cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

StockMarket.et

Join our Telegram channel for the latest news, analysis, and insights on the stock market, money, finance, and business. 🌐 Web: https://www.stockmarket.et/

Show more
Advertising posts
1 114
Subscribers
+224 hours
+977 days
+11030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

📖 ዛሬ ከካፒታል ገበያ መዝገበ ቃላት ስለ አርቢትሬጅ (Arbitrage) እናያለን። አርቢትሬጅ (Arbitrage) በተለያዩ የግብይት መድረኮች የሚሸጡ ተመሳሳይ ኢንቨስትመንቶች ላይ ሊፈጠሩ የሚችሉ የዋጋ ልዩነቶችን ለትርፍ መጠቀም ማለት ነዉ። ለምሳሌ የአንድ ኩባንያ አክሲዮን በአንድ የአክሲዮን ልውውጥ ገበያ 100 ብር በሌላ ግን 110 ብር እየተሸጠ ነው እንበል። በዚህ ሁኔታ የአርቢትሬጅ እድል ተፈጠረ ማለት ነዉ። አንድ ኢንቨስተር በአንደኛው አክስዮን ልዉዉጥ 100 ብር ገዝቶ ወዲያውኑ በ110 ብር በሁለተኛው በመሸጥ ለአንድ አክሲዮን 10 ብር ትርፍ ኪሱ ያደርጋል። ይህ ሂደት በተለያዩ ገበያዎች ዋጋዎችን ለማመጣጠን ይረዳል እና ንብረቶቹ በተቀላጠፈ ዋጋ እንደሚሸጡ ያረጋግጣል። ነገር ግን በአሁን ዘመን ባለው ፈጣን ቴክኖሎጂና ከፍተኛ ትስስር ባላቸው የካፒታል ገበያዎች ውስጥ ብዙ ነጋዴዎች እንዲህ ያሉ የአርቢትሬጅ እድሎችን በፍጥነት ለመለየት እና እርምጃ ለመውሰድ ፈጣን ኮምፒውተሮችን ስለሚጠቀሙ የአርቢትሬጅ እድሎቹን ሳናስተዉል በፊት በፍጥነት ይጠፋሉ። LinkedIn |𝕏| Facebook | Telegram |YouTube
Show all...
3

በዓሉ ሠላምን፣ ደስታን እና ትርፋማ ኢንቨስትመንቶችን እንዲያመጣልዎት ከልብ እንመኛለን!
LinkedIn |𝕏| Facebook | Telegram |YouTube
Show all...
👍 4😁 2
የበዓል እንቁላል ገዝታችሁ እንዴት ነው የምትይዙት? 🤔 Diversification ማለት ገንዘብዎን በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዓይነቶች ላይ ማሰራጨት ማለት ነው። ሁሉንም ገንዘብዎን በአንድ ኩባንያ ወይንም በአንድ አይነት የፉይናንስ መሣሪያ ላይ ብቻ ከማስቀመጥ ይልቅ በተለያዩ ኩባንያዎች ላይ አና እንደ አክሲዮኖች፣ ቦንዶች፣ ሪል እስቴት እና በሌሎችም ድብልቅ የፉይናንስ መሣርያዎች ላይ ኢንቨስት ማድረግ ማለት ነው። በዚህ መንገድ፣ አንዱ ኢንቨስትመንት ጥሩ ካልሰራ ሌሎቹ ገንዘቡን ማካካስ ይችላሉ። ስለዚህ የበዓል እንቁላልሉን ስትገዙ፣ በተለያዩ ቅርጫቶች አሰራጭቶ መያዝ። ድንገት አንዱ ቅርጫት ቢወድቅ፣ ሌለው አለ! መልካም የበዓል ዋዜማ ይሁንላችሁ 😊 LinkedIn |𝕏| Facebook | Telegram |YouTube
Show all...
9👍 1

ተጨማሪ የመንግስት የልማት ድርጅቶች በሰነደመዋለንዋይ ገበያው ላይ ይዘረዘራሉ።
ከቅርብ ጊዜያት በፊት ይፋ እንደሆነውም መንግሥት የኢትዮ ቴሌኮምን አሥር በመቶ ድርሻ ለሕዝብ እንደሚሸጥ ገልጾ ነበር፡፡ ምን ያህል መጠናቸው እንደሆነ ውሳኔ ላይ ባይደረስም ሌሎች አምስት የልማት ድርጅቶች ድርሻዎቻቸው በገበያው ላይ እንዲሸጡ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ መወሰኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ አብዱረህማን ዒድ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ድርሻቸው ለሽያጭ የሚቀርበው የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት (አባትሎአድ)፣ የኢትዮጵያ መድኅን ድርጅት፣ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት፣ የትምህርት ማምረቻና ማሠራጫ ድርጅትና የኢትዮጵያ የቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት ሲሆኑ፣ አምስቱ ተጨማሪ የልማት ድርጅቶች፣ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመሆን ስድስት ድርጅቶች ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ላይ ድርሻቸውን ይሸጣሉ፡፡ Reporter LinkedIn |𝕏| Facebook | Telegram |YouTube
Show all...
🔥 4👍 1
ዛሬ የሚከበረው አለምአቀፍ የላብ አደሮች ቀን መነሻ የሆነው እ.ኤ.አ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ ሰራተኞች ለተሻለ የስራ ሁኔታ ለምሳሌ አጭር የስራ ሰአት እና አግባብ ያለዉ ክፍያ ለማግኘት ያደረጉት ትግል ነዉ።  ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሠራተኞች እና መብቶቻቸው የሚከበርበት ቀን ነው። ከኢኮኖሚያዊ ፋይዳዉ አንፃር ስንመለከተዉ፤ አለምአቀፍ የላብ አደሮች ቀን ለሰራተኞች ፍትሃዊ አያያዝ እንደሚያስፈልግ ስለሚያስታውስ ይህም ደስተኛ ሰራተኞችን፣ የተሻለ ምርታማነትን እና በአጠቃላይ ጠንካራ ኢኮኖሚን ​​ያመጣል። LinkedIn |𝕏| Facebook | Telegram |YouTube
Show all...
🔉Exciting news! Applications for the 2nd cohort internship program are now open! Are you studying business, economics, finance, or related fields, or do you have a strong interest in financial and capital markets and want to deepen your knowledge? The StockMarket.et internship program offers just that! This 10-week remote program gives you practical insights and a well-rounded skill set. Internship Highlights: 1. Comprehensive overview of the Capital Market 2. Development of problem-solving skills 3. Practical application of programming in a business context 4. From planning to execution, learn to build a business from the ground up 5. Researching 6. Writing well-crafted articles 7. A chance to publish your articles 8. And a lot of more cool stuff  Don't miss out on this opportunity to take your career into new heights! Deadline: May 12, 2024 Apply here ➡️ https://www.stockmarket.et/internship-application/ For more information: https://t.me/stockmarket_et LinkedIn |𝕏| Facebook | Telegram |YouTube
Show all...
🔥 5👍 2🥰 2
🎥Wall Street (1987) በኦሊቨር ስቶን ዳይሬክት የተደረገዉ ይህ ክላሲክ ድራማ ፊልም፣ ጎርደን ጌኮ የተባለ ታዋቂ፣ ጨካኝና ሀብታም ኢንቨስተር እና በድ ፎክስ የተባለ ወጣትና ህልመኛ የአክሲዮን ደላላን ያጣምራል። ፊልሙ ሰዎች ሀብትን እንዴት እንደሚያሳድዱ፣ አደገኛ እንቅስቃሴዎችን እንደሚያደርጉ እና ከባድ ምርጫዎችን እንደሚጋፈጡ በአጠቃላይ በፋይናንስ አለም ስኬት ፍለጋ ዉስጥ የሚያጋጥሙትን የሞራል ግጭቶች ያሳያል። ተጋበዙልን😀🍿 LinkedIn |𝕏| Facebook | Telegram |YouTube
Show all...
👍 6🔥 2 1
የበርክሻየር ሃታዌይ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት ቻርሊ ሙንገር በኢንቨስትመንት ውስጥ ትዕግስት ያለውን ጠቀሜታ በማጉላት የሰጡት ጥቅስ እነሆ፡-
ትልቁ ገንዘብ በመግዛት ወይም በመሸጥ ላይ ሳይሆን በመጠበቅ ላይ ነው።
ትዕግስት በኢንቨስትመንት አለም ውስጥ ቁልፍ ሚና አለዉ። ይህም በስሜታዊነት ላይ የተመሰረቱ የኢንቨስትመንት ውሳኔዎችን እንድናስወግድ ይረዳናል። በትዕግስት መቆየት ለገቢያ ውጣ ውረድ ወይም አርዕስተ ዜናዎች አፋጣኝ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ በረጅም ጊዜ ግቦች ላይ በመመስረት ምክንያታዊና ጥንቃቄ የተሞሉ ምርጫዎችን እንድንወስድ ያስችለናል። LinkedIn |𝕏| Facebook | Telegram |YouTube
Show all...
👍 8 1