ!ሺህ ዓመት አይኖር! ፀጉርሽን በ 50 ብር ካስክ አፍሪካዊ ለዛውን ታሳጭዋለሽ።ተመስገን ነው!ሰሞኑን ማበጠሪያ አይሰበርብሽም!በፈቃደኝነት የሚያፈናቅል ሽታ ያለውን ሎሽንሽን መላ ሰውነትሽን ተቀብተሻል...ለእግርሽ ግጣም ከቆራሌው የተረፈች አንዲት ክፍት ጫማሽን ግጥም ታደርጊና ትሄጃለሽ !ወደ 'ዴትሽ' ሰውዬሽም ከሞላ ጎደል ዘንጧል። "ምን ይምጣ የሚበላ?" "አንተ የተመቸህ ይሁን" ጥብስ ይታዘዝና ጠበሳው ይቀጥላል ። ጥብሱ እስኪደርስ... "እና...ደሞዜ 3000 ብር ነው አልሺኝ?" "3200" "ያው ነው...አሁን እኔ ወደዚህ ስመጣ የኮንትራት ታክሲ 200 ብር ነው የከፈልኩት" ብሎ ኩም ያረግሻል።ጥብሱ ደርሶ ከተበላ በሁዋላ "እና የቤት ኪራይ 600 ብር ነው የምከፍለው አልሽኝ?" "550" "ያው ነው 50 ብር ማለትኮ ለአስተናጋጅ የሚሰጥ 'ቲፕ' ነው" "እሱሰ ልክ ነህ"ከጥቂት ዝምታ በሁዋላ "ተጫወች እንጂ ምነው?እኔ ዝም የሚል ሰው አልወድም...የምሬን ነው!የሚያስጨንቅሽ ነገር ካለ ንገሪኝ" "ኧረ የለም!አመሰግናለሁ" "ምስጋና ስንቅ አይሆንም ...ባይሆን..." "ባይሆን ምን?" "ባይሆን ሌላ ጊዜ በደንብ ታጫውችኛለሽ እ?ሃሃሃሃሃ" በኮንትሮባንድ የገባ ሳቅ ይለቅብሻል። "እንሂድ እየመሸ ነው"ትያለሽ ሰዓትሽን አየት ታደርጊና። "ኧረ ገና ምኑን ያዝነውና!አይዞሽ እኔ ራሴ ነኝ በኮንትራት ታክሲ ቤትሽ የማደርስሽ"ብሎ ሳይሰማሽ መጠጥ ያዛል ።'አልኮል አልጠጣም' ብለሽ ለመገገም ትሞክሪያለሽ። "ምናይነቷ ናት ባካችሁ?ልንዝናና አይደል ወይ የመጣነው?እንደ ህፃን ፋንታ ልትጠጪ ነው?"ብሎ እንደምንም ቀበጣጥሮ አንድ ቢራ ያስከፍትልሻል።እየተሽኮረመምሽ መቀማመስ ትጀምሪያለሽ።ሞቅ ሲልሽ ፍርሀት ቢጤ ይሰማሽና "እየመሸ ነው ብሄድ ሳይሻል አይቀርም"ስትይ ሰዓቱን አየት ያደርግና "ሆሆሆሆ እንዴት ያለችው ላይ ጣለኝ ባካችሁ?ገናኮ 3 ሰዓት ነው...ምን የሚያስቸኩል ነገር አለ?ገብተሽ አታበስይ ምናለሽ?" "እሱስ አላበስልም...አከራዬ ደስ አይላቸውም እንጂ..." "አአአአይ ...ለዛሬ የኪራይ ቤትሽን እርሻት...እዚሁ ቆንጆ room እይዝልሻለሁ" ሲልሽ መፍራት ትጀምሪያለሽ። "ኧረረረረ አያስፈልግም ቤት እገባለሁ"ስትይ "ለማንኛውም እየጠጣሽ "ይልሽና በተቀመጥሽበት ትቶሽ ወደ እንግዳ ተቀባዪአ ይሄዳል።ከቆይታ በሁዋላ አንድ ቁልፍ ይዞ ይመጣል። "ምን...ባክሽ...' 'ሩሞቹ' ተይዘው አልቀዋል' አለችኝኮ...አይዞሽ double bed ነው የያዝኩት...መቼም የመሸበት አላሳድርም አትይም ሃሃሃሃሃ" አሁን የምር...የምር...የምር ትፈሪያለሽ።ያቺ ተቆንጥጣ ያደገችዋ...ያቺ በዘመን ግሳንግስ ቀለሟን ያደበዘዝሽው አንቺነትሽ እየተፍገመገመች "አምልጪ!...ተበላሽ! ትልሻለች። "አአአአይ....ኧረ አትቸገር እዚሁ አካባቢ አንድ ጓደኛ አለችኝ እሷ ጋር እደውላለሁ..." "ቆይ አላመንሽኝም ማለት ነው?ስታስቢው በጥብስና በቢራ የሴትን ገላ የምገዛ ርካሽ እመስላለሁ?I really feel sorry እንደዛ ካሰብሽኝ" "ኧረ...እንደዛ ማለቴኮ አይደለም...አስቸገርኩህ ብዬ ነው እንጂ!እሺ በቃ" ትይውና "እሳትና ጭድ አንድ ክፍል ውስጥ ያድሩ ዘንድ ደግ አይደለም...አንዳቸው የሌላቸው መጥፊያ ይሆናሉና " የሚለውን ቃል ጥሳችሁ አንድ ጣራ ስር ታድራላችሁ። ጧት ለሰዓታት የተቃጠልሽበት ፀጉርሽ ፈርሶ...ጋኔል ያደረባት ጃርት መስለሽ ወደሰፈርሽ ትመለሻለሽ።ወደ መዳረሻሽ ገደማ ፋርማሲ ታይና ጎራ ትያለሽ።ሰው የተባለ ፍጡር ገና ከእናታቸው ማህፀን ሳሉ ጀምሮ የማያምኑት አከራይሽን ፋርማሲ ውስጥ ስታያቸው ልብሽ በአፍሽ ልትወጣ ትደርሳለች።በተጠራጣሪ አይኖቻቸው ከእግር እስከራስሽ አብጠርጥረው ያዩሽና "አንች የኔ ዓለም የት ጠፍተሽ ነው ስታሸብሪን ያመሸሽ?"ይሉሻል።
Show all...
ይሉኝታ(ክፍል 2)   ያገኘኝ ሁሉ ሲልከኝና ሲያዘኝ ውዬ የዛለ ሰውነቴን እየጎተትኩ ቤቴ እገባለሁ።እናቴ የቡና እቃዎቿን እያቀራረበች በመሀል ቀና እያለች ስታስተውለኝ ትቆይና "አዋጥተው እንደገዙት መጋዣ ሲጭኑህ ይውላሉ አይደል?እንደው እምቢ አልፈጠረብህም አቡሽ?እምቢ አትልም?" "ይረግሙኛል ብዬ ነውኮ" "ኤዲያ!የረገሙህስ እንደው?አንድ ሳህን  ጤፍ ይገዙልህ መሰለህ?አዬ አለመታደል!እንዲህ እብን ሆነህ ትቀር?አድገሀልኮ ደስታ!18 ሞላህኮ!ልጅ አትባል ከንግዲህ" ስትለኝ በመሀል አንድ ድምፅ አቋረጣት "እንዴት ውላችሁዋል እናንተ?"እያሉ ወደውስጥ ዘለቁ እትየ አትጠገብ።እኚህን ሴትዮ ሳያቸው ያጥወለውለኛል።በነገር ሰው ሲወጉ ወደርም የላቸው።በቀደም ከመሸ ተልኬ ስወጣ ከማህሌት(የሰፈሬ ልጅ) ጋር ሱቅ ተገናኘንና የሆነ ያልሆነውን እያወራን ስንራመድ እትየ አትጠገብ በዛ ረጅም ቁመታቸው ሀውልት መስለው ከፊትለፊታችን ተገነጨሩ።ማህሌት ትከሻ ላይ ጣል ያረኩትን እጄን በፍጥነት አውርጄ ሰላምታ አቀረብኩላቸው።በውሉ ያልተሰማኝን ነገር አልጎምጉመው ሄዱ።በነጋታው ቤታችን መጡና "እንዴት ውላችሁዋል ቤቶች?"አሉ በጎንዮሽ እያገረመረሙኝ።ወዲያው ወደኔ ዘወር አሉና "ደስታ...ምነዋ ዛሬስ የጋሽ አለሙ ልጅ የት ሄዳ ነዋ?"አሉኝ።በአስማት እንዳደረቁኝ ሁላ ቀጥ ብዬ ቀረሁ።አባቴ "ኧ?ደሞ የጋሽ አለሙ ልጅ እዚህ ምን ታረጋለች ?" ጥያቄአዊ አስተያየቱን እያነጣጠረብኝ። "አብረው አያጠኑም እንዴት?ትናንት እዚህ አምሽታ ስትወጣ ያየሁዋት መስሎኝ"ብለው እርርርፍ!ምን ያልተመኘሁላቸው ክፉ ነገር አለ?ሙሴ በበትሩ ለድድ ሩብ ጉዳይ የሆነ ጥርሳቸውን ቢያረግፈው ደስታዬ! ኢያሱ ያቆማት ፀሀይ እንትናቸውን ለምች ትስጠው!ሌላ ክፉ አልመኝም! "ኧረ ማታኮ ሱቅ ተገናኝተን እየሸኘሁዋት ነው ያዩን እዚህ አላመሸችም"አልኩኝ እየተርበተበትኩ። እናቴ 'ለዚህም ደርሰሀላ?!'አይነት አስተያየት አየችኝ።እየተጎተቱ መጥተው የነገር መርዛቸውን አርከፍክፈውት ሄዱ።ከዛ ወዲህ ቤታችን ሲመጡ በጤና አይመስለኝም።እስኪወጡ ሱባኤ እይዛለሁ።ዛሬ ደግሞ ምን ሊሉኝ ነው እያልኩ ስብሰለሰል "ደስታየ...ነገ ትምህርት አለህ?"አሉኝ። ይቀጥላል ማዕዶት ያየህ(ዘማርቆስ) (gize_yayeh) @wegoch @wegoch @paappii
Show all...
👍 5 2
ይሉኝታ እግዜሩ ያለ የሌለ አቅሙን ሙጥጥ አድርጎ የሰራውን ይሉኝታ ሁሉ የሆነ ጊዜ ላይ መሸከም ከብዶት ሳለ ወደ ቀራንዮ ጫፍ መስቀሉን ሲጎትት ቀረብ ብሎ እንዳገዘው ምስኪን እኔም ጠጋ ብዬ"አባት ሆይ! ይህን ሁሉ ይሉኝታ ብቻህን?ባይሆን ትንሽ ላግዝህ !"ብዬ ያንን ለምድር ለሰማይ የከበደ ይሉኝታ ተቀበልኩት።እሱም በይሉኝታ መቅረቤን አይቶ "ላለው ይጨመርለታል"በሚለው መርህ በእገዛ ሰበብ የተቀበልኩትን ይሉኝታ መልሶ ሳይወስድብኝ ቀረ።እነሆ እኔም ከዛ ወዲህ ትልቅ ትንሹ ሲያሻው እንደ ስጋጃ እየረገጠ፣ሲፈልግ እንደማስቲካ እያላመጠ፣ባስ ካለም እንደ እንቧይ እያፈረጠ በይሉኝታዬ እኔው ላይ ዳንኪራውን ይመታል። "ልጅ ደስታ!እስቲ ና ወዲህ" ይሉኛል እማ አልጣሽ ከመንገዱ ጫፍ ወገባቸውን ይዘው ይቆሙና። እማ አልጣሽን ሳያቸው አስማተኛ አሮጊት ይመስሉኛል።በፈገግታቸው ተሸፍኖ ያለውን ከባድ ቁጣ ከእግዚአብሔር በላይ ሳልፈራው አልቀርም።እንደው አንዲት ነገር አዝዘውኝ እምቢ ብላቸው ፈገግ ያለ ገፃቸውን በቅፅበት ክስክስ ያደርጉና በቅርባቸው ያለ ጭራሮ ቢጤ አንስተው ድግምት ነገር እያነበነቡ መሬቱን ጫር ጫር ቢያደርጉት ሽንቴን ልሸና ምናምኔን አውጥቼ ባንከፈረርኩበት እንደ እንጨት አድርቀው የሚያስቀሩኝ ይመስለኛል።ወይ ስፈራቸው!🙆 "አቤት እማ አልጣሽ" እላለሁ አጠገባቸው ስደርስ። "ደስታየነህ...እንደው መቸም አንዴ ሲፈጥርህ የአሮጅትና የሽማግሌ መጫወቻ ሁን ብሎሀል...አንተም ጣድቅ ነህ መቸም አልታዘዝም አትልም...እንደው እሱ መድሀኔዓለም ምቀኛህን ውጋት ይዘዝበት!" "አሜን እማማ" "እንደው ያችን እላይ መንደር ያለችዋን አትጠገብን አወቅሀትም አይደል?" "እትየ አትጠገብ የጋሽ ባህሩን ባለቤት አይደል?" "እ...የባህሩ ምሽት!ሰልስትና እለታ ቸግሮኝ 50 ሳህኔ ማሽላ ተበድሬአት ነበር...አሁን የሻለቃ(ሻለቃ ማለት በደርግ ጊዜ በውትድርና ያገለግል የነበረ ባለቤታቸው ነው።) ጡረታ ሲመጣ ሸምቸ መግባቴ ነው...ንስማ አድርሰህላት ና ጀታየነህ እመርቅሀለሁ"አሉኝ እግራቸው ስር በማዳበሪያ ታስሮ ወደተቀመጠው እህል እያዩ።የእትዬ አትጠገብን ቤት ርቀት ሳስብ ማዳበሪያው ገና ሳልሸከመው ደከመኝ።በመንገዴ የማገኛት ክፉ አቀበት ከጦሳ ተራራ ገዝፋ ብትታየኝም 'እምቢ' ግን አልልም።ይሉኝታዬን ለማን ሸጬው? እንደፈረደብኝ ያንን በግምት 65 ኪሎ የሚሆን ማዳበሪያ ተሸከምኩትና መንገዴን ጀመርኩ።እትየ አልጣሽ ከሁዋላዬ ሲመርቁኝ አልፎ አልፎም በሞኝነቴ ሙድ ቢጤ ሲይዙብኝ ይሰማኛል። "ተባረክ ደስታየነህ ብሩክ ሁን!አሁን የማን ልጅ እሽ ብሎ ይታዘዛል በዚህ ዘመን?እድሜ ይስጥህ!ወገብህን ተውልቃት፣እጅህን ተቁርጥማት ይሰውርህ!"ይሉና ደሞ ድምፃቸውን ዝቅ አድርገው "አይይይ እንደው መድሃኔዓለም!እንደው እንዲህ ማንም የሚጭነው አህያ ሆኖ ይቅር!ኧረ አህያስ ሲበዛባት ትለግማለች..." ሲሉ ከነሸክሜ ዞር ስል እንደገና ድምፃቸውን ሞቅ ያደርጉና "እንጀራ ይውጣልህ ደስታየነህ!ምቀኛህን እግሩን ያልምሸው የኔ ዓለም!ውለህ ግባልኝ ክፉ አይንካህ!" ይሉኛል። ማዕዶት ያየህ(ዘማርቆስ) (@gize_yayeh) 17/07/2015 ዓ.ም.
Show all...
6