cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የ ቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ ዲጅታል ቤተ-መጽሐፍ

ይህ የተለያዩ መንፈሳዊ መጻሕፍት የሚጋሩበት የ ቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ ዲጅታል ቤተ-መጽሐፍ ነው። ለ መወያየት : ለ ገንቢ ሀሳባት እና ለ መጻሕፍት ጥቆማ @Girmay_AD11 እንዲሁም @YNSel

Show more
Advertising posts
668
Subscribers
-224 hours
-17 days
+1530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የዩሀንስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፭ (15)
እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ ገበሬውም አባቴ ነው። ፍሬ የማያፈራውን በእኔ ያለውን ቅርንጫፍ ሁሉ ያስወግደዋል ፍሬ የሚያፈራውንም ሁሉ አብዝቶ እንዲያፈራ ያጠራዋል። እናንተ ስለነገርኋችሁ ቃል አሁን ንጹሓን ናችኹ በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ።ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው፥እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም። እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችኹ።ያለእኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በርሱ፥ርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል። በእኔ የማይኖር ቢኾን እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጭ ይጣላል ይደርቅማል እነርሱንም ሰብስበው ወደ እሳት ይጥሏቸዋል፥ያቃጥሏቸውማል። በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይኾንላችኹማል። ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከበራል። አብ እንደ ወደደኝ እኔ ደግሞ ወደድኋችኹ በፍቅሬ ኑሩ። እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደ ጠበቅኹ በፍቅሩም እንደምኖር፥ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችኹ። ደስታዬም በእናንተ እንዲሆን ደስታችኹም እንዲፈጸም ይህን ነግሬያችኋለኹ። እኔ እንደ ወደድኋችኹ ርስ በርሳችኹ ትዋደዱ ዘንድ ትእዛዜ ይህች ናት። . . . . . . . . . እናንተም ደግሞ ከመጀመሪያ ከእኔ ጋራ ኖራችኋልና፥ትመሰክራላችኹ።
Show all...
ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ እንደፃፉት
Show all...
ዳግማይ ትንሳኤ ምን ማለት ነው?
🔶🔶🔶 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በተነሳ በስምንተኛው ቀን በዕለተ እሁድ ደቀ መዛረሙርቱ አይሁድን ፈርተው በተሰበሰቡበት ዝግ ቤት ገብቶ "ሰላም ለእናንተ ይሁን "ብሎ ዳግም ስለ ተገለጠ # ዳግማይ _ትንሳኤ ተብሏል።
ሁለተኛ ለምን ተገለጠ?????
1, "ለሐዋርያው ቶማስ ትንሳኤውን ለማሳመን"
🔶🔶🔶የጌታችን ትንሳኤ ቶማስ ስለ ተጠራጠረ ጌታችን ቶማስ በተገኘበት ዝግ ቤት ተገልጦ ለቶማስ ና ወደኔ የተቸነከረውን እጄና ጉኔን ዳስስ ብሎታል። ቶማስም የተቸነከረው እጁን አይቶ የተወጋውን ጉኑ በእጁ ዳስሶ የጌታችን ትንሳኤ አምኗል ። ሀገረ ስብከቱም በሕንድ ስለ ነበረ ተጋድሎውም የፈጸመው እንዲሁም ሰማዕትነት የተቀበለው በሕንድ ነው ። ያቺ የጌታችንን ጎን የነካች (የዳሰሰች) እጅ ሳትበሰብስ ከታቦት ጋር በመንበሩ ላይ ተቀምጣለች ። እስካሁን ድረስ የሕንድ ሊቀ ጳጳስ ሲሾም በዛች እጅ ተመርጦና ተባርኮ እንደሚሾም አንዳንድ ሊቃውንት ይናገራሉ።
2, "ሰንበትን ሊያጸናልን"
🔶🔶🔶 የአይሁድ ሰንበት ፣ እግዚአብሔር 22 ፍጥረታትን ፈጥሮ ያረፈባትና እረፉባት ብሎ ያዘዘን ሰንበት ቀዳም (ቅዳሜ) ናት። በሐዲስ ኪዳንም ጌታችን የተጸነሰባት ፣ ከሙታን መካከል የተነሳባት ፣ አንዲሁም ደግሞ ለማጽናት ሁለተኛ የተገለጠባት (ዳግማይ ትንሳኤ) ፣ መንፈስ ቅዱስ የወረደባትና ሐዋርያት ከመጀመርያዋቹ ክርስቲያኖች ጋር በኅብረት ሆነው መንፈሳዊ ስራዋች የሚሰሩባት ቀን ዕለተ እሁድ ነበረች። ቤተ ክርስቲያናችን ለቅዳሜ ቀዳሚት ሰንበት ለእሁድ ደግሞ ሰንበተ ክርስቲያን እያለች ለሁለቱም ቀናት እኩል ታከብራቸዋለች። ጌታችንም ይቺ ቀን እረፍትነቷን ለማጽናት ሁለተኛ የተገለጠባት ቀን ናት። እረፍት ስንልም ስራችንን ትተን ቁጭ ብለን (ተኝተን) የምናሳልፈው ማለት አይደለም። እንደውም ከማንም ቀን በላይ አብዝተን መንፈሳዊ ስራዎች የምንሰራባቸው ቀናት ናቸው እንጂ።
3, "ምትሐት አለመሆኑ ለማስረዳት"
🔶🔶🔶ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምትሐት እንዳልሆነና ቀድሞ የተዋሃደው ስጋና መለኮት ፣ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ መሆኑ ለማስረዳት ለሁለተኛ ጊዜ ተገልጦላቸዋል ። በዝግ ቤት መግባቱ ደግሞ መለኮት እንዳልተለየውና ሥጋ ብቻው እንዳልሆነ ለማስረዳት ነው። መልካም ዳግማይ ትንሣኤን ተመኘን🙏🙏🙏
Show all...
6👍 2