en
Feedback
FeedPlus Chicken 🐔 permixes

FeedPlus Chicken 🐔 permixes

Open in Telegram

የተለያዩ የዶሮ መኖ ፕሪሚክስ ቫይታሚኖች አስመጭና አከፋፋይ 0911233319/0912700909

Show more
564
Subscribers
No data24 hours
-27 days
-230 days
Posts Archive
🔷ጥሩ የዶሮዎች አመጋገብ ሰዓት ➊ጠዋት 12:00 ➋ምሳ 5:00 ➌እራት 10:00 ሁሌም መኖ ይቀድማል ውሀ ይከተላል ደቀቅ ያለ መኖም ካለ በውሀ በማራስ መመገብ ይቻላል ለ1000 ዶሮ ባለ 58 ሳሜ
🔷ጥሩ የዶሮዎች አመጋገብ ሰዓት ➊ጠዋት 12:00 ➋ምሳ 5:00 ➌እራት 10:00 ሁሌም መኖ ይቀድማል ውሀ ይከተላል ደቀቅ ያለ መኖም ካለ በውሀ በማራስ መመገብ ይቻላል ለ1000 ዶሮ ባለ 58 ሳሜ የሆነ መመገቢያ 26 ብዛት ያስፈልጋል . መጠጫ ዙሪያው 45ሳሜ የሆነ መጠጫ ለ1000 ዶሮ 27 ያስፈልጋል . . አንድ ዶሮ በቀን የምትመገበውን እጥፍ ትጠጣለች መንጋው በቀን ምን ያህል መጠጣት እንዳለበት ማወቅ ይቻላል.

CHANGING FROM ONE FEED TYPE TO ANOTHER? you need to make the changes in the following ways; 1. It will take you between 3 to
CHANGING FROM ONE FEED TYPE TO ANOTHER? you need to make the changes in the following ways; 1. It will take you between 3 to 5 days to completely change to new feed. 2. On the first day of changing feed, you need to give 30% of new feed and 70% of the old feed. 3. On the second day of changing feed, you have to give 50% of new feed and 50% of old feed. 4. On the third day you are meant to give 70% new feed and 30% old feed. 5. On the fourth day you just have to roll out on new feed 100% 6. Prepare the birds for the changes and protect them against such stress by applying Animal Tonic or Multivitamin for a period of 7 days starting  a day before change of feed. Doing this, your birds shall just increase on performance, not affected by any changes in feed, improving appetite for the new feed, improving digestion of the new feed, no brown diarrhea resulting from new feed. https://t.me/Johnny590b

ነገረ - እንቁላል! የኢትዮጵያ ዶሮዎች ብዛት 60 ሚሊየን ያህል ነው ይባላል። በአፍሪካ ያሉት ዶሮዎች ግን ብዛታቸው 1ቢሊየን ይደርሳሉ። በህዝብ ብዛት ሲታይ፣ ከአፍሪካ ህዝብ 10% ያህሉ በኢትዮጵያ
ነገረ - እንቁላል! የኢትዮጵያ ዶሮዎች ብዛት 60 ሚሊየን ያህል ነው ይባላል። በአፍሪካ ያሉት ዶሮዎች ግን ብዛታቸው 1ቢሊየን ይደርሳሉ። በህዝብ ብዛት ሲታይ፣ ከአፍሪካ ህዝብ 10% ያህሉ በኢትዮጵያ ይኖራል። በዚህ ንጵጽር ቢያንስ 100 ሚሊየን ዶሮዎች ሊኖሩን ይገባ ነበር። እኛ ግን ያለን 60 ሚሊየን ዶሮዎች ብቻ ናቸው። ከዚህም ውስጥ እንቁላል ጣይ ዶሮዎች እጅግ ሲበዛ ትንሽ ናቸው። ኢትዮጵያ ብዙ እንቁላል ያስፈልጋታል። እንቁላል የምግብ እጥረትና የመቀንጨር ችግርን በመፍታት ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል። በጥንቃቄ ከተሠራ የዶሮ ሥራ አትራፊ ዘርፍ ነው። ብዙ ቦታ አይፈጅ፣ ብዙ ጊዜ አይወስድ፣ አያለፋ፣ ጥንቃቄና እውቀት ብቻ የሚጠይቅ ነው። የቻለ ሁሉ ዶሮ ያርባ። አንድ እንቁላል፣ ለአንድ ህጻን በየቀኑ!

ጥያቄ:- ዶሮዎች ለምንድ ነው እንቁላል ሚበሉት እንዴት መፍታት እችላለው መልስ:- ዶሮች እንቁላል የሚሰብሩትና የሚበሉት በመኖ ውስጥ የተመጣጠነ የምግብ ንጥረ ነገር አለመኖር ለምሳሌ የካልሺየም የፕሮ
ጥያቄ:- ዶሮዎች ለምንድ ነው እንቁላል ሚበሉት እንዴት መፍታት እችላለው መልስ:- ዶሮች እንቁላል የሚሰብሩትና የሚበሉት በመኖ ውስጥ የተመጣጠነ የምግብ ንጥረ ነገር አለመኖር ለምሳሌ የካልሺየም የፕሮቲን እጥረት ሲኖር መሬት ላይ ከእንቁላል መጣያ ውጪ ብርሀን በበዛበት የዶሮ ቤት እንቁላል ሲጥሉ የመሣሠሉት ሲሆን እንቁላል ዶሮች መብላት ከጀመሩ የሚወራረስ ባህርይ ስለሆነ እንቁላልን ፈጥኖ መሠብሰብ ከእንቁላል መጣያ ውጪ እንቁላል መጣል እንዳይለምዱ እንቁላል ለመጣል አንድ ወር ሲቀራቸው የእንቁላል መጣያ በዶሮች ቤት አስቀድሞ ማስገባት እንቁላል የሚሠብሩና የሚበሉትን ዶሮች ፈጥኖ መለየት የቤት ውስጥ ብርሃንን መቆጣጠር የተመጣጠነ መኖ ማቅረብ ለችግሩ እንደ መፍትሄ ይወሰዳሉ ። https://t.me/Johnny590b

የተመጣጠነ የዶሮዎች መኖ ውስጥ መኖር ያለባቸው የንጥረ ነገር ዓይነቶች በዶሮዎች መኖ ውስጥ የሚገኙ አስፈላጊ ንጥረ ነገሮች ፕሮቲን፣ ኃይል ሰጪ፣ ማዕድናት፣ ቫይታሚኖች እና ሌሎች የመኖ ተጨማሪዎች (
የተመጣጠነ የዶሮዎች መኖ ውስጥ መኖር ያለባቸው የንጥረ ነገር ዓይነቶች በዶሮዎች መኖ ውስጥ የሚገኙ አስፈላጊ ንጥረ ነገሮች ፕሮቲን፣ ኃይል ሰጪ፣ ማዕድናት፣ ቫይታሚኖች እና ሌሎች የመኖ ተጨማሪዎች (Feed-additives) በሚዘጋጀው መኖ ውስጥ መካተት ይኖርባቸዋል፡፡ የሃይል ሰጪ ምንጮች፡- በቆሎ ፣ማሽላ ፣ስንዴ ፣የዱቄት ፋብሪካ ተረፈ ምርቶች (ፉሩሽካ፣ ፉሩሽኬሎ፣ ወዘተ)፣ ሞላሰስ፣ ሞራ፣ ወዘተ… የፕሮቲን (ገንቢ) ምንጮች፡- የተለያዩ የቅባት እህል ፋጉሎዎች (አኩሪአተር፣ ለውዝ፣ ሰሊጥ፣ ጥጥ ፍሬ፣ ወዘተ)፣ የቄራ ተረፈ ምርቶች (ደርቆ የተፈጭ ስጋ፣ ደርቆ የተፈጭ ስጋና አጥንት፣ ደርቆ የተፈጭ ደም፣ ወዘተ)፣ ደርቆ የተፈጭ አሣ፣ ወዘተ የማዕድናት ምንጮች፡- ካልስየም፡- የተፈጨ በሃ ድንጋይ፣ የተፈጨ አጥንት ፎስፎረስ፡- የተፈጨ አጥንት ሶድየምና ክሎሪን፡- ጨው ንዑስ ማዕድናት፡- በፋብሪካ የተቀመመ የንዑስ ማዕድናት ጥንቅር (trace mineral premix) የቪታሚኖች ምንጮች፡- በፋብሪካ የተቀመመ የቪታሚኖች ጥንቅር (Vitamin premix) የጫጩቶች የመመገቢያ ቁሳቁስ የቦታ ስፋት ፍላጎት ለአንድ ጫጩት በረዥም መመገቢያ (Long/Linear feeder) 8 ሣ.ሜ ሂሣብ እና በክብ መመገቢያ (Round feeder) ከ 1- 2 ሳ.ሜ እስከ 12 ኛ ሳምንት ዕድሜ ድረስ ታሳቢ በማድረግ የቀን የመኖ ፍጆታቸው ለሶስት ጊዜ በማካፈል በመኖ መመገቢያዎቹ ቁሳቁሶች የተዘጋጀውን መኖ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ጊዜ የመመገቢያ ቁሳቁሶቹ በቀን አንድ ጊዜ ብቻ ባዶ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ https://t.me/Johnny590b

ድርጅታችን ቀለብ የእንስሳት መኖ ማቀናበሪያ የተለያዬ የእንስሳት መኖችን የላብራቶሪ ምርመራ በመታገዝ በተመጣጣኝ ዋጋ እያመረተ ይገናኛ ከነዚህም:- የእንቁላል ጣይ መኖ የእንቁላል ጣይ ከለር መኖ የቄ
ድርጅታችን ቀለብ የእንስሳት መኖ ማቀናበሪያ የተለያዬ የእንስሳት መኖችን የላብራቶሪ ምርመራ በመታገዝ በተመጣጣኝ ዋጋ እያመረተ ይገናኛ ከነዚህም:- የእንቁላል ጣይ መኖ የእንቁላል ጣይ ከለር መኖ የቄብ መኖ የጫጩት መኖ ፊንሸር ግሮወር የበሬ መኖ የበግ መኖ ስፔሻል የወተት መኖ የወተት ላም መኖ ይገኛሉ:: ስለዚህም ለተለያየ የእንስሳት መኖ ፍላጎታቹ የድርጅታችንን ምርቶች በመጠቅም ምርታማነታቹን ጨምሩ:: 0930208889/0911231651

እንቁላል ጣይ ዶሮዎች የእንቁላል ምርታቸውን ከሚቀንሱ ምክንያቶች ወይም መንስኤዎች መካከል ዋነኞቹ:- 1. የተዛባ የብርሃን ጊዜ ብርሀን በዶሮዎች እንቁላል የመጣል ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ሚና አለው። እንቁላል ጣይ ዶሮዎች እንቁላልን በአግባቡ ለመጣል እንደዝርያቸው ከ12 - 16 ሰዐት ተፈጥሮአዊ ወይም ሰው ሰራሽ ብርሀንን ይፈልጋሉ። ይህም ሳይሆን ሲቀር ወይም ሲዛባ እንቁላል ምርታቸው ላይ ከፍተኛ መቀነስ ሊከሰት ይችላል። 2. የዶሮ ቤት መጨናነቅ የዶሮ ቤት መጨናነቅ በዶሮ ቤት ውስጥ ከፍተኛ ሙቀትንና በዶሮዎች ላይ ደግሞ አላስፈላጊ ጭንቀትን በማስከተል ብሎም እንቁላል ለመጣል የሚያስፈልጋቸውን ምቾት በመንሳት የእንቁላል ምርታቸው ላይ ተፅእኖ ይኖረዋል። 3. አነስተኛ የአየር እንቅስቃሴ በዶሮ ቤት ውስጥ ዝቅተኛ የአየር ዝውውር ሲኖር በዶሮ ቤት ውስጥ የአሞኒያ ክምችት በመብዛት በዶሮዎች ላይ የመተንፈሻ አካል ችግር ያመጣል። ይህም ምርታቸውን ይቀንሰዋል። 4. የመኖ መዛባት ጥራት የሌለው መኖ ለዶሮዎች መመገብ ዶሮዎቹ እንቁላል ከመኖ ማግኘት ያለባቸውን ንጥረ ነገር ስለማያገኙ የእንቁላል ምርታቸው ይቀንሳል። 5. እድሜ በሀገራችን የሚገኙ ዝርያዎች እንደዝርያቸውና አስተዳደጋቸው ከ12 - 16 ወር እንቁላል ይጥላሉ። 6. የውሀ እጥረት ውሀ ዶሮዎች የተመገቡትን መኖ ወደ እንቁላል እና ሙቀት በመቀየር ሂደት ላይ ከፍተኛ ሚና አለው። 7. የዶሮዎች ላባ መቀየር ዶሮ ላባቸውን በሚቀይሩበት ጊዜ ከመኖ የሚያገኙትን protein ለእንቁላል ከመጠቀም ይልቅ ወደ ላባ ስለሚቀየር የእንቁላል ምርት ሊቀንስ ይችላል። 8. በሽታዎች ዶሮዎች በበሽታ በሚጠቁ ጊዜ ከመኖ የሚያነኟቸውን ንጥረ ነገሮች ለእንቁላልነት ከማዋል ይልቅ ለበሽታ መከለከያነት እና ለሙቀት ስለሚጠቀሙት ምርት ሊቀንስ ይችላል። 9. የቦታ መቀየር የቦታ መቀየር ወይም የዶሮ ቤት መቀየር በዶሮዎች ላይ ከፍተኛ መደናገጥን እና ፍርሀትን ሊፈጥር ስለሚችል እንቁላል የመጣል ሂደታቸውን ያዛባዋል። 10. ፈጣን የአየር ሁኔታ ለውጥ የአየር ሁኔታ ከቀዝቃዛ ወደ ሞቃት ወይም ከሞቃት ወደ ቅዝቃዜ በፍጥነት የሚቀየር ከሆነ ዶሮዎች የሰውነታቸውን ሙቀት ማስተካከል ስለሚኖርባቸው ምርት ይቀንሳል።

የትክክለኛ የዶሮዎች መኖና አመጋገብ አስፈላጊነት ውጤታማ የሆነ የሥጋ የዶሮ አርባታ ጥሩ ትርፍን ያስገኛል። ይህን ለማድረግ ደግሞ ዘመናዊ የሥጋ ዶሮዎች የሚፈልጉትን መኖ በጥራትና በብዛት ማቅረብ ይጠ
የትክክለኛ የዶሮዎች መኖና አመጋገብ አስፈላጊነት ውጤታማ የሆነ የሥጋ የዶሮ አርባታ ጥሩ ትርፍን ያስገኛል። ይህን ለማድረግ ደግሞ ዘመናዊ የሥጋ ዶሮዎች የሚፈልጉትን መኖ በጥራትና በብዛት ማቅረብ ይጠይቃል። ዶሮዎችን በዘመናዊ መልክ ለማርባት ከሚያስፈልገው ወጪ ከ50 እስከ 70% የሚሆነው ከመኖ ጋር የተያያዘ ነው። የዶሮዎችን ስነ-ፍጥረት ያገናዘበና ሳይንሳዊ መርሆዎችን የተከተለ አመጋገብ የምርት ወጪን በከፍተኛ ደረጃ በመቀነስ ውጤታማ ያደርጋል። እንደ ኢትዮጵያ የአየሩ ሁኔታ ውድ ቤቶችን መስራት በማይጠይቅበትና የሰው ጉልበት ወጪ ዝቅተኛ በሆነበት ሁኔታ የመኖ ወጪ ድርሻ ከላይ ከተጠቀሰውም በላይ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ በዶሮ እርባታ ስራ ላይ ወጪን ለመቀነስ መኖ ከፍተኛ አስተዋፅዖ አለው። ጥሩ የመኖ አቅርቦትና አመጋገብ ከዶሮዎች በምንፈልገው የምርት አይነትና መጠን ተመጥኖና ተሰልቶ ከተዘጋጀ የመኖ ብክነትን ይቀንሳል። ጥሩ አመጋገብ የዶሮዎችን በሽታ የመቋቋም አቅም በማሻሻል በበሽታ ሊደርስ የሚችል ጉዳትን ይቀንሳል። በተጨማሪም ከፍተኛ ምርት ለመስጠት እንዲችሉ የተሻሻሉ ዶሮዎችን በመጠቀም ለዶሮዎች አስፈላጊውን መኖ በተገቢው መንገድ ካቀረብን በሙሉ የማምረት አቅማቸው እንዲያመርቱ ዕድል እንሰጣቸዋለን። https://t.me/Johnny590b

premix ስለሚባለው የ ኬሚካል ውህድ ምንነት እና ግብአቶቹ 👉premix ማለት የ ሺታሚን አና የ ሚኒራል ውህድ ሲሆን በውስጡ እጅግ ብዙ ንጥረገሮችን ይዟል:: ያም ዶሮዎች ጥሩ እድገት አና አቋም
premix ስለሚባለው የ ኬሚካል ውህድ ምንነት እና ግብአቶቹ 👉premix ማለት የ ሺታሚን አና የ ሚኒራል ውህድ ሲሆን በውስጡ እጅግ ብዙ ንጥረገሮችን ይዟል:: ያም ዶሮዎች ጥሩ እድገት አና አቋም እንዲኖራቸው እና የ እንቁላል ምርታቸው ከፍ እንዲል ያደርጋል::/egg production/ 👉 premix በምግብ ውስጥ መደባለቃችን በቂ ቪታሚን እና ሚኒራል በውስጣቸው እንዲኖር በማረግ በምግብ እጥረት የሚከሰትን ሞት ይቀንሳል:: 👉 በመኖ ማቀነባበርያ ቦታዎች premix በማዘጋጀት የተለያዩ ግብአቶችን በመጠቀም አሁን በዝርዝር የምናየው በዋናነት በ premix ውስጥ መግባት ያለባቸው ንጥረ ነገሮች   - Choline             - Biotin        - Nicotinic acid       - vit B12,B6,B1,vitc, vit k3, vitD3, vitA   - selenium   - Iodine   - Cobalt                   - Maganese   - Zinc   - Copper              - Iron   - Magnesium   - Trayptophan   - Threonine   - Methionine   - Lysine   - protines https://t.me/Johnny590b

ለመኖ አዘገጃጀት የሚጠቅሙ እህሎች ዝርዝር 🐔በቆሎ 🐔የሩዝ ገለባ 🐔ፍሩሽካ 🐔ፍርስኬሎ 🐔የኑግ ፋጉሎ 🐔የአኩሪ አተር ፋጉሎ 🐔የኖራ ድንጋይ 🐔የበቆሎ ገለባ 🐔የለውዝ ፋጉሎ 🐔premix
ለመኖ አዘገጃጀት የሚጠቅሙ እህሎች ዝርዝር 🐔በቆሎ 🐔የሩዝ ገለባ 🐔ፍሩሽካ 🐔ፍርስኬሎ 🐔የኑግ ፋጉሎ 🐔የአኩሪ አተር ፋጉሎ 🐔የኖራ ድንጋይ 🐔የበቆሎ ገለባ 🐔የለውዝ ፋጉሎ 🐔premix 🐔Starter premix 🐔Layer concentrate 🐔Lysin 🐔Methionine 🐔toxindider 🐔amino acids

Kellb Animal Feed PLC እለታዊ የመኖ አወሳሰድ በምን ይወሰናል? መኖ ከተዘጋጀ በኋላ ለዶሮዎች በሚሰጥበት ወቅት በዶሮዎቹ ያለው ተበይነት ጥሩም መጥፎም ሊሆን ይችላል፡፡ የዶሮዎች ዕለታዊ የመኖ ፍጆታ በሚከተሉት ጉዳዮች ይወሰናል፡፡ 1) የዶሮዎች እድሜ (Age of the birds) 2) የዶሮ ዝርያ (Type of the birds) 3) የመኖው ጥራት እና አቀራረብ • መኖው ከአዘገጃጀት ጀምሮ እስከ ክምችት ጊዜ ድረስ በተገቢው ሁኔታ ካልተያዘ ለብልሽት ስለሚዳረግ የመኖው ተበይነት በጣም አጣራጣሪ ይሆናል፡፡ • በዘመናዊ ዶሮ እርባታ ለለጫጩቶች እና ለእናት ዶሮዎች የሚሰጠው መኖ በቂና ንጽህናው የተጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ • ጫጩቶች እድገታቸው እየጨመረ ስለሚሄድ የሚሰጠው የመኖ መጠን በማናጂመንት ማኑዋሉ መሰረት በየሣምንቱ ወይም በየቀኑ መጨመር ይኖርበታል:: • የሚሰጠውን መኖ ጫጩቶች በአግባቡ እንዲመገቡት ለማድረግ መመገቢያው ላይ ያለውን መኖ በየጊዜው ማገላበጥ አስፈላጊ በመሆኑ፤ ማንኛውም ዶሮ አርቢ ይህንን ስራ ተከታትሎ መተግበር አለበት:: • ለጫጩቶች በየእለቱ የሚያስፈልጋቸውን የመኖ መጠን በማስላት በቀን 3 ጊዜ ከፋፍሎ መስጠት ይታላል፡፡ መኖውን በቀን ውስጥ በሚከተለው አኳኋን ከፋፍሎ መስጠት ይቻላል፡፡ ▪ በጥዋቱ ከ12፡ዐዐ–1፡ዐዐ ሰዓት ▪ ረፋድ በ5፡ዐዐ ሰዓት ▪ ከሰዓት በ1ዐ፡ዐዐ ሰዓት አካባቢ • የዶሮዎች የመኖ አወሳሰድ በእድሜ፤ በዝርያ፤ በጤንነት፤ በእንቁላል ምርታቸው እና በክብደታቸው ስለሚለያይ በቀን ማግኘት የሚገባቸውን የመኖ መጠን በመስጠት፤ ከመንጋው ተመሳሳይ የክብደት መጠን እና ተክለ ቁመና የሌላቸውን ጫጩቶች (በእድገታቸው ቀጫጫና ደካማ የሆኑትን) ለብቻ በማግለል በቂ መኖና ውሃ እንዲያገኙ በማድረግ እድገታቸው እንዲስተካከል ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ • ለዶሮዎች አሸዋሣ ድንጋዩችን መስጠቱ በጣም ጠቀሚታ አለው፡፡ ዶሮዎቹ በጥርሳቸው ምትክ ጠንካራ ጡንቻ ያለው የምግብ መፍጫ አካል “መቋደሻ” አላቸው፡፡ የተስለቀጠው ማንኛውም ምግብ በዚህ ክፍል ተደቁሶ ስለሚያልፍ ምግቡን ለመደቆስ የሚረዳ ደግሞ ጠጠር ስለሆነ መቋደሻው ጠንካራ ትናንሽ ጠጠሮችን መያዝ ያስፈልገዋል፡፡ አንድ ጊዜ ወደ መቋደሻው የገባው ጠጠር ተልዕኮውን ሲያጠናቅቅ ማሙቶ ስለሚወጣ በሌላ አዲስ ጠጠር መተካት ይኖርበታል፡፡ • ከላይ ከተጠቀሱት የምግብ ዓይነቶች ሌላ በየቀኑ እንደየ ሁኔታውና እንደየ አካባቢው ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የመኖ አይነቶች በተጨማሪነት በመስጠት ጫጩቶቹ የተመጣጠነ መኖ ማግኘት እንዲችሉ ይረዳል፡፡ ▪ ማንኛውም የቤት ውስጥ /የማዕድ ቤት/ ትርፍርራፊ ▪ የአትክልትና ፍራፍሬ ውዳቂዎች ▪ የተፈጥሮ ሣርና ቅጠሎች /በአርንጓዴነታቸው/ ▪ የጭማቂ ተረፈ ምርቶች (ደረቅ አተላ፤ ብሪንጥ). https://t.me/Johnny590b

Kellb Animal Feeds. የመኖ ጥራት ግምገማ የእንቁላል ጣይ ዝርያ ዶሮ መኖ ጥራት ግምገማ ማለት የአንድን የተመጣጠነ የእንቁላል ጣይ ዶሮ መኖ ወይም ለመኖው ዝግጅት የሚውሉ ግብዓቶችን ይዘትና ለዶሮዎች ምግብነት መዋል መቻል አለመቻላቸውን የማወቅ ሂደት ነው። የመኖ ጥራት ግምገማ ለውጤታማ እርባታ ጉልህ ስፍራ አለው። የተሟላ የእንቁላል ጣይ ዶሮዎች መኖ ለማዘጋጀት ግብዓቶች አስቀድመው ጥራታቸውና ተስማሚነታቸው ሊፈተሽ ይገባል። መኖ ለማዘጋጀት የምንጠቀምባቸው ግብዓቶች ጥራት ለምናዘጋጀው የተቀነባበረ መኖ ጥራት መሠረት ነው። የዕንቁላል ጣይ ዶሮዎች መኖና የመኖ ግብዓቶች በውጫዊ ገጽታ (physically) ወይም በውስጣዊ ይዘታቸው (chemically) ሊለኩ ይችላሉ። የውጫዊ ግምገማ ማለት የመኖውን ናሙና በመውሰድ ክብደት፣ ሽታ፣ ቀለም (መልክ) እንዲሁም ከሌሎች በካይ ነገሮች (contaminants) ጋር አለመቀላቀሉን መመርመርና ማወቅ ነው። የውጫዊ ገጽታ ግምገማ የተቀነባበረውን መኖ ወይም የመኖ ግብዓቶችን የጥራት ደረጃ መሰረታዊ መረጃ ይሰጣል። በተቀነባበረ መኖ ወይም በመኖ ግብአቶች ውስጥ የሚገኙትን ንጥረ ምግቦች ትክክለኛ ይዘት በኬሚካላዊ ትንተና (Nutritive value analysis) ይታወቃል። የተለያዩ ውጫዊ ሁኔታቸውን በመፈተሸ የዶሮ መኖ ጥሬ ዕቃዎችን የጥራት ደረጃ መገምገም ይቻላል። ይህ ዘዴ በውስጣዊ ይዘት ላይ እንደተመሰረቱ መለኪያዎች የተሟላ ባይሆንም ጥሩ ቀለም፡- ማንኛውም የመኖ ጥሬ እቃ የሚታወቅ መደበኛ/የተለመደ ቀለም አለው። ከዚህ የታወቀ ቀለም ውጪ ያለው ከሆነ የሚያመለክተው የመኖ ግብዓቱ ወይም የተዘጋጀው ድብልቅ መኖ የተቀመጠበት ሁኔታ ተገቢ አለመሆንን ፣ በባዕድ አካላት መበከልንና በዚሁ ምክንያት የደረሰ ብልሽትን ያሳያል። • የመኖ ግብዓቶች የፍሬ መጠንና ቅርፅ ፡- ለመኖ ማዘጋጃ ግብዓትነት ለመጠቀም ያሰብነው የእህል ዓይነት ወፈር ያለ ሙሉ ፍሬ ካለው የሃይል ሰጪ ንጥረ ምግብ (ስታርች) ይዘቱ ከፍ ያለ መሆኑን ያሳያል። የሟሸሸ ፍሬ ያለው ከሆነ ግን የሃይል ሰጪ ንጥረ ምግብ (የስታርች) ይዘቱ ዝቅ ያለ መሆኑን ያሳያል። የሟሸሸ ፍሬ የውጪው ሽፋን በተነፃፃሪ ብዙ ስለሚሆን (የአሰር ይዘቱም ከፍ ስለሚል) የተፈጭነቱንም ደረጃ ዝቅተኛነት ያመለክታል። • ወጥነት፡- እንደ ገለባ፣ የተሰባበረ ፍሬ፣ የአረም ፍሬዎች፣ ከፊል አካሉ በነቀዝ መበላትና ከነዚሁ ጋር ተቀላቅሎ መገኘትና የባዕድ አካላቱ መጠን መብዛትና ማነስ የጥራት ደረጃ መለኪያ ሆኖ ያገለግላል። • ሽታ፡- ይህ የተበላሸውንና ያልተበላሸውን ጥሬ እቃ አሽትቶ ማወቅን ይጠይቃል። ከመደበኛው ሽታ የተለየ መጥፎ ሽታ ዝቅተኛ ደረጃንና መበላሸትን ይጠቁማል። ይህ በተለይ የተበላሹ የዘይት ጭማቂ ፋጉሎዎችን ለመለየት የሚያገለግል ጥሩ ዘዴ ነው። • በመዳሰስ፡- በቀላሉ የማይፈረከስ የተጣበቀና የተቋጠረ ነገር በጥሬ እቃው ውስጥ መገኘት ትክክለኛ ባለሆነ ክምችት፣ በርጥበት ምክንያት የደረሰ ብልሽትን ያመለክታል። ለዕንቁላል ጣይ ዶሮዎች የተመጣጠነ መኖ ዝግጅት የጥሬ ዕቃ ግዢ ታሳቢዎች በመኖ ጥሬ ዕቃ መረጣና ግዢ ወቅት የሚደረግ ጥንቃቄ የእርባታውን ውጤታማነት ይወስናል። ለታለመለት የዶሮ ዓይነትና የምርት ደረጃ የሚመጥኑ ጥሬ ዕቃዎች መመረጥ አለባቸው። ስለዚህ ለመኖ ማደባለቂያ ጥሬ ዕቃዎች ምርጫና ግዢ ወቅት የሚከተሉትን ነጥቦች ግምት ውስጥ ማስገባት ተገቢ ነው። • ጥሬ ዕቃው ለየትኛው የዕንቁላል ጣይ ዶሮዎች ዕድሜና የምርት ደረጃ የንጥረ ምግብ ፍላጎት ማሟያ እንደሆነ መታወቅ አለበት። አንዳንድ የመኖ ጥሬ ዕቃዎች ለዶሮ መኖ ግብዓትነት በተለያዩ ምክንያቶች ተስማሚ አይደሉም ወይም የአጠቃቀም መጠናቸው የተገደበ መሆን አለበት። ለምሳሌ፡-የጥጥ ፍሬ ፋጉሎ በዕንቁላል ጣይ ዶሮዎች መኖ ውስጥ ሌላ አማራጭ ካለ መጠቀም አይመከርም። ይህም በጥጥ ፍሬ ፋጉሎ ውስጥ የሚገኝ ጎሲፓል የሚባል ውሁድ በዕንቁላል ጥራት ላይ በሚያስከትለው አሉታዊ ተጽዕኖ ምክንያት ነው። የጥጥ ፍሬ ፋጉሎን የግድ መጠቀም ካለብን በዝቅተኛ መጠን ማካተት ይመከራል። ሞላሰስ በዶሮዎች መኖ የሚካተት ከሆነ መጠኑ ቢበዛ ከ5% መብለጥ የለበትም። ከዚህ የበለጠ ተጨምሮ በተለይ በሞቃታማ አካባቢዎች የሚከማች ከሆነ. https://t.me/Johnny590b

የተመጣጠነ የሥጋ ዶሮዎች መኖ ተፈላጊ ባህሪያት የተመጣጠነ መኖ ቀመር በሚዘጋጅበት ጊዜ ዶሮዎች የሚፈልጉት የመኖ መጠንና ንጥረ  ምግቦች ይዘት እንዲኖር ብቻ ሳይሆን ጥሩ ውጤት እንዲገኝ ሌሎችንም ተጨማሪ ባህሪያት  ታሳቢ ማድረግ ይገባል። ከነዚህ ባህሪያትም ዋነኞቹ የሚከተሉት ናቸው። • መኖው ለሥጋ ዶሮዎች የሚያስፈልገውን ማንኛውንም ንጥረ ምግብ በአስፈላጊው  መጠንና ጥምርታ የያዘ መሆን አለበት። • መኖው ዶሮዎች ሊበሉት የሚችሉት (Palatable)/ተወዳጅ መሆን ይገባዋል፣  • በሚዘጋጀው የመኖ ቅንብር ውስጥ በተቻለ መጠን በዛ ያሉ የመኖ ጥሬ ዕቃዎች  ለማካተት መሞከር ይጠቅማል። ከጥቂት ጥሬ ዕቃዎች ከሚዘጋጅ ድብልቅ ይልቅ በዛ  ካሉ ጥሬ ዕቃዎች የሚዘጋጀው የዶሮዎችን የተለያዩ ንጥረ ምግቦች ፍላጎት በተሻለ  ሁኔታ ሊያሟላ ይችላል። • በዶሮዎች ጤና፣ አካል ውስጥ በሚካሄዱ ፊዚዮሎጂያዊ ሂደቶችና መኖውን ጥቅም ላይ  እንዳይውል ከሚያደርጉ ውሁዶች ነፃ መሆን ይገባዋል። • መኖውን ከተመገቡ ዶሮዎች በሚገኘው ውጤት(ዕንቁላል/ሥጋ) የተመጣጠነ የሥጋ ዶሮዎች መኖ ቀመር ዝግጅት ታሳቢዎች የሥጋ ዶሮዎች መኖ ቀመር በሚዘጋጅበት ጊዜ ለሚከተሉት ታሳቢዎች ተገቢው ግምት • መሰረታዊ የሥጋ ዶሮ አመጋገብ ባህሪያትንና የንጥረ ምግብ ፍላጎትን በመገንዘብ በቀላል  ቀመሮች የሥጋ ዶሮዎችን ፍላጎት ማሟላት የሚያስችል ቀመር ማዘጋጀት። • የሥጋ ዶሮዎች በቀን መመገብ የሚችሉት መጠን የተወሰነ ቢሆንም በተለያዩ ሁኔታዎች  የተነሳ ይህ ሊቀያየር ይችላል። ከነዚህም መካከል ዝርያ፣ የሰውነት መጠን፣ የዶሮዎች  የውስጣዊ የሰውነት አሰራር ሁኔታ፣ የመኖው ተቀባይነት፣ የሃይል ሰጪ ንጥረ ምግብ  ይዘት እንዲሁም የአካባቢው የሙቀት መጠን፣ ወዘተ ይገኙባቸዋል። የመኖ ቀመር  በሚዘጋጅበት ጊዜ እነዚህ ጉዳዮች ግምት ውስጥ መግባት አለባቸው። • የሥጋ ዶሮዎች የንጥረ ምግብ ፍላጎት በተለያዩ ሁኔታዎች ሊለዋወጥ ይችላል። ከነዚህ  ውስጥ የሚከተሉት ይገኛሉ። • የሥጋ ዶሮዎች የቀን የመኖ ፍጆታ በመኖው ቅንብር ውስጥ መኖር ባለበት  የንጥረ ምግብ መጠን ላይ ተፅዕኖ አለው። • ብዙ በሽታዎች የንጥረ ምግብ አጠቃቀምንና የመኖ ፍጆታንም ሊቀንሱ  ስለሚችሉ በእንዲህ ዓይነት ወቅት ተገቢ የመኖ ንጥረ ምግብ ይዘት ማሻሻያ  ማድረግ ሊያስፈልግ ይችላል። • በተለያዩ የአያያዝ ሁኔታዎችም ሊደርሱ በሚችሉ የሥጋ ዶሮዎች ምቾት  መጓደል ማካካሻ ሊታሰብ ይገባል። ለምሳሌ መተፋፈግ፣ በቂ ያልሆነ የአየር  እንቅስቃሴ ሲኖር ዶሮዎች በበቂ ሁኔታ የማይመገቡ በመሆኑ እንዳይጎዱና  ዕድገታቸው እንዳይቀንስ በተለይ የቪታሚኖችንና የማዕድናትን መጠን ከፍ  ማድረግ ተገቢ ነው። • የሥጋ ዶሮዎች በዕድሜ እና በምርታማነት ደረጃ የንጥረ ምግብ ፍላጎታቸው  የሚለያይ በመሆኑ መኖን በመቀመር ሂደት ይህንን ግምት ውስጥ ማስገባት  ያስፈልጋል። ለምሳሌ፡ የሥጋ ዶሮዎች በጫጩትነትና ለዕርድ በሚደርሱበትጊዜ የሚያፈልጋቸው የንጥረ ምግብ መጠን ይለያያል። https://t.me/Johnny590b