cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የቅዱሳን ታሪክ

ማር16:16፤ያመነ፡የተጠመቀም፡ይድናል፥ያላመነ፡ግን፡ይፈረድበታል

Show more
Advertising posts
226
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

📘🌹#ቅዱስ_ይምርሃነ_ክርስቶስ_ማለት⁉🌹 ♨☞••ወር በገባ በ19 ታስቦ የሚውለው ንግሥናን ከቅድስና አስተባብሮ የያዘ የቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ ታሪክ፡፡☞ይምርሃነ ክርስቶስ የቅድስና ማዕረግ ከተሰጣቸው ከዛጉዬ ሥርወ መንግሥት ነገስታት አንዱ ነው፡፡ ☞የነበረበት ክፍለ ዘመን ከ10ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጨረሻ እስከ 11ኛውመቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ድረስ ነው፡፡ ☞ይህ ማለት ከ939-1036 ዓ/ም ሲሆን አባቱ ግርማ ስዩም ይባላል፡፡ ☞በእግዚአብሔር ፈቃድ በተነገረ ትንቢት መሠረት ነሐሴ 19 ተፀንሶ ግንቦት 19 ተወለደ፡፡ ☞የሰው ልጆችን በወንጌል ወደ ክርስቶስ መንግሥት ይመረልና ስሙን ይምርሃነ ክርስቶስ ብለው አወጡለት፡፡ ☞ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ ግንቦት 19 ቀን ሲወለድ ወደ ምስራቅ ዞሮ አምላኩን ያመሰገነ ሲሆን ቤቱም በብርሃን ተሞልቶ ታይቶ አዋላጆቹን ሁሉ አሰገርሟል፡፡ ☞እርሱ ገና ሳይወለድ በፊት አጎቱ ጠንጠውድም በንግሥና ላይ ሳለ ከአንተ በኃላ የሚነግሠው ይምርሐነ ክርስቶስ የሚባል ሰው ነው ተብሎ ሲነገረው እንዲህ የሚባል ሰው በቤተ መንግሥት አለን? በማለት ቢጠይቅ እንደ ነቢዩ ኤርምያስ ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ የተመረጠ ሕፃን እንደሚወለድ ነግረውታል፡ ☞በዚህ መሠረት 40 አመት የነገሰው ጠንደውደም ቀድሞ በትንቢት እንተነገረው ይምርኅነ ክርስቶ መወለዱን ሰማ ልጁን ያመጡት ዘንድ አዘዘ፡፡ ☞ንጉሡ በውስጡ ያሰበውን ተንኮል የይምርሐነ ክርስቶስ እናት ሰለገባት (ሰለተገለጸላት) ልጇን ደበቀችው፡፡ ☞በስውር የድቁናን ማዕረግ ካሰጠችው በኃላ ልጇን እንዳይሞትባት ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሸሽ ነገረችው፡፡ ☞በዚያም ለረጅም ጊዜ ከቆየ በኃላ በኢየሩሳሌም ሳለ ቅዱስ ሩፋኤል ከጠንጠውድም በኃላ የምትነግሰው አንተ ነህ በማለት ከነገረው በኃላ በመንገዱ ሁሉ አየተራዳው ወደ ኢትያጵያ ይዞት መጣ፡፡ ☞በላስታ ወረዳ ዛሬ ሽጉላ ማርያም ከምትባል ቦታ ደርሶ ወንጌልን እያስተማረ፤ ድውያንን እየፈወሰ ተቀመጠ፡፡ ☞ለቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ ቅዱስ መስቀልና ኅብስት ከሰማይ ይወርድለት ነበር፡፡ ☞ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ በትረመንግሥቱን ከያዘ በኅላ ሁሉም ሰው እንደ ወንጌል ቃል በአንድ ለአንድ ጋብቻ ተወስኖ እንዲኖሩ በግዛቱ ሁሉ አወጀ፡፡ ☞እግዚአብሔር የሚመሰገንበት ቤት መሥራት አሰበና የተፈቀደለት ቦታ አስከሚያገኝ ድረስ ዛዚያ በምትባል ልዩ በሆነች ስፍራ ድንኳን ተክሎ እንደሙሴ እግዚያብሔር ማገልገል ጀመረ፡፡ ☞ሰኔ 21ቀን ቀድሶ ሕዝቡን ከማቁረቡ በፊት ኅብስቱንና ጽዋውና የእግዚአብሔር መልአክ ሕዝብን ከሚባርክበት ሰማያዊ መስቀል ጋር ከሰማይ አምጥቶ ሰቶታል፡፡ ☞በዚህም ዓይነት ሁኔታ ሕዝቡን ከሰማይ በወረደለት መስቀል እየባረከና ሰማያዊውን ኅብስት ጽዋ እያቆረበ ለ22ዓመት በድንኳን ውስ ጥ ኖረ፡፡ ☞ለቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ ጌታችን ተገልጦለት ቤተ መቅደሱን በባሕር ላይ እንዲሰራ የእኔም ጌትነት የአንተም ቅድስና ሕይወት የሚነገርበት የሥጋህ የዕረፍት ቦታ የሚሆን መቅደስ ለምትሠራበት የሚሆን ሣር የማይፈልግ ሰፊ ዋሻ አለ በዚያ ቤተ መቅደስ ሥራ እኔም በምትሠራው ቤተ መቅደስ ከአንተ ጋር ለዘለአለም ቃል ኪዳኔን አቆማለሁ አለው፡፡ ☞በምታንጸው ቤተ መቅደስ ውስጥ አቤቱ የይምርሐነ ክርስቶስ አምላክ ሆይ ሰለወዳጅህ ሰለ ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ ብለህ ይቅረ በለኝ እያለ አባታችን ሆይ የሚለውን ጸሎት የሚጸለይ ዕለቱን እንደተጠመቀ አደርገዋለሁ፡፡ ☞ቁጥራቸው ከ5ሺ በላይ የሆኑ የሮምና የግብፅ ጳጳሳት የቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስን በረከት ሊቀበሉ መጥተዋል፡፡ ☞የእግዚአብሔርን ጌትነትና የይምርሐነ ክርስቶስ የቅድስና ሕይወት በዓለም ሁሉ መሰማት ጀመረ፡፡ ☞የሮም ሰዎች ወደ እርሱ መጥተው 55 ውድ መስቀሎችን በስጦታነት ገበሩለት፡፡ ☞እግዚአብሔር በእርሱ ላይ የሚደርገውን ተአምርና ቅድስናውን የሰሙ ቁጥራቸው 5740 የሆኑ የግበፅና የሮም ጳጳሳት ኤጲስ ቆጶሳት ቀሳውትና ዲያቆናት እንዲሁም መነኮሳት ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ የሚወርድለትን ሰማያዊ ኅብስትና ሰማያዊ ጽዋ በእጁ ለመቀበልና በመስቀሉ ለመባረክ መጡ፡፡ ☞ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶሰ ለመጡት 5740 ደጋግ ጳጳሳት፤ ኤጲስቆጶሳት፤ቀሳውስትና ዲያቆናት እንዲሁ መነኮሳት ሁሉ ቀድሶ ሰማያዊውን ሥጋ ወደሙ አቀበላቸው፡፡ ☞ቅድስ ይምርሐነ ክርስቶስ በ97 ዓመቱ ጥቅምት 19 በመዝሙር ዳዊት በይባቤ መላእክት ነፍሱ ከሥጋው ተለይታ ሰማያዊ ክብርን ተጉናፀፉለች፡፡ ☞የጻድቁ አባታችን የቅዱስ ይምረሐነ ክርስቶስ ታሪክ በእኔ በሀጢያተኛው የሚገለጽ ባይሆን ለበረከት ይቺን አልኩ፡፡ ☞ለበለጠ መረጃ(መዘገበ ቅዳሳን መጻሐፍ ይመልከቱ፡፡ ☞የቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ በረከቱ ይቅርባይነቱ አይለየን፡፡ ☞https://t.me/yekidusantaric ጆይን እያላችሁ ቻናላችሁ ይቀላቀሉ
Show all...
የቅዱሳን ታሪክ

ማር16:16፤ያመነ፡የተጠመቀም፡ይድናል፥ያላመነ፡ግን፡ይፈረድበታል

👍 1
††† እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ ††† ††† ይህ ቅዱስ ሐዋርያ በአባቶቻችን ሐዋርያት መካከል ትልቅ ሞገስ የነበረውና "የጌታችን ወንድም" ተብሎ የተጠራ ነው:: ቅዱስ ያዕቆብ ወላጅ አባቱ አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ (የእመቤታችን ጠባቂ) ሲሆን በልጅነቱ የሞተችው እናቱ ደግሞ ማርያም ትባላለች:: በቤት ውስጥም ስምዖን: ዮሳና ይሁዳ የተባሉ ወንድሞችና ሰሎሜ የምትባል እህትም ነበረችው:: እናቱ ማርያም ከሞተች በኋላ ዕጓለ-ማውታ (ደሃ አደግ) ሆኖ ነበር:: ነገር ግን በፈቃደ እግዚአብሔር አረጋዊ ዮሴፍ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከቤተ መቅደስ ሊጠብቃት (ሊያገለግላት) ተቀብሎ ሲመጣ ያ ቤተሰብ ተቀየረ:: የበረከት: የምሕረትና የሰላም እመቤት የአምላክ እናቱ ገብታለችና ያ የሐዘን ቤት ደስታ ሞላው:: እመ ብርሃን ግን ገና ወደ ዮሴፍ ልጆች ስትደርስ አለቀሰች:: የአክስቷ ልጆች የሚንከባከባቸው አጥተው ቆሽሸው ነበር:: በተለይ ደግሞ ትንሹ ቅዱስ ያዕቆብ ያሳዝን ነበር:: እመ ብርሃን ማረፍ አልፈለገችም:: ወዲያው ማድጋ አንስታ ወደ ምንጭ ወርዳ ውኃ አምጥታ የሕፃኑን ገላ አጠበችው:: (በአምላክ እናት የታጠበ ሰውነት ምስጋና በጸጋ ይገባዋል::) እመቤታችን ጌታ ከመወለዱ በፊት ለዘጠኝ ወራት: ከተወለደ በኋላ ደግሞ ለሁለት ዓመታት ሕፃኑን ያዕቆብን ተንከባከበችው:: ለሦስት ዓመት ከስድስት ወር ግን ድንግል ማርያም አምላክ ልጇን ይዛ ተሰዳለችና ተለያዩ:: ከስደት መልስ ግን ለሃያ አምስት ዓመታት ቅዱስ ያዕቆብ ከጌታችን ጋር ሲያድግ ወላጅ እናቱ ትዝ ብላው አታውቅም:: አማናዊቷ እናት ከጐኑ ነበረችና:: ሊቃውንት እንደ ነገሩን እመቤታችን ለቅዱስ ያዕቆብ ያልሰጠችው ነገር ቢኖር ሐሊበ ድንግልናዌ (የድንግልና ወተትን) ብቻ ነው:: ስለዚህም:- "እመ ያዕቆብ በጸጋ ማርያም ንግሥተ ኩሉ" ይላል መጽሐፍ:: (መልክዐ ስዕል) ††† ቅዱስ ያዕቆብ "የጌታ ወንድም" ተብሎ በተደጋጋሚ በሐዲስ ኪዳን ተጠርቷል:: ለዚህ ምክንያቱ 1.ለሰላሳ ዓመታት ሳይነጣጠሉ አብረው በማደጋቸው 2.የጌታችን የሥጋ አያቱ (የቅድስት ሐና) የእህት ልጅ በመሆኑ 3.በዮሴፍ በኩልም የአንድ ቅድመ አያት ልጆች በመሆናቸው 4.ጌታችን ከትህትናው የተነሳ ደቀ መዛሙርቱን "ወንድሞች" ይላቸው ስለ ነበር ነው:: (ሥጋቸውን ተዋሕዶ ተገኝቷልና::) ራሱ ቅዱስ ያዕቆብ ግን "የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ነኝ" ብሎ በፈጣሪና በፍጡር መካከል ያለውን ልዩነት ገልጧል:: (ያዕ. 1:1) ቅዱስ ያዕቆብ ጌታችን ሲያስተምር ተከተለው:: ¤ከሰባ ሁለቱ አርድእት ተቆጠረ ¤ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ወንጌልን ተማረ ¤ለመጀመሪያ ጊዜ ከድንግል ማርያምና ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ሆኖ "የጌታን ትንሣኤ ሳላይ እህል አልቀምስም" ብሎ ማክፈልን አስተማረ ¤መንፈስ ቅዱስን ተሞልቶ ወንጌልን አስተማረ ¤የኢየሩሳሌም የመጀመሪያው ሊቀ ጳጳስ ሆኖ አገለገለ ¤በመጀመሪያዎቹ የክርስትና ዘመናት የሐዋርያት ሲኖዶሶችን በሊቀ መንበርነት መራ ¤ሙታንን አስንስቶ ¤ድውያንን ፈውሶ ¤የመካኖችን ማኅጸን ከፍቶ: አጋንንትንም አስወጥቶ ብዙ ተዓምራትን ሠራ:: እጅግ ብዙ አይሁዳውያንን ወደ አሚነ ክርስቶስ መልሶ መልካሙን ገድል ተጋደለ:: በመጨረሻ ዘመኑ ያላመኑ የአይሁድ አለቆች ወደ ቤቱ ተሰብስበው "የናዝሬቱ ኢየሱስ ማነው? የማንስ ልጅ ነው?" ሲሉ ጠየቁት:: እነርሱ ሰይጣን በሰለጠነበት ልቡናቸው "የዮሴፍ ልጅ ነው: የእኔም ወንድሜ ነው" እንዲላቸው ጠብቀው ነበር:: (ሎቱ ስብሐት ወአኮቴት) ††† በልቡናቸው ያሰቡትን ተንኮል የተረዳው ሐዋርያ ወደ ቤቱ ጣራ ወጥቶ መናገር ጀመረ:: "ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ:- አምላክ: ወልደ አምላክ: ወልደ አብ: ወልደ ማርያም: ሥግው ቃል: እግዚአብሔር ነው:: እኔም ፍጡሩና ባሪያው እንጂ እንደምታስቡት ወንድሙ አይደለሁም" አላቸው:: ንዴታቸውን መቆጣጠር ያልቻሉት አይሁድ ከላይ ወጥተው ወደ መሬት ወረወሩት:: በገድል የተቀጠቀጠ አካሉንም እየተፈራረቁ ደበደቡት:: አንዱ ግን ከእንጨት የተሠራ ትልቅ ገንዳ አምጥቶ የቅዱሱን ራስ ደጋግሞ መታው:: ጭንቅላቱም እንዳልነበር ሆነ:: ሰማዕቱ ሐዋርያ ቅዱስ ያዕቆብ ወደ ወደደው ክርስቶስ በዚህች ቀን ሔደ:: ቅዱሱ ሐዋርያ ያዕቆብ ቤቱን እንደ ቤተ መቅደስ አበው ሐዋርያት ይጠቀሙባት ነበር:: በመላ ዘመኑ የሚያገድፍ ነገር (ጥሉላት) ቀምሶ : ጸጉሩን ተላጭቶ : ገላውን ታጥቦና ልብሱን ቀይሮ አያውቅም:: "ወዝንቱ ጻድቅ እኅወ እግዚእነ:: ኢያብአ ውስተ አፉሁ ሥጋ ወወይነ:: ወኢገብረ ሎቱ ክልኤተ ክዳነ" እንዲል:: ††† ከጾም : ከጸሎትና ከመቆሙ ብዛትም እግሩ አብጦ አላራምድህ ብሎት ነበር:: ስለዚህም አበው "ጻድቁ (ገዳማዊው) ሐዋርያ" ይሉታል:: ††† ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወንድሙ ይባል ዘንድ ካደለው ሐዋርያ በረከትን ያድለን:: በምልጃውም ምሕረትን ይላክልን:: ††† ሐምሌ 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ከሰባ ሁለቱ አርድእት-የመጀመሪያው የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳሳት) 2.ቅዱስ አትናቴዎስ ሰማዕት 3.ቅዱስ እንድራኒቆስ ሰማዕት 4.ዘጠኝ ሺህ ሰማዕታት (የቅዱስ ኤስድሮስ ማኅበር) ††† ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ፊልጶስ ሐዋርያ 2.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት (ረባን) 3.አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ 4.ማር ያዕቆብ ግብጻዊ ††† "የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ያዕቆብ: ለተበተኑ ለአሥራ ሁለቱ ወገኖች:: ሰላም ለእናንተ ይሁን:: ወንድሞቼ ሆይ! የእምነታችሁ መፈተን ትዕግስትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቁጠሩት:: ትዕግስትም ምንም የሚጐድላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ምሉዓን ትሆኑ ዘንድ ሥራውን ይፈጽም::" ††† (ያዕ. ፩፥፩) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††† https://t.me/yekidusantaric
Show all...
የቅዱሳን ታሪክ

ማር16:16፤ያመነ፡የተጠመቀም፡ይድናል፥ያላመነ፡ግን፡ይፈረድበታል

1
†††✝ እንኳን ለቅዱሳኑ ገብርኤል ሊቀ መላእክት: ቂርቆስ ወኢየሉጣ: በጥላን ጠቢብ እና ሰማዕታተ እስና ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† ✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን✝! ††† †††✝ ቅዱሳን ቂርቆስ ወኢየሉጣ: ወቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት †††✝ ††† ቅድስት ኢየሉጣ እናታችን በዘመነ ሰማዕታት ከነበሩና በዚህ ስም ከሚጠሩ ቅዱሳት አንዷ ናት:: በወቅቱ ቅዱስ ቂርቆስ የሚባል ደግ ልጅ ወልዳ ባሏ ባለመኖሩ በመበለትነት ትኖር ነበር:: የዚያ ዘመን ክርስቲያኖች ለክርስቶስ የነበራቸው ፍቅር ከመነገር በላይ ነው:: በዛው ልክ ደግሞ መከራው በጸጉራቸው ቁጥር ልክ ነበር:: ከሮም ግዛት በአንዱ ከቅዱስ ልጇ ጋር የምትኖረው ቅድስት ኢየሉጣ የስደቱ ዘመን ሲመጣ እርሷም እንደ ሌሎቹ ክርስቲያኖች ተሰደደች:: እስክንድሮስ የተባለው ከሃዲ ንጉሥ ግን ያለችበት ድረስ ተከትሎ እንድትያዝና እንድትቀርብ አደረገ:: ወዲያውም "ስምሽ ማን ይባላል?" ቢላት "ክርስቲያን እባላለሁ" አለችው:: ንጉሡ ተቆጣ:: "መዋቲ ስሜን ከፈለክ ኢየሉጣ ይባላል" አለችው:: ንጉሡ መልሶ "አሁን ለጣዖት ካልሠዋሽ ሲጀመር ስቃይ: ቀጥሎም ሞት ይጠብቅሻል" ቢላት ቅድስቲቱ መልሳ "በከተማ ውስጥ የሦስት ዓመት ሕፃን አለና እርሱን አምጣው:: ማንን ማምለክ እንዳለብን ይነግረናል" አለችው:: አስፈልጐ ቅዱስ ቂርቆስን አስመጣው:: "ስምህ ማን ይባላል?" አለ ንጉሡ:: "ከማይደፈርስ ከንጹሕ ምንጭ የተቀዳ ጥሩ ምንጭ ስሜ ክርስቲያን ይባላል:: መዋቲ ስሜን ከፈለግህ ግን ቂርቆስ ይባላል" አለው:: ንጉሡ ሊያታልለው "ደስ የተሰኘህ ሕፃን" ቢለው ቅዱሱ ሕፃን "ትክክል ተናገርክ: ለእኔ በሰማያት ደስታ ይጠብቀኛል:: አንተ ግን እውነተኛው አምላክ ይፈርድብሃል" አለው:: በሦስት ዓመት ሕፃን አንደበት ዘለፋ የገጠመው ከሃዲ ተቆጣ:: እናትና ልጅን በብዙ መክፈልተ ኩነኔ አሰቃያቸው:: ሰውነታቸውን ቸነከረ: አካላቸውን ቆራረጠ: ዓይናቸውን አወጣ:: ሌላም ሊናገሩት የሚጨንቅ ስቃይን አሰቃያቸው:: በዚህች ቀን ግን ትልቅ ድስት አሰርቶ ባሩድ: አረር: ስብና የመሳሰሉትን ጨምረውበት በእሳት አፈሉት:: የእሳቱ ወላፈን አካባቢውን በላው:: በድስቱ ውስጥ ያለው ነገር እየፈላ ሲገላበጥ እንደ ክረምት ነጐድጓድ ይጮህ ነበር:: የስድስት ሰዓት የእግር መንገድ ድረስም ተሰምቷል:: ቅድስት ኢየሉጣ ይሔኔ ነበር ልቧ ድንግጥ ያለው:: ሕፃኑ ቂርቆስ የእናቱን ፍርሃት ሲመለከት ጸለየ:: "ፈጣሪዬ! ፍሬው ያለ ግንዱ አይቆምምና እኔን እንዳጸናሕ እናቴንም አጽናት" ሲል ለመነ:: "እግዚኦ ትፈቅድኑ ለፍሬሁ ተአልዶ: እንዘ በእሳት ታውኢ ጉንዶ" እንዲል:: በዚያች ሰዓት ቅድስት ኢየሉጣ ዓይኖቿ ተከፍተው ሰማያዊ ክብርን ተመለከቱና ልቧ ወደ ድፍረቱ ተመለሰ:: ልጇንም "አንተ አባቴ ነህ: አንተን የተሸከመች ማኅጸኔ የተባረከች ናት" አለችው:: ከዚያም ሁለቱንም ወደ ፈላው ድስት ውስጥ ቢጨምሯቸው ፍጡነ ረድኤት ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወረደላቸው:: በበትረ መስቀሉ ባርኮ የፈላውን አቀዘቀዘው:: የነደደውን ውኃ አደረገው:: ቅዱሳኑ ቂርቆስና ኢየሉጣ ከብዙ መከራ በኋላ በሰማዕትነት አልፈዋል:: ††† ቅዱስ በጥላን ጠቢብ ††† ††† ቅዱሱ ከአሕዛብ ወላጆቹ ተወልዶ: ያደገውም በጣዖት አምልኮ ነው:: በሙያው እጅግ የተመሠከረለት ሐኪም ነበር:: የሃገሩ ሰዎች "ጠቢብ" እያሉም ይጠሩታል:: በጥላን ምንም ጣዖት አምላኪ ቢሆን በተፈጥሮው ተመራማሪና ቅን ነበር:: አንድ ካህንም በጐረቤቱ ነበርና ዘወትር ስለ ሃይማኖት ይከራከሩ ነበር:: ካህኑ ሌሊት ሌሊት ስለ በጥላን ተግቶ ይጸልይ ነበርና ተሳክቶለት አሳመነው:: አንድ ቀን በጥላን መንገድ ሲሔድ እባብ ሰው ነድፎ ለሞት ደርሶ አየውና ጸሎት አድርሶ ስመ ክርስቶስን ቢጠራ የተነደፈው ድኖ እባቡ ሞተ:: በዚህ ተዓምር ደስ ብሎት ወደ ካህኑ ሒዶ ተጠመቀ:: ከዚያም ጾም ጸሎትን ጀመረ:: በየቦታው እየዞረ ሕሙማንን እንደ ቀድሞው በመድኃኒት ሳይሆን በጸሎት ያድናቸው ነበር:: ስላዳናቸውም በርካቶቹ ወደ ክርስትና መጡ:: የአካባቢው ሰው: ወላጆቹን ጨምሮ ክርስቲያኖች ሆኑ:: በመጨረሻም ቅዱስ በጥላን: ቤተሰቦቹ: ካህኑና ከደዌ የዳኑት ወገኖቹ በአካባቢው ጣዖት አምላኪ ንጉሥ ፊት ቀርበው ክርስቶስን ሰብከው በሰማዕትነት ዐርፈዋል:: ††† ቅዱሳን ሰማዕታተ እስና ††† ††† እስና ማለት ግብጽ ውስጥ የምትገኝ የቀድሞ አውራጃ ናት:: በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በከተማዋ በርካታ ክርስቲያኖች ይኖሩ ነበር:: የእንዴናው መኮንን መጥቶ "ክርስቶስን ካዱ: ለጣዖት ስገዱ" አላቸው:: ሕዝቡ በአንድ ድምጽ መለሱ:- "ይሕማ ፈጽሞ ሊደረግ አይችልም::" መኮንኑ ተቆጥቶ "ሁሉንም ግደሉ" አለ:: ወታደሮቹ ሰው አልመረጡም:: ከታዘለ ሕፃን አልጋ ላይ እስካለ ሽማግሌ: ከጤነኛ እስከ ሕመምተኛ: ሁሉንም ጨፈጨፏቸው:: ከተማዋ በደም ተነከረች:: ከከተማዋ ክርስቲያኖች ወሬ ለመንገር አንድ ሰው እንኳ አልተረፈም:: ሁሉም ስለ ክርስትና ደማቸውን አፈሰሱ:: ††† ጌታችን ስለ ሰማዕታቱ ብሎ: ደማቸውንም አስቦ በሃይማኖታችን ያጽናን:: ከመከራም ይሰውረን:: በረከታቸውንም ያድለን:: ††† ሐምሌ 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት 2.ቅዱስ ቂርቆስ ወእሙ ኢየሉጣ 3.ቅዱስ በጥላን ጠቢብ ሰማዕት እና ማኅበሩ 4.ቅዱሳን ሰማዕታተ እስና ††† ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት 2.አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ 3.አቡነ ስነ ኢየሱስ 4.አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም ††† "ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ: ወይስ ጭንቀት: ወይስ ስደት: ወይስ ራብ: ወይስ መራቆት: ወይስ ፍርሃት: ወይስ ሰይፍ ነውን? 'ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን:: እንደሚታረዱ በጐች ተቆጠርን::' ተብሎ እንደተጻፈው ነው:: በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን::" ††† (ሮሜ. ፰፥፴፭-፴፯) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††† https://t.me/yekidusantaric
Show all...
የቅዱሳን ታሪክ

ማር16:16፤ያመነ፡የተጠመቀም፡ይድናል፥ያላመነ፡ግን፡ይፈረድበታል

♥#ወለተ_ጴጥሮስ_ማን_ናት⁉🌹          ➖━⊱✿⊰━➖ 📒☞ወር በገባ በ17 የእናታችን የቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ወርሀዊ መታሰቢያዋ ነው፡፡ይቺ ደገኛ ሴት አባቷ ባሕር ሰገድ እናቷ ክርስቶስ ዕበያ ይባላሉ፡፡ ☞የትውልድ ሀገሯ ጎንደር ደዋሮና ነው፡፡ ይቺ የተቀደሰች እናታችን ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ በሕግ በሥርዓት በሊቀ ጳጳስ ትዕዛዝ የንጉሥ ሱስንዮስን የአማካሪዎች አለቃ የሆነው መላክአ ክርስቶስን አግብታ ሦስት ልጆችን ወልዳለች፡፡ ባሏም ታላቅና እጅግ ባለጸጋ ነበርና ከልጆች ጋር በተድላ በደስታ መኖር እንደጀመረች፡፡ አቤቱ ፈጣሪዬ ሆይ እነዚህ ሦስት ልጆቼ አንተን የሚያስደስቱ ከሆነ በሞት ውሰዳቸው፡፡ ብላ ከጸለየችበኃላ እንደፋላጎቷ ሦስት ልጆቿ በሞት ተወስደውላታል፡፡ ☞ባለቤቷ እጅግ እየወደዳት እርሷ ግን ይህን ዓለም እንደ ጤዛ ያልፋል፡፡ ብላ ከሞላ ሀብቷ ከሞቀ ቤቷ ተለይታ ወጥታ በመመነን ጣና ገባች፡፡ በዚያም በተጋድሎ ስትኖር ባሏ አበምኔቱን ለምን ገዳም አሰገበሀት ብሎ ከሰሳቸውና ከገዳሙ አስወጣት፡፡ እርሷ ግን ተደብቃ አክሱም ሄዳ ደብረ በንኮል ገዳም ገባች፡፡ ተመልሳም መጥታ በጣና ባሕር ላይ ቆማ መጸለይ ጀመረች፡፡ በዘመኗ የነበረው ገዢ ጨካኝ ለጣዎት የሚሰግድ ሰለነበረ በትልቅ ገደል ወረውረው እንዲጥሏት አደረጋት፡፡ ነገር ግን መልአኩ ቅድስ ሚካኤል ከእግዚአብሔር ተልኮ መጥቶ በክንፋ ተቀብሏት ወስዶ ብሔረ ብፁዓን አሳይቶ መልሶ አምጥቶ ዋልድባ አደረሳት፡፡ ☞ቅድስት እናታችን ወለተ ጴጥሮስ ወደ ጉምዝ ሀገርም ተስዳ ሳለ በነደደ አሳትውስጥ ቢጨምሯት ምንም ሳያቃጥላት ወጥታለች፡፡ ተመልሳም በጣና ባሕርላይ ቆማ ስትጸልይ ልብሷ ለገዳሙ ያበራ ነበር፡፡ ቧላም እምነቱን ቀይሮ ከካቶሊኮች ጋር ሰለተዛመደ ቅድስ እናታችን ካቶሊኮቶችንና ባሏን አጥበቃ ሰለተቃወመች በገመድ አሰረዋት በጎንንደር ከተማ ጎዳና ላይ ጎትተው አሠቃያት፡ ☞ቅድስ ወለተ ጴጥሮስ ሰባት ገዳማትን ያቀናች ሲሆን ከ700በላይ በሚሆኑ ወንዶች መነኮሳትና ሴቶች መነኮሳት ላይ እመ ምኔት ሆና ተሹማ አገልግላለች፡፡ ☞ከመነነችበት ጊዜ ጀምሮ ምግቧም የመረረ ቅጠል፤ኮሶና አመድ ነበር፡፡ ቅድስት እናታችን ታላቁን የራማ መድሀኒአለም ቤተ ክርስቲያን ሠርታ ሙታንን እያነሳች ድውያንን እየፈወሰች በታላቅ ተጋድሎ እያገለገለች ሳለ ኅዳር 17ቀን በታላቅ ከብር ዐርፋለች፡፡ ወርሐዊ የመታሰቢያ ዕለቷ ወር በገባ በ17 ነው፡፡ በዕረፍቷም ጊዜ የብርሃን ምስሶ ከምድር ሰማይ ተተክሎ ታይቷል፡፡ ☞የቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ዐፅሟ በራሷ በመሠረተችው በሬማ መድኃኔአለም አንድነት ገዳም ውስጥ በክብር ተቀምጦ ይገኛል ፡፡በዚህ ገዳም ውስጥ በቅድስ ሥላሴ ምሳሌ የተሠሩ ሦስት የተለያዩ ድምፆችን የሚያወጡ ደወሎች ይገኛሉ፡፡ ሦስቱም ደውሎች የሚያወጡት ድምጽ ፍጽም የተለያየ ነው፡፡ ☞የእናታችን የወለተ ጵጥሮስ አማላጅነት አይለያችሁ፡፡ ☞የጽሁፍ ምንጭ☞መዝገበ ቅዱሳን ☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ ቤተሰብ ይሁኑን ብዙ የቅዱሳንን ታሪክ እናቀርብለወታለን https://t.me/yekidusantaric
Show all...
የቅዱሳን ታሪክ

ማር16:16፤ያመነ፡የተጠመቀም፡ይድናል፥ያላመነ፡ግን፡ይፈረድበታል

🌹አባ ገሪማ (ይስሐቅ )ማለት⁉🌹 «#ወር በገባ በ17 የአባ ገሪማ ዘመደራ ወርኀዊ መታሰቢያ በዓላቸው ነው አባ ገሪማ (ይስሐቅ) ዘመደራ🌹 📌•••አቡነ ገሪማ የተወለዱት በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ሮም ውስጥ ነው:: ወላጆቻቸው መስፍንያኖስና ሰፍንግያ እግዚአብሔርን የሚወዱ የሮም ከተማ ንጉሥና ንግሥት ነበሩ:: ልጅ በማጣታቸው እመቤታችንን ለመኑ:: +እመ ብርሃንም ደግ ፍሬ ሰጠቻቸው:: ስሙን #ይስሐቅ ብለው አሳደጉት:: ገና በልጅነቱ አባቱ ድንገት በመሞቱ ይስሐቅ በዙፋኑ ተተክቶ ነገሠ:: ለ7 ዓመታት ሕዝቡን በፍትሕ እያስተዳደረ : መጻሕፍትንም እያጠና ኑሯል:: +አንድ ቀን ግን ከግብፅ በርሃ የተላከ ደብዳቤ ደረሰው:: ላኪው #አባ_ዸንጠሌዎን ሲሆኑ መልዕክቱ "ምድራዊ ንግሥና ምን ያደርግልሃል? ይልቁኑስ በሰማይ ለዘለዓለም እንድትነግሥ ወደ በርሃ ና" የሚል ነበር:: +ንጉሥ ይስሐቅ አላመነታም ሌሊት ተነስቶ ወደ ፈጣሪው ጸልዮ በለበሳት ልብስ ብቻ ዙፋኑን ጥሎ መነነ:: ድንገት ግን #ቅዱስ_ገብርኤል ደርሶ በቀኝ ክንፉ ነጥቆ ግብፅ አባ ዸንጠሌዎን በዓት ላይ አኖረው:: +እርሳቸውም ተቀብለው ፍኖተ አበውን አስተምረው አመነኮሱትና ዘጠኝ ሁነው ወደ #ኢትዮዽያ መጡ:: ተስዓቱ ቅዱሳን በሃገራችን ብዙ ሲሰሩ አንዱና ታላቁ አባ ይስሐቅ (ገሪማ) ናቸው:: ሰውነታቸውን በገድል ቀጥቅጠውት ቆዳና አጥንታቸው ተጣብቆ ነበር:: +አንድ ቀን አባ ይስሐቅ በልቶ ቀደሰ ብለው ነግረዋቸው አባ ዸንጠሌዎን አዘኑ:: ልምከር ብለው "ልጄ ይስሐቅ የሰማውብህ ነገር አለና ሰዎችን አርቅልኝ" አሉ:: አባ ይስሐቅ ግን "ሰዎች ብቻ አይደሉም:: ዛፉም እንጨቱም ገለል ይበል" ቢሉ የቤተ ክርስቲያኑ አጸድ አንድ ምዕራፍ ተጠራርጎ ሸሸ:: +ይሕንን የተመለከቱት አባ ዸንጠሌዎን "ወልድየ ይስሐቅ ገረምከኒ" (ልጄ ይስሐቅ ገረምከኝ) አሏቸው:: ከዚያ ጊዜ ጀምሮም "#አቡነ_ገሪማ" ተብለው ቀሩ:: +አቡነ ገሪማ ወደ #መደራ ሲሔዱ እነዚያ የሸሹ ዛፍና ድንጋዮች "ገሪማ ለእኛም ግሩም ነህ" እያሉ በዝማሬ ተከትለዋቸዋል:: ይህም የተደረገው በዚህች ቀን (መስከረም 30) ነው:: +ጻድቁ ወንጌልን : ገዳማትን ከማስፋፋት ባለፈ ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል:- 1.ስንዴ ጠዋት ዘርተውት በ9 ሰዓት ያፈራ ነበር:: "ነግሃ ይዘርዕ ኪነቶ:: ወሠርከ የዓርር ገራኅቶ::" እንዲል:: 2.ጧት የተከሉት ወይን በ9 ሰዓት ያፈራ ነበር:: 3.አንድ ቀን ምራቃቸው ቢወድቅ ጸበል ሆኖ ዛሬም አለ:: 4.ብዕራቸው ወድቃ አብባ አፍርታለች:: 5.አንድ ቀን ድርሳን እየደረሱ (ወንጌለ ዮሐንስን ሲጽፉ) ሊመሽ በመሆኑ ፀሐይን አቁመዋታል:: +ከእነዚህ ሁሉ ዘመናት በሁዋላ #ጌታችን ተገልጦ በማይዋሽ ንጹሕ አንደበቱ ቃል ኪዳን ሰጣቸው:: "ስምሕን የጠራ : መታሰቢያህን ያደረገ : እስከ 12 ትውልድ እምርልሃለሁ:: አንተ ግን ሞትን አትቀምስም" ብሏቸው ተሰወረ:: ያን ጊዜ መላእክቱ በሠረገላ ጭነው እየዘመሩ #ብሔረ_ሕያዋን አድርሰዋቸዋል:: =>ቸሩ አምላካችን ከታላቁ ቅዱስ ጸጋ በረከት ይክፈለን:: በምልጃቸውም ይቅር ይበለን:: =>+"+ ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ:: ግርማው በእሥራኤል ላይ : ኃይሉም በደመናት ላይ ነው:: እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው:: የእሥራኤል አምላክ እርሱ ኃይልን : ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል:: እግዚአብሔርም ይመስገን:: +"+ (መዝ. 67:34)    <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር Join እያላችሁ ተቀላቀሉን https://t.me/yekidusantaric
Show all...
የቅዱሳን ታሪክ

ማር16:16፤ያመነ፡የተጠመቀም፡ይድናል፥ያላመነ፡ግን፡ይፈረድበታል

✞✞✞ ✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✝✞✞✞ ✞✞✞✝ እንኩዋን ለነቢዩ #ቅዱስ_ዮናስ እና ለእናታችን #ቅድስት_አውፎምያ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞✝ ✞✞✞ ✝ቅዱስ ዮናስ ነቢይ✝ ✞✞✞ =>በቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ ከ12ቱ #ደቂቀ_ነቢያት አንዱ የሆነው #ቅዱስ_ዮናስ ከክርስቶስ ልደት 800 ዓመታት በፊት እንደ ነበረ ይታመናል:: #ሊቃውንት እንዳስተማሩን ደግሞ እናቱ #ቅዱስ_ኤልያስን የመገበችው የሰራፕታዋ መበለት ናት:: ቅዱስ ዮናስ ገና ሕጻን ሳለ በእሥራኤል ምድር ዝናብ ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት ተከልክሎ ነበር:: +ይሕንንም ያደረገው ደጉ ነቢይ ኤልያስ ለአምልኮተ እግዚአብሔር ቀንቶ ነው:: በወቅቱ ኤልያስ በሰራፕታ ሳለ ሕጻኑ ዮናስ ታሞ ሞተ:: ልጇ የሞተባት መበለትም ኤልያስን ለመነችው:: ኤልያስም ወደ ፈጣሪው ማልዶ ሕጻኑን ዮናስን ከሞት አስነስቶታል:: ትንሽ ከፍ ባለ ጊዜም ከጉዋደኞቹ (ከነቢያቱ) #አብድዩና #ኤልሳዕ ጋር ሆነው ታላቁን ነቢይ ኤልያስን ተከትለውታል:: +ኤልያስ ካረገ በሁዋላ ሁሉም በየተሰጣቸው አገልግሎት ተሠማርተዋል:: ቅዱስ ዮናስን #እግዚአብሔር "ወደ ነነዌ ሒደሕ ንስሃን ስበክ" አለው:: ዮናስ ግን የፈጣሪውን መሐሪነት ጠንቅቆ ያውቃልና አልሔድም አለ:: (ተመልከቱ የየዋሕነት ብዛት) +እግዚአብሔር እየደጋገመ እንዲሔድ ሲነግረው ነቢዩ "እንዲሕ የሚዘበዝበኝ ከፊቱ ብቀመጥ አይደል" ብሎ ሊኮበልል ወጣ:: ነገር ግን አልቀናውም:: በእርሱ ምክንያት ማዕበል ተነሳ:: ሕዝቡም ሊያልቁ ሆነ:: ከእንቅልፉ የነቃው ዮናስ ከመርከቡ ላሉት አሕዛብ አምልኮተ እግዚአብሔርን ሰብኮላቸው: በእርሱ ጠያቂነት ሐምሌ 15 ቀን ወደ ባሕር ጥለውታል:: +አሣ አንበሪም ተቀብሎታል:: በግዙፉ አሣ ውስጥም ያለ እንቅልፍ በጾም: በጸሎትና በምስጋና 3 ለቀን ቆይቷል:: ሙስና ሳያገኘውም በዚህች ቀን አሣ አንበሪው #ነነዌ ዳር ላይ ተፍቶታል:: ቅዱስ ዮናስ እግዚአብሔር እንዳዘዘው "እስከ ሠሉስ ዕለት ትትገፈታእ ነነዌ ዓባይ ሃገር" /እስከ ሦስት ቀን ድረስ ነነዌ ትገለበጣለች (ዮናስ 3:4)/ ብሎ አሰምቶ ሰበከ:: +የነነዌ ሰዎችም በስብከተ ዮናስ አምነው: ንስሃም ገብተው ድነዋል:: በዚህም ጌታችን በወንጌል ላይ አመስግኗቸዋል:: ቅዱስ ዮናስ መኮብለሉ #በሐዲስ_ኪዳን ለሚደረገው ምስጢረ ትንሳኤ ጥላ (ምሳሌ) ነውና ይደነቃል:: (ማቴ. 12:38) ነቢዩ ግን በተረፈ ሕይወቱ ሕዝቡን ሲያስተምር: ፈጣሪውን ሲያገለግል ኑሮ በመልካም ሽምግልና ዐርፏል:: +"+ ቅድስት አውፎምያ ሰማዕት +"+ =>እናታችን #ቅድስት_አውፎምያ (ስሟ አፎምያ አይደለም:: በስሕተት "ው" መካከል ላይ የገባች እንዳይመስልዎ:: እስመ ከመዝ ስማ-ስሟ እንዲሁ ነው የሚጠራው) በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ከነበሩ ወጣት ክርስቲያኖች አንዷ ናት:: ገና ከልጅነቷ ልቧ በፍቅረ ክርስቶስ የተነደፈ ነበር:: +በዚህም ምክንያት ራሷን በጾምና በጸሎት ወስና ትኖር ነበር:: እድሜዋ ገና በአሥራዎቹ ቢሆንም በመንኖ ጥሪት መኖር ምርጫዋ ነበር:: ሊቃውንት አበው ከሰማዕትነቷ ደርበው "ጻድቅት አውፎምያ" እያሉም ይጠሯታል:: +አንድ ቀን ግን መንገድ ወጥታ ነበርና ክርስቲያኖች ሲሰቃዩ ተመለከተች:: ምንም ጥፋት ሳይገኝባቸው ክርስቶስን ስላመለኩ ብቻ ይሙት በቃ ተፈርዶባቸው ሊገደሉ እየተወሰዱ ነበር:: አሕዛብ ግብራቸው የአውሬ ነውና ርሕራሔ የላቸውም:: ሰማዕታቱ ደማቸው በየመንገዱ እየፈሰሰ ጥቁር ሰንሰለት በአንገታቸው: በእጃቸውና በእግራቸው ላይ አድርገው ይጐትቷቸው ነበር:: +ቅድስት አውፎምያ የተደረገውን ሁሉ ተመልክታ አምርራ አለቀሰች:: ፈጠን ብላም ወደ መኮንኑ ቀርባ ገሰጸችው:: "አንተ አእምሮ የጎደለህ! እንዴት ክርስቲያኖችን እንዲህ ታሰቃያለህ? አምላካቸው #ጌታ_ክርስቶስ ታጋሽ ባይሆን ኑሮ በቅጽበት ከገጸ ምድር ባጠፋህ ነበር" አለችው:: +በድፍረቷ የተገረመው መኮንኑ "አንቺስ ማንን ታመልኪያለሽ?" ሲል ጠየቃት:: እርሷም "ሰማይና ምድርን የፈጠረውን: ስለ እኛ ሲል በቀራንዮ አንባ የተሠዋውን #ኢየሱስ ክርስቶስን አመልካለሁ" ስትል መለሰችለት:: በዚያች ሰዓት የመኮንኑ ቁጣ በቅድስቷ ላይ ነደደ:: +ነገር ግን ቁጣውን ከቁም ነገር አልቆጠረችውምና እንዲያሰቃዩዋት አዘዘ:: ወታደሮቹ ሥጋዋን በብዙ አሰቃዩ:: ብላቴናዋ አውፎምያ ግን ጽንዕት ናትና አልቻሏትም:: በመጨረሻ በእሳት ተቃጥላ ትሞት ዘንድ ተፈረደባት:: +እሳቱ ከመሬት ከፍ ባለ ጊዜ ወደ ውስጥ ወረወሯት:: በእሳቱ መካከል ቁማ ለረዥም ጊዜ ጸለየች:: ከዚያም ነፍሷን አሳልፋ ሰጠች:: ምዕመናን በክብር ገንዘው ቀብረዋታል:: =>አምላካችን ከነቢዩና ከሰማዕቷ ወዳጆቹ በረከት ይክፈለን:: =>ሐምሌ 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ ዮናስ ነቢይ (ከአሣ አንበሪ ሆድ የወጣበት) 2.ቅድስት አውፎምያ (ጻድቅትና ሰማዕት) 3.ቅዱስ ዮስጦስ ሰማዕት (ታላቁ) 4.ቅዱስ ዘካርያስ =>ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት (ቀዳሜ ሰማዕት) 2.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ ዘብዴዎስ) 3.ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ 4.አባ ገሪማ ዘመደራ 5.አባ ዸላሞን ፈላሢ 6.አባ ለትጹን የዋህ 7.ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ (ዘደሴተ ቆዽሮስ) =>+"+ በዚያን ጊዜ ከጻፎችና ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ መለሱና:- 'መምሕር ሆይ! ከአንተ ምልክት እንድናይ እንወዳለን' አሉት:: እርሱ ግን መልሶ እንዲህ አላቸው:- 'ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል:: ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም:: ዮናስ በአሣ አንበሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል:: የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነስተው ይፈርዱበታል:: በዮናስ ስብከት ንስሃ ገብተዋልና:: እነሆም ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ:: +"+ (ማቴ. 12:38) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ https://t.me/yekidusantaric
Show all...
የቅዱሳን ታሪክ

ማር16:16፤ያመነ፡የተጠመቀም፡ይድናል፥ያላመነ፡ግን፡ይፈረድበታል

🌹#ባለህበት_አመሥጋኝ_ሁን🙏💝 📌"በየትኛውም የህይወት እርከን ላይ ልትሆን ትችላለህ እግዚአብሔር ለማመሥገን ግን የሚከለክል አንዳች ችግር የለም።ከመሬት በላይ እስካለህ ድረስ በቅጽበት ህይወት መልኳን ትቀይራለች ካለህበት ወይ ትወርዳለህ ወይ ከፍ ትላለህ የቅንጦት መጨረሻው አይታወቅም የጉስቁልናም እንዲሁ፣ ስለዚህ ባለህበት አመሥጋኝ ሁን። #መልካም ዕለተ ሰንበት💚💛💝🌹 ፈንታነሽ የእመ ብርሃን ልጅ በዚህ ደግሞ ቴሌግራም ይከታተሉ❤ https://t.me/yekidusantaric
Show all...
የቅዱሳን ታሪክ

ማር16:16፤ያመነ፡የተጠመቀም፡ይድናል፥ያላመነ፡ግን፡ይፈረድበታል

ኪዳነ ምህረት♥🙏 🖊 ኪዳነምህረት ስንል የምህረት ቃልኪዳን ማለት ነው፡፡በዚህ ውስጥም ምህረት አድራጊው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ምህረት ተቀባይም መላው የአዳም ዘር ነው፡፡እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በምድራዊ ቆይታዋ ዘውትር ወደ ክርስቶስ መካነ መቃብር ጎለጎታ እየወረደች ትፀልይ ነበር፡፡ ልጇ እና ወዳጇ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገችው ልመናና ፀሎት ተመልክቶና ሰምቶ የምህረት ቃል ኪዳን ገባለት ፡፡ 🖊እንኳን የእናቱን ፀሎት እና ልመና ቀርቶ ዘውትር በሀጥያት የምንዘፈቀውን እኛን ክፉዎቹን የሚሰማ አምላክ ስለ አንቺ ፣ ስለ እናቴ ክብርና ፀጋ ስል ይኸው ቃሌ ብሎ ቃልኪዳን አደረገ፡፡ « ከመረጥሁት ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ። … » መዝ, 89 : 3 እንዲል መፅሐፉ፡፡ 🖊ስሟን ለሚጠሩ፣በእርሷ አማላጅነት ለሚታመኑ በምድር በረከትን በሰማይ የዘለዓለም መንግስትን እንደሚወርሱ የምህረት እና የቸርነት ቃልኪዳን ሰጥቷታል ፡፡ ታላቁ መፅሐፍ እንዲህ ይላል፦ ቀስቲቱም በደመና ትሆናለች፤በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል ያለውን የዘላለም ቃል ኪዳን ለማሰብ አያታለሁ።" ኦሪት ዘፍ. 9 : 16 🖊በዚህም መሠረት ቃልኪዳኗን ምክንያት በማድረግ ኪዳነ-ምህረት እያልን እንጠራታለ እንኳን ለ«ኪዳነምህረት» አደረሳችሁ። የእመቤታችን ምህረት እና ረድዔት፤በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን!🙏 https://t.me/yekidusantaric
Show all...
የቅዱሳን ታሪክ

ማር16:16፤ያመነ፡የተጠመቀም፡ይድናል፥ያላመነ፡ግን፡ይፈረድበታል

♨ወር በገባ በ16 የቅዱስ አቡናፍር ወርኃዊ በዓሉ ነው ።🌹      #ገዳማዊ አቡነ አቡናፍር 🎚+ ❖ ይኸውም ቅዱስ አቡናፍር ጥቂት የሰሌን ፍሬዎችን ብቻ እየተመገበ በበረሃ ውስጥ 60 ዓመት የኖረ ታላቅ ጻድቅ ነው፡፡ ❖ በእነዚህ ድፍን 60 ዓመታት ውስጥ ከቶ የሰውን ፊት አላየም፤ ዛሬ ከምስር ከተማ ውጪ የተሠራች ቤተክርስቲያኑ የከበረችበት ዕለት ነው፡፡ ❖ አቡነ አቡናፍር መልካም ሽምግልና ያለው ስም አጠራሩ የከበረ በገዳም የሚኖርና በገድል የተጠመደ አባት ነው፤ ከላይኛውግብፅ የተገኘ ሲሆን ታሪኩን የተናገረለት ጻዲቁ አባ በፍኑትዮስ ነው፡፡ ❖ ይኸውም አባ በፍኑትዮስ ወደ በረሃ ውስጥ በገባ ጊዜ አንዲት የውኃ ምንጭና አንዲት የሰሌን ምንጣፍ አግኝቶ በዚያ እየተጋደለ ብዙ ዘመን የኖረ ነው፡፡ ❖ በአንዲት ዕለት አባ በፍኑትዮስ ወደ እርሱ ሲመጣ አባ አቡናፍር አየው፤ አባ በፍኑትዮስም የሰይጣንን ምትሐት የሚያይ መስሎት ደነገጠ፡፡ ❖ አባ አቡናፍር ፀጉሩና ጽሕሙ ሰውነቱን ሁሉ ሸፍኖታል እንጂ በላዩ ላይ ልብስ አልነበረውም፤ አባ በፍኑትዮስንም በመስቀል ምልክት ባርኮ አጽናናው፡፡ ❖ አቡነ ዘበሰማያትንም ከጸለየ በኋላ ‹‹አባ በፍኑትዮስ ሆይ ወደዚህ መምጣትህ መልካም ነው›› ብሎ በስሙ ከጠራው በኋላ ፍርሃቱን አራቀለት፡፡ ❖ ከዚህም በኋላ ሁለቱም በጋራ ጸልየው የእግዚአብሔርን ገናናነት እየተነጋገሩ ተቀመጡ፤ አባ በፍኑትዮስም አኗኗሩንና እንዴት ወደዚህ በረሃ እንደመጣ ታሪኩን ይነግረው ዘንድ አባ አቡናፍርን ለመነው፡፡ ✍‹እኔ ደጋጎች እውነተኞች መነኮሳት በሚኖሩበት ገዳም ውስጥ እኖር ነበር፤ የገዳማውያንን ልዕልናቸውን ሲናገሩ ሲያመሰግኗቸውም ሰማሁ፤ እኔም ‹ከእናንተ የሚሻሉ አሉን› ብዬ ጠየኳቸው፡፡ ❖ እነርሱም ‹አዎን እነርሱ በበረሃ የሚኖሩ በእግዚአብሔር ዘንድ የከበሩ ናቸው፤ እኛ ለዓለም የቀረብን ስለሆንን ብንተክዝና ብናዝን የሚያረጋጋን እናገኛለን ብንታመም የሚጠይቀንና የፈለግነውን ሁሉ እናገኛለን፣ በበረሃ የሚኖሩ ግን ከዚህ ሁሉ የራቁ ናቸው› አሉኝ፤ ይህንንም ስሰማ ልቤ እንደ እሳት ነደደና ወደ ፈቀደው መንገድ ይመራኝ ዘንድ በእኩለ ሌሊት ተነሥቼ ጸለይኩ፡፡ ❖ ከዚህም በኋላ ተነሥቼ ወጥቼ ስጓዝ አንድ አባት አገኘሁና የገዳማውያንን ገድላቸውን እያስተማረኝ ከእርሱ ጋር ተቀመጥኩኝ፡፡ ያዘጋጀልኝን ይህችን ሰሌን አገኘኋት፤ በየዓመቱ 12 ዘለላ ታፈራለች፤ ለየወሩም የምመገበው አንዱ ዘለላ ይበቃኛል ውኃም ከዚህች ምንጭ እጠጣለሁ፡፡ ❖ በዚህችም በረሃ እስከዛሬ 60 ዓመት ኖርኩ፤ ከአንተም በቀር የሰው ፊት ከቶ አይቼ አላውቅም›› ብሎ አቡነ አቡናፍር ጣፋጭ ታሪኩን በዝርዝር ነገረው፡፡ ❖ ይህንንም ሲነጋገሩ የታዘዘ መልአክ መጥቶ የጌታችንን ሥጋና ደም አምጥቶ አቆረባቸው፤ ቀጥለውም ጥቂት የሰሌን ፍሬ ተመገቡ፤ ወዲያውም የአቡነ አቡናፍር መልኩ ተለወጠ፤ እንደ እሳትም ሆነ፤ ወደ እግዚአብሔርም በተመስጦ እየጸለየ ሳለ ቅድስት ነፍሱ ከሥጋው ተለየች፤ አቡነ በፍኑትዮስም በፀጉር ልብሱ በክብር ገንዞ ቀበረው፡፡ ❖ ከዚህም በኋላ አባ በፍኑትዮስ በዚያች ቦታ ይኖር ዘንድ ወደደ ነገር ግን ያቺ የሰሌን ዛፍ ወደቀች፤ የውኃዋም ምንጭ ደረቀች፡፡ በረከታቸው ረድኤታቸው ይደርብን፤ በጸሎታቸው ይማረን                     አርኬ ✍️ሰላም ለቅዳሴ ቤትከ በአፍኣ ሀገር ዘምስር። እንተ ሐነፅዋ ኬነውት ወጠበብተ ምክር። አቡናፍር አቡየ ሠውረኒ አመ ዕለተ ፍዳ ወፃዕር። በዘከደነከ እምሐሩር ወቊር። እምነ ርእስከ ወጽሕምከ ዘወረደ ጸጒር። https://t.me/yekidusantaric
Show all...
የቅዱሳን ታሪክ

ማር16:16፤ያመነ፡የተጠመቀም፡ይድናል፥ያላመነ፡ግን፡ይፈረድበታል

✝✝††† እንኳን ለታላቁ ሊቅና አፈ በረከት ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። ††† †††✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††✝ ††† ✝ቅዱስ ማሪ ኤፍሬም ሶርያዊ ✝††† ††† እንደ ቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ቅዱስ ኤፍሬም የተወለደው ንጽቢን በምትባል የሶርያ ግዛት ውስጥ በ298 / 306 ዓ/ም ነው:: ወላጆቹ በክርስቶስ የማያምኑ አላውያን ነበሩ:: (ምንም አንዳንድ ምንጮች ክርስቲያኖች ነበሩ ቢሉም) ቅዱሱ ተወልዶ ባደገባት ንጽቢን ጵጵስናን የተሾመ ቅዱስ ያዕቆብ የሚባል ታላቅ ሰው ነበር:: የሰማዕትነት: የሐዋርያነት: የጻድቅነትና የሊቅነት ግብር ያለው አባት ነው:: ታዲያ ቅዱስ ኤፍሬም ይሔ አባት ሁሌ ሲያስተምር ይሰማው ነበርና በስብከቱ ተማርኮ ደቀ መዝሙሩ ለመሆን በቃ:: ቅዱስ ኤፍሬም በቅዱስ ያዕቆብ እጅ ከተጠመቀ በኋላ ሙሉ የወጣትነት ጊዜውን ያሳለፈው በትምሕርት ነው:: የሚገርመው መምሕሩ ቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢን እመቤታችን ድንግል ማርያምን በፍጹም ልቡ የሚወድና ጠርቷት የማይጠግብ አባት ነውና ለልጁ ለቅዱስ ኤፍሬም ይሕንኑ አጥብቆ አስተምሮታል:: ቅዱስ ኤፍሬም ክርስትናን ሲመረምር የእመቤታችን ፍቅር ይበዛለት ጀመር:: ምክንያቱም እመ ብርሃንን ሳይወዱ ክርስትና የለምና:: እንደ እርሱ የሚወዳት የለም እስኪባል ድረስ ያገለግላት: ይገዛላትም ገባ:: እንዲህ እንደ ዛሬ የድንግል ማርያም ምስጋና በአንደበት እንጂ በመጽሐፍ አይገኝም ነበር:: እርሱ ግን ከወንጌለ ሉቃስ በስድስተኛው ወርን (ይዌድስዋን) እና ጸሎተ ማርያምን(ታዐብዮን) አውጥቶ በየዕለቱ በዕድሜዋ ልክ ስልሳ አራት ስልሳ አራት ጊዜ ያመሰግናት ነበር:: በእንዲህ ያለ ግብር እያለ አርዮስ በመካዱ እርሱን ለማውገዝና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ለማጽናት በ317 (325) ዓ.ም ሦስት መቶ አሥራ ስምንቱ ሊቃውንት በኒቅያ ሲሰበሰቡ አንዱ መምሕረ ኤፍሬም ቅዱስ ያዕቆብ ነበር:: በዚህ ምክንያት ቅዱስ ኤፍሬም ከሊቃውንቱ ትምሕርትና በረከትን አግኝቷል:: ከጉባዔ መልስ መንገድ ላይ በራዕይ የብርሃን ምሰሶ አይቶ "ጌታ ሆይ! ምንድን ነው?" ብሎ ቢጠይቅ "ይሕማ ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ ነው::" አለው:: እርሱም መምሕሩን ቅዱስ ያዕቆብን ተሰናብቶ ወደ ቅዱስ ባስልዮስ (ቂሣርያ) ወረደ:: ተገናኝተውም በአንድ ሌሊት ቋንቋ ተገልጦላቸው ሲጨዋወቱ አድረዋል:: በቦታው ብዙ ተአምራት ተደርጓል:: ቅዱስ ኤፍሬም ከታላቁ ባስልዮስ ከተማረ በኋላ ሃገረ ስብከት ተሰጥቶት ያስተምር ጀመር:: ሁል ጊዜ ታዲያ ጸሎቱ ይሔው ነበር:: "እመቤቴ ሆይ! ምስጋናሽ እንደ ሰማይ ከዋክብት: እንደ ባሕር አሽዋ በዝቶልኝ: እንደ እንጀራ ተመግቤው: እንደ ውኃ ጠጥቼው: እንደ ልብስም ተጐናጽፌው" እያለ ይመኝ ነበር:: አፍጣኒተ ረድኤት: ፈጻሚተ ፈቃድ እመ ብርሃንም በገሃድ ተገልጻ የልቡን ፈቃድ ፈጸመችለት:: ዛሬ ጸጋ በረከት የምናገኝበትን ውዳሴ ማርያምን ደረሰላት:: ሲደርስላትም እርሷ አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን አስከትላ ወርዳ: በፊቱም ተቀምጣ ሲሆን እርሱ ደግሞ ባጭር ታጥቆ: በፊቷ ቆሞ: በመንፈስ ቅዱስም ተቃኝቶ ነው:: ውዳሴዋን በሰባት ቀናት ከደረሰላት በኋላ በብርሃን መስቀል ባርካው: ሊቀ ሊቃውንትም እንዲሆን ምሥጢር ገልጣለት ዐረገች:: ከዚህ በኋላ በምሥጢር ባሕር ውስጥ ዋኝቶ አሥራ አራት ሺህ ድርሰቶችንም ደርሷል:: ዛሬ ሶርያ ውስጥ የምንሰማውን ዜማም የደረሰው ይህ ቅዱስ ነው:: እንዲያውም አንድ ቀን የምሥጢር ማዕበል ቢያማታው "አሃዝ እግዚኦ መዋግደ ጸጋከ" ብሎ ጸልዩዋል:: (የጸጋህን ማዕበል ያዝልኝ) እንደ ማለት ነው:: ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ በመጨረሻ ሕይወቱ ተክሪት በምትባል ሃገር ኤጲስ ቆጶስ ሆኖ ተሹሟል:: በጣፋጭ ስብከቱ ብዙዎችን ካለማመን መልሷል:: የምዕመናንንም ሕይወት አጣፍጧል:: ለመናፍቃንና ለአርዮሳውያን ግን የማይጋፉት ግድግዳ ሆኖባቸው ኑሯል:: በዘመኑም ብዙ ተጋድሎ አፍርቷል:: ተአምራትንም ሠርቷል:: በተወለደ በስልሳ ሰባት ዓመቱ በ365 (373) ዓ.ም ዐርፎ ተቀብሯል:: ††† ቅዱሱ ለሶርያ ብቻ ሳይሆን እመቤታችንን ለምንወድ የዓለም ክርስቲያኖች ሁሉ ሞገሳችን ሆኗል:: ስለዚህም እንዲህ እያልን እንጠራዋለን:- 1.ቅዱስ ኤፍሬም 2.ማሪ ኤፍሬም 3.አፈ በረከት ኤፍሬም 4.ሊቀ ሊቃውንት ኤፍሬም 5.ጥዑመ ልሳን ኤፍሬም 6.አበ ምዕመናን ኤፍሬም 7.ርቱዐ ሃይማኖት ኤፍሬም . . . አባታችን አንተ ነህ:: ††† ጽንዕት በድንግልና: ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ለቅዱስ ኤፍሬም የሰጠሽውን ጸጋውን: ክብሩን: አእምሮውን: ለብዎውን በልቡናችን ሳይብን: አሳድሪብን . . . አሜን:: †††✝ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ✝††† ††† ዳግመኛ በዚህ ቀን ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ ይታሠባሉ:: ቅዱሳኑ ሶርያ አካባቢ ውስጥ ወደምትገኝ አንዲት ሃገር ገብተው ሕዝቡን ከንጉሣቸው ጰራግሞስ ጋር አሳምነው አጥምቀዋል:: ነገር ግን እነርሱ ሲወጡ ሰይጣን አስቶት አጥፊ ሰው ወደ መሆን ተመልሶ ንጉሡ ሐዋርያትን አሰቃይቷቸዋል:: ስለ ቅዱሳኑ ግን ፈረሶቹ ሰግደው: በሰው አንደበት ቅድስናቸውን መስክረዋል:: በመጨረሻም ንጉሡን ከነ ሕዝቡና ሠራዊቱ በዓየር ላይ ሰቅለው ንስሐ ሰጥተውታል:: በእነዚህ ተአምራትም ሁሉም አምነው ለከተማዋና ለሕዝቡ ድኅነት ተደርጓል:: ††† ✝ከአባቶቻችን አበው ሐዋርያት በረከት ይክፈለን::✝ ††† ሐምሌ 15 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ማሪ ኤፍሬም ሶርያዊ (አፈ በረከት) 2.ብርሃናተ ዓለም ቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስ ወጳውሎስ 3.አባ ሓርዮንና ደቀ መዛሙርቱ (ሰማዕታት) 4.አባ ፍሬምናጦስ መስተጋድል ††† ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ 2.ቅዱስ ሚናስ (ማር ሚና) ሰማዕት 3.ቅድስት እንባ መሪና 4.ቅድስት ክርስጢና ††† "ለምኑ ይሰጣችሁማል:: ፈልጉ ታገኙማላችሁ:: መዝጊያ አንኳኩ ይከፈትላችሁማል:: የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና:: የሚፈልገውም ያገኛል:: መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል::" ††† (ማቴ. ፯፥፯) ††† "የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል:: አንደበቱም ፍርድን ይናገራል:: የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው:: በእርምጃውም አይሰናከልም::" ††† (መዝ. ፴፯፥፴) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††† ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ https://t.me/yekidusantaric
Show all...
የቅዱሳን ታሪክ

ማር16:16፤ያመነ፡የተጠመቀም፡ይድናል፥ያላመነ፡ግን፡ይፈረድበታል