en
Feedback
FeedPlus Chicken 🐔 permixes

FeedPlus Chicken 🐔 permixes

Open in Telegram

የተለያዩ የዶሮ መኖ ፕሪሚክስ ቫይታሚኖች አስመጭና አከፋፋይ 0911233319/0912700909

Show more
564
Subscribers
No data24 hours
-27 days
-230 days
Posts Archive
በርቱ አሁን የተቸገርነው የመኖ አምራቾች በጣም ደረጃው የወረደ መኖ ለገንዘብ ሲሉ እያመረቱ እየሸጡ ነው በጣም ትላልቅ ኩባንያወች በጣም ያሳዝናል ያውም ኩባንያው ድረሰ ሔደን ገዝተን እናንተና እናንተን የሚመሰሉ አዳዲሶች በርቱ የተሻለ ሰራ ትሰራላችሁ የባለሞያ ሰብሰብም ሰለሆናችሁ በርቱ ገዝቼው የዶሮወቹንና የላሞችን እየተጠቀምኩኝ ነው

1.3 መኖ መደባለቅ ለመኖ የሚያስፈልጉት ጥሬ ዕቃዎች ከተሟሉ በኋላ መከካት ያለባቸው ተከክተው እንደ እርባታ ዓይነት በተዘጋጅ ቀመር መሰረት ማደባለቅ ያስፈልግል፡፡ ሶስት ዓይነት የመኖ ማደባለቂያ ዘዴዎች ሲኖሩ እነሱም በሲሚንቶ ወለል የማደባለቅያ ዘዴ፣ ዘመናዊ የመኖ ማደራጃዎችን የመጠቀም ዘዴ እንዲሁም ከበርሜል የሚሰራ የእጅ ማደባለቂያ ዘዴ ናቸው፡፡ በተጨማሪም መኖ እንዳይባክንና እንዳይበላሽ ሊከላከሉ የሚችሉ እንደ ሸራና የተለያዩ ዓይነት ላስቲኮች በመጠቀም በትንሽ በትንሹ ማደባለቅ ይቻላል፡፡ በትልቅ ደረጃ የሚሄድ የዶሮ እርቦታ ከሆነ ግን ይህን አይነቱን ዘዴ መጠቀም ብዙ ጊዜና ጉልበትን የሚጠይቅ በመሆኑ ተመራጭ አይደለም፡፡ 1.4. የመኖ ቅርፅ ዘመናዊ የመኖ ማደራጃዎችን በመጠቀም እንደ እርባታው አይነትና የአርቢው ፍላጎት እንዲሁም የማሽኖች ዓይነት መኖ በሶስት ዓይነት ቅርፅ ማዘጋጀት ይቻላል፡፡ ደረቅ ድቁስ፡- በጣም ሳይደቅ ተፈጭቶ የሚሰጥ የመኖ አይነት ነው፡፡ በጣም ከደቀቀ መኖ በመንቁራቸው ውስጥ እየተለጠፈ ስለሚያቸግር ዶሮዎች በተገቢው መጠን መመገብ አይችሉም፡፡ ትናንሽ ደረቅ ክብ ቁርጥራጮች /Pellets/፡- የዳቦ ቆሉ ዓይነት ቅርጽ ያለው የመኖ አይነት ሲሆን አበዛኛውን ጊዜ ለሥጋ ዶሮዎች የሚዘጋጅ የመኖ አቀራርብ ነው፡፡ የሥጋ ዶሮዎች መኖ ሳይመርጡ እንዲበሉና በአጭር ጊዜ ውስጥ ለገበያ እንዲደረሱ በሚፈለግበት ጊዜ የሚዘጋጅ ነው፡፡ ክራምብስ፡- ይህ የመኖ አይነት የሚዘጋጀው ትናንሽ ክብ እና አነስ በማለት ነው፡፡ ይሄም ትልልቅ ቁርጥራጮችን ለመመገብ የሚያስከትለው ችግር ያቃልላል፡፡ 1.5. የምግብ አቀራረብ ነፃ አቅርቦት /Free choice feeding/ ዶሮዎች የፈለጉትን ያህል መኖ ያለ ምንም ገደብ እንዲበሉ የሚፈቅድ የአመጋገብ ስልት ሲሆን ብዙ ጊዜ ተግባራዊ የሚሆነው ለዕንቁላል ጣይ ዶሮዎች ነው፡፡ የተገደበ አቀርብት /Restricted feeding/ ከላይ ከተጠቀሰው የአመጋገብ ስልት የሚለይና እንደ አስፈላጊነቱ የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም የመኖ  አቅርቦት የሚገደብበት የአመጋገብ  ስልት ነው፡፡ ቁጥጥር  የሚደረግበት  አመጋገብ ተግባር ላይ የሚውለው ፈጣን ዕድገት ያላቸውን የሥጋ ዶሮዎች ብዙ በመመገብ የሚከሰተውን ድንገተኛ ሞት ለመቀነስ ነው.https://t.me/keleb2

በ Kellb Animal Feeds የሚዘጋጅ የመኖ ዓይነት :- 🐔 የእንቁላል ጣይ መኖ (ከ17 ሳምንት ጀምሮ) 🐔 የቄብ መኖ (ከ11-16 ሳምንት) 🐥 የእንቁላል ጣይ አሳዳጊ መኖ (ከ5-10 ሳምን
በ Kellb Animal Feeds የሚዘጋጅ የመኖ ዓይነት :- 🐔 የእንቁላል ጣይ መኖ (ከ17 ሳምንት ጀምሮ) 🐔 የቄብ መኖ (ከ11-16 ሳምንት) 🐥 የእንቁላል ጣይ አሳዳጊ መኖ (ከ5-10 ሳምንት) 🐣 የእንቁላል ጣይ ጫጩት መኖ (ከ1 ቀን እስከ 4 ሳምንት) 🐣 የስጋ ዶሮ ጀማሪ መኖ 🐥 የስጋ ዶሮ ኣሳዳጊ መኖ 🐓 የስጋ ዶሮ የመጨራሽ መኖ 🐄 የወተት ላም መኖ 🐄 የጊደር መኖ 🐐 የፍየል እና በግ መኖ 🐂 የስጋ ከብት ማደለብያ መኖ 💥 አድራሻችን :-አዲስ አበባ ሲኤምሲ ፊጋ ስልክ:- ☎️ 0911231651/0930208889

Repost from AJ Vet Services
የዶሮ አርቢዎች የሚፈጽሙቸው ትልልቅ ስህተቶች እኔ እንደ አንድ የዶሮ እርባታ ባለሙያነቴ ሸገር ከተማ ዙርያ ብዙ የዶሮ እርቢዎችን በመጎብኛት ብዙ ችግሮችን ተመልክቻለሁ ለምሳሌ 1.አንዳንድ አርቢዎች መኖ በሚዘን ሳይመዝኑ በዘፈቀዳ የሚሰጡት አርቢዎች ገጥሞኛል። 2ኛ 8×12=72 ካሬ ቤት ውስ 500 አከባቢ ዶሮዎች ማስገባት ሲገበው 1000 ያስገባ አርቢም ገጥሞኛል። 3.ምንም አይነት ሳጋቱራ ወይንም ጭድ ሳይጨምር 420 ዶሮ የሚያረባና ቤቱ የተጋገረ ጭቃ በመሆን ግቢው እጅግ የሚሸትም አለ። 4.የቤቱ አሰራር ቆርቆሮ በቆርቆሮ የሆኔ አየር ማስገብያ የሌለው መስኮት የሌለውም ገጥሞኛል። 5.ጥሩ የቤት አሰራር ጥሩ አየር ማስጉብያ፣ጥሩ ጉዝጋዝ ኖሮት በቂ መመገብያና መጠጫ ያላስቀመጡ ሰዎችም አሉ ለምሳሌ ለ 500 ዶሮ 10 መጠጫ መኖር ሲገባ 4 መጠጫና 4 መመገብያ ብቻ ያስቀመጡም አሉ። 6.የዶሮ ቤት መግብያ በር ላይ የሚረገጠውን ኬሚካል የማይጠቀሙም በብዛት አሉ። 7.ጠዋት መኖና ውሃን እየሰጡ እስከ 10 ሰዓት የሚጠፉ ሌላ ስራን የሚሰሩትንም ታዝበናል ውሃ በ6:00 ሰዓት ከጨረሱስ እስከ 10 ያለ ውሃ ይቆያሉ ማለት ነው የዶሮ እርባታ የቅርብ ክትትል ይፈልጋል ። 8.የሳሶ ጫጩት አሳዳግዎችም ከዚህ በፊት ጥቅም ላይ የዋለውን ጎዝጓዝ ሳያስወግድና ቤቱን ሳያጸዱ ጫጩት የሚያስገቡ አሉ። 9.የሳሶ ጫጩት የሚየሳድጉ ሰዎች ተገብውን ክትባት ያለመስጣትና ጫጩቶችን በስጋ ዶሮ መኖ የማሳደግ ችግርም አለ። Abdi Yadasa

ቀለብ የእንስሳት መኖ ማቀናበሪያ አድራሻችን አዲስ አበባ ሲኤምሲ ፊጋ ☎️ 0911231651/0930208889
ቀለብ የእንስሳት መኖ ማቀናበሪያ አድራሻችን አዲስ አበባ ሲኤምሲ ፊጋ ☎️ 0911231651/0930208889

የተመጣጠነ የዶሮ መኖ ማዘጋጀት ለዶሮዎች የሚሰጣቸው ጠቀሜታ!! በዘመናዊ ዶሮ እርባታ ሾል ውስጥ አብዛኛውን 60–70% የእርባታ ወጪ የሚወስዱት መኖና ከመኖ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ናቸው፡፡ በመሆኑም በመኖ ወጪ ላይ አግባብነት ያለው ቁጠባ ማድረግ ለእርባታው ትርፋማነት እና ቀጣይነት አስፈላጊ ነው፡፡ ዶሮዎችን በዘመናዊ መንገድ ለማርባት እና ተገቢውን ምርት ለማግኘት ከተፈለገ በመጠን እና በአይነት ተገቢውን የመኖ አይነት ማቅረብና አስፈላጊውን የአመጋገብ ስርዓት መከተል የግድ ነው፡፡ ለዶሮዎች የሚሰጠው ምግብ  (መኖ) አይነት እና መጠን ለሚፈለገው ምርት ወይም እድገት ተስማሚና ተፈላጊ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ የተሻሻሉ የዶሮ ዝርያዎች ጥሩ ምርት ሊሰጡ የሚችሉት አመጋገባቸው የተስተካከለና የሚሰጣቸው መኖ የተመጣጠነ ከሆነ ነው፡፡ የምናዘጋጀው መኖ ለዶሮዎች በምንፈልገው የምርት አይነት እና መጠን ተመጥኖ ከተዘጋጀ ዶሮዎች በየቀኑ  የሚወስዷትን የመኖ ፍጆታ ይቀንሣል፡፡ ዶሮዎች የተገኘውን የተለያየ የመኖ አይነት የመመገብ ባህርይ ያላቸው እንስሳት  ናቸው፡፡ አንዲት ዶሮ እንቁላላ ለማምረት በቂ የገንቢ (የኘሮቲን) እና የካልሲየም ምንጭ የሆኑትን የምግብ ንጥረ ነገሮች  ማግኘት አለባት፡፡ ዶሮዎቹ ለአድገታቸውና ምርት ለመስጠት የተለያየ የምግብ አይነት ያስፈልጋቸዋል። አንዲት ዶሮ የአመጋገብ ሁኔታዋ የተስተካከለና የተመጣጠነ ከሆነ በአምስት ወር እድሜዋ እንቁላል መጣል ትጀምራለች፡፡  👉 ነገር ግን የተመጣጠነ መኖ ያላገኘች ዶሮ እስከ 8 ወር እድሜዋ ድረስ እንቁላል መጣል አትጀምርም፡፡ አንስት ዶሮዎች እንቁላል ለመጣል የግድ አውራ ዶሮ አያስፈልጋቸውም፡፡ ሴት ዶሮ በጫጩትነት እድሜ ጀምሮ በማህፀኗ በጣም በርካታ ያልዳበሩ እንቁላሎች ስላሏት እንቁላል መጣል ስትጀምር ካሉት እንቁላሎች ውስጥ አንድ በአንድ እየዳበሩ በእንቁላል መገንቢያ የማህፀን ግድግዳ ውስጥ ሲያልፉ ሙሉ እንቁላል ሆነው ይወጣሉ፡፡ ስለዚህ እንቁላል የወንድ ዘር አገኘ አላገኝ  መጣሉ አይቀርም፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ እንቁላሉን ለማስታቀፍ አገለግሎት የምናውለው ከሆነ ከሴት (እንስት) ዶሮ ጋር የአውራው መኖር የግድ አስፈላጊ ነው፡፡ አንድ አውራ ዶሮ ከሴቷ ጋር ግንኙነት ሲያደርግ በይዘቱ አነስተኛ የሆነ ነገር ግን  በጣም በብዙ ሚሊዩን የሚቆጠሩ የወንዴ የዘር ህዋስ ያመርታል፡፡ በመሆኑም አውራ ዶሮው ጤናማ የዘር ህዋስ ለማምረት የተመጣጠነ መኖ ያስፈልገዋል፡፡  አንድ ጤነኛ የሆነ አውራ ዶሮ 1ዐ ሴት ዶሮዎችን በማጥቃት የለማ እንቁላል ለማምረት ይረዳል፡፡በአጠቃላይ ለዶሮዎች የተመጣጠነ መኖ መመገብ የሚከተሉትን ጥቅሞች ያስገኛል፤ 1. እንስሳቱን በህይወት ለማቆየት እና ለመንቀሳቀስ (Maintenance) 2. ለእድገት (Growth) 3. ለእንቁላል እና ስጋ ምርት ማስገኘት (Production) እና 4. በሽታን ለመከላከል (Disease Prevention) https://t.me/keleb2

Kellb የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ኢንተርፕራይዝ አገር አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የእንስሳት መኖዎችን በማምረት ላይ ይገኛል:: የምናመርታቸው መኖዎች ልዩ ልዩ ጥቅሞች 👉በቀላሉ በእንስሳት ሆድ ውስጥ መፈጨት(Palatablity) 👉በአጭር ጊዜ እንስሳትን ለውጤት ማብቃቱ(productivity) 👉ያለመባከኑ(absorbality) 👉በቀላሉ ያለመበላሸቱ(dryness) የምናመርታቸው መኖዎች የምጥጥን ሁኔታና ይዘት 👉የምናመርታቸው መኖዎች ከ 10-15 ካላነሱ የተለያዩ የእህል እና የጥራጥሬ ምርቶች የተዘጋጀ(በቆሎ: አኩሪአተር: ቦሎቄ: ዘንጋዳ: ሩዝ: ኑግ ...) 👉እንዲሁም የፋብሪካ ተረፈ ምርቶች ተገቢውን ምጥጥን እና ሳይንሳዊ ይዘቱን በጠበቀመልኩ በተገቢው ጥንቃቄ የተዘጋጁ የእንስሳት የመኖ አጠቃቀም ሁኔታ 1.የእንቁላል ጣይ ዶሮ አመጋገብ     1.1 ከ1-26ቀን ዶሮ :- ስታርተር መኖ በቀን 0.7kg በአማካኝ     1.2 ከ27-70ቀን ዶሮ:- የጫጩት መኖ በቀን 1.5kg የፕሮቲን መጠን 20%     1.3 ከ71-112ቀን ዶሮ:- የቄብ ዶሮ መኖ በቀን 4.5kg የፕሮቲን መጠን 16.8%    1.4 ከ175-189ቀን ዶሮ:- የእንቁላል ጣይ ፌዝ(1) መኖ በቀን 110-120gram የፕሮቲን መጠን 17%     1.5 ከ190ቀን በላይ ዶሮ:- የእንቁላል ጣይ ፌዝ(2) መኖ በቀን 120gram የፕሮቲን መጠን 16.5% 2.የስጋ ዶሮ አመጋገብ      2.1 ከ1-21ቀን ዶሮ :- ስታርተር መኖ በቀን 450g በአማካኝ     2.2 ከ22ቀን በላይ ዶሮ :- የስጋ ዶሮ መኖ በቀን ከ2-3kg በአማካኝ N.B የጫጩት መመገቢያ ለመጀመሪያወቹ ቀናት ዝርግ በሆነ ነገር መሰጠት አለበት:: 3.የወተት ላም አመጋገብ - ላሟ ከመታለቧ በፊት ድርቆሽ በቅድሚያ ሊሰጣት ይገባል -ከድርቆሽ በኃላ የተመጣጠነ 1 K.g ምጥን መኖ እንደየ እድሜዋ እንዲሁም ዝርያ አይነት ሊሰጣት ይገባል:: 4. የድልብ በሬ አመጋገብ -በቅድሚያ ድርቆሽ(ሣር) ወይም በአካባቢው የሚገኝ ልላ ምግብ ከመኖው በፊት መሰጠት አለበት - የተመጣጠነ መኖ በቀን የክብደቱን መጠን 3% መመገብ አለበት:: ለምሳሌ በሬው 800Kg ቢሆን የክብደቱ 3% ማለትም 24 Kg በቀን መመገብ አለበት ማለት ነው:: - ምንጊዜም ቢሆን ድርቆሽ ከመመገቢያው ማጣት የለበትም . https://t.me/keleb2

photo content

ድርጅታችን ቀለብ የእንስሳት መኖ ማቀናበሪያ የተለያዬ የእንስሳት መኖችን የላብራቶሪ ምርመራ በመታገዝ በተመጣጣኝ ዋጋ እያመረተ ይገናኛ ከነዚህም:- የእንቁላል ጣይ መኖ የእንቁላል ጣይ ከለር መኖ የቄ
+2
ድርጅታችን ቀለብ የእንስሳት መኖ ማቀናበሪያ የተለያዬ የእንስሳት መኖችን የላብራቶሪ ምርመራ በመታገዝ በተመጣጣኝ ዋጋ እያመረተ ይገናኛ ከነዚህም:- የእንቁላል ጣይ መኖ የእንቁላል ጣይ ከለር መኖ የቄብ መኖ የጫጩት መኖ ፊንሸር ግሮወር የበሬ መኖ የበግ መኖ ስፔሻል የወተት መኖ የወተት ላም መኖ ይገኛሉ:: ስለዚህም ለተለያየ የእንስሳት መኖ ፍላጎታቹ የድርጅታችንን ምርቶች በመጠቅም ምርታማነታቹን ጨምሩ:: 0930208889/0911231651

✔ በእርባታ ወቅት ለምንጠቀመው የመጠጥ ውሃ እና መኖ ንፅህና ምንያህል እንጨነቃለን? ☑ ለዶሮዎቹ የምናቀርበው የመጠጥ ውሃ ንፅህና እና ጤናማነት ካልተጠበቀ በከፍተኛሁኔታ በሽታ ሊያሰራጭ ስለሚችል የውሃ አያያዝ እና አጠቃቀም ላይ ጥንቃቄ ከማድረግ በተጨማሪ ቢያንስ በአመት ሁለቴ የውሃ ምንጫችንን ማስመርመር ይመከራል፡፡ ☑ መኖ በስነስርዐት ካልተቀመጠ የተለያዩ በዐይን የማይታዩ ነፍሳት እና ተህዋሲያን ሊከማቹበት ይችላል፡፡ በመሆኑም መኖ በምናስቀምጥበት ግዜ ከወለል ከፍ በማድረግ እንዲሁም ከግድግዳዎች አርቀን ቢሆን ይመረጣል፡፡ https://t.me/keleb2

በአሁኑ ጊዜ በአገራችን ውስጥ እየተስፋፋ ከሚካሄዱ የሥራ ዘርፎች አንዱ የዶሮ ርባታ ነው፡፡ ዶሮ ለማርባት ሲታሰብ የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች በማጤን የሚቋቋመውን የዶሮ እርባታ ጣቢያ ትርፋማነት ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ አንድ ሰው ዶሮዎችን የሚያረባው ከአርባታው ትርፍ ለማግኘትና ለመጠቀም ከሆነ አያያዙ በጣም የተለየ መሆን አለበት፡፡ ዶሮዎች በተለይ ደግሞ ከፍተኛ ምርት የሚሠጡ ዝርያዎች ልዩ እንክብካቤን ይፈልጋሉ፡፡ በመሆኑም አንድ ዶሮ አርቢ ወደ ዶሮ እርባታ ስራ ከመግባቱ በፊት በዋና ዋና ነገሮች ላይ በቂ ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ ከነዚህም መካከል እንደ የዝርያ መገኘት፣ የመኖ አቅርቦትና ዋጋ፣ ለዶሮ እርባታ ተስማሚ ቦታ መምረጥ የሚመረተውን ምርት ለመሸጥ የሚያስችል ገበያ መኖሩን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ሸማቹ የሚያስፈልገውን የምርት ዓይነት፣ የሚፈልግበትን ወቅት፣ እንደ ዕንቁላል አስኳልና የዶሮ ላባ ቀለም ወዘተ ያሉትን ፍላጎቶች ማወቅ ጠቃሚ ነው፡፡ እነዚህን ፍላጎቶች ማለቅ የሚመረጠውን የዝርያ አይነት ለመወሰን ጠቃሚ ነው፡፡ ዶሮዎችን ማርባት በሚታሠብበት ጊዜ ዓላማው እንቁላል፣ ሥጋ ወይም ሁለቱንም ለማምረት መሆኑን በቅድሚያ መወሰን ያስፈልጋል፡፡ ብዙ ጊዜ እንደመተዳደሪያ የገቢ ምንጭ የሚካሄድ እርባታ ከሥጋ ወይም እንቁላል ማምረት አንዱን መያዝ ይመረጣል፡፡ የመኖ ምንጮችን፣ የአቅርቦት መጠንና ዋጋ መለየትና ከየትና እንዴት እንደሚገኙ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ የመኖ ምንጮች ዕፅዋት፣እንሰሳትና ሌሎችም ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የዶሮ እርባታ ስልቶችን ምንጊዜም ቢሆን የታመመን ዶሮ ከማዳን በሽታን መከላከል አዋጭ የሆነ ተግባር ነው፡፡ ስለሆነም የርባታውን ትርፋማነት ለማሳደግ የዶሮዎችን ጤና ጠብቆ ማቆየት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ የጤና አገልግሎት ወዘተ/ላይ ባለመገንዘብ ወይም ባለማጤን ያለጥናት ዶሮ ላርባ ብሎ መነሣት ትርፋ ኪሣራ ነው፡፡ ሌሎች በስራው የተሠማሩ አርቢዎችን ልምድ በተቻለ መጠን መቅሠም ከነሱ ችግሮች በመማር የተሻለና ውጤታማ ሥራ ለመሥራት ያስችላል፡፡ https://t.me/keleb2

የዶሮ መኖ አዘገጃጀትና አመጋገብ የዶሮ እርባታ ሥራ ሲታሰብ የዶሮ መኖ ወጪ ከፍተኛውን ድርሻ ከመያዙ በተጨማሪ ምርትና ምርታማነትም በመኖ አቅርቦትና አመጋገብ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ በመሆኑም የዶሮ መኖ አቅርቦት፣ አዘገጃጀትና የመኖ አመጋገብ መሠረታዊ ታሳቢዎችን ማወቅ ተገቢ ይሆናል፡፡ የዶሮ መኖ ሲዘጋጅ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የዶሮዎችን ባህሪ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ዶሮዎች ፈጣን እድገት ያላቸው ፣ የሰውነት ሙቀታቸው ከሌሎች እንሰሳት ከፍ ያለ መሆኑና በዶሮዎች አካል ውስጥ የሚካሄድ ኬሚካላዊ ለውጦች የተሟላና የተመጣጠነ መኖ ሰለሚፈልጉ፡ የዶሮ መኖ ንጥረ ምግብ ዶሮዎች ለመኖር፣ ለማደግ፣ የዕንቁላል ምርት ለመስጠት፣ ለመራባት፣ ከበሽታ ለመከላከል የተመጣጠነ መኖ ያስፈልጋቸዋል፡፡በመሆኑም የተመጣጠነ የዶሮ መኖ በውስጡ የሚይዛቸው ንጥረ ነገሮች 1. ኃይልሠጪ 2. ገንቢ ቅባት (ስብ) 3. ቫይታሚን (በሽታን ተከላካይና አልሚ ምግብ) 4. ማዕድናት 5. ውሃ ተብለው ሊዘረዘሩ ይችላሉ፤ ኃይል ሠጪ በተመጣጠነ መኖ ውስጥ አብዛኛውን ድርሻ የሚወስደው የኃይል ሠጪነት ይዘት ያላቸው የመኖ ጥሬ ዕቃዎች ሲሆኑ ለዶሮዎች ጤናማ የሠውነት አሠራርና ዕድገት አስፈላጊናቸው፡፡ የሃይል ሰጭ ንጥረ ነገር ይዘት ያላቸው ከጥራጥሬ እህሎች ለምሳሌ በቆሎ፣ ከሰንዴ ተረፈ ምርቶች (ፊኖ፣ ፉሩሽካ) ገብስ፣ ማሽላና ከሸንኮራ አገዳ ሞላሠስ በኃይል ሰጪነት የሚካተቱ ናቸው፡፡ እነኚህ ኃይል ሰጪ ምግቦች ከተፈጩ በኋላ ከሌሎች እልሚ ምግብ ከያዙ ምግቦች ጋር በሚያስፈልገው መጠን ተመጥኖ መደባለቅ ይችላል፡፡ የገንቢ ንጥረ ምግብ፡- የገንቢ ንጥረ ነገር ለዕድገት፤ ለዕንቁላል ምርትና ለጤና ወሳኝ ነው፡፡ ቅባትነት ያላቸው በተመጣጠነ ዶሮ መኖ ቅንብር ውስጥ በአነስተኛ መጠን እንዲሆኑ ይጠበቃል፡፡ የገንቢ ንጥረ ምግብ ይዘት ያላቸው ጥሬ ዕቃዎች ከእፅዋት እና ከእንስሳት ይገኛሉ ፡፡ ከእንሳሰት የሚገኙ ተረፈ - ምርቶች የተፈጨ ሥጋና አጥንት ደርቆ የተፈጨ ደም ደርቆ የተፈጨ ዓሣና የዓሣ ተረፈምርት...ወዘተ ናቸው፡፡ የሰብል ተረፈ-ምርቶች፣ የኑግ ፋጉሎ አኩሪ አተር የጎመን ዘር ፋጉል የጥጥ ፍሬ ፋጉሎ የተልባ ፋጉሎ የኦቾለኒ፤ የሰሊጥ ፋጉሎና የመሳሰለት ናቸው፡፡ የቫይታሚን ንጥረ ነገሮች ቫይታሚኖች ለጤናማ ዕድገት መሠረት ከመሆናቸው በተጨማሪ ሌሎች ንጥረምግቦች በተገቢው መንገድ ጥቅም ላይ እንዲውሉ የማድረግ ኃይል አላቸው፡፡ በአብዛኛው የሚዘጋጀው የተመጣጠነ መኖ የቫይታሚን እጥረት ስላለው ገበያ ላይ በሽያጭ የሚገኙ ቫይታሚኖችን በመግዛት መጠቀም ይቻላል። ለምሳሌ በውሃ ተበጥብጠው የሚሰጡ ቫይታሚኖችና በተጨማሪም አረንጓዴ ቅጠላ ቅጠሎች የቫይታሚን ይዞታቸው ከፍተኛ በመሆኑ ለዶሮዎች በተጨማሪነት እንዲመገቡ ማድረግ ከፍተኛ ውጤት ማግኘት ከማስቻሉ በተጨማሪም ወጪቆጣቢ ነው፡፡ ማዕድናት፡- በተመጣጠነ የዶሮ መኖ ውስጥ የሚገኙ ማዕድናት ለአጥንት ዕድገትና ለዕንቁላል ቅርፊት ዝግጅት በዋነኝነት ይጠቅማል፡፡ የማዕድናት እጥረት የአጥንት መወላገድና መሰበር፣ የዕንቁላል ቅርፊት መሣሣትና መሠበር የዶሮዎች ዕድገት መቀጨጭና ለተለያዩ በሽታዎች የመጋለጥና የመሳሰለትን እንዲፈጠር ያደርጋል ፡፡ በተመጣጠነ የዶሮ መኖ ውስጥ የካልሲየምና ፎስፈረስ ይዘት ልዩ ትኩረት የሚሻል ሲሆን በዝግጅት ወቅትም የሁለቱ ማዕድናት አቀያየጥ በሚፈለገው መጠን ተደጋጋፎ መሆን ይኖርበታል፡፡ ለምሳሌ የፎስፈረስ መጠን ከካልሲየም ከበዛ ካልሲየሙ ጥቅም ላይ እንዳይውል ሰለሚያደርግ 4፡2 መሆን አለበት፡፡ የተፈጨ አጥንት፣ የተፈጨ ሥጋና አጥንት፣ የተፈጨ በሃ ድንጋይ፣ ጨው፣ የዕንቁላል ቅርፊትና ለዶሮ መኖነት ሊውሉ የሚችሉ በፋብሪካ ተዘጋጅተው የሚቀርቡ በማዕድን የበለፀጉትን ያካትታል፡፡ የዶሮ መኖ ፍላጎት ዶሮች እንደእድገታቸው፣ዝርያች እድሜያቸውና የምርት አሰጣጥ ደረጃቸው የተለያየ የመኖ ፍላጎት አላቸው፡፡ በመሆኑም በተሻሻለ ዶሮ እርባታ ሥራ የመኖ አቅርቦት መሠረት ማድረግ ያለበት እንደ ዶሮዎች መኖ ፍላጎት በመሆኑ አርቢው የዶሮዎችን መኖ ፍላጎት በመረዳት አስፈላጊውን መኖ ማቅረብ ካልቻለ ውጤታማ ሊሆን እንደማይችል በቅድሚያ ሊገነዘብ ይገባል። የተሻለ ውጤት ለማግኘት የባለሞያ ድጋፍና ክትትል ወሳኝ ነው በአጠቃላይ አምስት ዓይነት የተመጣጠነ መኖ ማዘጋጀት ይችላል፡፡እነሱም፡- 1. የጀማሪዎች መኖ (starter ration)፦ ከተፈለፈሉጊዜ ጀምሮ እሰከ 4 ሣምንታት ዕድሜ የሚቀርብ በመጠኑም ደቀቅ ያለና ከፍተኛ የፕሮቲን ይዘት ያለው ከ20% -22% እና ከ2800-2900ኪሎ ካሎሪ በላይ በኪሎግራም ያለው መሆን አለበት ። 2. ጫጩትመኖ (Rearing)፦ ከ4-8 ሣምንታት ዕድሜ ውስጥ ጫጩቶችን የምንመግባቸው መኖ በንጥረ ምግብ ይዘቱም ከ18-20% ፕሮቲን እንዲሁም 2900 ኪሎካሎሪ በኪ.ግ መያዝ ይገባዋል፡፡ 3. ቄብ ዶሮመኖ(Pullet)፡- ከ8-20 ሣምንታት ዕድሜ ውስጥ የምንመግባቸው መኖ ለቀጣይ ዕንቁላል ምርት ውጤታማነት ወሳኝ ነው፡፡ መኖውም የፕሮቲን ይዘቱ ከጫጩት መኖ ያነሰ መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም የፕሮቲንነት ይዘት ያላቸውን ማብዛቱ የመኖ ወጪን ከመጨመሩ በተጨማሪ በእንቁላል ምርት መቀነስ ላይ አስተዋፅኦ ስላለው ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በመሆኑም የፕሮቲን መጠኑ ከ15-16% መሆን ይኖረበታል፣ የኃይል ሰጪ ንጥረ ምግብ ከ8-14 ሣምንት ዕድሜ 2900 ኪሎ ካሎሪ በኪሎ ከ14-20 ሣምንታት ባለው ዕድሜ ደግሞ የስብ ክምችትን ለመከላከል ወደ 2750 ኪሎ ካሎሪ መቀነስ ይኖርበታል፡፡ ቄብ ዶሮዎች እንቁላል መጣል ከሚጀምሩበት ጥቂት ቀደም ብሎ የመኖ ለውጥ ቀስ በቀስ መጀመር አለበት፡፡ የእንቁላል ምርት ፍላጎትን ለማርካት የካልሲየም አቅርቦት መጨመር አለበት፡፡ ይህም ማለት የማዕድንና የቫይታሚን ድብልቅ በተጨማሪነት መመገቡ ጥሩ ውጤት ያስገኛል፡፡ 4. የእንቁላል ጣይ ዶሮች መኖ የእንቁላል ጣይ ዶሮ መኖ 2አይነት ሲሆን ለጀማሪ (Phase1) እና ለጣይ (Phase 2), ይህ መኖ 2850 ኪሎ ካሎሪ በኪ.ግ መኖ የኃይል ምንጭ ሊኖረው ይገባል፡፡ በተጨማሪ 16.5% የፕሮቲን መጠን ሊኖረው ይገባል፡፡ 5. የሥጋ ዶሮዎች መኖ፡- የሥጋ ዶሮዎች በተቻለ ፍጥነት አድገው ገበያ መቅረብ ስላለባቸው ጥራት ያለው የተመጣጠነ መኖ በማንኛውም ወቅት የፍላጎታቸውን ያህል ማግኘት አለባቸው፡፡ የሥጋ ዶሮዎች መኖ በ3 ይከፈላል፦ Starter Grower Finisher https://t.me/keleb2

ጥጃን መንከባከብ ከልጅነት ጊዜ ጀምሮ የመንከባከብ ሂደትን ያመለክታል። ለስኬታማ የጥጃ እንክብካቤ አንዳንድ ምክሮች እነሆ፡ 1. የኮሎስትረም አስተዳደር፡ ኮሎስትረም ላም ከወለደች በኋላ የሚመረተው የመጀመሪያው ወተት ነው። ለጥጃው በሽታ የመከላከል ስርዓት አስፈላጊ በሆኑ ንጥረ ነገሮች እና ፀረ እንግዳ አካላት የበለፀገ ነው። ጥጃው ከተወለደ በኋላ ባሉት 6 ሰዓታት ውስጥ እና ቢያንስ 10% የሰውነት ክብደት በመጀመሪያዎቹ 24 ሰዓታት ውስጥ ኮሎስትረም መቀበሉን ያረጋግጡ። 2.መመገብ፡- ጥጃዎች በቀን ቢያንስ ሁለት ጊዜ ወተት ወይም ወተት መተካት አለባቸው እና ጥጃው ሲያድግ የሚመገቡት መጠን ቀስ በቀስ መጨመር አለበት። የበሽታን ስርጭት ለመከላከል የአመጋገብ መሳሪያው ንጹህ እና በፀረ-ተባይ አለመያዙን ያረጋግጡ. 3.መኖሪያ ቤት፡- ጥጃዎች በንፁህ፣ ደረቅ እና አየር በሚገባበት አካባቢ መቀመጥ አለባቸው። መኖሪያ ቤቱ ጥጃዎቹ እንዲዘዋወሩ እና ንጹህ ውሃ እንዲያገኙ እና እንዲመገቡ የሚያስችል በቂ ቦታ እንዲኖር ተደርጎ መቀረጽ አለበት። 4. የጤና አያያዝ፡ ጥጆች እንደ ተቅማጥ፣ ማሳል እና የአፍንጫ ፍሳሽ ያሉ የሕመም ምልክቶችን መከታተል አለባቸው። ክትባቶች እና ትል ማድረቅ በአንድ የእንስሳት ሐኪም ምክሮች መሰረት መደረግ አለባቸው. 5. ጡት ማጥባት፡- ጥጆች እንደ ክብደታቸው እና የጤና ሁኔታቸው ከ8-10 ሳምንታት እድሜያቸው ጡት መጣል ይችላሉ። ቀስ በቀስ ጡት ማጥባት የሚቀርበውን ወተት መጠን በመቀነስ እና ቀስ በቀስ ጠንካራ ምግብን በማስተዋወቅ ሊከናወን ይችላል. 6. መዝገብ መያዝ፡ የእያንዳንዱን ጥጃ የትውልድ ቀን፣ ክብደት እና የጤና ሁኔታ ይከታተሉ። ይህ መረጃ እድገትን ለመከታተል፣ የጤና ችግሮችን አስቀድሞ ለመለየት እና በመረጃ የተደገፈ የአስተዳደር ውሳኔዎችን ለማድረግ ሊያገለግል ይችላል። https://t.me/keleb2