cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Mamsha Tube 🟢🟡🔴

ጥሩ ሃሳብ ,አዉንታዊ ስሌት Good idea, realistic calculation. The world of entertainment is a channel where rumors, self-talk, and various issues are discussed ለመረጃ....@Adamuawoke

Show more
Advertising posts
189
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-1130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

💧mamsha Tube Find us on • ꜰᴀᴄᴇʙᴏᴏᴋ https://fb.me/Adamu Awoke • yᴏᴜᴛᴜʙᴇ https://https://www.youtube.com/@Mamsha16 • ᴛɪᴋᴛᴏᴋ https://tiktok.com/@mamsha19 • ɪɴꜱᴛᴀɢʀᴀᴍ https://instagram.com/mamshaye16 ለመረጃ....@Adamuawoke
Show all...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

አምስት ሚሊዮን ዩሮ ከአሰሪዋ የተሰጣት እድለኛዋ ሞግዚት የ80 አመቷ አዛውንት ያላትን ገንዘብ ሁሉ ለዓመታት ስትንከባከባት ለቆየችው ሞግዚት አውርሳለች አምስት ሚሊዮን ዩሮ ከአሰሪዋ የተሰጣት እድለኛዋ ሞግዚት ማሪያ ማልፋቲ የተሰኘች የ80 ዓመት አዛውንት በጣልያኗ ትሬንቶ ግዛት በምትገኘው ሮቬርቶ ከተማ ነዋሪ ነበረች፡፡ የቀድሞ ቬና ምክር ቤት አባል የሆችው እኝህ አዛውንት ልጅም ሆነ ትዳር አልነበራቸውም፡፡ እድሜያቸው እየገፋ ሲመጣም አዛውንቷ ስምንት እህት እና ወንድም ልጆች ንብረታቸውን እንደሚወርሱ እርግጠኞች ነበሩ፡፡ አክስታቸውን ሳይንከባከቡ ንብረታቸውን ብቻ ሲያዩ የቆዩት እነዚህ ሰዎች በመጨረሻም በእርጅና ምክንት ህይወታቸው ያለፈችውን አክስታቸውን ንብረት ለመውረስ ቢሞክሩም አልተሳካም፡፡ እኝህ አዛውንት ህይወታቸው ከማለፉ በፊት ለረጅም ዓመታ ስትንከባከባቸው ለነበረችው አልባኒያዊት ሞግዚታቸው 5 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸውን ንብረቶች እና በባንክ የሚገኝ ገንዘባቸውን አውርሰዋል፡፡ አዛውንቷ ሲያመኝ እ ሰው ሲያስፈልገኝ የጠየቀኝ ሰው የለም፣ ዘመዶቼ ይልቅ ሞግዚቴ ብዙ ነገሮችን አድርጋልኛለች ንብረተንም ለዚች ሰው አውርሻለሁ ሲሉ አስቀድመው መጨረሳቸውን ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡ የአክስታቸውን ንብረት ለመውረስ አስበው የነበሩት ዘመዶቿም በውሳኔው መደንገጣቸውን እና ያልጠበቁት እንደገጠማቸው በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡ እነዚህ የሟች ዘመዶችም ሞግዚቷ የአክስታቸውን መጃጀት በመጠቀም ንብረቶቿን ሁሉ እንዲያወርሷት ሳታደርግ እንዳልቀረች ጥርጣሬ እንዳላቸው ተናግረዋል፡ አል ዓይን Adamu Awoke
Show all...
ሶማሊያ ዜጎቿን በሞት የምትቀጣበት የባሕር ዳርቻው የእግር ኳስ ሜዳ በሽብር፣ በቦምብ ጥቃት የምትታወቀው ሶማሊያ ነጭ አሸዋ የተንጣለሉባቸው ውብ የሆኑ የባሕር ዳርቻዎች መገኛ ናት። ሰማያዊ የሆነውን የሕንድ ውቅያኖስ ተንተርሶ የሚገኘው የሞቃዲሾ የባሕር ዳርቻም አንደኛው ነው። በባሕር ዳርቻው አሸዋ ላይ በቆሙት ምሰሶዎች ታዳጊዎች እግር ኳስ ይጫወቱበታል። ይህ ስፍራ ከውብነቱ እና ከመዝናኛነቱ ባሻገር ሶማሊያ አጥፍተዋል ያለቻቸውን ሰዎች በሞት የምትቀጣበት ስፍራም ነው። ማስጠንቀቂያ፦ ይህ ጽሑፍ አንዳንድ ሰዎችን ሊረብሹ የሚችሉ ይዘቶች አሉት። አብዛኛውን ጊዜ የፀጥታ ኃይሎች ወንዶችን በዚህ ስፍራ ይዘው ይመጣሉ። ከምሰሶዎቹ ጋር በፕላስቲክ ገመድ ጠፍረው ያስሩዋቸው እና ጥቁር ልብስ ጭንቅላታቸው ላይ አጥልቀው ጥይት ይተኩሱባቸዋል። እነዚህን ወንዶች የሚገድለው ተኳሹ ቡድን አባላትም ፊታቸው የተሸፈነ ነው። እነዚህ የተገደሉ ሰዎች ጭንቅላታቸው ዘንበል ቢልም ሰውነታቸው በገመድ ከምሰሶዎቹ ጋር ተጠፍሮ ቀጥ እንዳለ ይታያል። ልብሶቻቸውን ንፋሱ እያውለበለበው አካላቸው ሲጋለጥም በዚያ አካባቢ ማየት የተለመደ ነው። አንዳንዶቹ ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ያህል ሽብርን በማስፋት እና ሰፊውን የአገሪቱን ክፍል የተቆጣጠረው አልሻባብ አባል ናችሁ በሚል በወታደራዊው ፍርድ ቤት የሞት ቅጣት የተፈረደባቸው ናቸው። በዚህ የእግር ኳስ ሜዳ በግድያ የሚቀጡት ሌሎቹ ደግሞ ሰላማዊ ዜጎችን ወይም ባልደረቦቻቸውን በመግደል ጥፋተኛ ሆነው የተገኙ ወታደሮች ናቸው። አልፎ አልፎም ይህ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ወንጀላቸው ከበድ ያለ ሲቪሎች ላይም ብያኔ ያስተላልፋል። ባለፈው ዓመት ቢያንስ 25 የሚሆኑ ሰዎች በባሕር ዳርቻው ላይ ተገድለዋል። በቅርቡ የሞት ፍርድ ተፈጻሚ የሆነበት ሰኢድ አሊ ሞአሊም ዳውድ ይሰኛል። ግለሰቡ ሉል አብዲአዚዝ የተሰኘችውን ባለቤቱን በአንድ ክፍል ውስጥ ቆልፎ በሕይወት እያለች አቃጥሎ በመግደሉ በሞት እንዲቀጣ ተፈርዶበታል። ሚኒስቱን እንዲህ ባለ ጭካኔ የገደላትም ፍቺ ስለጠየቀችው እንደሆነ ተናግሯል። ግድያዎች ከሚፈጸሙበት ስፍራ በስተጀርባም ጊዜያዊ መጠለያዎች እና የፈራረሱ መኖሪያ ቤቶች ያሉበት መደበኛ ያልሆነ ሰፈር አለ። የቀድሞ የፖሊስ አካዳሚ በነበረበት በዚህ ስፍራ ከ50 በላይ አባወራዎች ይኖራሉ። የእነዚህ ነዋሪዎች ልጆችም መዋያቸው ይህ የሞት መቀጫው የእግር ኳስ ሜዳ ነው። “አምስቱ ትንንሽ ልጆቼ ከትምህርት ቤት ወዲያውኑ ተመልሰው ወደ ባሕር ዳርቻው እግር ኳስ ሜዳ ለመጫወት ይሮጣሉ” ትላለች በስፍራው ነዋሪ የሆነችው ፋርቱን መሐመድ እስማኤል። ህጻናቱ ግድያዎቹ የሚፈጸሙባቸውንም ምሰሶዎች እንደ ጎል እንደሚጠቀሙባቸውም ይህቺው እናት ትናገራለች። “ሰዎች ተተኩሶባቸው በሚገደሉበት እና ደም በሚረጭበት ስፍራ ስለሚጫወቱ የልጆቼ የጤንነት ሁኔታ ያስጨንቀኛል” ስትልም ለቢቢሲ ገልጻለች። “ግድያዎች ከተፈጸሙም በኋላ አካባቢው አይጸዳም።” ተተኩሶባቸው የተገደሉ የእነዚህ ግለሰቦች መቃብሮች በባሕር ዳርቻው አካባቢዎች ይገኛሉ። Naima Said Salah ለአስርት ዓመታት በግጭት በምትናጠው ሞቃዲሾ ውስጥ የተወለዱት ልጆቿ አመጽ እና ሁከትን መላመዳቸውን ይህችው እናት ትናገራለች። ሆኖም እሷም ሆነች ሌሎች ወላጆች የግድያ ቅጣቶች በሚፈጸምበት ሜዳ ውስጥ ልጆቹ መጫወታቸው የሚረብሽ እንደሆነ ያምናሉ። ነገር ግን ልጆቹ ከጓደኞቻቸው ጋር በባሕር ዳርቻው ሜዳ ላይ እንዳይገኙ መከልከል ኑሮን ለማሸነፍ ለሚሯሯጡት ወላጆች ፈታኝ ተግባር ሆኖባቸዋል። የሞት ቅጣቶቹ አብዛኛውን ጊዜ የሚፈጸሙት ማለዳ ከ12 እስከ 1 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ነው። እነዚህን የሞት ቅጣቶች እንዲያዩ የሚጋበዙት ጋዜጠኞችም ቢሆኑ ህጻናትን ጨምሮ የአካባቢው ነዋሪዎች መሰብሰብ እና መመልከትን የሚከለክላቸው የለም። ይህ የባሕር ዳርቻው ሜዳ ለግድያ ስፍራነት የተመረጠው በአውሮፓውያኑ 1975 በሲያድ ባሬ አገዛዝ ዘመን ነበር። ይህ ስፍራ እንዲመረጥ ዋነኛ ምክንያት የነበረው በአቅራቢያው ያሉ ነዋሪዎች እንዲመለከቱ በሚል ነው። የወቅቱ ወታደራዊ አገዛዝ ለሴቶች እና ወንድ ልጆች በውርስ ላይ እኩል መብት እንዲኖራቸው የሚደነግገውን የቤተሰብ ሕግ የተቃወሙ የእስልምና የሃይማኖት አባቶችን ለመግደል ነበር ምሶሶዎቹን ያቆማቸው። AFP ወላጆች በአሁኑ ወቅት እያስጨነቃቸው ያለው ግድያዎቸን መመልከታቸው የልጆቻቸውን መንፈስ ይረብሻል የሚል ብቻ ሳይሆን፣ ድንገተኛ ተባራሪ ጥይት ሊያገኛቸው ይችላል የሚለው ስጋት ጭምር ነው። ልጆቹ በሚያዩዋቸው ግድያዎች ምክንያት ፖሊስ እና ወታደሮችን በከፍተኛ ሁኔታ ይፈራሉ ይላሉ። “ጠዋት ላይ የተኩስ ድምጽ ስሰማ ሰው መገደሉን አውቃለሁ” ትላለች። “ልጆቼ ከቤት እንዳይወጡ ለማድረግ እሞክራለሁ። ወደ ውጭ ስንወጣ በአሸዋው ላይ የምናየው ደም የሚዘገንን ነው” በማለትም ታስረዳለች። ምንም እንኳን ግድያዎቹ በሚፈጸሙበት ስፍራ የሚኖሩት አብዛኞቹ በዚህ ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታ ቢሸበሩም፤ በርካታ ሶማሊያውያን የሞት ቅጣትን በተለይም በአልሻባብ አባላት ላይ መፈጸሙትን ይደግፋሉ። አንዳንዶች ግን የሞት ቅጣትን ይጸየፉታል። በተለይም የጽዳት ሠራተኛ የነበረው የ17 ዓመት ልጇ ከሁለት ዓመት በፊት በሞቃዲሾ በተፈጸመ የመኪና የቦምብ ጥቃት የተገደለባት ፋዱማ ይህንን መቃወሟ የሚገርም ነው። በዚህ ጥቃት ልጇን ጨምሮ ከ120 በላይ ሰዎች ሲገደሉ፣ 300 ሰዎች ቆስለዋል። ለዚህም ጥቃት አልሻባብ ተጠያቂ ነው ተብሏል። “እየተገደሉ ያሉ ሰዎችን በግሌ አላውቃቸውም ነገር ግን ድርጊቱ ኢ-ሰብዓዊ ነው ብዬ አምናለሁ” በማለትም ታስረዳለች። በዚህ የባሕር ዳርቻ የግድያ ስፍራ አሸዋማው ሜዳ ላይ የሚጫወቱት የዚያ ሰፈር ልጆች ብቻ አይደሉም። በተለይም የሶማሊያ የእረፍት ቀን በሆነው አርብን ጨምሮ በበዓላት ቀናት ከተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች የሚመጡ ታዳጊዎችም መሰባሰቢያ ነው። ከመካከላቸው አንዱ የ16 ዓመቱ አብዲራህማን አደም ነው። “እኔ እና ወንድሜ በየሳምንቱ አርብ የምንመጣው ለመዋኘት እና በባሕር ዳርቻው ላይ እግር ኳስ ለመጫወት ነው” ይላል። “እህቴም ዝንጥ ብላ ከእኛ ጋር ትመጣለች። ፎቶ ለመነሳት እና ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ለመለጠፍ ነው አምሮባት የምትመጣው” በማለት ይገልጻል። ከሌሎች ሰፈሮች የሚመጡት ታዳጊዎች በባሕር ዳርቻው የሚፈጸሙ ግድያዎችን ቢያውቁም ወደዚያ መምጣታቸውን አያቆሙም። የቦታው ማማር እና ማዕከላዊ ቦታ ላይ መገኘቱ የበለጠ ይማርካቸዋል። “የክፍል ጓደኞቻችን ፎቶዎቹን ሲያዩ ይቀናሉ። ነገር ግን ያላወቁት ጉዳይ ይህ የግድያ ስፍራ መሆኑን ነው” ሲልም ያስረዳል። *ይህንን ጹሁፍ የጻፈችው በሶማሊያ የሴቶች ብቻ የሆነው ቢላን ሚዲያ የተሰኘው ጋዜጠኛ ናኢማ ሰኢድ ናት። Adamu Awoke
Show all...
ከሞተ ከሶስት አመት በኋላ ጌዬ ወደ ሮክ ኤንድ ሮል ኦፍ ፋም ገባ። ከችግር ህይወት ቆንጆ ጥበብን መፍጠር ጌይ ደጋግሞ የራሱን ራዕይ፣ ወሰን እና ጥበብ ወደ አለም መድረክ አመጣ። በሙያው መጨረሻ ላይ ሙዚቃን ለደስታ እንዳልሠራ ተናግሯል; ይልቁንም "ሰዎችን የሚያስፈልጋቸውን እና የሚሰማቸውን ለመመገብ እቀዳለሁ. ተስፋ አደርጋለሁ, አንድ ሰው መጥፎ ጊዜ እንዲያሸንፍ መርዳት እችል ዘንድ እቀዳለሁ." ፈጣን እውነታዎች ስም: ማርቪን ጌዬ የትውልድ ዓመት: 1939 የትውልድ ቀን፡- ኤፕሪል 2፣ 1939 የትውልድ ከተማ: ዋሽንግተን ዲ.ሲ. የትውልድ አገር: ዩናይትድ ስቴትስ በጣም የሚታወቀው፡ ማርቪን ጌዬ በ1960ዎቹ እና 1970ዎቹ ከMotown ጋር የነፍስ ዘፋኝ-ዘፋኝ ነበር። የራሱን መዝገቦች አዘጋጅቷል እና ብዙ ጊዜ አወዛጋቢ ጭብጦችን ያነሳ ነበር። አስደሳች እውነታዎች ማርቪን ጌዬ እንደ ብቸኛ አርቲስት ከማድረጉ በፊት እንደ ስቴቪ ዎንደር እና ዘ ሱሊምስ ላሉ አርቲስቶች ከበሮ ተጫውቷል። የሞት አመት: 1984 የሞት ቀን፡- ሚያዝያ 1 ቀን 1984 ዓ.ም የሞት ግዛት: ካሊፎርኒያ የሞት ከተማ: ሎስ አንጀለስ የሞት አገር: ዩናይትድ ስቴትስ via _Biography .com    Writer . Adamu Awoke
Show all...
ማርቪን ጌዬ በ1960ዎቹ እና 1970ዎቹ ከMotown ጋር የነፍስ ዘፋን-ዘፋኝ ነበር። የራሱን መዝገቦች አዘጋጅቷል እና ብዙ ጊዜ አወዛጋቢ ጭብጦችን ያነሳ ነበር. (1939-1984) ማርቪን ጌዬ ማን ነበር? ማርቪን ጌዬ ከሞታውን ጋር ከመፈረሙ በፊት በአባቱ ቤተ ክርስቲያን እና በሙንግሎውስ ዘፈነ። ምን እየሄደ ነው በሚለው የተቃውሞ አልበም (1971) ላይ የራሱ አዘጋጅ ከመሆኑ በፊት በSmokey Robinson ዘፈኖችን ቀርጿል። በኋላ የጌይ መዝገቦች የአመራረት ስልቱን አዳብረዋል እና “እናስረክበው”፣ “ወሲብ ፈውስ” እና “በወይኑ ወይን ሰማሁ”ን ጨምሮ በርካታ ስኬቶችን አስገኝቷል። ጌዬ በ1984 ከአባቱ ጋር በተፈጠረ የቤት ውስጥ አለመግባባት ተገደለ። የመጀመሪያ ህይወት ዘፋኙ ማርቪን ፔንትስ ጌይ፣ ጁኒየር፣ "የነፍስ ልዑል" በመባል የሚታወቀው በዋሽንግተን ዲ.ሲ፣ ሚያዝያ 2, 1939 ተወለደ። ጌይ ያደገው በአባቱ ሬቨረንድ ማርቪን ጌይ ጥብቅ ቁጥጥር ስር ነው። ጌዬ በልጅነቱ በልጅነቱ ፒያኖን እና ከበሮዎችን በመቆጣጠር በሙዚቃ ውስጥ ብዙ ጊዜ ሰላም አግኝቷል። እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ድረስ፣ የዘፈን ልምዱ በቤተ ክርስቲያን መነቃቃት ላይ ብቻ ተወስኖ ነበር፣ ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ ለ R&B እና ዱ-ዎፕ ለሙያው መሠረት የሚሆን ፍቅርን አዳበረ። በ1950ዎቹ መገባደጃ ላይ ጌዬ ዘ ኒው ሙንግሎውስ የተባለውን የድምጽ ቡድን ተቀላቀለ። ጎበዝ ዘፋኙ ሶስት ዓይነት የድምፅ ዘይቤዎችን የሚሸፍን አስደናቂ ክልል ነበረው እና ብዙም ሳይቆይ የቡድኑን መስራች ሃርቪ ፉኳን አስደነቀ። ብዙም ሳይቆይ ጌዬ እና ፉኩዋ ሁለቱም ወደ ዲትሮይት ሙዚቃ ኢምሬሳሪዮ ቤሪ ጎርዲ ጁኒየር ከመምጣታቸው እና ወደ ጎርዲ ታዋቂው ሞታውን ሪከርድስ የተፈራረሙት። Motown መዛግብት የጌይ በራሱ ስም ለመጀመሪያ ጊዜ የተመሰከረለት ስኬት እስከ 1962 ድረስ አይመጣም ነገር ግን በሞታውን የመጀመሪያ አመታት ከትዕይንት በስተጀርባ ስኬቶች የተሞላ ነበር። እንደ ትንሽ እስቴቪ ዎንደር፣ The Supremes፣ The Marvelettes እና ማርታ እና ቫንዴላስ ላሉ የሞታውን አፈታሪኮች የክፍለ-ጊዜ ከበሮ ሰሪ ነበር። ግርፋቱን እንደ ሞታውን ህዳሴ በማሳየት፣ ጌዬ በ1962 በብቸኛ ነጠላ ዜማው ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ Top 40 ለመግባት ቀጠለ። እ.ኤ.አ. በ1960ዎቹ በሙሉ፣ ጌዬ እንደ ዲያና ሮስ እና ሜሪ ዌልስ ካሉ ተወዳጅ ሰሪዎች ጋር በብቸኝነት ዳንስ ስኬቶችን እና የፍቅር ዱላዎችን በማሳየት እጅግ በጣም ግዙፍነቱን ያሳያል። "ምሥክር ማግኘት እችላለሁ" እና "በወይኑ ወይን ሰማሁት" በወቅቱ የጌይ ትልቅ ተወዳጅነት ያተረፉ ሲሆኑ የኋለኛው ደግሞ በ1960ዎቹ የMotown ምርጥ የተሸጠው ነጠላ ዜማ ሆኖ ተገኝቷል። ለሶስት ከፍተኛ በረራ ዓመታት ጌዬ እና ታሚ ቴሬል እንደ "የተራራ ከፍታ አይበቃኝም" እና "መላውን አለም ባንተ ዙሪያ መስራት ከቻልኩ" በተሰኘው የሙዚቃ ትርኢት ሀገሪቱን አስደምመዋል። እንደ አለመታደል ሆኖ በ1970 ቴሬል የአንጎል ዕጢ በያዘ ጊዜ የግዛት ዘመናቸው አብቅቷል ። የሚወደው የትዳር ጓደኛው ሞት ዘፋኙ ከሌላ ሴት ድምፃዊ ጋር በጭራሽ አጋር እንደማይሆን በማለ እና መድረኩን እንደሚተወው በማስፈራራት የጨለማ ጊዜ ውስጥ አስከትሎ ነበር። ጥሩ. ፖለቲካዊ መልእክት እ.ኤ.አ. በ1970 በቬትናም ጦርነት ምክንያት በተባባሰ ብጥብጥ እና ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ተመስጦ ጌዬ “ምን እየተካሄደ ነው” የሚለውን አስደናቂ ዘፈን ጻፈ። በዘፈኑ የፈጠራ አቅጣጫ ላይ ከሞታውን ጋር ቢጋጭም ነጠላ ዜማው በ1971 ተለቀቀ እና ቅጽበታዊ ሰበር ሆነ። ስኬቱ ጌይ በሙዚቃም ሆነ በፖለቲካዊ መልኩ የበለጠ አደጋዎችን እንዲወስድ አነሳሳው። እ.ኤ.አ. በ1971 የጸደይ ወራት ሲለቀቅ፣ ምን እየተካሄደ ያለው አልበም Motown ተከታዩን እየጠበቀ ጌይን ለአዳዲስ ታዳሚዎች ለመክፈት አገልግሏል። ከተሞከረው እና እውነተኛው የሞታውን ፎርሙላ ወጥቶ፣ ጌዬ በራሱ በኪነጥበብ ወጥቷል፣ ይህም እንደ Wonder እና Michael Jackson  ያሉ ሌሎች የሞታውን አርቲስቶች በኋለኞቹ አመታት ቅርንጫፍ እንዲሰሩ መንገድ ጠርጓል። አልበሙ በእኩዮቹ ላይ ተጽእኖ ከማሳደሩ ባለፈ የሮሊንግ ስቶን አልበም የዓመቱን ሽልማት በማግኘቱ ሰፊ አድናቆትን አግኝቷል። ተሻጋሪ ስኬት እ.ኤ.አ. በ 1972 ጌይ ወደ ሎስ አንጀለስ ተዛወረ እና ብዙም ሳይቆይ ከጃኒስ ሀንተር ጋር ተገናኘ ፣ እሱም በኋላ ሁለተኛ ሚስቱ ይሆናል። በአዲሱ የነጻነቱ መንፈስ ተመስጦ ጌዬ በዘመናት ከነበሩት እጅግ የተከበሩ የፍቅር መዝሙሮች አንዱን "እንስራው" ሲል መዝግቧል። ዘፈኑ የእሱ ሁለተኛ ቁጥር ሆነ። 1 ቢልቦርድ በመምታት የመሻገሪያ ይግባኙን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አጠናክሮታል። ብዙም ሳይቆይ ሞታውን ጌይን በቅርብ ጊዜ ያገኘውን ስኬት ለመጠቀም ወደ ጉብኝት ገፋው፤ ዘፋኙ-ዘፋኙ ሳይወድ ወደ መድረክ ተመለሰ. በአብዛኛዎቹ የ1970ዎቹ አጋማሽ ጌዬ እየጎበኘ፣ እየተባበረ ወይም እያመረተ ነበር። ከዲያና ሮስ እና ከተአምራቱ ጋር በመስራት እስከ 1976 ድረስ ሌላ ብቸኛ አልበም መልቀቅን አቆመ።እፈልጋለው (1976) ከተለቀቀ በኋላ ጉብኝቱን ቀጠለ እና በ1977 በዳንስ ነጠላ ዜማ 1 መምታት ካስመዘገበ በኋላ። ኢት አፕ” በ1978 የመጨረሻውን አልበሙን ለሞታውን ሪከርድስ (እዚህ፣ የእኔ ውድ) አወጣ። (ከአሥርተ ዓመታት በኋላ፣ «Got to give It Up» የትልቅ ውዝግብ ማዕከል ይሆናል። ትራክ ለ "ድብዘዛ መስመሮች" ሜጋ-መታ። ትርፍ ማጋራቶች ዳኞች ዊሊያምስም ሆነ ቲክ ሆን ብለው ጥሰት እንዳልፈጸሙ ወስኗል። ከሁለት አስርት አመታት በኋላ በሞታውን፣ ጌዬ በ1982 ከሲቢኤስ's Columbia Records ጋር ተፈራረመ እና በመጨረሻው አልበም Midnight Love ላይ መስራት ጀመረ። የዚያ አልበም መሪ ነጠላ ዜማ "ወሲብ ፈውስ" ለ R&B ኮከብ ትልቅ ተመልሷል እና የመጀመሪያዎቹን ሁለት የግራሚ ሽልማቶችን እና ለተወዳጅ ሶል ነጠላ የአሜሪካ የሙዚቃ ሽልማት አግኝቷል። የግል ሕይወት እ.ኤ.አ. በ1975 የጌይ ሚስት አና ጎርዲ—የቤሪ ጎርዲ እህት—የፍቺ ጥያቄ አቀረቡ፣ እና ከሁለት አመት በኋላ ጌይ ሀንተርን አገባ፣ እሱም ሴት ልጃቸውን ኖና (ሴፕቴምበር 4፣ 1974 ተወለደ) እና ልጃቸውን ፍራንኪን (ህዳር 16 ተወለደ) ወለዱ። , 1975). ጌዬ ከቀድሞው ጋብቻ የማደጎ ልጅ (ማርቪን ፔንትስ ጋዬ III) ነበረው። የዘፋኙ ከአዳኝ ጋር ያለው ጋብቻ አጭር እና ውዥንብር የታየበት ሲሆን በ1981 በፍቺ አብቅቷል። ሞት እና ውርስ እ.ኤ.አ. በ1980ዎቹ መጀመሪያ ላይ በተሳካ ሁኔታ ተመልሶ ቢመጣም ፣ ጌዬ አብዛኛውን ህይወቱን ሲያሰቃየው ከነበረው የአደንዛዥ ዕፅ ሱሰኛ እና የመንፈስ ጭንቀት ጋር በጣም ታግሏል። ከመጨረሻው ጉብኝት በኋላ ወደ ወላጆቹ ቤት ሄደ. እዚያም እሱና አባቱ ቤተሰቡን ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሲያንዣብቡ የነበሩ ግጭቶችን የሚያስታውስ ኃይለኛ ጠብና ጠብ ውስጥ ወድቀዋል። እ.ኤ.አ. ኤፕሪል 1፣ 1984 ማርቪን ጌይ ሲር አካላዊ ግጭት ከተፈጠረ በኋላ ልጁን ተኩሶ ገደለው። አባቱ ራሱን ለመከላከል እንደሰራ ቢናገርም በኋላ ላይ ያለፈቃድ ግድያ ወንጀል እንደሚፈረድበት ተናግሯል።
Show all...
"ማርቪን ጌይ" ቤልጂም ውስጥ የተገኙት ተሰምቶ የማያውቀው የማርቪን ጌይ ሙዚቃ እና ንብረቶቹ ማርቪን ጌይ ከሞተ ከ40 ዓመታት በኋላም የሙዚቃ ሥራዎቹ አሁን ድረስ ተወዳጅነታቸው እና ተደማጭነታቸው አልቀነስም። ከእሱ ጋር እንዲህ ያለውን ዘመን ተሻጋሪ ዝናን የሚጋሩት ኤልቪስ ወይም ዘ ቢትልስ ናቸው። የማርቪን ጌይ ሥራዎች በሸክላ ቴፖች ላይ ከመቀረጽ ጀምረው፣ የቴፕ ካሴቶች እና የሲዲ ዘመንን ተሻገረው በበይነ መረብ የሙዚቃ ማዳመጫ የቴክኖሎጂ ወቅት ላይ ደርሰዋል። ማርቪን ጌይ ከ40 ዓመታት በፊት ሕይወቱ ያለፈው ቤት ውስጥ በተፈጠረ ከባድ የቤተሰብ አለመግባባት ምክንያት በአባቱ በጥይት ተመትቶ ነበር። ነገር ግን ሙዚቃዎቹ አሁንም ድረስ በወር ወደ 20 ሚሊዮን ጊዜ ያህል በኢንተርኔት ላይ ይደመጣሉ፣ ይወርዳል። ከታሚ ቴሬል ጋር የተጫወተው ‘አይን ኖ ማውንቴን’ የተጫወተው ሙዚቃ ደግሞ ከአንድ ቢሊዮን ጊዜ በላይ በበይነ መረብ ላይ ተደምጧል። ስለዚህ አሁንም በማርቪን ጌይ የተቀዳ አዲስ ሙዚቃ የያዙ የድምጽ ካሴቶች መገኘት ሊኖረው የሚችለው ተጽእኖ የጎላ ነው። አሁን ከአርባ ዓመታት በላይ ቤልጂየም ውስጥ ተደብቆ የተገኘው ሥራው ከሙዚቃው ኮከቡ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ቅርሶች ክምችት አካል ነው። ይህም አሁን ይፋ ሆኖ የዓለም ሙዚቃ ርዕሰ ጉዳይ ሊሆን ነው። በአንድ የምሽት ክበብ ውስጥ ከአንድ የቤልጂየም የኮንሰርት ፕሮሞተር ጋር በተገናኘበት ጊዜ ለንደን ነዋሪ የነበረው ማርቪን፣ የኮኬይን ዕጽ ሱሰኛ ነበረ። የፕሮሞተሩን አድራሻ ከተቀበለ ከሳምንት በኋላ ደውሎለት ወደ ቤልጂየም የባሕር ዳርቻ ከተማዋ ኦስቴንድ ለመሄድ ዝግጅት አደረገ። ይህ ጉዞው የሙዚቀኛውን ሕይወት ከዕጽ ጉዳት ታድጎታል ቢባል ማጋነን አይሆንም። ማርቪን ጌይ በአውሮፓውያኑ 1984 የሞተው በአባቱ በተተኮሰበት ጥይትተመትቶ ነበር 🔘 በሜዳማው የሰሜን ባሕር ዳርቻ ላይ በመሮጥ እና ብስክሌት እየጋለበ እንደገና ወደ ጤናማ ሕይወት ተመልሶ ከታላላቅ ምርጥ ሥራዎቹ አንዱ የሆነውን ‘ሴክሽዋል ሂሊንግ’ የተሰኘውን ሙዚቃን ሠራ። ማርቪን ለተወሰነ ጊዜ በኖረበት በቤልጂየማዊው ሙዚቀኛ ቻርለስ ዱሞሊን ቤት ውስጥ የተዋቸው የመድረክ አልባሳት፣ የማስታወሻ ደብተሮች እና የቴፕ ካሴቶች ስብስብ በአሁኑ ጊዜ በቻርልስ ቤተሰብ እጅ ይገኛል። ማርቪን ቤልጂየም ውስጥ በቆየበት ጊዜ የተቀዳ ተሰምቶ የማያውቅ እና ከአርባ ዓመታት በላይ ተደብቆ የቆየ አዲስ ሙዚቃ እንዳለ ቢቢሲ ይፋ የማድረግ ዕድልን አግኝቷል። በንብረቶቹ ላይ የይገባኛል ጥያቄ ያቀረበው የቤተሰብ የንግድ ሸሪክ የሆነው የቤልጂማዊው ጠበቃ አሌክስ ትራፕፔኒየርስ፣ እጅግ በጣም ውድ በሆኑት የማርቪን ጌይ የመድረክ አልባሳት፣ የማስታወሻ ደብተሮች እና ያልተሰማ ሙዚቃው ዕጣ ፈንታን የሚወስን ሰው ነው። ይህንን ለቢቢሲ በተለይ ያሳወቀው ጠበቃ፣ በጉዳዩ ላይ የሕግ አቋም ምን እንደሆነ አስርድቷል። እቃዎቹ “ከ42 ዓመታት በፊት ቤልጅየም ውስጥ ስለቀሩ የቤተሰቡ ንብረት ናቸው” ይላል። “ማርቪን ‘ማድረግ የምትፈልጉትን አድርጉ’ ብሏቸው ተመልሶ አልመጣም። ስለዚህ ይህ ወሳኝ ነገር ነው።” ከሁሉ ከሁሉ የዚህ ታሪክ ዋነኛው ነገር የሚሆነው ግን ከዚህ በፊት ተሰምቶ የማያውቀው አዲሱ ሙዚቃው ነው። ጠበቃው አሌክስ፤ የማርቪን ሙዚቃውን ሲለማመድ የሚደመጥበትን አጭር እና ገላጭ የሆነውን ናሙና ለቢቢሲ አሰምቷል። ይህም የሙዚቃው ልዑሉ ማርቪን ጌይ እንደገና በሙዚቃው መድረክ ላይ መነጋገሪያ ሊያደርገው የሚችል አዲስ ሥራ ነው። የሙዚቃ ቅጂዎቹን በአንድ ዓይነት ቅደም ተከተል መልክ የማስያዙ ሥራ ቀላል አልነበረም። ነገር ግን ይህ አዲስ የተገኘው ሙዚቃ ምን ያህል ትልቅ እና ምን ያህል አስፈላጊ ሊሆን እንደሚችል ግልጽ ፍንጭን የሚሰጥ ነው። ሙዚቃዎቹን በሚሰማበት ጊዜ “ማርቪን መዝፈን ሲጀምር አዲስ የሙዚቃ መሳሪያ ስለሚጀምር ቁጥር እሰጥ ነበር” ሲል አሌክስ ይናገራል። “ሁሉንም 30 ካሴቶች ሳዳምጥ መጨረሻ ላይ የ66 አዳዲስ ዘፈኖችን ማሳያን አገኘሁ። አንዳንዶቹ የተሟሉ እና ሌሎቹ ደግሞ ከ‘ሴክሽዋል ሂሊንግ’ ጋር በተመሳሳይ ጊዜ የተሠሩ ስለነሆኑ ድንቅ ናቸው።” ከሁሉ በላቀ በአንዱ አዲስ የሙዚቃ ትራክ አማካኝነት የማርቪን ጌይ ሌላ ዓለም አቀፋዊ ስኬት ሊያንሰራራ ይችላል ብሎ አሌክስ ያምናል። ይህም በአንጻራዊነት ቀደምት የቢትልስ ቅጂዎች ታድሰው ለመደመጥ የበቁበት ሁኔታ ለማርቪን ጌይ ሥራም ሊውል እንሚችል ይታሰባል። አሌክስ ትራፕፔኒየርስ የማርቪን ጌይ ሙዚቃ የተቀዳበትን ካሴት ይዞ አሌክስ ዘፈኑን ለማንም አላሰማም ለሚስቱም ጭምር፤ ነገር ግን በቀላሉ እንዲህ ሲል ይገልጸዋል “አንድ ዘፈን አለ ለአስር ሰከንድ ያህል ብቻ አዳምጬው ሙዚቃው ቀኑን ሙሉ በጭንቅላቴ ውስጥ ሆኖ አገኘሁት። ቃላቶቹ ቀኑን ሙሉ በጭንቅላቴ ውስጥ ሲያቃጭሉ ውለዋል” ይላል። ሥራዎቹ የማርቪን ጌይ ስለመሆናቸው ምንም የሚያጠራጥር ነገር የለም። ቢቢሲ ቤልጂየም ኦስቴንድ ውስጥ በሚገኝ አንድ የሰነዶች ማስቀመጫ ውስጥ ያሉ የማርቪን ጌይን አጠቃላይ ሕይወትን የሚመለከቱ ሰነዶችን ገጽ በገጽ ተመልክቷል። በዚህም በኮንሰርት ዝግጀት ወቅት የሚቀርቡ ሙዚቃዎች ቅደም ተከትልን የሚገልጹ በታይፕ የተጻፉ ወረቀቶች፣ ሙዚቃውን ለሚቀርጽለት ኩባንያ የጻፋቸው ቁጣን ያዘሉ ደብዳቤዎች፣ የአዳዲስ ሙዚቃዎች ረቂቅ ግጥሞች እንዲሁም የግል ሃሳቡን ያሰፈረባቸው ማስታወሻ ደብተሮች አሉ። ቢቢሲ ሙዚቃ ለማቅረብ ከአገር አገር በሚዘዋወርበት ጊዜ ይለብሰው የነበረውን መለያው የሆነውን ቀይ ኮትን ጨምሮ ልብሶቹን እና የመድረክ አልባሳቱን የያዘ መደርደሪያን ለመመልከትም ችሏል። ይህም ከአጠቃላዩ የተወሰነው ማሳያ ብቻ መሆኑ ተገልጿል። ነገር ግን ከሁሉ በላይ የሚሆነው ያልተሰማው አዲሱ ሙዚቃው ነው። ይህም ከሚፈጥረው ጥልቅ ስሜት አንጻር የሚኖረውን ከፍ ያለ ዋጋ አሌክስ ትራፕፔኒየር አይጠራጠርም። “የጊዜ ቁልፍን እዚህ ከፍተን የማርቪንን ሙዚቃ ለዓለም ማካፈል እንችላለን” በማለት “በጣም ግልጽ ነው፤ ማርቪን አሁንም አለ” ይላል። ነገር ግን ስለአእምሯዊ ንብረት እና ስለ ሙዚቃ ህትመት መብቶች ያሉት ሁኔታዎች ግልጽ አለመሆናቸው ጥያቄን ማስነሳታቸው አልቀረም። የማርቪን ግልጽ ውሳኔ በአውሮፓውያኑ 2019 ለሞተው ቻርልስ ይህንን ቅርስ ለመስጠት መወሰኑ ንብረትነቱ ሙሉ ለሙሉ የዱሞሊን ቤተሰብ ነው ማለት ቢያስችልም ተጨማሪ የባለቤትንት ጥያቄም ይኖራል። ቤልጂየም ያላት ለየት ያለሕግ አንድ ሰው የተሰረቀም ይሁን በሌላ መንገድ እጁ ያስገባውን ንብረት ይዞ 30 ዓመታት የቆየ እንደሆነ የባለቤት መብትን ያገኛል። ስለዚህ በቤልጂየም ከ40 ዓመታት በላይ የቆዩት የማርቪን ጌይ ንብረቶች የባለቤትንት ጉዳይ ብዙም የሚያጠያይቅ አይሆንም። ሙዚቃው የተቀዳበት ካሴት እና ካሴቱ ላይ ያለው ሙዚቃ ንብረትነታቸው በተለያዩ ሰዎች እጅ ነው ነገር ግን ይህ ሕግ ሙዚቃን በመሳሰሉ በአእምሯዊ ንብረትነት በሚካተቱት ላይ የሚሠራ አይደለም። ስለዚህም አሌክስ ትራፕኒየርስ እና አጋሮቹ የማርቪን ጌይ ዘፈኖችን የማተም መብት ሳይኖራቸው፣ ሙዚቃው የተቀዳባቸው ካሴቶች ብቻ ባለቤቶች ሊሆኑ ይችላሉ።
Show all...
እናም በአሜሪካ የሚገኙት የማርቪን ጌይ ወራሾች ከሙዚቃው ጥቅም የማግኘት ንድፈ ሃሳባዊ መብት አላቸው። ነገር ግን ሙዚቃው የተቀዳበት ካሴት ባለቤትነት መብት የሌላ ሰው ስለሆነ አንዳች ስምምነት እስካልተደረሰ ድረስ የሚጠቀሙበት ዕድል የለም። ነገር ግን በአሌክስ ዕይታ ይህ ሁኔታ ንብረቱ በእጃቸው ላይ ባለው እና በወራሾቹ መካከል አንድ ዓይነት ሰጥቶ የመቀበል የስምምነት በር መኖሩን ያሳያል። “የማርቪን ቤተሰብ እና ሙዚቃው እጃቸው ላይ ያለው (ዱሞሊን ወራሾች) ሁለታችንም ጥቅም የምናገኝበት ይመስለኛል፤ ከተባበርን እና በዓለም ላይ ትክክለኛ ሰዎችን ካገኘን....አድምጠን የሚቀጥለውን አልበም እንሥራ” በማለት አሌክስ ሃሳብ አቅርቧል። የማርቪን ጌይ ንብረቶች ቤልጂየም ውስጥ በምሥጢር የተጠበቁበት እና ይፋ የሚደረግበት ሁኔታ ስብስቦቹ ምን ዓይነት ዓለም አቀፋዊ ተጽእኖ ሊኖራቸው እንደሚችል ለመገመት አስቸጋሪ ያደርገዋል። አሁንም በጣም ወሳኝ የሚሆነው የማርቪን ጌይ ልጆች የሆኑት ማርቪን፣ ኖና እና ፍራንኪ እንዲሁም የንብረቱ አስተዳዳሪዎች ይህንን ሁኔታ እንዴት ይቀበሉታል የሚለው ጥያቄ ነው። ቢቢሲ የማርቪን ጌይ ቤተሰቦች ምላሽ እንዲሰጡ ጠይቆ ነበር። ከሦስቱ ልጆቹ የሁለቱ ጠበቆች ቤልጂየም ውስጥ ስላሉት ንበረቶች ያውቃሉ። ምናልባት ድርድሮች ሊኖሩ የሚችሉ ሲሆን፣ እስካሁን ግን ምንም የተጀመረ ነገር የለም። በዚህም የማርቪን ጌይ ሙዚቃ የተቀዳበት ካሴት ባለቤት በሆኑት እና የሙዚቃው ባለመብት በሆኑት ወገኖች መካከል በሚደረግ ድርድር መስማማት ላይ ሊደረስ ይችላል። ከሞራል አኳያ አንዳንዶች ሰነዶቹ፣ አልባሳቱ እና የሙዚቃ ቅጂዎቹ ስብስብ የጌይ ቤተሰብ ንብረቶች እንደሆኑ በማሰብ በቀላሉ ለእነሱ መሰጠት አለባቸው ይላሉ። አሌክስ ግን የሕግ ጉዳይ ያን ያህል ግልጽ እንዳልሆነ እና እሱ እና አጋሮቹ ሙሉውን ንብረት በቀላሉ የመሸጥ መብት እንዳላቸው ይከራከራል። የማርቪን ጌይ ንብረቶችን በተመለከተ በርካታ ያልተቋጩ አወዛጋቢ ጉዳዮች አሉ። እነዚህም ልጆቹን እና ንብረቱን በውርስ ያገኘውን ቤተሰብ በማቀራረብ በሚያስማማ መልኩ ሊቋጩ እና ሙዚቃው ለአድማጭ መድረሱ የመጨረሻው ግብ ነው። ይህ ደግሞ በአርባዎቹ ዕድሜው መጀመሪያ ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ በአባቱ የተገደለውን ማርቪን ጌይን ከአርባ ዓመታት በኋላ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ በሙዚቃው ዓለም የዜና መድረክ ላይ ትልቁ መነጋገሪያ ያደርገዋል። የማርቪን ጌይ የሙዚቃ ሥራዎች ብቻ ሳይሆኑ አልባሳቱም ቤልጂየም ውስጥ ይገኛሉ። Via _BBC 💧ማርቪን ጌይ ማን ነዉ ? ከሙሉ መረጃ ጋር እመለሳለሁኝ!
Show all...