cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Andalus Academy G-8

▶ ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች፦ ➤ በተለያቱ ትምህርት ቤቶች የተዘጋጁ:- ➢ Models ➢ Worksheets ➢ Short notes ➢ ከምትማሩት ትምህርት ጋር የሚሄዱ ቪድዮዎችን ➢ Ministry Exams ➤ የአጠናን ስልትና የፈተና ጊዜ ሲቃረብ በአላህ እገዛ ጭንቀትን ለማስወገድ የሚረዱ ጥቆማዎችን እንለቃለን። Founder: Reshad Muzemil For more: t.me/ReshadMuzemil

Show more
Advertising posts
724
Subscribers
-524 hours
+17 days
+15730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ስሜቴን በቃል መግለፅ ሲያቅተኝ በፅሑፍ ብዙ ነገር ልነግራችሁ ፈልጌ ነበር፤ ግን አልነገርኳችሁም። ለእናንተ ያለኝን ፍቅርና አክብሮት ልነግራችሁ ፈልጌም ነበር፤ ነገር ግን አልነገርኳችሁም። አዎ ውድ የኔው ንፁህ ወንድምና እህቶቼ ብዙ ነገር መናገር ፈልጌ ግን አልተናገርኩም። 🇵🇸 እናንተ ለኔ የአላህ ስጦታዎች ናችሁ። አላህ በዱንያና በአኺራ ያማረ ህይወትን ይስጣችሁ! 🇵🇸 አዎ እናንተ ለኔ ባለ ንፁህ ልብ እህት ወንድሞቼ ናችሁ። አላህ በሄዳችሁበት ቦታ ሁሉ ወደ መልካም የሚጣራና ከመጥፎ የሚከለክል ወዳጅ (ጓደኛ) ያብዛላችሁ። 🇵🇸 አዎ! እናንተ ለኔ የአላህ አደራዎች ናችሁ። አላህ ለዚህ ኡማ (ማህበረሰብ) ስኬትና ተድላ ሰበብ የሚሆንን ያማረ ውጤት ይስጣችሁ። ▮ሁላችሁንም ለአላህ ብየ እወዳችኋለሁ፤ አከብራችኋለሁ። ይህ ወንድማችሁ እስትንፋሱ እስካለ ድረስ በዱዓ አይረሳችሁም። ኢንሻአላህ!! ▮ በአላህ እዝነት ሁሌም በልቤ ውስጥ ትኖራላችሁ!! ⭕️ ይህ መልዕክት የአንዱስ ት/ቤት ለ8ኛ ክፍል 2016 ዓ.ል ውድ ተማሪዎቼ (ወንድም እህቶቼ) ይድረስልኝ❗️ ✍️ ወንድማችሁ: ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
Show all...
❗️አስደሳች ዜና ለወላጆች እና ለሴቶች ❗️ የኮምፒተር እውቀት የለኝም ብለው ሳይጨናነቁ ከ zero ↗️ Full-Stack MERN web developer ልናደርጎ መሆኑን  ስናበስሮ በደስታ ነው። ስለ ልጅዎ ይህን ክረምት በምንስ ቢያሳልፍ ይሻላል ብለው ተጨንቀዋል? የሀይስኩል ተማሪዎችስ ለቀጣይ ትምህርት ብቁ እንዲያደርገኝ ይህንን ክረምት ምን ብማር ይሻላል የሚለው አሳስቧቹሀል? እናቶችስ ከቤት ሳቶጡ ገቢ ምታገኙበት ስራ የሚያስገኝ ትምህርት ምን ይሆን? ብለው ግራ ተጋብተዋል? ለሁሉም እኛ ጋ መልሱን ያገኛሉ በአጭር ጊዜ የሚያልቅ ቢሉ የረጅም Riseup tech solution ለሴቶች እና ከ12 አመት በታች ለሆኑ ህፃናት   ህይወታቸውን ቀለል የሚያደርግላቸውን እና ከቴክኖሎጂ ዘመን ጋር ፈጥነው እንዲቀላቀሉ የሚያስችላቸውን የፕሮግራሚንግ ትምህርት በonline እና በአካል ለማስተማር ዝግጅታችንን አጠናቀን በምዝገባ ላይ ነን። ቦታ ሳይገድቦ ያሉበት ቦታ ሆነው በonline አልያም በአካል መማር ይችላሉ። -እንዲሁም በግሩፕ ሆነው ለሚመጡ ልዩ ቅናሽ አለን። -ከአንድ ቤት ሁለት ሰው ሲመዘገብ፤ መክፈል ሚጠበቅባቹ የአንድ ሰው ነው የሚሰጡ ኮርሶች:- ✅ front end website development ለ3 ወራት የሚቆይ ኮርስ ሲሆን፤ ኮርሱ  -Basic Computer Skill -HTML -CSS -Media Query -Bootstrap -UX/UI Design -Building your portfolio website -Java Script (JS) እና ሎሎችንም  የሚያካትት ይሆናል። ✅ መሰረታዊ የኮምፒውተር እውቀት ለ2 ወራት የሚቆይ ኮርስ ሲሆን፤ ኮርሱ -Microsoft Word -Microsoft Excel -Microsoft PowerPoint -Microsoft publisher እና ሌሎችንም ያካትታል ✅እንዲሁም ለ Full stack web development (MERN) course በምዝገባ ላይ እንገኛለን። ኮርሱ 8 ወራት የሚቆይ ሲሆን ከcomputer አከፋፈት ጀምሮ የተዋጣለት ዌብሳይት አበልፃጊ እና ችግር ፈቺ የሆኑ ሲስተሞችን መስራት የሚያስችሎትን ፕሮግራሞች ያካተተ ነው። -Basic Computer Skill -HTML -CSS - Media Query - UX/UI Design -Javascript - jQyery - Algorithm -Git/GitHub -Bootstrap5 -Design Theory -OOP -Developer Tools -Domains and Deployment - Express - React.js -React Router -React Hooks -API - Node - PHP አላማችን ጥራት ያለው ትምህርት በጥራት መስጠት በመሆኑ የምንቀበለው ውስን ተማሪ ነው። ስለሆነም ፈጥነው ይመዝገቡ። በዌብሳይታችን http://www.riseuptechsolution.com በመግባት signup የሚለውን ነክተው  የሚጠይቆትን መስፈርት በማሟላት ይመዝገቡ።             ለበለጠ መረጃ አድራሻችን ቤተል ወደ ዌራ መሄጃ አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ ያለበት ህንፃ 3ኛ ፎቅ Mobile +251907667777                +251936775727 Telegram @riseuptechsolution ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ✦Join➬ 🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻 Telegram: t.me/BasicComputer_Skills tiktok.com/@basiccomputerskills instagram.com/basiccomputerskills Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil ╚═══📌Share📌════
Show all...
Basic Computer Skills

#በዚህ የቴሌግራም ቻናል ↪️ LOGO programming Concepts ↪️ ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችን ↪️ ኮምፒውተር ነክ ትምህርቶችን ↪️Basic Computer Skills ↪️ Computer and Android Phone App or Software ↪️ ICT Edu ከላይ_የተዘረዘሩትና ሌሎችም ገራሚ ትምህርቶች ይለቀቅበታል! t.me/Basic_ComputerSkills 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

Photo unavailableShow in Telegram
🇵🇸 የአላህ ለእህት ወንድሞቻችን ያማረ ውጤትን ስጣቸው! 🇵🇸 የአላህ በሄዱበት ሁሉ መልካም ነገርን አግራላቸው። የአላህ ወደ መልካም የሚጣራ ወዳጅ አበርክትላቸው! 🇵🇸አብሽሩ፤ እየተገፋ ላለው ማህበረሰብ ግርማ-ሞገስ የሆነን ውጤት አላህ ይሰጣችኋል!! ኢንሻአላህ!! ◆ ለአላህ ብዬ ሁላችሁን እውዳችኋለሁ! ለ8ኛ ክፍል Ministry ለተፈተናችሁ ወንድም እህቶቼ!! ✍️ የእናንተው ወንድም
Show all...
👍 6 3
Photo unavailableShow in Telegram
🔰 አላህ ይርዳችሁ! 🔰 አላህ ውጤቱን ያማረ ያድርግላችሁ! 🔰 አላህ በእናንተው ጥረት ብቻ ሰይሆን በሱ (በአላህ) እዝነት መልካም የሆነ ውጤትን ይስጣችሁ!! 🇵🇸 አብሽሩ፤ በአላህ እዝነት ሁሉም ነገር ያማረ ይሆናል!! ▮የእናንተው ወንድም
Show all...
👍 7 4
Photo unavailableShow in Telegram
የሚኒስትሪ መልስ መስጫ ወረቀት አጠቃቀም መመሪያ ለተማሪዎች ➊ የተማሪዎች መለያ ቁጥር እና የትምህርት ዓይነት መለያ ቁጥር ለእያንዳንዳቸው በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ከላይ ወደ ታች መፃፍ አለበት፡፡ ❷ በተፃፈው መለያ ቁጥር ፊት ለፊት የተፃፈውን ቁጥር የያዘውን ክብ ብቻ መጠቆር አለበት፡፡ ➌ ተማሪዎች የመረጡትን መልስ ትይዩ በተሰጠው ክብ ላይ በትክክል ማጥቆር አለባቸው፡፡ ❹ ተማሪዎች ያጠቆሩትን መልስ መቀየር ቢፈልጉ መጀመሪያ ያጠቆሩትን ክብ በደንብ ማጥፋት አለባቸው፡፡ ❺ በአንድ ረድፍ ከአንድ በላይ ክብ ማጥቆር የተከለከለ ነው፡፡ ❻ ለመፃፍ እና ለማጥቆር ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ምንም አይነት ፅሁፍም ሆነ ጭረት ማድረግ የተከለከለ ነው፡፡ ❼ ለመፃፍ ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ተፅፎ ወይም ትንሽ ጭረት እና ነጥብ ከተገኘ የመልስ መስጫ ወረቀቱ ሙሉ  በሙሉ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ❽ መልስ በሚጠቆርበት ጊዜ እርሳሱ ከተሰጠው የክብ ሳጥን መውጣት የለበትም። ከወጣም በማጥፊያ (Eraser/Rubber) ማጥፋት ይጠበቅባችኋል። ❾ መልስ መስጫ ኮርነር ላይ ያሉትን አራት ጠርዞች መንካትም ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡ ➓ ተፈታኞች የመልስ መስጫ ወረቀታቸውን በንፅህና መያዝ አለባቸው ማለትም እንዳይቆሽሽ፣ እርጥበት  እንዳይነካው፤ እንዳይቀደድ እና እንዳይታጠፍ መጠንቀቅና ሙሉ ኃላፊነት መውሰድ አለባቸው፡፡ 11. በእስኪብርቶ መፃፍ አይፈቀድም። ስለዚህ እርሳስ፣ ላጲስ እና መቅረጫ አይለያችሁ 12. ፈተና ጨረስኩ ብሎ አላስፈላጊ ነገር ስዕል ወይም ሌላ ከጀርባም ይሁን ከፊት አይፃፍበትም 13. በጣም የተቀረፀ ሹል እርሳስ በምንጠቀም ወቅት ወረቀቱ እንዳይቀደድ መጠንቀቅ አለብን።
Show all...
👍 7
መልዕክት ❷ ◆ ፈተና ከጀመርን በኋላ ማድረግ የሚገቡን ነገሮች (ፈተና ላይ እያለን) ❗️ ◉ ወደ ፈተና ከመሄዳችን ቀደም ብለን ለፈተና የሚረዱንን መሳሪያዎች እና የመፈተኛ ቁሶችን ማዘጋጀት። ◉ አብዝተን ፈተናን እና የምናመጣውን ነጥብ ስሌት አለመገመት ። 🔰 ፈተና ስንጨርስ የተሳሳትነውን ጥያቄ አብዝቶ ማሰብ እና ሌላ ተማሪ መጠየቅ ጭንቀት ውስጥ ስለሚከተን ከዚህ ይልቅ  እረፍት ማድረግ እና ለቀጣይ ፈተና መዘጋጀት ። ◉ በፈተና ጊዜ ድንገተኛ ጭንቀት እና ድንጋጤ ከገጠመን ወዲያው የምንሰራውን ገታ አድርገን በጥልቀት አየር በአፍንጫችን ስበን ወደ ሳንባ እያስገባን መልሰን ማስወጣት ይህንንም እስክንረጋጋ መደጋገም። ከዚህ በመቀጠል የማረጋጊያ ቃላትን ለራስዎ መንገር:: ◉ ፈተና በምንሰራ ጊዜ ግራ ያጋባንን እና እርግጠኛ ያልሆንበትን ጥያቄ በይለፍ ማቆየት እና ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ይህም ጊዜያችንን በአግባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። ነገር ግን ምልክት አድርገን ማለፍ፤ ◉ በተመሳሳይ እርግጠኛ ያልሆልንበትን መልስ ላይ ተደናግጠን መሰረዝ እና መደለዝን መቀነስ ይህም ስንደነግጥ እና ስንጨነቅ የምናውቀውን መልስ ትተን ወደ ሌላ መልስ እንድሰጥ ስለሚያረግ መሰረዝና መደለዝን መቀነስ ። ◉ ፈተናውን ወደ ማገባደድ ስንደርስ በይለፍ ያስቀመጥናቸውን ግራ ያጋቡንን ጥያቄዎች ጥቂት አስበንበት መልስ መስጠት ፤ ካልሆነም ደግሞ ብልሀት ተጠቅመን የግመታ መልስ ሰጥተን ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ። ◉ በተደጋጋሚ ሰአት በቃን አልበቃን እያልን አለመጨነቅ። ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ ➚ ሁሉም ነገር አላህ ከወሰነው ውጭ እንደማይሆን እርግጠኛ መሆንና ፈተና ማለት ለጀነትና ለጀኃነም ማለፊያ ትኬት እንዳልሆነ እርግጠኛ መሆን። ▮ከኛ የሚጠበቀው የአቅማችንን ያህል ማድረግ ሌላውን ለአላህ መተው ነው‼️ ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ ◉ ወቅቱ የፈተና ወቅት በመሆኑ ተማሪዎች ይህን ማስታወሻ እንዲጠቀሙበት  አሳስባለሁ። 🔰 አላህ ይርዳችሁ! 🔰 አላህ ውጤቱን ያማረ ያድርግላችሁ! 🔰 አላህ በናተው ጥረት ብቻ ሰይሆን በሱ (በአላህ) እዝነት መልካም የሆነ ውጤትን ይስጣችሁ!! ▮ወንድማችሁ: ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ⭕️ መልዕክቱን ለወንድም እህቶቻችሁ አጋሯቸው። ══════════════ ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇👇 share👇 ➊ t.me/AndalusGrade7and8t.me/AcademicEducationst.me/BasicComputer_Skillst.me/AndalusGrade5and6
Show all...
👍 7
⭐️ በፈተና ጊዜ የሚፈጠርን ጭንቀት ወይም ቴንሽንን ልንቆጣጠር የምንችልባቸው ዘዴዎች! ======================== ⭐️ ፈተና የመፈተኛ ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ ነገር ነው:: ⭐️ ከፈተና በፊት ይህን አይነቱን ከፍተኛ ውጥረት መቆጣጠር የምንችለበት መንገድ:- -------------------------------- ✅ ፈተና ሲመጣ መጠነኛ ውጥረት እና ጭንቀት ተፈጥሮአዊ እና ሁሉም ተፈታኝ ተማሪ እንደሚያጋጥመው መረዳት። ✅ ለፈተና ስንዘጋጅ አዎንታዊ እና በጎ ሀሳቦችን ማሰብ፡፡ ✅ ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ እንጂ የኛ የህይወት ምዕራፍ ማብቂያ ወይም አጠቃላይ ችሎታችንን የሚያመላክት አይደለም ።  ✅ ማወቅ ያለብን አንድ ነገር ቢኖር መሳሳትን አለመፍራት እና ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጅ መሆንን ነው ። እንዲሁም አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን። ✅ ከጓደኞቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ፡፡ ይህ ዘዴ ይበልጥ የማስታወስ ብቃታችንን እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያረጋል ። ከዚህም በተጨማሪ የተሳሳትነውን ነገር ድጋሚ እንድንከልስ እና እርማት እንድናረግ ያግዘናል። ✅ የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ  መተኛት ። ይህም ጭንቀትን ይቀንስልናል፣ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል። ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ ◆ በተጨማሪም የአቅማችሁን (የምትችሉትን) ያህል ጥረት አድርጋችኋልና የቀረውን ለአላህ መስጠት (በአላህ ተወኩል ማድረግ)! ➤ አላህ ነገሮቻችንን እንዲያገራላችሁ ዱዓ (ፀሎት) ማድረግ!! ➤  ከሰዎች (ከጓደኞቻችሁ) ጋር ትንሽም ቢሆን ተጋጭታችሁ ከሆነ፤ ውስጣችሁ ሰላምና ደስታ እንዲሰማችሁ፣ በንፁህ (Fresh) አዕምሮ ፈተና ላይ እንድትቀመጡ እንዲያግዛችሁ፣ ጌታችን አላህ እንዲደሰትባችሁም ጭምር ከጓደኞቻችሁ ጋር ይቅር ተባባሉ። ይቅር መባባል ለልብ ነፃነትን ለአዕምሮ ደግሞ ጤናን ይሰጣልና❗️ ▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬ አላህ ይርዳችሁ! አላህ ለማህበረሰቡ የሚጠቅምና ቤተሰብ የሚያኮራ ውጤት ይስጣችሁ። አላህ ሰዎች የሚያዝኑቧችሁ ሳይሆን በመልካም ነገራችሁ የሚደሰቱቧችሁ ያድርጋችሁ! ⭕️ መልዕክቱን ለወንድም እህቶቻችሁ አጋሯቸው። ══════════════ ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇👇 share👇 ➊ t.me/AndalusGrade7and8t.me/AcademicEducationst.me/BasicComputer_Skillst.me/AndalusGrade5and6
Show all...
👍 7👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
GRADE 8 MSLCE- ministry EXAM 2015 EC (From our esteemed members) By: Addis Ababa City Administration Education Bureau - AACAEB Join🔻 ══════════════ • https://t.me/ETMathsNetwork • Don't forget to react and share. •♥•♥ Many Thanks ♥•♥• 𝐃𝐈𝐆𝐈𝐓𝐀𝐋 𝐄𝐃𝐔𝐂𝐀𝐓𝐈𝐎𝐍 𝐅𝐎𝐑 𝐀𝐋𝐋
Show all...
GRADE 8 AMHARIC (2015 MINISTRY EXAM).pdf8.15 KB
GRADE 8 CITIZENSHIP (2015 MINISTRY EXAM).pdf5.85 KB
GRADE 8 ENGLISH (2015 MINISTRY EXAM).pdf6.17 KB
GRADE 8 GENERAL SCIENCE (2015 MINISTRY EXAM).pdf5.72 KB
GRADE 8 MATHEMATICS (2015 MINISTRY EXAM).pdf4.13 KB
GRADE 8 SOCIAL STUDIES (2015 MINISTRY EXAM).pdf5.77 KB
👍 3🥰 1
Photo unavailableShow in Telegram
የአላህ ወንድም እህቶቻችንን እርዳቸው!! የአላህ ሁሉንም ነገር ገር አድርግላቸው!! የአላህ ባማረ ውጤት አስደስታቸው!! የአላህ መጥፎ ነገሮችንና እንቅፋቶችን አርቅላቸው! አሚን የአላህ! 🤲 🤲 🤲 🤲 ለ8ኛ ክፍለ ተማሪዎች (ለወንድም እህቶቼ)!
Show all...
👍 12🙏 10🥰 5