en
Feedback
አዲስ የኦርቶዶክስመዝሙሮች እና አባባሎች

አዲስ የኦርቶዶክስመዝሙሮች እና አባባሎች

Open in Telegram

በዚህ ቻናል የተለያዩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙራት እና የፕሮፋይል ፎቶ የሚሆኑ ምስለ ስዕል የሚገኝበት ቻናል ነው....................................................................

Show more
304
Subscribers
+224 hours
+77 days
+6430 days
Posts Archive
"ገብረ መንፈስ ቅዱስ የዓለም ብርሃን ናቸው" | ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ገብረመንፈስ ቅዱስ የአለም ብርሀን ናቸው ፤ ፪ ይኸው ለዘላለም ያበራል ሥራቸው። ፪ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

“ርስታችን ነሽ ” ርስታችን ነሽ እንወርስሻለን፣ በምድርሽ ወይንን እንለቅማለን። ይትረፈረፋል ጽዋችን ሞልቶ፣ አንቺን ይዘናል አናፍርም ከቶ። የእንጀራ ምድር የፍቅር ሐገር፣ የለንም ወገን ካንቺ በስተቀር። በአክዓብ መሬት የማንቀይርሽ፣ ደጅሽ ቁመናል ባርኪን በእጆችሽ። ዳዊት አባትሽ እንዳለው፣ብረሳሽ ቀኘ ትርሳኝ፣ በልቤ ላይ ነግሰሻል ምልጃሽ እየጠበቀኝ። ርስታችን ነሽ እንወርስሻለን፣ በምድርሽ ወይንን እንለቅማለን። ይትረፈረፋል ጽዋችን ሞልቶ፣ አንቺን ይዘናል አናፍርም ከቶ። ወደ ምድራችን መጥተን ስንገባ፣ አንቺን አገኘን ታላቋን መባ፣ የሕይወት ውኃ ፈልቋል በሆድሽ፣ እንዳንጠማ ድንግል ልጆችሽ። ዳዊት አባትሽ እንዳለው ብረሳሽ ቀኘ ትርሳኝ፣ በልቤ ላይ ነግሰሻል ምልጃሽ እየጠበቀኝ። ርስታችን ነሽ እንወርስሻለን፣ በምድርሽ ወይንን እንለቅማለን። ይትረፈረፋል ጽዋችን ሞልቶ፣ አንቺን ይዘናል አናፍርም ከቶ። አሁን በደስታ ሥፍራ ይዘናል፣ መስቀል ላይ ሁኖ ጌታ ሰጥቶናል። ከዚህች ርስት ሚነቅለን የለም፣ አትሞበታል የደሙን ማህተም። ዳዊት አባትሽ እንዳለው ብረሳሽ ቀኘ ትርሳኝ፣ በልቤ ላይ ነግሰሻል ምልጃሽ እየጠበቀኝ። ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

ነፍሴ አደራ በሰማይ በመልዓከ ሰላም ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ አይራየኒ ዓይነሞት ወይርከበኒ ኩነኔ ነፍሴን አደራ በሰማይ(፬) ተክልዬ ፀሐይ ፅላል ዘረሬ ነይ መ ስክሪ የተክለሃይማኖትን ዝና አውሪ የእንቁርቁሪት ፀበል ማር ወተት ሁሉም ተፈወሱ ሲጠጡት(፪) ትህትናህ ግሩም ነው ቅድስናህ ሃይቅ እስጢፋኖስ አገልግላህ ደብረ ዳሞ ዘልቀህ ክንፍ አወጣህ ደብረ ሊባኖስ ላይ ፍፁም ፀናህ ደብረ ሊባኖስ ላይ አርፏል አፅምህ አተታና ዳሞ ተሻግረህ ማንያንን ሁሉ አሳፈርህ በንብ ቀፎ አርገው ቢጥሉህ ሚካኤል በክንፉ አቀፈህ(፪) በደብረ አስቦ ውስጥ ጦር ተክለህ ሃያ ዘጠኝ ዘመን ተጋድለህ ወዝህ ያረፈበት ነጠብጣቡ ድውይ ይፈውሳል ቃል ኪዳኑ (፪) ይህን ሁሉ ፀጋ ተችረሃል ቁጥርህ ከመላእክት ጋር ተስተካክሎዋል አባቴ (፪) ስልህ ነፍሴን ታደግልኝ በምልጃህ(፪ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

"በፍቅር ላዚምህ" ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ በፍቅር ላዚምህ በፍቅር ላዚምህ ፍቅር ነህ ጌታዬ በደም የገዛኸኝ ባለውለታዬ በቃየን ጎዳና እንዳልጓዝ እርዳኝ በቀናው መንፈስህ ወደ ጽድቅ ምራኝ በልቤ ትከሻ በቀል ተሸክሜ ወንድሜን ጠልቼ ካንተ ፊት መቆሜ ፃድቅ ቢያስመስለኝ በሰዎች እይታ ጉዴን ስለምታውቅ እስራቴን ፍታ(፪) አዝ = = = = = ዙሪያውን ተከቦ በእሾህ ጥላቻ ስብከቴ መዝሙሬ ሆኗል የቃል ብቻ ማረኝ እና ይብቃኝ ለኃጢአት መዝመቱ ፍቅር የሌለው ሰው ነው የከንቱ ከንቱ(፪) አዝ = = = = = አሸንፈህልኝ እኔ ግን ተሸነፍኩ በእጄ ማልነካውን ለሰው እያሸከምኩ በቃሌ ጠርቼ በግብሬ ረገምኩህ በአስመሳይ ማንነትእየሸነገልኩህ(፪) ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

"እግዚአብሔር መልካም ነው" እግዚአብሔር መልካም ነው በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው/2/ አዝ ------------- ከገነት ሲሰደድ አዳም አባታችን ሞት ነግሶብን ሳለ በእኛ በሁላችን ቃል እንደገባለት ተወልዶ ሊያድነን በመከራ ጊዜ መሸሸጊያ ሆነን/2/ አዝ ------------- አብርሃም ከካራን ከእናት ከአባቱ ቤት ከነአን ሲገባ ሲሰደድ በእምነት ከተሰጠው ተስፋ አንዳች ሳይጎልበት እንደ ምድር አሸዋ ዘሩን አበዛለት/2/ አዝ ------------ በሐዘን በችግር በመከራ ጊዜ ጭንቀቴን የሚያርቅ ነው የፍሴን ትካዜ የቀደመው እባብ ሰላሜን ሲነሳኝ እግዚአብሔር መልካም ነው ሐዘኔን አስረሳኝ የቀደመው እባብ ሰላሜን ቢነሳኝ ክርስቶስ ኢየሱስ ሐዘኔን አስረሳኝ ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

“ እመቤቴ የአምላክ እናት" ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ እመቤቴ የአምላክ እናት ላመስግንሽ ቀን ከለሊት ለልጅሽም ክብር ዉዳሴ ታቀርባለች ዘወትር ነብሴ(2) ልቤ ተነሳሳ ተቀኘ ለክብርሽ በፍፁም ትህትና ሊያመሰግንሽ ጽዩን መጠጊያ ነሽ የአብረሐም ድንኳን የታጠረች ድንኳን እመ ብረሐን አዝ የለመለመች መስክ አመላክ የመረጣት የጽላቱ ኪዳን ታቦቱ ድንግል ናት የሰማይ የምድር ንግስት ነሽና ከብር ይገባሻል ዘወትር ጠዋት ማታ አዝ አደራሽን ማሪያም የሁሉ እናት በምልጃሽ አስቢኝ ሗላ ስራቀት ያንን የእሳት ባሕር አሻግሪኝ ድንግል ሆይ እንዳልወድቅ እንዳልሞት ከቶ እንዳላይ ስቃይ አዝ እመብርሐን ለሀገራችን ሰላም ለህዝባችን ፍቅር አንድነት ትስጥልን🙏 ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

"ኃያልነህ ነህ አንተ ኃያል ደጉ መልአክ ገብርኤል" ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ኃያል_ነህ(አምባሰል) ኃያል ነህ አንተ ኃያል ደጉ መልአክ ገብርኤል(፪) ይውደቅ ይሸነፍ ጠላት አንተ ተራዳን በእውነት(፪) በዱራ ሜዳ ላይ ገብርኤል ጣዖት ተዘጋጅቶ ” ” ሊያመልኩት ወደዱ ” ” አዲስ አዋጅ ወጥቶ ” ” ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ጸኑ ጣዖቱን እረግጠው በእግዚአብሔር አመኑ ተቆጣ ንጉሡ ገብርኤል በሦስቱ ሕፃናት ” ” ጨምሯቸው አለ ” ” ወደ እቶን እሳት ” ” ከሰማይ ተልኮ ደረሰ መላኩ ከሞት አዳናቸው በእሳት ሳይነኩ ከቶኑ ስር ሆነው ገብርኤል ዝማሬ ተሞሉ ” ” ገፍተው የጣሏቸው ” ” በእሳቱ ሲበሉ ” ” አልተቃጠለችም የራሳቸው ፀጉር አዩት መኳንቱ የእግዚአብሔርን ክብር ናቡከደነፆር ገብርኤል እጁን በአፉ ጫነ ” ” ሠለስቱ ደቂቅን ” ” ከእሳት ስላዳነ ” ” ይክበር ጌታ አለ የላከው መልአኩን ሊያመልከው ወደደ ስላየ ማዳኑን ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

" ከእኔ የበረታችሁ" ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ከኔ የበረታችሁ\2\ አስቡኝ በፀሎታችሁ\2\ ***** የትናንት ትጋቴ ባይኖር ከእኔ ጋራ እኔን ባታዩኝም በመልካሙ ስራ ሸክሜን ተሸክሙ አትፍረዱ በእኔ ነጌ መውደቅ አለ የቆምከው ወገኔ ***** ከበሮ የያዝሺው የሙሴ እህት ማርያም፣ ሀጥያት ያደረገው ሙሴ ቢመስልሽ ጥቁሪቱን አጋባ ወድቋል አትበይ ነገ መውደቅ አለ የቆምከው ወገኔ ***** ከትእዛዛቱ አትወድቅም አንዲቱ የህግ ትንሽ የለም እኩል ነው ቅጣቱ ቢመስልም በፊትህ ስራዬ የከፋ ፍርዱን ተወውና ፀልይ እንዳልጠፋ ***** አዋቂ ነው ጌታ ሁሉን ይመዝናል ድካምን ሳይቆጥር በፀጋው ያቆማል ብርቱ የሆናችሁ ለደካማው ትጉ ለፍርድ እጅን ሳይሆን ርህራሄን ዘርጉ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

🔴 አዲስ ዝማሬ " ይችላል ሚካኤል " ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

እልልል እልልል ደስ ይበለን እልል ደስ ይበለን (2) አጅበን መጣን ታቦተ ህጉን እልልል ብላችሁ ተቀበሉን (2) የቃልኪዳን ታቦት እልል ደስ ይበለን የክብሩ ዙፋን እልል ደስ ይበለን ከመንበሩ ወርዶ እልል ደስ ይበለን እየባረከን እልል ደስ ይበለን ቅዱሱ መፅሀፍ እልል ደስ ይበለን እንደነገረን እልል ደስ ይበለን ወጣን ከሠፈሩ እልል ደስ ይበለን እየተከተልን እልል ደስ ይበለን አጅበን መጣን ታቦተ ህጉን እልልል ብላችሁ ተቀበሉን (2) የሠማዩ መቅደስ እልል ደስ ይበለን በላይ ሲከፈት እልል ደስ ይበለን ተገልጦ አየንው እልል ደስ ይበለን የክብሩ ታቦት እልል ደስ ይበለን እልልታ ዝማሬ እልል ደስ ይበለን እናቅርብ ምስጋና እልል ደስ ይበለን ታቦቱ ልጆቹን እልል ደስ ይበለን ሊባርክ ነውና እልል ደስ ይበለን አጅበን መጣን ታቦተ ህጉን እልልል ብላችሁ ተቀበሉን (2) በውስጥና በውጭ እልል ደስ ይበለን በወርቅ ተለብጦ እልል ደስ ይበለን የእግዚአብሔር ቸርነት እልል ደስ ይበለን በርሱ ላይ ተገልጦ እልል ደስ ይበለን እስራኤል በምህረት እልል ደስ ይበለን ከሞት ተከለለ እልል ደስ ይበለን ታቦቱ ሲነካው እልል ደስ ይበለን ባህር ተከፈለ እልል ደስ ይበለን አጅበን መጣን ታቦተ ህጉን እልልል ብላችሁ ተቀበሉን (2) በእግዚአብሔር ጣቶች እልል ደስ ይበለን ተቀርፆ ትዛዙ እልል ደስ ይበለን ካህናቱ ይዘው እልል ደስ ይበለን በስርአት ሲጉዋዙ እልል ደስ ይበለን ወድቀን እንሰግዳለን ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

"እርሱ ፍጹም ሊልቅ" ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ✞ እርሱ ፍጹም ሊልቅ እኔ ላንስ ይገባል ከኔ ይልቅ ጌታ እጅግ ይበረታል እኔ ለንስሐ በውሃ አጠመቅኳችሁ በእሳት ያጠምቃል ይመጣል ያልኳችሁ(፪) ጫማውን ልሸከም ከቶ የማይገባኝ እኔን አስቀድሞ ለአገልግሎት ጠራኝ ከኋላዬ የመጣው ነበረ ከፊቴ በስሙ ታምኑ ዘንድ እርሱ ነው ስብከቴ አዝ= = = = = በምድረ በዳ ላይ የጮህኩለት ንጉሥ የኃያላን ኃያል ተገልጿል ኢየሱስ ለኃጢያት ስርየት ይሰዋል ይኄ በግ ለዓለም ሁሉ መዳን በቀራንዮ ሠርግ አዝ= = = = = ለንስሐ የሚሆን ፍሬ ዛሬ አድርጉ በሠርጉ ሊጠራን መጥቷልና በጉ ከሚመጣው ቁጣ በእርሱ እንድታመልጡ የእፉኝት ልጆች ከባቢሎን ውጡ አዝ= = = = = የአብርሃም ልጆች ነን በማለት ላትድኑ የመዳኑን ሰዓት ቀኑን አታባክኑ ለአብርሃም ልጆች ከድንጋይ ያስነሳል መንሹንም በእጁ ነው አውድማው ይጠራል አዝ= = = = = ጠማማው ልብ ይቅና ጥርጊያው ይደላደል ፍሬ የሌለው ዛፍ በእቶን ሳይቃጠል ምሳር በዛፎች ስር ዛሬም ተቀምጧል ንስሐ ግቡ ነው የመጨረሻው ቃል "እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል" ዮሐ ፫ ፥ ፴ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

"በእደ ዮሐንስ ተጠምቀ" ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ በእደ ዮሀንስ ተጠምቀ ኢየሱስ ናዝራዊ ሰማያዊ ሰማያዊ ሰማያዊ ኢየሱስ ናዝራዊ እንኳን ለጌታችን እና ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀቱ በሰላም እና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ !! "ያመነ የተጠመቀ ይድናል ያላመነ ግን ይፈርድበታል" ማር 16÷16 ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

+6
የኦርቶዶክስ መዝሙሮች: 💚@mzemur_orthodox💚 💛@mzemur_orthodox💛 ❤@mzemur_orthodox❤ 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

+5
የኦርቶዶክስ መዝሙሮች: 💚@mzemur_orthodox💚 💛@mzemur_orthodox💛 ❤@mzemur_orthodox❤ 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

Ye temket mezmur kalachu please lakulegh 🙏🙏

የኦርቶዶክስ መዝሙሮች: 💚@mzemur_orthodox💚 💛@mzemur_orthodox💛 ❤@mzemur_orthodox❤ 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

🔴 "እግዚኡ መርሐ" ሊቀ መዘምራን ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ * "እግዚኡ መርሀ" እግዚኡ መርሀ ዮርዳኖስ አብጽሃ፤(2) ወበህየ ዮሐንስ (2) ፍጽመ ተሰብሃ ጌታውን መራና ዮርዳኖስ አደረሰው (2) በዚያች ዕለት ዮሐንስ (2) በፍፁም ደስ አለው ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

+++++++ የጥበብ ሰዎች መጡ +++++++ ሰማይና ምድር የማይወስኑትን ተወስኖ አየነው በጠባብ ደረት ዘጠና ዘጠኙን መላእክትን ትቶ አገኘነው ዛሬ በበረት ተኝቶ አዝ ------------ የጥበብ ሰዎች መጡ/2/ ሰምተውት በዜና /2/ እያበራላቸው ኮከብ እንደፋና /2/ አዝ ----- ድንግል እመቤቴ ሰላምታ ይድረስሽ ለአምላክ ወገኖች መመኪያቸው የሆንሽ ከአንቺ ተወለደ የዓለም መድኅን ኩነኔን አጥፍቶ ጽድቅን ሊያወርሰን አዝ --------------------- ጌታችን ሲወለድ በቤተልሔም ሐዘን ተደምስሶ ሰፈነ ሰላም እንጨቶች አፈሩ ፍሬ በረከት ወንዞች ሁሉ ሆኑ ማርና ወተት አዝ --------------------- ሰብአ ሰገል መጡ ሊሰግዱ በሙሉ የእስራኤል ንጉሥ ወደ የት አለ እያሉ እጅ መንሻውን ሰጡት እንደየሥርዓቱ እጣኑን ለክህነት ወርቁን ለመንግሥቱ አዝ --------------------- ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

ወዳንቺ የመጣው (ዘማሪ ይልማ ኃይሉ) ወዳንቺ የመጣው በብሩህ ደመና ከሦስቱ አካል አንዱ ክርስቶስ ነውና የጠፋ በግ አዳም ታደሰ በጌታ ባንቺ ተፈፀመ የሰው ልጆች ደስታ አዝ …………… ደይን የተባለች ሄዋን ተደሰተች የደስታ መፍለቂያ አንቺን ስላገኘች የበረከት ፍሬ ካንቺ ተገኘልን የወይን ቦታ ነሽ ድንግል እናታችን አዝ …………… ወልድም ባህሪሽን ባህሪ አድርጐት ለፍጥረታት ጌታ መዓዛሽ ተስማምቶት ካንቺ ይወለድ ዘንድ ፍፁም ሊላላክሽ በጥቂቱ አደገ ተልኮና ታዞሽ አዝ …………… ከድንግልና ጋር አንድ የሆነ ሀሊብ በሩካቤ ሳይሆን በመስማት እንደ ንብ ከሆድ መጥበብ ጋራ የመለኮት ስፋት አንቺ ሆነሽ ሳለ ታናሿ ሙሽሪት አዝ …………… በፍጡር ህሊና የማይመረመር እፁብ ነው ድንቅ ነው የመፅነሷ ነገር እሳት ወነበልባል በሆድሽ ውስጥ ሲያድር ነደ ነበልባሉ አልፈጀሽም ነበር ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09

አንቺ አንቺ ቤተልሔም አንቺ አንቺ ቤተልሔም የይሁዳ መሬት ባንቺ ተወለደ የዓለም መድኃኒት(፪) ለአዳምን ክብር ሲሻ ----> ቤተልሔም ለሁሉም ሰላም ----> ቤተልሔም ጌታ ተወለደ ----> ቤተልሔም ከድንግል ማርያም ----> ቤተልሔም አዝ .... እጅ መንሻ አቀረቡ ----> ቤተልሔም የምስራቅ ነገሥታት ----> ቤተልሔም ሕፃኑን ከእናቱ ----> ቤተልሔም ተኝቶ ላገኙት ----> ቤተልሔም አዝ .... እስራኤልን በግብፅ ----> ቤተልሔም የሚጠብቃቸው ----> ቤተልሔም ከአንቺ ይወጣል ብሎ ----> ቤተልሔም እንደነገራቸው ----> ቤተልሔም አዝ .... ቅዱሳን መላእክት ----> ቤተልሔም ያሸበሸቡብሽ ----> ቤተልሔም ስብሐት ለእግዚአብሔር ----> ቤተልሔም ብለው ዘመሩብሽ ----> ቤተልሔም አዝ .... አንቺ ቤተልሔም ----> ቤተልሔም እንዴት ታድለሻል ----> ቤተልሔም ኢዮርና ራማ ----> ቤተልሔም ኤረርን መስለሻል ----> ቤተልሔም ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09