en
Feedback
Economics department @ AAU

Economics department @ AAU

Open in Telegram

This group help undergraduate students to get academic materials of economics department.for any suggestion contact with this @fesehatsion12 user name.

Show more
834
Subscribers
+724 hours
+147 days
+8030 days
Posts Archive
micro II ppt.pptx6.24 KB

AAU Micro II module.doc1.51 MB

micro economics ..(1).pdf2.61 MB

AAU Micro II module.doc1.97 MB

Microeconomics I0.14 KB

👇👇👇Those are all microeconomics notes prepared by d/t lecturer's

,Those are the researches done in different areas of study. 👆👆👆👆

If you want econometrics guidance book 👆

#Concept_Note _አሰራር አንድ ጥናት ወይም ፈንድ ለማፈላለግ ከሚሰራ ፕሮጀክት (ከፕሮፖዛል በፊት) በፊት የሚዘጋጅ ሃሳባዊ መግለጫ ሲሆን ከተቻለ በአንድ ገጽ ካልተቻለ በሁለት ገጽ እንዲሆን ይመከራል (ነገር ግን እንደ ተቀባይ ድርጅት ወይም የትምህርት ተቋም የገጽ መጠኑ በጥቂቱ ከፍ ሊል ይችላል)፡፡ ርዕስ 1.የፕሮጀክት ፈንድ ፍቃድ (የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግ ለመጠየቅ የሚሰራ) አልያም ለመስራት የምታስቡትን ማንኛውም የጥናት ርዕስ በተገቢው መጥቀስ:: መግቢያ (Introduction) 1.ለመስራት ያሰባችሁት ጥናት አልያም የፕሮጀክት ፈንድ ፍቃድ ጥያቄ ጭብጥ በአጭሩ ማስረዳት፤ 2.የጥናቱን ወይም የፕሮጀክት ፈንድ ፍቃድ ጥያቄ አስፈላጊነት በአግባቡ ማስረዳት፤ 3.የጥናቱን ወይም የፕሮጀክት ፈንድ ፍቃድ ጥያቄ ስለሚፈታቸው ችግሮች ወይም ስለሚያረጋግጠው ጉዳይ ማስረዳት፤ 4.እንደ አስፈላጊነቱ ከማህበራዊ፤ ፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ፋይዳዎች አንጻር ምን እንደሚመስል ማስረዳት፤ ዓላማ (Objectives) 1.ዋና የጥናቱ ውጤት መግለጫ ዓላማ (General Objective) እና ትክክለኛ ገላጭ የሆኑ ዝርዝር ዓላማዎች (Specific Objectives) መግለጽ፤ የጥናት ስልት (Research Methodology) 1.የታሰበውን ጥናት ከክፍተት መነሳቱን ማረጋገጥ (Research Gaps)፤ 2. የታሰበውን ጥናት ትክክለኛ ስልት (Research Design) ማቅረብ፤ 3. የታሰበውን ጥናት ትክክለኛውን የናሙና አመራረጥ/ስብጥር ስልት ማቅረብ፤ 4.የታሰበውን ጥናት የውጤት ትንተና ስልቶቹ (Data Analysis Methods) ትክክለኛነት ማረጋገጥ፤ 5.የታሰበውን ጥናት የጥናቱን ጥራት (Validity እና Reliability) ስለሚረጋግጥበት መንገድ ማስረዳት፤ የሚጠበቅ ውጤት (Impact) 1.ከታሰበው ጥናት ይመጣሉ የሚባሉ ውጤቶች እንዴት እንደሚለኩ ማስረዳት፤ 2. የሚመጣውን ጥናት ግኝት እንዴት ወደ ተጠቃሚዎች ማስተላለፍ እንደሚቻል ማስረዳት፤ የጊዜ እና የወጪ ሰሌዳ (Work Plan and Budget Schedule) 1.ትክክለኛ የጥናቱን እና የፕሮጀክቱን የጊዜ ሰሌዳ መግለጽ፤ 2.ለጥናቱ ወይም ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልግ የበጀት ዝርዝር ማቅረብ፤ ዋቢ ጽሁፍ (Reference) 1. በአጭር ሰነድ ውስጥ የተጠቀማችሁት ዋቢ ካለ ትክክለኛ መንገዱን ተከትሎ መጥቀስ፤

Article Review ለማድረግ 1.የአርቲክሉ 1. ርዕስ 2. ጸሃፊዎቹ 3. አሳታሚው 4. አርቲክሉ የታተመበት ቦታ 5. አርቲክሉ የታተመበት ቀን 6. የአርቲክሉ ህትመት ቁጥር 7. አርቲክሉ ስንተኛ ገጽ ላይ እንደሚገኝ 2. ርዕሱ እና አጻጻፉ ላይ ያለ ጠንካራ እና ደካማ ጎን 1. ርዕሱ ከጽሁፉ ጋር ያለው ገላጭነት 2. ትክክለኛውን የጥናት አጻጻፍ ሂደት ስለመከተሉ 3. አጭር መግለጫው ወይም Abstract ላይ ያለ ጠንካራ እና ደካማ ጎን 1. ገላጭ ስለመሆኑ 2. ዓላማውን ስለመግለጹ 3. የጥናት ስልቱን ስለመግለጹ 4. ዋና ዋና ግኝቶች ስለመገለጻቸው 5. ትክክለኛ መጠን መያዙ 6. የመፍትሄ ሃሳብ መጥቀሱ 7. ቁልፍ/key words ቃላትን ማካተቱ 4.የጥናቱ ሃተታ Problem Statement ላይ ያለ ጠንካራ እና ደካማ ጎን 1. የጥናቱ መነሻ ሃሳብ በአግባቡ ስለመጠቀሱ 2. በጥናቱ የሚሞላው Research Gap ስለመጠቀሱ 3. ጥናቱ የሚመልሳቸውን ጥያቄዎችን ስለመጥቀሱ 5.የጥናቱ ዓላማ Research Objectives ላይ ያለ ጠንካራ እና ደካማ ጎን 1. ዋና እና ዝርዝር ዓላማዎች ስለመኖራቸው 6.የጥናቱ መላምት Hypothesis ላይ ያለ ጠንካራ እና ደካማ ጎን 1. ግልጽ፤ ከመርህ/ከቀደመ ጥናት ግኝት የተወሰደ እና የሚለካ ስለመሆኑ 7.ሀተታዊ ጽሁፍ Literature Review ላይ ያለ ጠንካራ እና ደካማ ጎን 1. ከአመክንዮ ስለመነሳቱ 2. የቀደሙ ጥናቶችን ስለማጣቀሱ 3. ስዕላዊ መግለጫ Conceptual frame work ስለመስጠቱ 4. ጥራቱን የጠበቀ ስለመሆኑ 8.የጥናቱ ስልት Research Methodology ላይ ያለ ጠንካራ እና ደካማ ጎን 1. ትክክለኛ የጥናት ስልት ስለመምረጡ 2. ትክክለኛውን የናሙና አመራረጥ ስልት ስለመጠቀሙ 3. የትንተና ስልቶቹ ትክክለኛነት 4. የጥናቱን ጥራት ስለሚሪጋግጥበት መንገድ 5. የስነ ምግባር ጉዳይ ስለመጠቀሱ 9.የውጤት ትንተና ክፍሉ Data Analysis ላይ ያለ ጠንካራ እና ደካማ ጎን 1. የጥናቱን ዓላማ የሚመልሱ ስለመሆናቸው 2. ትክክለኛ የውጤት መተንተኛ ቀመሮች ስለመጠቀሙ 3. ግኝቱን ከሌሎች ጋር ስለማመሳከሩ 4. ስለውጤቱ ትክክለኛነት የሚያቀርበው ማረጋገጫ 10.ማጠቃለያ እና የመፍትሄ ሃሳቦቹ Conclusion and Recommendation ላይ ያለ ጠንካራ እና ደካማ ጎን 1. የሚተገበር እና ተዓማኒነት ያለው የመፍትሄ ሃሳብ ስለመቅረቡ 2. የመፍትሄ ሃሳቡ ከጥናቱ ግኝት ብቻ ስለመነሳቱ 11.ዋቢ አጠቃቀስ Reference ላይ ያለ ጠንካራ እና ደካማ ጎን 1. ወጥ እና ትክክለኛ ዋቢ ስለመጠቀሱ 2. የቅርብ ጊዜዎች ላይ ስለማተኮሩ 3. ተመሳሳይ ብቻ ያልሆነ የዋቢ ምንጮች ስለመጠቀሙ

የጥናት ፕሮፖዛል (Research Proposal) መስፈርቶች 1. Title 2. Summary/Abstract 3. Introduction 4. Background 5. Statement of the Problem 6. Conceptual Framework 7. Research Objectives (Main and Specific) 8. Research Questions/Research Hypotheses 9. Significance 10. Scope, Thematic 11. Description of the Study Area 12. Research Methods and Procedures (Research Design (Research Paradigm) #Research Approach (Deductive, Inductive, Exploratory, Explanatory, Qualitative, Quantitative, Mixed). #Research Type (Descriptive, Analytical, Evaluative, etc.) #Research Strategy (Experiment, Survey, Case Study, Grounded Theory, Ethnography, Action Research, etc.) #Time Dimension (Cross sectional, Longitudinal (time series), panel)  #Method of Data Collection (Type of Data, Instrumentation (Questionnaire, Interview, Focus Group Discussion, Document Review, Observation Etc.) #Sampling Methods (Sampling Technique, target population, Sampling Frame, Sampling Unit, Sample Size) #Operationalization Framework (Variables and Description, Measurement Type, Expected Sign etc.).  #Method of Data Analysis: Data quality assurance (Validity, Reliability, etc.) 13. Limitations 14. Ethical Considerations 15. Organization of the Paper 16. Work Plan  17. Budget 18. References 19. Appendices (Questionnaire, Schedule of Interview, FGD questions for etc.) በቪዲዮ በዝርዝር ከነምሳሌው ለምትፈልጉ https://youtu.be/nNgAqBe1jFg

የተሟላ ምርጥ የጥናት ፕሮፖዛል አዘገጃጀት (ከሀ እስከ ፐ) (How to Write an Excellent Research Proposal?) https://youtu.be/nNgAqBe1jFg

#Research_Gap ማውጣት የምትችሉባቸው 9 አማራጮች፦ አዲስ ጥናት ለመስራትም ሆነ ከዚህ በፊት ከተጠኑ ጥናቶች በመነሳት አዲስ ነገር ለመጨመር እና ጥሩ ጥናት ለማከናወን Research Gap የሚለይባቸው በርካታ አማራጮችን አስቀምጫለሁ እስከመጨረሻው ተጠቀሙበት ሌሎችም እንዲጠቀሙ አጋሩ። https://youtu.be/yxh5T8vbI5o

በጥናት ስራ ወቅት የኮተሪን/C.R. Kothari ስም አለመስማት አይቻልም! በተለይ ናሙና እንዴት እንደሚወጣ በደንብ በሚያስረዱት ፎርሙላዎቹ ብዙዎቻችሁ ታውቁታላችሁ፡፡ ይህ መጽሃፍ የጥናት ርዕስ እን
በጥናት ስራ ወቅት የኮተሪን/C.R. Kothari ስም አለመስማት አይቻልም! በተለይ ናሙና እንዴት እንደሚወጣ በደንብ በሚያስረዱት ፎርሙላዎቹ ብዙዎቻችሁ ታውቁታላችሁ፡፡ ይህ መጽሃፍ የጥናት ርዕስ እንዴት እንደሚለይ፤ ጥናት የሚገነባበት ስልት (Research Design)፤ ናሙና አወሳሰድ፤ መረጃ አተናተን፤ መላምት እንዴት እንደሚለካ (Testing of Hypotheses) እና የሞዴል ውጤት እንዴት እንደሚተነተን ትረዱበታላችሁ፡፡ ይህንን መጽሃፍ ስላጋራኋቹ ደስ ብሎኛል! ያለንበት ዲጂታል ወቅት ከአስተማሪ ብዙ እና በቂ የሚጠበቅበት ነው ብዬ አላምንም! (ለብዙዎች በአግባቡ አለመማር፤ ሳይገባቸው መጨረስ፤ በአድቫይዘር በቂ ድጋፍ ያለማግኘት፤ ከስራ ጋር በመማር በክፍል አለመገኘት፤ ጊዜ ማጣት፤ ወዘተ) የሚነሱ ችግሮች ናቸው፡፡ ስለዚህ ወቅቱ ማንም የፈለገውን በኢንተርኔት ታግዞ ማንበብ እና ማየት የሚችልበት በመሆኑ ሰበብ ከመደርደር ይልቅ ወሳኝ የሚባሉ እና ለትምህርት እና ለስራችሁ የሚያስፈልጋችሁን ጽሁፎች በቀን ውስጥ በምትገኝ #ተባራሪ_ደቂቃ በሞባይልም ቢሆን ማንበብ መለማመድ ግድ ነው፡፡ ይህ ልምድ በአስተማሪ፤ በአድቫይዘር፤ በጊዜ ላይ የሚኖሩንን ሰበቦች ይቀንሳል የሚል ግምት አለኝ፡፡

አዲስ እና ጥሩ የጥናት ርዕስ ለማግኘት ለተቸገራችሁ ሰዎች በዚህ ወቅት ብትሰሩባቸው ጥሩ እና በብዛት ያልተሰሩ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረጉ 10 ርዕሶችን ልጠቁማችሁ እስከመጨረሻው ተከታተሉት። https://youtu.be/lSK51l3_pLw

ጥሩ እና በተደጋጋሚ ያልተሰራ የጥናት ርዕስ ለማግኘት የብዙ ተመራቂዎች ጭንቀት ነው። ስለዚህ በቀላሉ አዲስ፤ መረጃ ያለው እና አቅምን ያገናዘበ የመመረቂያ የድግሪ እና የማስተርስ ርዕስ ማገኘት እንደሚቻል ይህንን ምክረ ሃሳብ አቅርበናል ተጠቀሙበት። https://youtu.be/X4jlW1cp6Qo

ለአጥኚዎች ተጨማሪ ትኩረት! ሁል ጊዜም Impact, Determinant, Effect፤ ወዘተ አይነት ይዘት ያላቸው ርዕሶች ስንመርጥ ስለ የምንጠቀመው Econometrics ሞዴልም አብሮ ማሰብ ያስፈልጋል። ትክክለኛውን ሞዴል ለመምረጥ ደግሞ የጥገኛ ተለዋዋጫችንን(Dependent Variable) ትክክለኛው ልኬት ልንጠቀም ይገባል። #ለምሳሌ፦ "The impact of unemployment on household welfare" ለሚለው ምሳሌ Unemplyment በኢኮኖሚያዊ ትዮሪ ውስጥ የሚለካው በRate ማለትም በመጠን ነው(ስለዚህ Continous variable) ነው። ስለዚህ ትክክለኛው ሞዴል መሆን ያለበት ለCross-sectional data (በአብዛኛው በአንዴ የሚወሰድ መረጃ ሲሆን) OLS regresion ለtime series data (ዳታው ከ31 አመት በላይ ከሆነ) ደግሞ የVAR ወይም ARDL ሞዴሎች ትክክለኛዎቹ አማራጮች ሊሆኑ ይችላሉ። ነገር ግን ብዙ አጥኚዎች የስራ አጥነት ተፅኖን ለማጥናት ያለ አግባብ Binary outcome models - Logit ወይም Probit ሲጠቀሙ ይታያሉ። ይህ ግን #አንደኛ የስራ አጥነትን (Unemployment) ባህሪ አይገልፅም! ልኬቱ ትክክል ባለመሆኑ Non-sampling error እንዲጨምር ያደርጋል። #ሁለተኛ Logit ወይም Probit ለመጠቀም አጥኚው የግድ Dependent Variableን በሁለት መክፈል አለበት። ስራ ያለው እና ስራ የሌለው (Employed እና Unemployed) በማለት። ነገር ግን ይህ ከሆነ አጥኚው ሁለት የማይነፃፀሩ ነገሮችን እያነፃፀረ በመሆኑና የተነሳበት ዓላማ ግን ስራ አጥነት በስራ አጦች ድህነት(Welfare) ያለውን ተፅኖ መለየት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ውጤቱ ተቀባይነት አይኖረውም። #ሶስተኛው ተማራማሪው መረጃ ለመሰብሰብ የናሙናው ወኪሎች ስራ አጦች ሆነው ሳለ ግን Model specification ላይ ደርሶ ስራ አጦች ስራ ካላቸው (Employed እና Unemployed) እያለ ሲከፋፍል በመረጃ ስብሰባ ወቅት ስራ ያላቸውን ተጠይቆ መረጃ ካላካተተ ንፅፅሩ ግልፅ አይሆንም። ስለዚህ የምርምሮቻችንን አርስት ስንመርጥ ሁሌም ስለ Variables (Depedent እና Indepedents) ትክክለኛ መለኪያ እና ከእርሱ ጋር አብሮ ስለምሄድ ሞዴል አስቀድመን ልናነብና ልንጠነቀቅ ይገባል። እንደ እኔ እምነት ግን እንደ ስራ አጥነት ያሉ ኡኮኖሚያዊ ቀውሶች በገላጭ የጥናት ስልት (Descriptive design) ቢጠኑ ችግሩን በደንብ የሚገልፁ ይሆናሉ። ምክንያቱም ስራ አጥነት በሰው ህይወት ላይ ያለውን ተፅኖ የርስ በርስ ተፅኖ ፈጣሪ (Explanatory design) ለማጥናት #ለምሳሌ፦ ከIndependent Variable መካከል ገቢን(income) ወስደን Significant እና Negative sign ያለው ሆኖ ብናገኝ፡ የሰዎች ገቢ በአንድ ብር ሲጨምር ስራ አጥነት ባገኘነው Cofficient ልክ ይቀንሳል ልንልና በመጨረሻም የመፍትሄ ሀሳብ ላይ የስራ አጥነትን ተፅኖ ለመቀነስ የሰዎችን ገቢ መጨመር ያሻል ልንል ነው። ነገር ግን ትንታነያችን ፖሊሲ አውጪዎችን አያሳምንም። ምክንያቱም ጥናታችን በቤተሰብ ደረጃ የገቢ ምንጭ ስለሌላቸው ሰዎች አጥንተን ስናበቃ #ገቢያቸው_ከጨመረ የሚል የመፍትሄ ሃሳብ ሲቀርብ ብዙም ትርጉም አይሰጥም። በዚያ ላይ ስራ አጥነት እና ገቢ በተቃራኒ መዛመዳቸው ለስራ አጡ ሰው ምን ይፈይደዋል? ስራ አጥነት ያደረሰበትን ዘርፈ ብዙ ቀውስስ ይገልፃል? በሌላ በኩል ምርምራችን በቤተሰብ ደረጃ ከነበረ ደግሞ አንድም የሀገራዊ ገቢ መጨመር ብቻውን ስራ አጥነትን አይቀንሰውም! በተቃራኒው የስራ አጦች መብዛት በራሱ ሀገራዊ ገቢን ሊቀንስ ይችላል። ስለዚህ በገላጭ የጥናት ስልት (Descriptive design) ከሆነ ጥናቱን የምናጠናው እያንዳንዱ ስራ አጥ ስራ በማጣቱ ምክንያት የደረሰበትን ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ሌላም ተፅኖዎች በቀላሉ እንዲዘረዝርልን በማድረግ በቀላሉ ግባችንን ማሳካት እንችላለን። የዝርዝር ተፅዕኖዎችን ክብደት ደግሞ ተጠኚው ወኪል-ስራ አጡ በጥሩ ቃላት ይገልፅልን ይሆናል! ይህም የፖሊሲ አውጭውን ልብ ሊነካ ይችላል! ያም እንግዲህ የማህበራዊ ሳይንስ ጥናት የፈለገ ሳይንሳዊ ቢሆንም በተወሰ ደረጃ እውነታዊ ስሜቶች እንዳለባቸው ያመለክታል። ይህ ሲሆን ግን ሳይንሳዊ ጥራቱን ደግሞ infrential statitical በመጠቀም ማስጠበቅ የግድ ይላል። ብዙ ኢኮኖሚስቶች የግድ ውስብስብ ሞዴል ካልተጠቀሙ በቀር ጥሩ ጥናት የሰሩ አይመስላቸውም! ብዙ መምህራንም የተመራቂዎችን ስራ ከዚሁ አንፃር በማየት ብቻ ሲያጣጥሉ ይስተዋላሉ። ዳሩ ግን ገላጭ ጥናት (Descriptive research) ለማህበራዊ ሳይንስ በጣም ገላጭ እና ተመራጭ መሆን ይችላል። የርስ በርስ ተፅኖ መለኪያ (Explanatarory research) ግን መላምት (Hypothesiss) ለመለካት ጥረት ከማድረጉ ጋር ተያይዞ ለአላስፈላጊ Manipulation ሊዳርግ እና የጥናቱን ተጠባቂ ውጤት ተዓማኒነት (Understimate) ሊያደርግ ይችላል። #ለምሳሌ፦ ስራ አጥነት በዋናነት ሁለት ኢኮኖሚያዊ ተፅኖዎች አሉት እነሱም ገቢ ማሳጣቱ እና ምርትና ምርታማነት መቀነሱ ናቸው። እነዚህ ሁለቱ ግን በራሳቸው ለዘርፈ ብዙ የህይወት ተግዳሮቶች ይዳርጉ ይሆናል፣ ታዲያ እነዚህን ተግዳሮቶች ካለየን ምኑን የተሻለ ጥናት ሰራን? ስንለያቸው ደግሞ ሁሉም መለኪያ ላይኖራቸው ስለሚችል ወደ ሞዴል እንዴት እናስገባቸዋለን? ስለዚህ ልናልፋቸው ነው? በጥናት መለየት የነበረበት የማህበረሰቡ ችግር ይቀጥል ማለት ነው። ተጨማሪ ሃሳቡን በኮሜንት ያካፈላችሁ #Kidane_Alemu_Ago ነው።

B31-Research Methodology- Kotari.pdf1.73 MB

ወደብ ጠቃሚ ሆኖ አንገብጋቢ የማይሆንበት ወቅት ይኖራል! የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ያለ ወደብ ባለቤትነት በጠቅላላ ሀገራዊ ምርት መጠን (GDP) ደካማ የሚባል አይደለም! (በአፍሪካ ከ100ቢሊዮን ዶላር በላይ GDP ካላቸው ጥቂቶች መካከል አንዱ ነው (የIMF ሪፖርት ዋቢ ከተደረገ!)። ይህ ቁጥር ሰፋፊ ወደብ ካላቸው የምስራቅ እና የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ነው። በዓለም ላይ 44 ሀገራት የወደብ ባለቤትነት የላቸውም! ከአፍሪካ 16 ሀገራት፤ ከአውሮፓ 16 ሀገራት (የበለጸጉትን ሉግዘምበርግ፤ ኦስትሪያ እና ሲዊዘርላንድን ጨምሮ) እና ከላቲን አሜሪካ 2 ሀገራት (ቦሊቪያ እና ፓራጓይ)፡፡ በዓለም ላይ ካዛኪስታን እና ኢትዮጲያ ግዙፍ ቆዳ ስፋት ይዘው ወደብ አልባ ከሚባሉት ሀገራት መካከል ናቸው፡፡ በዓለም ላይ ጎረቤቶቻቸው ሳይቀር ወደብ አልባ የሆኑ ሀገራት (Double Landlocked Countries) ሁለት ሲሆኑ፡ Liechtenstein (ጎረቤቶቿ ኦስትሪያ እና ሲዊዘርላንድን ሲሆኑ ወደብ የላቸውም) እና Uzbekistan (በአምስት ወደብ አልባ ሀገራት ተከባለች) ናቸው፡፡ ብዙ ድሃ ሀገራት ወደብ ቢኖራቸውም በየብስ ከጎረቤቶቻቸው ጋር የንግድ ግንኙነት በማድረግ ከወደብ የሚገኝን እድል ያልተጠቀሙ አሉ (ደካማ የውጪ ንግድ ተሳትፎ አላቸው)፡፡ የሱዳን፤ የጅቡቲ፤ የኤርትራ፤ የሴራሊዮን፤ የላይቤሪያ፤ የጊኒ፤ የቡርኪና ፋሶ፤ በአፍሪካ የግዙፍ ወደብ ባለቤቶች መካከል ሞዛምቢክ እና ማዳጋስካር፤ ወዘተ ኢኮኖሚ ከወደብ ጋር በጣም ደካማ ነው፡፡ ወደብ ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚ የውጪ ንግድን ከማሳደግ ጀምሮ የውጪ ባለሃብቶችን እስከመሳብ የደረሰ ሰፊ እድል ይሰጣል፡፡ በፖለቲካል ሪፎርም የተነሳ ወደብ አልባ ቢሆኑም ፈጣን እድገት እያስመዘገቡ ያሉት ቦትስዋና እና ሩዋንዳ ደግሞ ከወደብ ውጪ ኢኮኖሚ ሪፎርም ሊደረግ እንደሚችል ያሳያሉ፡፡ ኢኮኖሚ ከወደብ ሊያስቀድመው የሚችለው አንገብጋቢ ችግር ሊኖርበት ይችላል! በብዙ የአፍሪካ ሃገራት ፖለቲካል አለመረጋጋት ኢኮኖሚውን ወደብ ከማጣቱ በተጨማሪ ይፈትነዋል፡፡ ለምሳሌ፡ ባለፉት 3 ዓመታት ማሊ፤ ሱዳን፤ ቡርኪና ፋሶ እና ኒጀር በድምሩ ወደ 7 ጊዜ በመፈንቅለ መንግስት ድርጊት እና ሙከራ ኢኮኖሚያቸው ይንገዳገዳል)፡፡ ኢትዮጲያ 9 የየብስ የወደብ በሮች ሲኖራት 95 ከመቶ የውጪ ንግዷን በጅቡቲ ወደብ በመጠቀም ከቢሊየን ዶላር በላይ በዓመት ታወጣለች፡፡ የወደብ ባለቤት ሆና ቢሆን ኖሮ የውጪ ንግድ መጠኗን ከማሳደጓ በተጨማሪ የወደብ ክፍያን በማስቀረት በዓለም ገበያ በቀነሰ የትራንስፖርት ዋጋ በሚቀርብ ምርት የገበያ ተፎካካሪነቷን ማሳደግ ትችል ነበር፡፡ ነገር ግን አሁን ላይ ፖለቲካሊ በነበረ ሂደት ወደብ በኢትዮጲያ ኢኮኖሚ ውስጥ የለም! ወደብ አስፈላጊ ቢሆንም በወቅታዊ ሁኔታ አንገብጋቢው የውስጥ ፖለቲካል አለመረጋጋት እና የምርት አቅም መዳከም ነው፡፡ ፖለቲካል አለመረጋጋት የወደብም ሆነ የከፍተኛ ማዕድን ባለቤት ለሆኑ የአፍሪካ ሀገራት እያመጣ ያለው መከራ ከባድ ነው፡፡ ኢትዮጲያ በሊበራላይዜሽን መርህ Comparative Advantage የያዘችባቸውን ሴክተሮች (በጋራ ተጠቃሚነት ስልት) ኢኮኖሚያዊ እድል በምታገኝባቸው የውጪ ኢንቨስትመንቶች ላይ በመሳተፍ ወደብ ለማግኘት ብትችል መጥፎ አይሆንም፡፡ ነገር ግን ወደብ ለማግኘት ሰፊ Opportunity Cost ያለውን አይነት መንገድ (ጦርነት ተያይዞም ዓለም አቀፍ ውግዘት) ከተከተለች ግን ኢኮኖሚው ይበልጥ ፈተና እንዳያገኘው ያሰጋል፡፡

በየዓመቱ ሀገራት የጠቅላላ ሀገራዊ ምርት መጠን (GDP) እድገትን ሪፖርት ያደርጋሉ! እንዴት ይሰላል? በኢትዮጵያ የGDP አድገት ቁጥር  ክርክር አያጣውም! በቀላል ለመረዳት የሚከተለውን https://youtu.be/f8MZGRpyfpA በምሳሌ የተቀመጠ ቀመር ተመልከቱ።