en
Feedback
FeedPlus Chicken 🐔 permixes

FeedPlus Chicken 🐔 permixes

Open in Telegram

የተለያዩ የዶሮ መኖ ፕሪሚክስ ቫይታሚኖች አስመጭና አከፋፋይ 0911233319/0912700909

Show more
564
Subscribers
No data24 hours
-27 days
-230 days
Posts Archive
የዶሮ መኖ አዘገጃጀትና አመጋገብ የዶሮ እርባታ ሼል ሲታሰብ የዶሮ መኖ ወጪ ከፍተኛውን ድርሻ ከመያዙ በተጨማሪ ምርትና ምርታማነትም በመኖ አቅርቦትና አመጋገብ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ በመሆኑም የዶሮ መኖ አቅርቦት፣ አዘገጃጀትና የመኖ አመጋገብ መሠረታዊ ታሳቢዎችን ማወቅ ተገቢ ይሆናል፡፡ የዶሮ መኖ ሲዘጋጅ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የዶሮዎችን ባህሪ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ዶሮዎች ፈጣን እድገት ያላቸው ፣ የሰውነት ሙቀታቸው ከሌሎች እንሰሳት  ከፍ ያለ መሆኑና በዶሮዎች አካል ውስጥ የሚካሄድ ኬሚካላዊ ለውጦች የተሟላና የተመጣጠነ መኖ ሰለሚፈልጉ፡ የዶሮ መኖ ንጥረ ምግብ ዶሮዎች ለመኖር፣ ለማደግ፣ የዕንቁላል ምርት ለመስጠት፣ ለመራባት፣ ከበሽታ ለመከላከል የተመጣጠነ መኖ ያስፈልጋቸዋል፡፡በመሆኑም  የተመጣጠነ የዶሮ መኖ በውስጡ የሚይዛቸው ንጥረ ነገሮች 1. ኃይልሠጪ 2. ገንቢ ቅባት (ስብ) 3. ቫይታሚን (በሽታን ተከላካይና አልሚ ምግብ) 4. ማዕድናት 5.  ውሃ ተብለው ሊዘረዘሩ ይችላሉ፤ ኃይል ሠጪ  በተመጣጠነ መኖ ውስጥ አብዛኛውን ድርሻ የሚወስደው የኃይል ሠጪነት ይዘት ያላቸው የመኖ ጥሬ ዕቃዎች ሲሆኑ ለዶሮዎች ጤናማ የሠውነት አሠራርና ዕድገት አስፈላጊናቸው፡፡ የሃይል ሰጭ ንጥረ ነገር ይዘት ያላቸው ከጥራጥሬ እህሎች ለምሳሌ በቆሎ፣ ከሰንዴ ተረፈ ምርቶች (ፊኖ፣ ፉሩሽካ) ገብስ፣ ማሽላና ከሸንኮራ አገዳ ሞላሠስ በኃይል ሰጪነት የሚካተቱ ናቸው፡፡ እነኚህ ኃይል ሰጪ ምግቦች ከተፈጩ በኋላ ከሌሎች እልሚ ምግብ ከያዙ ምግቦች ጋር በሚያስፈልገው መጠን ተመጥኖ መደባለቅ ይችላል፡፡   የገንቢ ንጥረ ምግብ፡- የገንቢ ንጥረ ነገር ለዕድገት፤ ለዕንቁላል ምርትና ለጤና ወሳኝ ነው፡፡ ቅባትነት ያላቸው በተመጣጠነ ዶሮ መኖ ቅንብር ውስጥ በአነስተኛ መጠን እንዲሆኑ ይጠበቃል፡፡ የገንቢ ንጥረ ምግብ ይዘት ያላቸው ጥሬ ዕቃዎች ከእፅዋት እና ከእንስሳት ይገኛሉ ፡፡ ከእንሳሰት የሚገኙ ተረፈ - ምርቶች የተፈጨ ሥጋና አጥንት ደርቆ የተፈጨ ደም ደርቆ የተፈጨ ዓሣና የዓሣ ተረፈምርት...ወዘተ ናቸው፡፡ የሰብል ተረፈ-ምርቶች፣ የኑግ ፋጉሎ አኩሪ አተር የጎመን ዘር ፋጉል የጥጥ ፍሬ ፋጉሎ የተልባ ፋጉሎ የኦቾለኒ፤ የሰሊጥ ፋጉሎና የመሳሰለት ናቸው፡፡ የቫይታሚን ንጥረ ነገሮች ቫይታሚኖች ለጤናማ ዕድገት መሠረት ከመሆናቸው በተጨማሪ ሌሎች ንጥረምግቦች በተገቢው መንገድ ጥቅም ላይ እንዲውል  የማድረግ ኃይል አላቸው፡፡ በአብዛኛው የሚዘጋጀው የተመጣጠነ መኖ የቫይታሚን እጥረት ስላለው ገበያ ላይ በሽያጭ የሚገኙ ቫይታሚኖችን በመግዛት መጠቀም ይቻላል። ለምሳሌ በውሃ ተበጥብጠው የሚሰጡ ቫይታሚኖችና በተጨማሪም አረንጓዴ ቅጠላ ቅጠሎች የቫይታሚን ይዞታቸው ከፍተኛ በመሆኑ ለዶሮዎች በተጨማሪነት እንዲመገቡ ማድረግ ከፍተኛ ውጤት ማግኘት ከማስቻሉ በተጨማሪም ወጪቆጣቢ ነው፡፡ ማዕድናት፡- በተመጣጠነ የዶሮ መኖ ውስጥ የሚገኙ ማዕድናት ለአጥንት ዕድገትና ለዕንቁላል ቅርፊት ዝግጅት በዋነኝነት ይጠቅማል፡፡ የማዕድናት እጥረት የአጥንት መወላገድና መሰበር፣ የዕንቁላል ቅርፊት መሣሣትና መሠበር የዶሮዎች ዕድገት መቀጨጭና ለተለያዩ በሽታዎች የመጋለጥና የመሳሰለትን እንዲፈጠር ያደርጋል ፡፡ በተመጣጠነ የዶሮ መኖ ውስጥ የካልሲየምና ፎስፈረስ ይዘት ልዩ ትኩረት የሚሻል ሲሆን በዝግጅት ወቅትም የሁለቱ ማዕድናት አቀያየጥ በሚፈለገው መጠን ተደጋጋፎ መሆን ይኖርበታል፡፡ ለምሳሌ የፎስፈረስ መጠን ከካልሲየም ከበዛ ካልሲየሙ ጥቅም ላይ እንዳይውል ሰለሚያደርግ 4፡2 መሆን አለበት፡፡ የተፈጨ አጥንት፣ የተፈጨ ሥጋና አጥንት፣ የተፈጨ በሃ ድንጋይ፣ ጨው፣ የዕንቁላል ቅርፊትና ለዶሮ መኖነት ሊውሉ የሚችሉ በፋብሪካ ተዘጋጅተው የሚቀርቡ በማዕድን የበለፀጉትን ያካትታል፡፡ የዶሮ መኖ ፍላጎት ዶሮች እንደእድገታቸው፣ዝርያች እድሜያቸውና የምርት አሰጣጥ ደረጃቸው የተለያየ የመኖ ፍላጎት አላቸው፡፡ በመሆኑም በተሻሻለ ዶሮ እርባታ ሼል የመኖ አቅርቦት መሠረት ማድረግ ያለበት እንደ ዶሮዎች መኖ ፍላጎት በመሆኑ አርቢው የዶሮዎችን መኖ ፍላጎት በመረዳት አስፈላጊውን መኖ ማቅረብ ካልቻለ ውጤታማ ሊሆን እንደማይችል በቅድሚያ ሊገነዘብ ይገባል። የተሻለ ውጤት ለማግኘት   የባለሞያ ድጋፍና ክትትል ወሳኝ ነው በአጠቃላይ አምስት ዓይነት የተመጣጠነ መኖ ማዘጋጀት ይችላል፡፡እነሱም፡- 1. የጀማሪዎች መኖ (starter ration)፦ ከተፈለፈሉጊዜ ጀምሮ እሰከ 4 ሣምንታት ዕድሜ የሚቀርብ በመጠኑም ደቀቅ ያለና ከፍተኛ የፕሮቲን ይዘት ያለው ከ20% -22% እና ከ2800-2900ኪሎ ካሎሪ በላይ በኪሎግራም ያለው  መሆን አለበት ከበዛ 3000 ኪሎ ካሎሪ  ። Starter Feed Formulation 1. maize            CP  4.18% 2. Furshika,       CP  1.54% 3. soya               CP  9.90% 4. Nuge             CP  2.40% 5. Mbm              CP  2.20% 6. Lim stone     CP   0 7. Premix           CP Trace 8. salt                 CP  0 9. Lysine            CP  0 10. Dl meth        CP  Trace 11. Toxin biner   CP Trace 12.Molasses     0.5 CP Trace 13. groundnet cake Replaced soya      Total Crude Protein = 20.22% 2. ጫጩትመኖ (Rearing)፦ ከ4-8 ሣምንታት ዕድሜ ውስጥ ጫጩቶችን የምንመግባቸው መኖ  በንጥረ ምግብ ይዘቱም ከ18-20% ፕሮቲን እንዲሁም 2900 ኪሎካሎሪ በኪ.ግ መያዝ ይገባዋል፡፡ Rearing Feed Formulation 1. maize          CP  4.37% 2. Furshika,    CP  1.54% 3. soya            CP  8.10% 4. Nuge           CP  3.2% 5. Mbm            CP  1.65% 6. Lim stone    CP   0 7. Premix          CP Trace 8. salt                 CP  0 9. Lysine            CP  0 10. Dl meth        CP  Trace 11. Toxin bin     CP Trace 12.Molasses  0.5 CP 0.5%      Total Crude Protein = 18.86% 3. ቄብ ዶሮመኖ(Pullet)፡- ከ8-20 ሣምንታት ዕድሜ ውስጥ የምንመግባቸው መኖ ለቀጣይ ዕንቁላል ምርት ውጤታማነት ወሳኝ ነው፡፡ መኖውም የፕሮቲን ይዘቱ ከጫጩት መኖ ያነሰ መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም የፕሮቲንነት ይዘት ያላቸውን ማብዛቱ የመኖ ወጪን ከመጨመሩ በተጨማሪ በእንቁላል ምርት መቀነስ ላይ አስተዋፅኦ ስላለው ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በመሆኑም የፕሮቲን መጠኑ ከ15-16% መሆን ይኖረበታል፣ የኃይል ሰጪ ንጥረ ምግብ ከ8-14 ሣምንት ዕድሜ 2900 ኪሎ ካሎሪ በኪሎ ከ14-20 ሣምንታት ባለው ዕድሜ ደግሞ የስብ ክምችትን ለመከላከል ወደ 2750 ኪሎ ካሎሪ መቀነስ ይኖርበታል፡፡ ቄብ ዶሮዎች እንቁላል መጣል ከሚጀምሩበት ጥቂት ቀደም ብሎ የመኖ ለውጥ ቀስ በቀስ መጀመር አለበት፡፡ የእንቁላል ምርት ፍላጎትን ለማርካት የካልሲየም አቅርቦት መጨመር አለበት፡፡ ይህም ማለት የማዕድንና የቫይታሚን ድብልቅ በተጨማሪነት መመገቡ ጥሩ ውጤት ያስገኛል፡፡https://t.me/keleb2

ቀለብ የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ የምናቀርባቸው ምርቶች 🐓የእንቁላል ጣይ መኖ ፌዝ 1 እና ፌዝ 2 (Layer feed phase 1 and phase 2)፣ 🐓የቄብ ዶሮ መኖ (pullet feed)፣ 🐓ሬሪንግ (layer rearing crumble  feed)፣ 🐓የእንቁላል ጣይ ጫጩት መኖ (layer starter crumble feed)፣ 🐓የስጋ ዶሮ ጫጩት መኖ ( broiler starter pellet feed) ፣ 🐓የስጋ ዶሮ ማሳደጊያ መኖ በፔሌት (broiler grower feed pellet)፣ 🐓የስጋ ዶሮ ማደለቢያ መኖ በ ፔሌት ( broiler finisher feed pellet) ፣ 🐓 የወተት ላም መኖ ሱፐር. እና ኤክሰለንት በፔሌት  ( Dairy feed super pellet and dairy excellent pellet) ፣ 🐓የበሬ ማደለቢያ መኖ (Beef fatteng super pellet  and beef fattening normal pellet) 🐓የፍየልና የበግ መኖ ( sheep and goat feed)፣ 🐓የጊደር መኖ (heifer feed mash ) 🐓የጥጃ መኖ (calf feed) 🐓የግመል መኖ (camel feed) 🐓 የፈረስ መኖ (horse maintainance feed) እና የመሳሰሉትን ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እናቀርባለን ። Kellb Animal feed processingየዶሮ እንቁላል የስጋ የከብቶች የበግ የፍየል መኖ ማምረቻ 0930208889/0911231651 https://t.me/keleb2

photo content

በክረምት ወቅት የሚከሰት  የዶሮ በሽታ በክረምት ወቅት በዶሮዎችን የሚከሰቱ በሽታዎች ምክንያቱ  በክረምት ዶሮ ቤት ውስጥ መጨናነቅ እና ቫይታሚኖች እና ማይክሮኤለሎች እጥረት በመኖሩ ነው። በክረምት ወቅት በጣም የተለመደው የዶሮ በሽታ - ኢመርሚዮሲስ በትክክል የሚከሰተው በትንሽ አካባቢ ውስጥ የእንስሳት መጨናነቅ ነው። በክረምት ወቅት የእንቁላል ምርት መቀነስ በአነስተኛ የቀን ብርሃን ሰዓታት ምክንያት ሊሆን ይችላል ፣ ከዚያ እንቁላሎችን በመቁረጥ ፣ እና አንዳንድ ጊዜ ላባ መቀደድ እና ሰውነትን በስጋ መለጠፍ በውጥረት ወይም በአነስተኛ ምግቦች እጥረት ምክንያት ሊከሰት ይችላል። በአንድ ክፍል ውስጥ በጣም ጥቅጥቅ ባሉ ዶሮዎች መትከል በሚያስከትለው ውጥረት ፣ ዶሮዎች በአቪዬር ውስጥ የእግር ጉዞዎችን ያደራጃሉ ፣ ወደ ዶሮ ቤት ወደ ማታ ቤት ብቻ ያስገቧቸዋል።በቀሪው ጊዜ ዶሮዎች ወደ ጎተራ ለመግባት እና ለመውጣት ነፃ ናቸው።ዶሮዎች እራሳቸውን ሲያሰራጩ እና እንቁላሎችን ሲበሉ ፣ የኖራን እና የመመገቢያ ድኝን ወደ አመጋገብ ይጨመራሉ። “በእግራቸው ላይ መቀመጥ” ኢንፌክሽን ካልሆነ ፣ ከእንቅስቃሴ እጦት የመነጨ ነው ፣ እና ዶሮዎችን በተዘጋ የዶሮ ጎጆ ውስጥ በክረምቱ ውስጥ ማቆየት በመተንፈሻ አካላት ላይ ጎጂ ውጤት አለው ፣ ይህም ባለቤቶቹ ጎተራዎችን ሲከፍቱ ጎልቶ ይታያል።https://t.me/Johnny590b

እናመሠግናለን ለመልካም አስተያየትህ

ቀለብ የእንስሳትት መኖ የተለያዩ የእንሰሳት መኖዎችን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በባለሙያዎች በመታገዝ ለተጠቃሚዎቹ በጥራት እያመረተ ይገኛል::
ቀለብ የእንስሳትት መኖ የተለያዩ የእንሰሳት መኖዎችን ደረጃውን በጠበቀ  መልኩ በባለሙያዎች በመታገዝ ለተጠቃሚዎቹ በጥራት እያመረተ ይገኛል::

አስደሳች ዜና! ድርጅታችን ቀለብ የእንስሳት መኖ ማቀናበሪያ በትግራይ ክልል በአድግራት ከተማ ሽያጭ የጀመረ መሆኑ ለደንበኞቻችን በደስታ እንገልፃለን::
አስደሳች ዜና! ድርጅታችን ቀለብ የእንስሳት መኖ ማቀናበሪያ በትግራይ ክልል በአድግራት ከተማ ሽያጭ የጀመረ መሆኑ ለደንበኞቻችን በደስታ እንገልፃለን::

በዛሬ ቀን የቀለብ ምርት በኣዲግራት ከተማ መሸጥ ጀምረናል ።

ለተሰጠን መልካም ምላሽ ከልብ እናመሰግናለን!