en
Feedback
አዲስ የኦርቶዶክስመዝሙሮች እና አባባሎች

አዲስ የኦርቶዶክስመዝሙሮች እና አባባሎች

Open in Telegram

በዚህ ቻናል የተለያዩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙራት እና የፕሮፋይል ፎቶ የሚሆኑ ምስለ ስዕል የሚገኝበት ቻናል ነው....................................................................

Show more
304
Subscribers
+224 hours
+77 days
+6430 days
Posts Archive
ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን (2) ለታላቁ ክብር ለዚህ ያበቃን ከሞት ወደ ሕይወት ያሸጋገረን ኑ በእግዚአብሔር ኑ በድንግል ደስ ይበለን፤ የሰማዩን መንግሥት እርስቱን ለሰጠን ከጨለማ አውጥቶ ብርሃንን ላሳየን ለዚህ ድንቅ ውለታው ምሥጋና ያንሰዋል በርሱ ደስ ይበለን ክብር ይገባዋል፤ ………አዝ……… ከዓለት የፈለቀ ውሃ ጠጥተናል ሰማያዊ መና አምላክ መግቦናል ፍቅርህ የበዛልኝ ምን ልክፈልህ ጌታ ስምህን ላመስግን ከጧት እስከ ማታ ………አዝ……… በቃዴስ በረሃ ምንም በሌለበት በኤርትራ ባሕር ወጀብ በበዛበት ለእርሱ መንገድ አለው ምን ተስኖት ልባችሁ አይፍራ በፍጹም እምነት፤ ………አዝ……… በባርነት ሳለን በድቅድቅ ዓለም ብርሃንን አገኘን በድንግል ማርያም ያጣነውን ሰላም ዛሬ አገኘን እጅግ ደስ ይበለን በእመቤታችን ………አዝ……… የሐና የእያቄም የእምነታቸው ፍሬ በእግዚአብሔር ፈቃድ ተወለደች ዛሬ የእያቄም ስዕለት የሐና እምነት ለምኝልን ለእኛ ኪዳነ ምሕረት ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇

መርቆሬዎስ /2/ የችግሬ ደራሽ ና በፈረስ እንባዬን ልታብስ ፈጥነህ ድረስ ባስልዮስ ጎርጎሪወቀስ ሰምሯል ልመናቸው ስዕሉ ዘለለ ታምራት አያችሁ እናንተን የረዳ መጥቶ በፈረስ ዛሬም ለኛ ይድረስ ይምጣ መርቆሬዎስ አዝ_____ ዑልያኖስ ተገድሏል ሃይማኖት ይስፋፋል ብሎ መሰከረ መርቆርዮስ ሃያል ገፀ ከላባቱ ባህርይ ቀየሩ እርሱን ለማገልገል ከእግሩ ስር አደሩ አዝ_____ ትካዜ ሀዘኔ ይርቃል ጭንቀቴ መርቆርዮስ ሲመጣ ሲገባ ከቤቴ በፀሊም ፈረሱ እየገሰገሰ መርቆሬዎስ ወዳጄ ስጠራው ደረሰ አዝ_____ ስቃዩን ሊያረዝም ዳኪዎስ ወደደ ከጨለማ እስር ቤት ታስሮ ተወሰደ በጋለ ሹል ብረት መርቆሬዎስ ተወጋ ስሙ ተሰየመ ከሰማዕት ጋ አዝ_____ አልፈራም መከራ አልፈራም ችግር መፍቅሬ አብ ካለ ያኘሎፓዴር ቂሳርያ እስር ቤት መርቆሬዎስ ታሰረ ወህኒ ቤቱ በራ እግዚአብሔር ከበረ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

"ጌታዬ ከሰጠኝ" ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ጌታዬ ከሰጠኝ አልፈራም ልወስድሽ የሀዘኔ መርሻ ማርያም እናቴ ነሽ . . . . . . . . . . .. . . . . . . . . . እናት አግኝቻለሁ ከመስቀሉ ግርጌ ስሟን እየጠራሁ ከፍ እንዲል ማረጌ ምርኩዝ ድጋፍ ሆኖኝ ድንግል ሆይ ፀሎትሽ በእፎይታ ሞልቶኛል የሰላምታ ድምፅሽ ፍጹም ላይረሳኝ ገብቶ በደም ስሬ ይቀሰቅሰኛል ክብርሽ ለዝማሬ አዝ…………….. በልጅሽ መከራ ቀራንዮ ያለሽ አትዘነጊኝም ዛሬም ከእኔ ጋር ነሽ ማታወክ መጨነቅ ከቤቴ እንዲነቀል የበረከት ቁልፍ ሰቶኛል ከመስቀል ከጣሪያ በታች መነጨ ደስታ ለጠቆረው ፊቴ እምቤቴ አብርታ አዝ.. . . . . . . . . . በራስ ቅል ተራራ በነፍስሸ ሰይፍ አልፎ ካሳ ሆነ ፍቅርሽ በልቤ ተፅፎ እነኋት እናትህ ሲለኝ በርትቻለሁ በልጅነት ክብር ከፊትሽ ቆሚያለሁ የመስቀል ስጦታ እነኋት እናቴ ማንንም ሳልፈራ ወሰድኳት ከቤቴ አዝ . . . . . . . . . . በመስቀል ላይ ሆኖ ልጅሽ እራራልኝ በእናትነት ፍቅርሽ ቤቴን ሸለመልኝ የሚያፅናናው ቃሉ መሰበሬን ክሶ በልቤ ተከለ አፅናኟን ምስሶ ሞኝነት አይደለም ነገረ መስቀሉ እጅግ ማትረፊያ ነው አንቺን መቀበሉ ጌታዬ ከሰጠኝ አልፈራም ልወስድሽ የሀዘኔ መርሻ ማርያም እናቴ ነሽ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

"በፍቅር ላዚምህ" ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ በፍቅር ላዚምህ ፍቅር ነህ ጌታዬ በደም የገዛኸኝ ባለውለታዬ በቃየን ጎዳና እንዳልጓዝ እርዳኝ በቀናው መንፈስህ ወደ ጽድቅ ምራኝ በልቤ ትከሻ በቀል ተሸክሜ ወንድሜን ጠልቼ ካንተ ፊት መቆሜ ፃድቅ ቢያስመስለኝ በሰዎች እይታ ጉዴን ስለምታውቅ እስራቴን ፍታ(፪) አዝ = = = = = ዙሪያውን ተከቦ በእሾህ ጥላቻ ስብከቴ መዝሙሬ ሆኗል የቃል ብቻ ማረኝ እና ይብቃኝ ለኃጢአት መዝመቱ ፍቅር የሌለው ሰው ነው የከንቱ ከንቱ(፪) አዝ = = = = = አሸንፈህልኝ እኔ ግን ተሸነፍኩ በእጄ ማልነካውን ለሰው እያሸከምኩ በቃሌ ጠርቼ በግብሬ ረገምኩህ በአስመሳይ ማንነትእየሸነገልኩህ(፪) ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

"ጽዮንን ባሰብናት ጊዜ" መጋቤ ምሥጢር ሰሎሞን ተስፋዬ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

"አብሠራ ገብርኤል" አብሰራ ገብርኤል ለማርያም ወይቤላ /2/ ትወልዲ ወልድ ሚካኤል መላዕክ በክነፍ ፆራ መንጦላዕት ደመና ሰወራ ንፅህት በድንግልና አልባቲ ሙስና ተወልደ ወልድ እምኔሐ ገብርኤል ማርያምን አበሰራት አበሰራት ወንድ ልጅም ትወልጃለሺ አላት ሚካኤል መላዕክ በክንፋ ከለላት የሰማይ መጋረጃውን ሸፈናት ንፅህት ናትና በድንግልና /2/ ጥፋት የለባትምና ወንድ ልጅም ወልዳልናለችና አዳም በጥፋቱ ከገነት ሲባረር በሚካኤል ክንፎች ቀድሞ አይቶሽ ነበር ሔዋንን ሲጠራት ሕይወቴ ነሽ አላት እንደሚድን አውቆ ድንግል በአንች ምክንያት ንፅህት ናትና በድንግልና /2/ ጥፋት የለባትምና ወንድ ልጅም ወልዳልናለችና እግዚአብሔር የላከው የከበረው መላዕክ ድንግል ሆይ ለክብርሽ ዐየን ሲንበረከክ በፍቅር በትህትና በፍፁም ሰላምታ የጌታ ሰው መሆን የነገረሽ በደስታ ንፅህት ናትና በድንግልና /2/ ጥፋት የለባትምና ወንድ ልጅም ወልዳልናለችና ደስተኛዬቷ ሆይ ደስ ይበልሽ ድንግል የአብ ቃል ክርስቶስ ሥጋሽን ይለብሳል አንቺም ትይዋለሽ ስሙን ኢየሱስ መድኋኒት ነውና ለሥጋ ወነፍስ ንፅህት ናትና በድንግልና /2/ ጥፋት የለባትምና ወንድ ልጅም ወልዳልናለችና አንደ ኒቆዲሞስ ሳትከራከሪ አንደ ዘኬርያስ ሳትጠራጠሪ ይሁነኒ ብለሽ ቃልን ተቀበልሽ ከፍጥረት ማነው አንቺ የሚመስልሽ ንፅህት ናትና በድንግልና /2/ ጥፋት የለባትምና ወንድ ልጅም ወልዳልናለችና ዘማሪ ዲያቆን ፍሬዘር ደሳለኝ ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

"እግዚአብሔር መልካም ነው" እግዚአብሔር መልካም ነው በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው/2/ አዝ ------------- ከገነት ሲሰደድ አዳም አባታችን ሞት ነግሶብን ሳለ በእኛ በሁላችን ቃል እንደገባለት ተወልዶ ሊያድነን በመከራ ጊዜ መሸሸጊያ ሆነን/2/ አዝ ------------- አብርሃም ከካራን ከእናት ከአባቱ ቤት ከነአን ሲገባ ሲሰደድ በእምነት ከተሰጠው ተስፋ አንዳች ሳይጎልበት እንደ ምድር አሸዋ ዘሩን አበዛለት/2/ አዝ ------------ በሐዘን በችግር በመከራ ጊዜ ጭንቀቴን የሚያርቅ ነው የፍሴን ትካዜ የቀደመው እባብ ሰላሜን ሲነሳኝ እግዚአብሔር መልካም ነው ሐዘኔን አስረሳኝ የቀደመው እባብ ሰላሜን ቢነሳኝ ክርስቶስ ኢየሱስ ሐዘኔን አስረሳኝ ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

"ኪዳነ ምሕረት" ዘማሪት ሲስተር ፋሲካ መኮንን ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

"ሚካኤል ስዩም " ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ እንኳን አደረሳችሁ ለቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ሚካኤል ስዩም /3/ሊቀ መላእክት መዝገበ ርራሄ/3/ወየዋህ የደሀ አደጉን ልጅ ስለተቀበልከኝ በአውደ ምህረትህ በፍቅር አሳደከኝ ከመቅደስ ተክለህ መገብከኝ ህይወት አዘጋጅተኸኛል ለሰማይ መንግስትህ አዝ ...... በከንቱ እንዳልደክም ነብሴ እንዳትዝል ትመግበኝ ነበር የህወትን ቃል ወጣሁኝ ከአለም ተሰሎንቄን ረሣሁ መጠማቴ ቀረ የህይወት ውሀ ጠጣሁ አዝ ......... መዳንን እንድወርስ ሞትን እንዳላይ ትረዳኝ ነበረ ከኔ ሣትለይ በመንገዴ ሁሉ ከፊቴ ቀደምክ አማኑኤል ብዬ ጌታን እንዳመልክ አዝ ........ ምልጃህን ታምኜ ስኖር በመቅደስህ ታሻግረኝ ነበር እጆቼን ይዘህ በጎልማሣ ነቴ ነህና ከጎኔ ጉልበቴም አንተው ነህ በእርጅና ዘመኔ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

ያዳነኝን አውቀዋለሁ ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ያዳነኝን አውቀዋለሁ የሞተልኝ እየሱስ ነው(2) ስለሌለኝ የምከፍለው ስጦታዬ ምስጋና ነው ጨለማዬን አስወግዶ ያበራልኝን እኔ አውቃለሁ ሙሉ ሰው ነኝ ከንግዲህስ ስከተለው እኖራለሁ የብርንን ልዩ ውበት ፊት ለፊቴ ቆሞ አየሁት ፍቅሩ ማርኮኝ በመቅደሱ ሰገድኩለት አመለኩት ላመስግነዉ ላመስግነዉ ላመስግነዉ (3) ፍቅሩ ማያልቅ ነው አሳደገኝ በእቅፉ መጠውለጌን አለምልሞ በመስቀል ላይ ተሰቀለ ዳንኩኝ እኔ እርሱ ታሞ በማይዝለዉ ክንዶቹ ላይ እኔን በክብር እያኖረ እንዲመቸኝ ዝቅ ብሎ በበረት ውስጥ እርሱ አደረ ላመስግነዉ ላመስግነዉ ላመስግነዉ(3) ፍቅሩ ማያልቅ ነው ቅኔ ባፈስ ምን ይደንቃል ደሙን በመስቀል አፍስሶ ስለ ልጁ መዳን ብሎ ነብሱን ሳይቀር ለኔ ክሶ ፍቅር ይዞት ከፀባኦት በትህትና መጥቶ አደረ ተቀደስኩኝ በነጩ በግ ቀራንዮ ጌታ ታርዶ ላመስግነዉ ላመስግነዉ ላመስግነዉ (3) ፍቅሩ ማያልቅ ነው አክሊለ እሾክ አጠለቀ ግርማ ክብሩን ሁሉ ትቶ አሻገረኝ ወደ ክብሬ በቅዱስ እኔን ዋጅቶ አጎንብሶ ቀና አደረገኝ ፊቴን በፅድቅ እያበራ እኖራለሁ ለዘላለም ካከበረኝ ጌታ ጋራ ላመስግነዉ ላመስግነዉ ላመስግነዉ ፍቅሩ ማያልቅ ነው ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

#የሥላሴን_መንበር የሥላሴን መንበር ቅዱሳን ከበውት ኪሩቤል በደመና ዙፋኑን ይዘውት ድንግልን ከመሐል ሚካኤልን ከፊት አእላፍ መላዕክት ሲሰግዱ በፍርሐት እዩት ተመልከቱት የሰማዩን ድምቀት/2/ #አዝ የሥላሴን መንበር ቅዱሳን ከበውት እያሸበሸቡ የሰማይ መላእክት ካህናተ ሰማይ ሥሉስ ቅዱስ ሲሉት ይህን ታላቅ ክብር ሊያዩ የታደሉ በጽድቅ ሥራቸው በምድር ይታያሉ/2/ #አዝ የቅዱሳን ሕብረት የቅዱሳን ሐገር ሲያወድስ ይኖራል የሥላሴን መንበር ጽድቅና ርህራሄ የተሞላች ሰማይ እግዚአብሔር ያድለን በትንሣኤ እንድናይ/3/ ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

“ርስታችን ነሽ ” ርስታችን ነሽ እንወርስሻለን፣ በምድርሽ ወይንን እንለቅማለን። ይትረፈረፋል ጽዋችን ሞልቶ፣ አንቺን ይዘናል አናፍርም ከቶ። የእንጀራ ምድር የፍቅር ሐገር፣ የለንም ወገን ካንቺ በስተቀር። በአክዓብ መሬት የማንቀይርሽ፣ ደጅሽ ቁመናል ባርኪን በእጆችሽ። ዳዊት አባትሽ እንዳለው፣ብረሳሽ ቀኘ ትርሳኝ፣ በልቤ ላይ ነግሰሻል ምልጃሽ እየጠበቀኝ። ርስታችን ነሽ እንወርስሻለን፣ በምድርሽ ወይንን እንለቅማለን። ይትረፈረፋል ጽዋችን ሞልቶ፣ አንቺን ይዘናል አናፍርም ከቶ። ወደ ምድራችን መጥተን ስንገባ፣ አንቺን አገኘን ታላቋን መባ፣ የሕይወት ውኃ ፈልቋል በሆድሽ፣ እንዳንጠማ ድንግል ልጆችሽ። ዳዊት አባትሽ እንዳለው ብረሳሽ ቀኘ ትርሳኝ፣ በልቤ ላይ ነግሰሻል ምልጃሽ እየጠበቀኝ። ርስታችን ነሽ እንወርስሻለን፣ በምድርሽ ወይንን እንለቅማለን። ይትረፈረፋል ጽዋችን ሞልቶ፣ አንቺን ይዘናል አናፍርም ከቶ። አሁን በደስታ ሥፍራ ይዘናል፣ መስቀል ላይ ሁኖ ጌታ ሰጥቶናል። ከዚህች ርስት ሚነቅለን የለም፣ አትሞበታል የደሙን ማህተም። ዳዊት አባትሽ እንዳለው ብረሳሽ ቀኘ ትርሳኝ፣ በልቤ ላይ ነግሰሻል ምልጃሽ እየጠበቀኝ። ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

"ለወዳጅህ ያኔ" ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

ብርና ወርቅ ሳይዙ ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ብርና ወርቅ ሳይዙ ዓለማትን ዞሩ ብርና ወርቅ ሳይዙ ዓለማትን ዞሩ ቅዱሳን ሐዋርያት ቃሉን እየዘሩ ሙታን እያስነሡ ድውያን ፈወሱ ስሙን ብቻ ይዘው(፪)ታምነው በንጉሡ ከቀራጩ መደብ ከሐጥያት ገበታ ከጥብርያዶስ ባሕር ከጠራቸው ጌታ ስሙን ተሸክመው ቃሉን መሰከሩ በመንፈስቅዱስ ኃይል ድንቅን እየሠሩ የነገስታቱን ቃል ዛቻውን ሳይፈሩ የመንግስቱን ወንጌል ለዓለም አስተማሩ ይሻለናል አሉ ማድላት ለእግዚአብሔር ለሰው ከመታዘዝ ዘላለም ለማይኖር ቆዳቸው ተገፎ በሰይፍ ተሰየፉ ስለጌታ ፍቅር በመከራ አለፉ የድንጋዩን ናዳ የእሣቱን ነበልባል የጀርባን ግርፋት በእምነት ታግሰዋል ስደት ነው መከራ ረሀብ ነው ወይስ ጥም ከክርስቶስ ወንጌል ከእውነት የሚያስቆም በእርሱ ስላመኑ በጽድቅ ተጋደሉ ደግሞም በእርሱ በላይ እንዳለ በቃሉ በዙርያችን ከበው ካሉ እንደ ደመና እነርሱን እያሰብን በእምነት እንፅና በእውነት እንደኖሩ መሥለው ክርስቶስን እኛም በኑሮችን እንምሰል እነርሱን ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

ፈቃዴ ነው የሰውን ነገር ላልናገር ሊቀ መዘምራን ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ፈቃዴ ነው የሰውን ነገር ላልናገር (×2) የኔ ተሸፍኖ ከቆምኩኝ በክብር ፈቃዴ ነው የሰውን ነገር ላልናገር ❖ ህይወቴ በሙሉ በሀጢአት ተመልታ አምላኬ ከማረኝ በፍቅር ዝምታ የሰው በደል ላላይ በእውነት ምያለሁ እኔን ከታገሰኝ ፍቅር ተምሬያለሁ(×2) ❖አዝ በአይኔ ፊት ተጋርዶ ያለውን ምሶሶ እያየ ካለፈኝ በምህረት ታግሶ የሰው ጉድፍ ላላይ በእውነት ምያለሁ እኔን ከታገሰኝ ፍቅር ተምሬያለሁ (×2) ❖ አዝ አንተ ቀራጩ ሰው ያለህ አቀርቅረህ በምህረት ተመለስክ ከኔ ይልቅ ድነህ በአንተ ላይ ስጠቁም የኔን ፀሎት ትቼ የመዳኑ ሰአት አለፉ ቀኖቼ (×2) ❖ አዝ ተቆጥሮ የማያልቅ በደሌ ተከድኖ በሞትና በደል ሀጢአቴን ሸፍኖ ሰው አርጎኝ በሰው ፊት አቁሞኝ ጌታዬ በማንም አልፈርድም ሀጢአተኛ ብዬ/በደለኛ ብዬ (×2) ❖❖❖ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

" ያጣነውን ሰላም " ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ «ወንድምህን አትናቀው» ወዳጄ ሆይ! ክርስቲያን ነህን? እንኪያስ በፍጹም ወንድምህን አትናቀው። እህትህን አትናቃት። ምንም ይሁን ምን ሰው አትናቅ ። ይህ የምትንቀው ወንድም በተለይ ክርስቲያን ከሆነ ክርስቶስን እየሰደብከዉ እንደሆን አስተውል ። "እንዴት"? ያልከኝ እንደሆንም ይህ የምትንቀው ወንድምህ የክርስቶስ ሕዋስ (ብልት) ሆኗል። የክርስቶስ ሕዋስ ከሆነ ደግሞ እሱን ናከው ማለት ክርቶስን ናከው ማለት ነው። ወንድምህን የምትንቅ ከሆነም በጲላጦስ አደባባይ ጌታን ከገረፉት ፣ እራቁቱን ከሰቀሉት፣ ሐሞትንና ከርቤን ቀላቅለው ከሰጡት፣ በፊቱ ላይም ከተፉበት ሰዎች በምንም አትተናነስም ። ስለዘህ ወንድምህን ከመናቅ ተጠንቀቅ ። + ከቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ + ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

"ቅድስት ሥላሴ" ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ "ኦ ርህሩሀነ ልቦና አፍቅሮተ ሰብእ ልማድክሙ በጥቡዕ ልብ ንስእለክሙ ሥሉስ ቅዱስ ምሕረተክሙ አዝንሙ ክሳደ ጸርነ በሰይፍክሙ ግዝሙ ወዲበ ርእስነ ካዕበ እዴክሙ ሲሙ !" ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

"መሠረቷ ጉልላቷ እርሱ ነው" ሙሽራዋም መስቀል ላይ የሞተው ዛሬም ነገም ያው ነው ለዘለዓለም አትንገሩን አዲስ ጌታ የለም /2x +++ የእንግዳው ትምህርት የጠላት እንክርዳድ በመከሩ ጊዜ ይለያል ሲታጨድ ጌታ ጌታ ያለው እንዲሁ በብልጠት አይወርስም ፈጽሞ የሰማዩን ርስት +++ አዝ+++ ራስ ለሆነለት ሆናለች አካሉ ትታዘዘዋለች ዘወትር ለቃሉ የፊት መጨማደድ ሳያገኛት ድካም ታምና ትኖራለች እስኪመጣ ዳግም +++ አዝ+++ የሰማዕታት ደም የከፈሉት ዋጋ የመላዕክቱ ዜማ የሰማዩን ፀጋ የሐዋርያት ስብከት የነቢያት ትንቢት ይገኛል በውስጧ በፀጋዋ ግምጃ ቤት +++ አዝ+++ ጎዳናውን ጥሰን ብንጓዝ በሐሰት ለአንደበታችን አውጀን አርነት አይዘጋም ደጅዋ አይጠፋም መብራቷ ኢየሱስ ነው ክብሯ ጌጥና ውቤቷ +++አዝ+++ ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

“አትፈርስም” ዘማሪ ዲ/ን ሙሉቀን ከበደ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09