405
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Data loading in progress...
Similar Channels
No data
Any problems? Please refresh the page or contact our support manager.
Tags Cloud
No data
Any problems? Please refresh the page or contact our support manager.
Incoming and Outgoing Mentions
---
---
---
---
---
---
Attracting Subscribers
September '23
September '23
+14
in 0 channels
August '23
+31
in 0 channels
Get PRO
July '23
+28
in 0 channels
Get PRO
June '23
+40
in 0 channels
Get PRO
May '23
+57
in 0 channels
Get PRO
April '23
+14
in 0 channels
Get PRO
March '23
+25
in 0 channels
Get PRO
February '23
+21
in 0 channels
Get PRO
January '23
+25
in 0 channels
Get PRO
December '22
+35
in 0 channels
Get PRO
November '22
+257
in 0 channels
| Date | Subscriber Growth | Mentions | Channels | |
| 23 September | 0 | |||
| 22 September | +1 | |||
| 21 September | 0 | |||
| 20 September | 0 | |||
| 19 September | +3 | |||
| 18 September | 0 | |||
| 17 September | 0 | |||
| 16 September | +1 | |||
| 15 September | +1 | |||
| 14 September | +1 | |||
| 13 September | 0 | |||
| 12 September | +2 | |||
| 11 September | +1 | |||
| 10 September | +2 | |||
| 09 September | 0 | |||
| 08 September | 0 | |||
| 07 September | +2 | |||
| 06 September | 0 | |||
| 05 September | 0 | |||
| 04 September | 0 | |||
| 03 September | 0 | |||
| 02 September | 0 | |||
| 01 September | 0 |
Channel Posts
🚫ልቅ የሆኑ የወሲብ ፊልሞችና ምስሎችን በመመልከት ለተለከፉ ሁሉ!
♻️እነዚህ ፊልሞችና ምስሎች የጀሀነም በሮች ናቸው!
📵እነዚህን የበከቱና የተግማሙ ዝሙተኞችን በማየት እስረኛ የሆንክ/ሽ ሁሉ በዚህ ሰበብ ምን እንደሚከተልህ/ሽ ተከታዩን እስተውለህ/ሽ አንብብ/ቢ!
☞ለላጤዎችና ለባለትዳሮች መጨረሻ ላይ የተቀመጠውን መፍትሄ በጥሞና አንብቡት!
☞የተራቆቱ ዝሞተኞችን ማየት እጅግ ከባባድ ወንጀሎች ውስጥ እንደሚካተቱ ታውቃለህ?
☞እነዚህን ዝሙተኞች መመልከት ውርደትና ደካማነት እንደሚያወርስ ታውቃለህ?
☞እነዚህን ዝሙተኞች መመልከት በሰዎች አይን ያነስክና ወራዳ እንደሚያደርግህ ታውቃለህ?
☞እነዚህን አፀያፊ ምስሎችና ቪድዮዎች በማየት የተለከፈ ወጣት በቀላሉ ካገኘው ተቃራኒ ፆታ ጋር ሁሉ ዝሙት ላይ የሚወድቅ ይሆናል። እንዲሁም ራስን ወደ ማርካት (masturbation) ሱስና የስንፈተ ወሲብ አደጋ ተጋላጭ የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው።
☞እነዚህን የዝሙት ዌብሳይቶችና የቪድዮ ምስሎች መመልከት በአእምሮህና በአይንህ ላይ ድክመትን እንደሚከስት ታውቃለህ? ይህን በመመልከት ሱሰኛ የሆነ ሰው ቀለል ያሉ ጉዳዮችን በቀላሉ ይረሳል። ይህ አደጋ እያደገ ሲሄድ የአእምሮ ድክመት አስከትሎበት እንዴት መናገር እንዳለበት ሁሉ ላያውቅ ይችላል! ሌሎችም ብዙ የጤና እክሎች ያጋጥሙታል!
☞ይህ ወንጀል አላህ ዘንድ ወራዳ ሰው እንደሚያደርግህ ታውቃለህ?
☞የእነዚህ ዝሙተኞች ምስል አእምሮህ ላይ ተቀርፇል? (ይህ የአላህ ቁጣ ምልክት ነው!)
☞እነዚህን ነገሮች መመልከት ትንንሽ ነገሮችን ሁሉ የምትሰጋ ፈሪና ልፍስፍስ እንደሚያደርግህ ታውቃለህ?
☞ይህን እርቃን ብልግና የምትመለከት ሆይ! የሸሪዓ እውቀትን ብርሃን በፍፁም ማግኘት እንደማትችል ታውቃለህ?
☞በዚህ ወንጀልህ ከምትወዳትና ከምትወድህ የህይወት አጋርህ ባለቤትህ ጋር የተረጋጋ ህይወት መኖር እንደምትነፈግ ታውቃለህ?
☞ይህን አስቀያሚ ተግባር የምትመለከት ከሆነ ደጋግ የአላህ ባሪያዎች ይህን ቀፋፊ ተግባርህን ባትነግራቸውም እንኳን ሊጠሉህ እንደሚችሉ ታውቃለህ?
☞እነዚህን ዝሙተኞችን ማየት ግዴታ የሚሆንብህ በዝሙት ወንጀላቸው በድንጋይ ተወግረው ሲገደሉ ብቻ እንደሆነ ታውቃለህ?
☞ ከዚህ ከምትመለከተው ቀፋፊ ምልከታ እውነተኛ ተውበት አድርገህ ወደ አላህ ካልተመለስክ እጅግ ከባድ ዋጋ ለወደፊት እንደሚያስከፍልህ ታውቃለህ?
☞እጅግ የምትወደውና የምትቀርበው ሰው ሞት ዜና ይህን ነገር እየተመለከትክ ብትሰማ ትወዳለህ?
☞ ከዚህ ወንጀል አፀያፊነት የተነሳ አላህ መሬትን ደርምሶ ሊያስውጥህ እንደሚችል ታውቃለህ?
☞በዚህ ቀፋፊ ምልከታ ላይ ሆነህ ሞት ሊመጣህ እንደሚችል ታውቃለህ? አስከፊ ኻቲማ ሊያስደነግጥህ እንደማይችል እርግጠኛ ነህ?
☞ጌታህ ቻይ ነው! ለግዜው ይተውኃል፤ ነገር ግን በምትሰራው ወንጀል ደስተኛ ሆኖ እንዳይመስልህ! ከዚህ ወንጀልህ ተውበት ካላደረክ ለወደፊትም ቢሆን ከባድ መከራ ትጋረጣለህ!
☞ የዒባዳህን ጥፍጥና እንደሚያሳጣህ አምልኮ ላይ ደካማ እንደሚያደርግህ ታውቃለህ?
ለዒባዳ በቆምክ ቁጥር የምታያቸው ምስሎች አዕምሮህን ተቆጣጥረው እንደሚፈታተኑህ ታውቃለህ? በዚህም ከአምልኮ መሸሽና ተስፋ ቢስነት ሊሰማህ ይችላል። ይህ ደግሞ ወደ አደገኛው አዘቅት ክህደት የሚጎትት ጠንቅ ነው።
☞ ራስህን የምትጠላ የወንጀል ምርኮኛ እንደሚያደርግህ ታውቃለህ?
☞ለአላህ ብሎ አንዳች ነገርን
የተወ ሰው አላህ የተሻለ መልካም ነገር እንደሚተካለት ታውቃለህ?
☞አላህ በባሪያው መመለስ የሚደሰት የተብቃቃና ምስጉን ጌታ መሆኑን ታውቃለህ?
☞ከወንጀል ጥብቅ ከሆንክ አላህ ከችሮታው እንደሚያብቃቃህ ታውቃለህ?
☞ለደቂቃዎች (ሻህዋ) ስሜት ተብለው የሚሰሩ ወንጀሎች የአመታት ቅጣት እንደሚያመጡ ታውቃለህ?
☞ዛሬ በዱንያ ላይ የምትሰራቸው ወንጀሎች፦ የተከለከለን ማየት፣ መስራትና ሌሎችንም በዱንያ ላይ ቅጣቱን በድህነት፣ በአደጋ፣ ሪዝቅህን በመከልከል በቤተሰብህ፣ በልጆችህና በቅርብ ሰዎች ላይ አደጋ ሊከስት እንደሚችል ታውቃለህ?
☞ይህ ወንጀል አእምሮህን ተቆጣጥሮ ከምትመለከታት ሴት ሁሉ ቀፋፊው ዝሙት ላይ ለመወደቅ እንደሚገፋፋህ ታውቃለህ?
✅✅✅✅✅
☞ለላጤዎች ምክር!
♻️ያላገባህ እንደሆነ በተቻለህ መጠን ለማግባት ሞክር!
♻️ስለ ትዳር በቂ እውቀት ይዘህ ወደ ትዳር ግባ!
♻️ ማግባት ካልቻልክ ትርፍ የምትለውን ግዜህን በመልካም ነገር አሳልፍ፦ በፆም፣ በንባብ፣ ስፖርት በመስራት፣ መልካም ኢስላማዊ ትምህርቶችን በመማር፣ በመስማትና በማየት.......
♻️በብዛት ብቻህን ከመሆን ተቆጠብ
♻️አላህን ከዚህ ቀፋፊ ወንጀል ነፃ እንዲያደርግህ ተማፀን!
♻️መልካም ሰዎች ጋር ለመቀማመጥ ሞክር!
♻️ሸይጣን ይህን ወንጀል ባስታወሰህ ቁጥር ቆራጥ ሆነህ ላለመመለስ ሞክር! መጀመሪያው ቢከብድብም በሂደት አላህ ይረዳሃል!
☞ለባለ ትዳሮች ምክር
♻️አግብተህ ከሆነ ከትዳር አጋርህ ጋር ስለ ህይወታቹህ ያለ እፍረት በግልፅ በመነጋገር የምትፈልጉትን እርካታ ሁሉ ማግኘት እንደምትችል እውቅ!
♻️ በኢስላም ጥላ ስር ያሉ ታማኝ ከትዳር ህይወት ጋር የተያያዙ አስፈላጊ ትምህርቶችንና ጥናታዊ ፅሁፎችን አንብብ!
♻️ በዚህ ላይ የተሻለ እውቀት ያላቸውን አላህን የሚፈሩ ብለህ የምታስባቸውን ወንድሞችህን አማክር!
♻️ ሚስትም የዘመኑን ክፋት ልትረዳና ነቃ ብላ ከትዳር አጓሯ ጎን ልትቆም ይገባል። በግልፅ ማውራትና ፍላጎቱን ማሟላት ብልግና ሳይሆን ብልጠት መሆኑን አውቃ በተቻለ መጠን ውበቷን በመጠበቅ የባሏ ልብ እንዳይሸፍትና እንዳይሰላች የበኩሏን ጥረት ሁሉ በማድረግ ባለቤቷን ማስደሰት አለባት!
✖️እነዚህ የተግማሙና የበከቱ ዝሙተኞች ይህችን አጭር ህይወትን እንዲያበላሹ አትፍቀድ! ጀግና ሁን/ሁኚ!
♻️በመጨረሻም የመልካም ሰዎችን ታሪክ አንብብ! እንዴት አላህን እንደሚጠነቀቁ አስተውል። አስተንትን! በዚህ ወንጀልህ የሰማያትና የምድር ጌታን እያመፅክ መሆኑ ይሰማህ!
ኮምፒዩተሮችህና ስማርት ስልኮችን የመዋረጃህ ሰበብ አታድርጋቸው!
ኢብኑ'ል ወርዲይ በግጥማቸው እንዲህ ብለዋል ፦
إنَّ أحلى عيشةٍ قضيتُها
ذهبتْ لذاتُها والإثمُ حلْ
ስሜቴን ያራገፍኩባቸው ጣፋጭ ግዜያቶች
ጥፍጥናቸው ሄዷል ወንጀሉ ቅን ቀርቷል/ተመዝግቧል
♻️ሁላችንንም አላህ ለሚወደው ይምራን!
✍ዐብዱረዛቅ
| 2 | _የፖርኖግራፊ_ሱስ_ስብዕናህን_እንዲያዝገው_አትፍቀድ_በፖርን_ሱስ_ለተጠመዱ_ቁርኣናዊ_መፍትሄ_በኑዕማን.mp3 | 151 |
| 3 | دعاء_يخرج_كل_عين_وسحر_من_الجسد_القارئ_حمزة_بوديبMP3_160K.mp3 | 170 |
| 4 | No text... | 200 |
| 5 | 👆👆👆
🔈#የድግምት መስፋፋት ምክንያቱና እንዴት መከላከል እንደሚቻል እንዲሁም በሩቃ ስም ከሚደረጉ ግሳንግስ ተግባሮች ማስጠንቀቅ!! | 209 |
| 6 | -> የማታው ፕሮግራም በዚህ መልኩ ወደ ድምፅ ፋይል ተቀይሮላችኋል!
ተፈኩር | 179 |
| 7 | የጠንቋይ ጎረቤት.mp3 | 192 |
| 8 | ጠንቋዮችና መሰሎቻቸው !!!.mp3 | 190 |
| 9 | +9 ⤴️⤴️⤴️
የቪዲዮ ብይን በኢስላም
【ክፍል አንድ】
🎙 በኡስታዝ ባሕሩ ተካ አቡ ዑበይዳህ ሀፊዘሁሏህ
➡️ መግቢያ ከሸኽ ሙሀመድ ብን ሳሊህ አል ዑሰይሚን ምክር ጋር | 163 |
| 10 | የፎቶ መዘዝ ......የአላህ እርግማን በሳሂሮች ላይ ይሆን የስንቱን ህይወት አመሰቃቀሉ! | 87 |
| 11 | +8 ስለ ፎቶ ሸሪዓዊ ፍርድ
📷🤳 ♨️♨️❌❌
╭─••°─═•°•═─•••─╮
📷🤳 ክፍል ❶ ↩️❌
╰─••°─═•°•═─•••─╯ | 86 |
| 12 | ውድ የአላህ ባሪዎች!
ከሲህርና ከአድራጊዎቹ ሁሉ በአላህ እንጠበቃለን።
በየሶሻል ሚዲያው ፎቶዎቻችሁን ከማሰራጨት ተቆጠቡ!
ነፍሶቻችሁን ከጥፋት ታደጉ።
በገዛ እጃችሁ በለቀቃችሁት ፎቶ ሲህር እየተሰራ ይገኛል።
ፎቶዎችን በሚዲያ በመልቀቅ ለሳሂሮች ነፍስህን / ነፍስሽን አታመቻቹ / ፈተና ላይ አትጣሉ
ይህ በተጅሩባ የተረጋገጠ ነው። ከየሚዲያው እየተወሰደ ሲህር እየተሰራ ይገኛልና እንጠንቀቅ።
አላህ ከደጋሚዎች (ከሳሂሮች) ሁሉ ተንኮል ከድግምት(ከሲህር) ይጠብቀን። | 97 |
| 13 | 𑁍ነብያዊ ሕክምና𑁍 .apk | 165 |
| 14 | 𑁍አዲስ አፕልኬሽን𑁍
𑁍ነብያዊ ሕክምና𑁍
﹌﹌﹌﹌﹌﹌﹌﹌﹌
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኁሩህ እጀግ በጣም አዛኝ በሆነው፤ የአላህ ሰላትና ሰላም በውዱ ነብያችን ላይ ይስፈን።
በመቀጠልም በዚህ አፕ በተለያዩ ግዜያት ለሚያጋጥሙን ህመሞች ሸሪአዊ መፍቴሄዋቻቸውን ከቁርአንና ከሀዲስ ለማግኘት የሚቻልባቸውን መንገዶች በቀላል አቀራረብ በአማርኛና ኦሮሚኛ ቋንቋዋች ለማቅረብ ተሞክሯል።
አፑን ለሙስሊሙ ኡማ በማሰራጨት የኸይር ሰበብ የአጅር ተቋዳሽ ይሁኑ።
ዝግጅት፦ አቡ ሩሀማ
አፕልኬሽን ስራ፦ HUDA SOFT || ሁዳ ሶፍት
---------------------
#Afan Oromo
Maqaa Rabbii Akkaan Mararfataa Akkaan Rahmata Godhaa Ta’eetiin
Nagaafi Rahmatni Rabbii Nabiyyi Keenya Irratti Haa Ta'u.
Itti ansuudhaan Applikashiina kanaan dhiibeele yeroo adda addaa keessatti nu qunnamaniif furmaatoowwan sharii'a Qur'aanaafi Hadiisa irraa karaa salphaatiin dhiiheesuuf yaalamee jira.
Applikeeshina kana ummata Muslimaatiif raabsuuf ajirri irraa qooda fudhataa ta'a.
Qopheessaan: Abuu Ruhaamaa
Hojii Applikashina:Huda Soft
መተግበሪያውን በሚከተለው ሊንክ ይጫኑ፦
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.PropheticMedicine.Hudasoft | 164 |
| 15 | 𑁍ዓለሙል ጂንኒ ወሽ-ሸያጢን𑁍.apk | 481 |
| 16 | 𑁍አዲስ አፕልኬሽን𑁍
𑁍ዓለሙል ጂንኒ ወሽ-ሸያጢን𑁍
﹌﹌﹌﹌﹌﹌﹌﹌﹌
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኁሩህ እጀግ በጣም አዛኝ በሆነው፤ የአላህ ሰላትና ሰላም በውዱ ነብያችን ላይ ይስፈን።
በመቀጠልም ይህ አፕ ጂንኒ፣ ሸይጧን፣ ኢብሊስ ትርጓሜያቸው፣አንድነትና ልዩነታቸው፣ከነሱ መጠበቂያ መንገዶችና ሌሎችም አጫጭር መግለጫዋችን ለመረዳት ቀላል በሆነ መልኩ አካቶ ይዟል።
አፑ ከተከበረው ቁርአን፣ሐዲስና የዑለሞች ንግግርን መሰረት በማድረግ የቀረበ ነው።
አፑን ለሙስሊሙ ኡማ በማሰራጨት የኸይር ሰበብ የአጅር ተቋዳሽ ይሁኑ።
✍ፀሐፊ፦ አብዱ ሙሰማ ሀሰን
📱አፕልኬሽን ዝግጅት፦ HUDA SOFT || ሁዳ ሶፍት
መተግበሪያውን በሚከተለው ሊንክ ያውርዱ፦
𑁍https://play.google.com/store/apps/details?id=com.alemulJinn.Hudasoft | 339 |
| 17 | 📱አዲስ አፕልኬሽን ተለቀቀ📱
“ከዑለሞች ንግግር” ከ100 በላይ ድንቃ ድንቅ የዑለሞች ንግግር የያዘ አፕ!
በአላህ ስም በጣም አዛኝና ሩህሩህ በሆነው የአላህ ሰላትና ሰላም ከፍጡራን ሁሉ ምርጥ በሆኑት በነብያችን ﷺ ላይ ይውረድ።
ይህ አፕ ከ100 በላይ የዑለሞች ድንቃ ድንቅ ንግግሮች በአጭሩ አካቶ ይዟል። አፑ በውስጡ ካካተታቸው ነገራቶች በጥቂቱ፦
✑የወደዷቸውን ንግግሮች በቀላሉ ለማግኘት እንዲረዳዋት ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
✑ቀልቦትን የገዛዋት ንግግር መርጠው ለፕሮፋይል የሚሆኑ ፒክቸሮችን በቀላሉ ማዘጋጀት ይችላሉ።
✑ከድንቅ ንግግሮች መርጠው ለሌሎች ማጋራት ይችላሉ።
✑ለእይታ አመቺ ይሆን ዘንድ የቀንና የማታ ገፅታ ታክሎበታል።
✑ሌሎችም ብዙ ድንቅ ነገራቶችን አካቷል…
ከቀደምት ዑለሞች ወርቃማ ንግግሮች እራሳችንን እንድናስተምር ይረዳን ዘንድ ይህን ጠቃሚ አፕ አዘጋጅተን አቅርበንላችኋል። ከአጅሩ ተቋዳሽ እንዲሆኑ አንብበው ለሌሎችም ያጋሩ።
✍ዝግጅት፡ ወንድም አብዱ ሙሰማ ሀሰን
💻አፕልኬሽን ስራ፡ ሁዳ ሶፍት||HUDA SOFT
አፑን በሚከተለው ሊንክ ያውርዱ፦
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.UlemaSpeech.Hudasoft | 181 |
| 18 | No text... | 205 |
| 19 | ሩቂያ_መንፈሳዊ_ህክምና_com_Ruqa_HudaSoft_1_0_1.apk | 1 294 |
| 20 | No text... | 1 136 |
