cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የተሃድሶ አገልግሎት በአሰላ

፦በእዚህ ገፅ ፦የስብከታችን ዋና እና የአምልኳችን ዋና የሆነውን ክርስቶስ እየሱስን መግለጥ፣ መስበክ ፦እንዲሁም የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶችን ያገኛሉ ፦ጥዑመ ያሬዳዊ ዝማሬዎችን ያገኛሉ ፦የበሚለቀቁት ትምህርቶች ላይ ጥያቄ፣ሀሳብ ካልዎት .....መጠየቅ ይችላሉ 👉 @Nigaaat @bibi_son

Show more
Advertising posts
199Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር የተናገረበት የመጨረሻው"የፍቅር ድምፅ" ነው ሌሎች ድምፆች ( የአባቶች ) ይኼንን የፍቅር ድምፅ የሚገልጡ ብቻ ናቸው ! ይኼንን ድምፅ መስማት ይኹንልን 🙏
Show all...
የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ምልከታ (St. John chrysostom's  observation )  በጥንቲቷ ቤተ ክርስቲያን የቍስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳስ የነበረው ዮሐንስ አፈወርቅ (John chrysostom ) ቅዱሳን መጽሐፍት በግልጥ የሚያትቱትን የክርስቶስ አስታራቂነት,ሊቀ ክህነት ለማስገንዘብ እንዲህ ይጠይቃል .... "ከእርሱ( ከኢየሱስ)  በቀር ራሱ ብቻውን ኃጢያት ማሥተሰረይ የሚችል የታመነ አስታራቂ ማነው ? ለማስታረቅ ኃጢያትንስ ለማስተሰረይ ያቀረበው መሥዋዕትስ ምንድነው?" (ሃይማኖተ አበው, ዘዮሐንስ አፈወርቅ ክፍል 2, ምዕራፍ 82, ቁጥር 14) ከክርስቶስ ውጪ አማላጅ አስታራቂ ሊቀ ካህን መካከለኛ እንዳላችሁ የምታስቡ ወገኖች : አሉን ያላችኋቸው ሊቀ ካህናት  ኃጢያትን ማስተሰረይ ችለው ይሆንን ?? ያቀረቡትስ መስዋዕት ምን ይሆን ? " የሚል እንድምታ ያለው  መጠይቅ ነው  ..መጠይቁ ተገቢ እና አሁንም መጠየቅ ያለበት ነው ! በዚህ አዕላፉ አዕላፍ "አስታራቂ?" አንግቦ በሚኳትንበትም ዘመን የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን ጥያቄ ደጋግመን እንጠይቃለን "ከእርሱ( ከኢየሱስ)  በቀር ራሱ ብቻውን ኃጢያት ማሥተሰረይ የሚችል የታመነ አስታራቂ ማነው ? ለማስታረቅ ኃጢያትንስ ለማስተሰረይ ያቀረበው መሥዋዕትስ ምንድነው?" እርሱ [ኢየሱስ] ግን 🛑 ባሕርያችንን ባሕርይ አድርጎ #ሊቀ ካህናት #( አስታሪቂ ) ሆነን እንጂ ስለ እኛም ሥጋውን መሥዋዕት አድርጎ ወደ አባቱ አቀረበ : እንጂ በታመመበት በሥጋው ለርሱ ገንዘብ ለመሆን አበቃን !   ሃይማኖተ አበው, ዘዮሐንስ አፈወርቅ ክፍል 2, ምዕራፍ 62, ቁጥር 16) 🛑ከዚህም በኃላ የምናምንበትን #አስታራቂ ሐዋሪያ እርሱም አብነት አድርጉት አለ አብ : ከወዲያ ዓለም ወደዚህ ዓለም ስለ ላከው ሐዋሪያ አለው ስለ አመንብት በጎ ስራ ለመስራት የምንቀና ደግ ወገን አድርጎ ገንዘብ አደረገን : ለእኛ #ማልዶልናልና የምናምንበት #ሊቀ ካህነት ( አስታራቂ ) ነው  !!! (ሃይማኖተ አበው, ዘዮሐንስ አፈወርቅ ክፍል 2, ምዕራፍ 63, ቁጥር 26) 🛑ክርስቶስ ስጋውን መስዋዕት አድርጎ  አቀረበ #ሊቀ ካህናታችን ነውና ወደ እርሱ ስላቀረበው በስልጣኑ ስለ አሳረገው ስለ ስጋው : ስለ ደሙ  ወደ እርሱ መቅረብ ከተቻለው ከዚህ መስዋዕት የተነሳ አብ አደነቀ ( ዕብ 10 : 1 - 15,) (ሃይማኖተ አበው, ዘዮሐንስ አፈወርቅ ክፍል 23, ምዕራፍ 66, ቁጥር 23) በአጠቃላይ ....ከሰው መካከል ሊቤዥ ሀጢያትንም ሊያተሰረይ የሚችል አንድም እንኳ ስላልነበረ.. አካላዊው ቃል (እግዚአብሔር ወልድ) - ቃልነቱ ሳይለወጥ ስጋ ሆኖ ,የሰውነትን ባሕርይ ተገንዝቦ ( ከኃጢያት በቀር) #ራሱንም( ደሙን, ስጋውን) ንጹህ መስዋዕት አድርጎ አቀረበ ! በዚህም በእግዚአብር አብ እና በእኛ መካከል ያለውን የጥል ግድግዳ አፍርሶ  ከአብ ጋር አስታረቀን( አማለደን) , በርሱም #የኃጢያት ስርየት ሆኖልናል ! በምድር ላይ ካሉት ስጋ ለባሾች, በሰማይ ካሉ  መላዕክቶች መካከል ይሄንን ያደረገ ማን ነው ? የኃጢያት ዕዳ በመስቀል የከፈለ? ቅዱስ ደሙን, ክቡር ስጋውን ለመሰዋዕት አቅርቦ አብን ደስ ያሰኘ ያስታረቀንስ ማን ነው ??? ማንም የለም!! .. ከ ኢየሱስ በቀር.... 🗣ወኮነ አራቂ ለአዲስ ኪዳን                                  ሊቀ ካህናት ኢየሱስ🙌 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 🙏
Show all...
1ኛ ዮሐንስ 5 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁰ በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን ሁሉ በልቡ ምስክር አለው፤ ማንም እግዚአብሔርን የማያምን ሁሉ እግዚአብሔር ስለ ልጁ የሰጠውን ምስክርነት ስላላመነ ሐሰተኛ አድርጎታል። ¹¹ ምስክርነቱም ይህ ነው፤ እግዚአብሔር የዘላለምን ሕይወት ሰጠን፤ ይህም ሕይወት ያለው በልጁ ነው። ¹² ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም። … ¹³ በእግዚአብሔር ልጅ ስም የምታምኑ እናንተ፣ የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ ይህን እጽፍላችኋለሁ፤ 🔴 በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅነት ፣ ቤዛነት ፣ መካከለኝነት የምታምኑ ሆይ ደስ ይበላችሁ " የዘላለም ሕይወት " አላችሁ 🔴 በክርስቶስ ኢየሱስ የማታምኑ ወይንም ከሌሎች ጋር ተቀላቅሎ የመስቀሉ ስራ የደበዘዘባችሁ ... ሁሉ ' ሌላ በር ፣ ሌላ መንገድ ፣ ሌላ ሕይወት ስላሌለ ወደ እርሱ መምጣት ይሁንላችሁ 🙏
Show all...
እግዚአብሔር እና ሰው የታረቁበት "የእርቅ ደብዳቤ " ስግው ቃል ፣ አምላክ-ሰው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ! እግዚአብሔር አብ ከክርስቶስ ኢየሱስ ውጪ ለዓለም የላከው " የእርቅ ደብዳቤ"  በፍጹም የለውም ! ነገር ግን ስለዚህ የዕርቅ ደብዳቤ አጥብቀው የሚናገሩ ሌሎች ደብዳቤዎችን ልኳል እነኚህም ቅዱሳት መጻሕፍት የተካተቱ ናቸው   ! የተጻፈው ቃል ' ስለ አካላዊው ቃል " ይተርካል ❤
Show all...
#ስንቶቻችን ነን በእግዚአብሔር ዘንድ ለኛ ርስት እንዳተመደበልን  ምናቀው ? #የተመደበልንን ርስት ለመቀበልስ ምን ያክል ዝግጁ ነን ? #ምን ያክልስ ብቁ ነን ? ““አንተ ግን እስከ ፍጻሜው ድረስ ሂድ፤ ታርፋለህ፤ በቀኖቹ መጨረሻም ተነሥተህ የተመደበልህን ርስት ትቀበላለህ።””   — ዳንኤል 12፥13 (አዲሱ መ.ት) https://t.me/ELI_ADONAI “ስለዚህም የተጠሩት፣ ተስፋ የተሰጠውን የዘላለም ርስት እንዲቀበሉ ክርስቶስ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው፤ በመጀመሪያው ኪዳን ሥር በነበሩበት ጊዜ ከሠሩት ኀጢአት ነጻ ለማውጣት ቤዛ ሆኖ ሞቶአልና።”   — ዕብራውያን 9፥15 (አዲሱ መ.ት) እግዚአብሔር ይመስገን!!!! join us https://t.me/ELI_ADONAI
Show all...
የተሃድሶ አገልግሎት በአሰላ

፦በእዚህ ገፅ ፦የስብከታችን ዋና እና የአምልኳችን ዋና የሆነውን ክርስቶስ እየሱስን መግለጥ፣ መስበክ ፦እንዲሁም የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶችን ያገኛሉ ፦ጥዑመ ያሬዳዊ ዝማሬዎችን ያገኛሉ ፦የበሚለቀቁት ትምህርቶች ላይ ጥያቄ፣ሀሳብ ካልዎት .....መጠየቅ ይችላሉ 👉 @Nigaaat @bibi_son

Show all...
ስብሐት ለክርስቶስ ❤

ኢየሱስ ክርስቶስ ብሉይ ኪዳን ባመስጥሮ ,ሀዲሱ ኪዳን ደግሞ በገሀድ የሚተርኩት የቅዱሱ ቃል አማናዊ ግልጠት ነው!!! .... በዘመን መጨረሻ እግዚአብሔር የተናገረበት እንከን የለሽ ንፁህ መስዋዕት !!! በሞቱ ሞታችን ሞቷልና, በህይወቱ ህይወታችን ኖሯልና , በደስታ ስብሐት እንለዋለን ❤ @Nigaaat

የኢየሱስ ክርስቶስ ስሞች #ስም  የማንነት፣ የባሕሪ፣ የተግባር መገለጫ ሆኖ ያገለግላል፡፡ የእግዚአብሔር ወልድ ሥጋ በመሆኑ ቅድመ ዓለም ከነበረው መጠሪያ ውጪ በበርካታ ስሞች ተጠርቶአል፡፡ 1. ኢየሱስ (ማቴ 1፡16፡21) እግዚአብሔር ወልድ ሰው ሆኖ ሲወለድ የተሰጠው ስም ‹‹ኢየሱስ›› የሚል ነው፡፡ ኢየሱስ ማለት ‹‹እግዚአብሔር ደኀንነት›› (አዳኝ) ማለት ነው፡፡ ኢየሱስ የአዳኝነት ስሙ ነው፡፡ 2. አማኑኤል (ኢሣ.7:14፤ ማቴ 1:23) እግዚአብሔር ወልድ ሰው በመሆኑ ከተሰጠው ስሞች ውስጥ ሌላው ደግሞ ‹‹አማኑኤል›› የሚል ነው፡፡ ‹‹አማኑኤል›› ማለት ‹‹እግዚአብሔር ከእኛ ጋር›› ማለት ነው፡፡ ይህ ስም እግዚአብሔር ወልድ እግዚአብሔርና ሰውን ለማስታረቅ መካከለኛ ሆኖ የመጣበትን አመጣጥ ያመለክታል (1ጢሞ 2:5፤ዕብ12፡ 24)፡፡ 3. ክርስቶስ (ማቴ 16፡16፤ 11፡1-6) እግዚአብሔር ወልድ ሰው በመሆኑ ከተሰጠው ስሞች ውስጥ ሌላው ስም ደግሞ ‹‹ክርስቶስ›› የሚል ነው፡፡ እርሱ በዕብራይስጥ ‹‹መሲህ››፣ በግሪኩ ደግሞ ‹‹ክርስቶስ›› ተብሏል፡፡ መሲህ ወይም ክርስቶስ ማለት ‹‹የተቀባ›› (የተሾመ) ማለት ነው፡፡ ይህ ስም በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ለመግባት፣ የመዋጀትንና የማስታረቅን ተግባር (አገልግሎት) ለመፈጸም መሾሙን ያመለክታል ፡፡ 4. ጌታ (ሐዋ.2፡ 36፤ ሮሜ 10፡9፤ 1ቆሮ 12፡3፤ ፊልጵ 2፡11) እግዚአብሔር ወልድ ሰው በመሆኑ ከተሰጠው ስሞች ውስጥ ሌላኛው ደግሞ ‹‹ጌታ›› የሚል ነው፡፡ ጌታ የሚለው ስያሜ የክርስቶስን ከአብ ጋር አቻ ንግሥና ያለው መሆኑን ያመለክታል፡፡ 5. የሰው ልጅ (ዳን 7፡13-14፤ ማቴ 19፡28፤ ማር 10፡45) እግዚአብሔር ወልድ ሰው በመሆኑ ‹‹የሰው ልጅ›› ተብሎ መጠራቱ በእርግጥ ፍጹም ሰው መሆኑን (የመጨረሻው አዳም፤ ሁለተኛ ሰው) መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ 6. የእግዚአብሔር ልጅ(ዮሐ 3፡16-17፤ ማቴ 26፡62-66)ይህ መጠሪያ ስም ኢየሱስ ክርስቶስ ለዘላለም የእግዚአብሔር ‹‹አንድያ ልጅ›› (አንድና ብቸኛ ልጅ) መሆኑን ያመለክታል፡፡ የተሃድሶ አገልግሎት በአሰላ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 ይ🀄️ላ🀄️ሉን https://t.me/ELI_ADONAI https://t.me/ELI_ADONAI 👆👆👆👆👆👆👆👆👆
Show all...
የተሃድሶ አገልግሎት በአሰላ

፦በእዚህ ገፅ ፦የስብከታችን ዋና እና የአምልኳችን ዋና የሆነውን ክርስቶስ እየሱስን መግለጥ፣ መስበክ ፦እንዲሁም የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶችን ያገኛሉ ፦ጥዑመ ያሬዳዊ ዝማሬዎችን ያገኛሉ ፦የበሚለቀቁት ትምህርቶች ላይ ጥያቄ፣ሀሳብ ካልዎት .....መጠየቅ ይችላሉ 👉 @Nigaaat @bibi_son