cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Al EHSAN አል_ኢህሳን

የቻናሉ አላማ 1 ባለን አቅም እስልምናን በአግባቡ ለኡማው ማድረስ 2 ሙስሊሞችን በድናቸውም ይሁን በዱኒያ እውቀታቸው የነቁ እንድሆኑ መገፋፋት 3 ለወጣቶች ምክር 4 በልዩ መልኩ ሴቶችን ማንቃትና ሌሎቹም አለማዊና መንፈሳዊ ት/ቶች ይገኙበታል። ውድና የተከበራቹ የአል ኢህሳን ቻናል ቤተሰቦች ሆይ ውብና ማራኪ የሆኑ ሀሳብ አስተያያታቹ እንዳይለይን ♥♥ ለአስተያት @S1u9l አሁኑኑ ይቀላቀሉን 👇

Show more
Advertising posts
189
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-1130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

✍ ብዕረ ሐኒፍ #3 🔖ሟች እና አልቃሽ ☞የሟችና አልቃሽ አስገራሚ ገፅታ! በበስራ ከተማ ኗሪ የሆነ አላህን በጣም የሚያመልክ ሰው ወደ ሞት እየተቃረበ መጣ። በዙሪያው ያሉ ቤተሰቦቹ ማልቀስ ጀመሩ። ከዛም ይህ ሞት የተጣደው ሰው ለቤተሰቦቹ "ቁጭ አድርጉኝ" አላቸው።  ደግፈው አስቀመጡት። ከዛ ወደ አባቱ ዞረና "አባቴ ለምንድነው ምታለቅሰው?" አለው።  አባትም" አንተን ማጣቴ ካንተ ቡሃላ ብቸኛ መሆኔ ነው ያስለቀሰኝ።" አለው። ወደ እናቱም ዞረና "እናቴ ምንድነው ያስለቀሰሽ?" አላት። እሷም "የልጅ ማጣት መሪር ሀዘን ነው ያስለቀሰኝ።" አለችው። ወደ ሚስቱም ዞረና "ምንድነው የሚያስለቅስሽ?" አላት እሷም "ያንተን መልካም ነገር ስለማጣ ወደ ሌላ ሰው ስለምከጅል ሸክም ስለምሆን።" አለችው። ወደ ልጆቹም ዞረና "ምንድነው የሚያስለቅሳቹ?" አላቸው። እነሱም "ከአንተ በኋላ ወደ የቲምነት፣ ወደ ውርደትና ደጋፊ ወደ ማጣት ስለምንጓዝ" አሉ። ይሁን ሁሉ ከሰማ በኋላ ሟቹ በጣም አለቀሰ። ቤተሰቦቹም  "ለምን ታለቅሳለህ?" አሉት። እሱም "ሁላቹም ለኔ ብላቹህ ሳይሆን ለራሳቹህ ጥቅም ነው የምታለቅሱት። ይህን ስላየሁ አለቅሳለሁ።" አለ። "ከናንተ ውስጥ ለጉዜዬ መርዘም ለስንቄ ማነስ የሚያለቅስልኝ የለም? ከናንተ ውስጥ ከዚህ በኋላ መኝታዬ ለብቻዬ አፈር ለመሆኑ የሚያለቅስ የለም? ከእናንተ ውሰጥ ከዚህ  በኋላ አስደንጋጭ ሂሳብ ስለሚጠብቀኝ የሚያለቅስ ሰው የለም? ከእናንተ ውስጥ የአለማት ጌታ ፊት መቆሜን አስታውሶ የሚያለቅስልኝ የለም? አለና በፊት ለፊቱ ተደፋ።  ቢያንቀሳቅሱትም ህይወቱ አልፋለች። ሞቷል። سَفَري بَعيدٌ وَزادي لَنْ يُبَلِّغَنـي *وَقُوَّتي ضَعُفَتْ والمـوتُ يَطلُبُنـي وَلي بَقايــا ذُنوبٍ لَسْتُ أَعْلَمُها *الله يَعْلَمُهــا في السِّرِ والعَلَنِ. ጉዞዬ ሩቅ ነው ስንቄም አያደርሰኝ ሀይሌም ተዳከመ ሞትም ፈላለገኝ የማላቃት ወንጀል አለች አሰፍስፋ አላህ የሚያውቃት በምስጥር በይፋ ✍ በዐብዱረዛቅ አል–ሐበሺይ @HanifMultimedia
Show all...
👍 1
01:38
Video unavailableShow in Telegram
"ሙስሊም ነበርን" በሚል በፕሮቴስታንቱ አለም የሚገኙ ስመ ሙስሊሞች ምዕመኑን እንዴት እንደሚያታልሉት ከዚህ መመልከት ይቻላል። ትውልደ ሶማሌ የሆነችው ይህች ሴት በGMM ቲቪ የራሷ ፕሮግራም ያላት ሲሆን ሶማሌውን ለማክፈር ሆርን ኦፍ አፊሪካ ከአሜሪካ ከነ ቤተሰቧ አምጥቶ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን እያሰራት ይገኛል። ከስሟ ውጭ ግን ስለ እስልምና ምንም የምታቀው ነገር የላትም። በተለያዩ መድረኮች ግን "ሙስሊም ናት፣ የሸይኽ ቤተሰብ ናት" እየተባለች ተጋብዛ ምዕመኑን በሀሰት ትርክት ታታልለዋለች፥ ያሳዝናል..! መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ! የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇 https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf
Show all...
1.61 MB
የትናንቱን ወንጀላችንን ሳንረሳ፣ የምሽቱ ኃጢታችን ሳይደርቅ ዛሬም በማለዳ ተነስተን ሌላ የምንጀምረው ነገርስ። አላህ ሆይ!አልፋታ ብሎ ዕድሜ ልካችንን የሚከታተለንን ጥፋታችንን ቁረጥ። ኃጢአቱ አብሮት ያልተነሳ ሰው ምንኛ ታደለ!ለንፁህ ተውበት አድለን - ያ ረብ። =t.me/+CL_1nL1UHLFhZjU8
Show all...
فقد يكرهك البعض لأنك مختلف ...لكن في داخلهم يتمنون أن يكونو مثلك.. ስለተቃረንካቸው ብቻ ከፊሎቹ ሊጠሉህ ይችላሉ ግን በውስጣቸው አንተን መምሰልን ይመኛሉ። http://t.me/nuredinal_arebi
Show all...
✍ያልገባኝ ነገር ይህ ነው። ➯እንደምንሞት በርግጠኝነት እናውቃለን ነገር ግን ከሞት በኋላ ላለው ህይወት አልተዘጋጀንም በጤና ነው ወይ ቤተሰብ!!!?
Show all...
01:44
Video unavailableShow in Telegram
#Palestine ዛሬ አይርላንድ ፣ ኖርዌይ እንዲሁም ስፔን ለፍልስጤም የነጻ ሀገርነት እውቅና እንደሚሰጡ በይፋ አስታወቁ። " የዛሬው ቀን ለፍልስጤም እጅግ ታሪካዊ ቀን ነው " ተብሏል። የአየርላንድ ጠ/ሚኒስትር ሲሞን ሃሪስ " ዛሬ አየርላንድ ፣ ኖርዌይ እና ስፔን ለፍልስጤም የነጻ ሀገርነት እውቅና ሰጥተናል። ውሳኔውን ተግባራዊ ለማድረግ እያንዳንዳችን ማንኛውንም አይነት ብሔራዊ እርምጃ እንወስዳለን " ብለዋል። ጠ/ሚኒስትሩ ፥ " #በሚቀጥሉት_ሳምንታት ተጨማሪ ሀገራት ይህን ጠቃሚ እርምጃ ለመውሰድ ከእኛ ጋር እንደሚተባበሩ እርግጠኛ ነኝ " ሲሉ አክለዋል። የአይርላንድ መንግሥት ይህ የሀገርነት እውቅና የሁለት ሀገር መፍትሄን እንደሚደግፍና ለቀጠናው ዘላቂ ሰላም አስፈላጊ መሆኑን ገልጿል። የስፔኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ እና የኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ኢስፔን ባርት ኢይድ ሀገራቸው ከግንቦት 28 (እ.ኤ.አ) ጀምሮ ለፍልስጤም ግዛት እውቅና እንደሚሰጡ በይፋ አሳውቀዋል። የስፔኑ ጠ/ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ፥ " ምንም እንኳን ከአሸባሪው ቡድን #ሃማስ ጋር የሚደረገው ውጊያ ህጋዊ ቢሆንም ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ለፍልስጤም የሰላም ፕሮጀክት የላቸውም " ብለዋል። የኖርዌይ ጠ/ ሚኒስትር ጆናስ ጋህር ስቶር በበኩላቸው ፥ " እውቅና ከሌለ (የፍልስጤም) በመካከለኛው ምስራቅ ምንም ሰላም ሊኖር አይችልም " ብለዋል። " ሽብር የተፈፀመው በሃማስና የሁለት ሀገር መፍትሄን በማይቀበሉ እንዲሁም የእስራኤልን መንግሥት በማይደግፉ ታጣቂ ቡድኖች ነው። " ሲሉ አክለዋል። " ፍልስጤም ነጻ አገር የመሆን መሠረታዊ መብት አላት " ብለዋል። የፍልስጤም #የነጻ_ሀገርነት እውቅና መስጠት በይፋ ከተሰማ በኃላ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር #በኖርዌይ እና #በአይርላንድ የሚገኙ አምባሳደሮችን በአስቸኳይ ወደ እስራኤል እንዲመለሱ አዘዋል። ሚኒስትሩ፤ " የዛሬው ውሳኔ ሽብርተኝነት እንደሚከፍል ለፍልስጤማውያን እና ለዓለም መልእክት ያስተላለፈ ነው " ብለዋል። መረጃው የስካይ ኒውስ ነው። More - @thiqahEth
Show all...
1.04 MB
ኢማሙ አሽ _ሻፊዒይ ከኢማሙ አህመድ ጋር ኢማሙ አህመድ ከኢማሙ አሽ _ሻፊዒይ ከትልልቅ ተማሪዎች አንዱ ነው። ኢማሙ አህመድ ኡስታዛቸውን በጣም ይወዷቸው ነበር በሰዎች እና በልጆቻቸውም አጠገብ ያወድሷቸው ነበር ስለ ጀግንነታቸውም ያነሱ ነበር።ከዚህ የተነሳ የኢማሙ አህመድ ልጃቸው ሁልጊዜ ኢማሙ አሽ _ሻፊዒይን ለማየት ዒባዳቸው እንዴት እንደሆነ ለማየት ትጓጓ ነበር።         ከእለታት አንድ ቀን ኢማሙ አሽ _ሻፊዒይ ወደ ኢማሙ አህመድ ቤት እንግድነት ሄደው አደሩ ።የኢማሙ አህመድ ልጅ ሁኔታቸውን በማየት ነበር እና ከኢማሙ አሽ _ሻፊዒይ የማይጠበቅ 3 ነገራቶችን ተመለከተች። 1ኛ  ምግብ ቀረበላቸው እና ኢማሙ አሽ _ሻፊዒይ ምግቡን አብዝተው በሉ ሆዳቸው እሰከሚሞላ ድረስ። 2ኛ   ከበሉ በኋላ ገብተው ተኙ ሰላተ ለይል ሳይሰግዱ አደሩ። 3ኛ  የሱብሂ አዛን ሲደረግ ውዱእ ሰያደርጉ ወደ መስገጃ ቦታ ሄደው ሰገዱ። ከእነዚህ ክስተቶች የተነሳ ኢማሙ አሽ _ሻፊዒይን በጠበቀቻቸው መንገድ ስላላገኘቻቸው በጣም ደነገጠች ፈዘዘችም መታገስ አቃታት ። አባቷን እንዲህ ብላ ጠየቀች፦ እንዴት ኢማሙ አሽ _ሻፊዒይን በመሰለ ትልቅ ዓሊም እነዚህ ነገሮች ይታያሉ? ኢማሙ አህመድም ይህን ጉዳይ ከራሳቸው መስማት አለብኝ ብለው ሄደው ስለ ሁሉም ነገር ጠየቋቸው። ኢማሙ አሽ _ሻፊዒይም እንዲህ ብለው መለሱላቸው፦ 1ኛ  ምግቡን ሆዴ እስከሚሞላ የበላሁት ምግብህ ከሀላል መሆኑን ስላወኩኝ እና የደጋግ ሰዎች ምግባቸው መዳኒት መሆኑን ስላወኩኝ ነው።የበላውት ስለራበኝ ሳይሆን ለመዳኒትነት ነው የበላውት። 2ኛ ስለመተኛቴ ደሞ ወሏሂ አይኖቼ ሳይተኙ ነው ያደሩት ምክንያቱም ፊቅሃዊ በሆነ በአንድ መስአላ( በአንድ ሀዲስ)  ላይ እያስተነተንኩኝ ነው ያደርኩት በአንዷ ሀዲስ ውስጥ 72 ለሙስሊሞች የሚጠቅሙ ነገራቶችን አውጥቼበታለው በእውቀት ፍለጋ ቢዚ መሆን ከሌሊት ሰላት ስለሚበልጥ ነው። 3ኛ  ውዱእ ሳላደርግ የሰገድኩት ስላልተኛውኝ ውዱእ አልፈታውም። ባላወቅነው ነገር ሰውን ከመፈረጅ እንጠንቀቅ ኢንሻአላህ በሌላ እውነተኛ ታሪክ እመለሳለው። قصة الإمام الشافعي مع الإمام أحمد كان الإمام أحمد من أبرز طلاب الإمام الشَّافعي وكان يحبُّه حباً كبيراً، وكان دائم الثناء عليه أمام النَّاس وأمام أبنائه، فلمَّا قام الإمام أحمد باستضافة الإمام الشَّافعي في بيته، كانت ابنة الإمام أحمد متشوِّقة إلى رؤية الشَّافعي وعبادته.[٣] ولمَّا وُضع الطعام أكثر الشَّافعي من تناول الطَّعام، ثمَّ نام إلى الفجر ولم يقم الَّليل، وقام فصلَّى بهم الفجر بدون وضوء، فذُهلت ابنة الإمام أحمد لما رأته، ولم تطق صبراً، فسألت أباها عن ذلك إذ كيف يمكن أن يصدر هذا من إمامٍ بوزن الشافعي؟.[٣] فدخل الإمام أحمد إلى الشَّافعي وسأله عن تلك الأمور، فقال له الإمام الشافعي: أمَّا الطعام فما أكثرت منه إلَّا لأنِّي أعلم أنَّ طعامك حلالٌ، وطعام الصَّالحين شفاءٌ، فما أكلت جوعاً إنَّما أكلت تداوياً، وأمَّا نومي بعد الطعام وعدم قيامي لليل فوالله ما نامت عيني وإنَّما كنت أتفَّكر في مسائلَ من الفقه، فاستنبطت اثنتين وسبعين مسألةً ينتفع بها المسلمون، أمَّا صلاتي بكم الفجر بدون وضوء، فما نمت حتى أتوضأ، إنَّما كنت مستيقظاً طول الَّليل.
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
🎊🎊ታላቅ የምስራች🎊🎊 🎉🎉🎓🎓በአይነቱ ልዩ የሆነ የዳዕዋ እና የተመራቂ ተማሪዎች WELL GO ፕሮግራም በወራቤ ዩኒቨርሲቲ🎓🎓🎉🎉 🎓🎓እነሆ የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ የዘንድሮ ተመራቂ ሙስሊም ወንድም እህቶቻችንን ምክንያት በማድረግ የፊታችን እሁድ ማለትም በ ቀን 11/09/2016 ዓ.ል በአይነቱ ልዩ የሆነ የዳዕዋ እና የ WELL GO ፕሮግራም አሰናድቶ ይጠብቃችኃል።🎓🎓 በፕሮግራሙ ከሚታደሙ እንቁ ተጋባዥ የሱና ዱዓቶች እና እንግዶች መካከል:- 🎋(ከአዲስ አበባ)🎋 🔖ኡስታዝ ጂብሪል አክመል (ኢንጂነር) 🔖ኡስታዝ ኢብራሂም ሙሳ 🎋(ከወራቤ)🎋 🔖ሸይኽ ኑረዲን ኸሊል 🔖ኡስታዝ ሙሀመድ ሰኢድ 🔖ኡስታዝ ኻሊድ ሙሀመድ 🎋(ከሻሸመኔ)🎋 🔖ወንድም አብዱልመሊክ አደም 🎋(ከጂማ)🎋 🔖ወንድም ሙባረክ ሙኽታር
🎋🎋በእለቱም የግጥም ፣ የሰነፅሁፍ እንዲሁም አጓጊ ሽልማቶችን የያዙ ጥያቄ እና መልሶችም ይኖራሉ።🎋🎋
🛍🎁በአላህ ፍቃድ ከ G.C ተማሪዎች ብዙ ተሞክሮዎችን እንቀስማለን ፣ ዲናችንን እንማማራለን ፣ የማይረሳ ጊዜን አብረን እናሳልፋለን!!!🎊🎓
N.B 1.በእለቱም የሻይ ቡና & የምሳ ፕሮግራም ተሰናድቶ ይጠብቃችኋል። 2. ዉድ ተመራቂ ተማሪዎች በእለቱ የፕሮቶኮል ጉዳይ ይታሰብበት።
https://t.me/wru_ms_officialgroup https://t.me/WRU_MSJ_Official_channel
Show all...
በኮንትራት ለስራ የሄዳችሁ ወገኖች ~ ከአሰሪያችሁ ጋር ለምሳሌ የሁለት አመት የስራ ውል (ኮንትራት) ገብታችሁ የተቀጠራችሁ ወገኖች ቃላችሁን ጠብቁ። የተሻለ ደመወዝ ፍለጋ በሚል ምክንያት አትጥፉ። ማንም ቢሆን ወጭ አውጥቶ ቃል አስገብቶ ካገሩ ያስመጣው ሰራተኛ ቃሉን አፍርሶ ጥሎት ቢጠፋ ደስ አይለውም። ራሳችሁ ላይ እንዲሆን የማትፈልጉትን ነገር ሌሎች ላይ አታድርጉ። ቃል ያስጠይቃል። አላህ እንዲህ ይላል፦ { وَأَوۡفُوا۟ بِٱلۡعَهۡدِۖ إِنَّ ٱلۡعَهۡدَ كَانَ مَسۡـُٔولࣰا } "በቃል ኪዳናችሁም ሙሉ፡፡ ቃል ኪዳን የሚጠየቁበት ነውና። [አልኢስራእ: 34] አስገዳጅ ሁኔታ ካልገጠመ በስተቀር። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
Show all...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

Photo unavailableShow in Telegram
ስለ የታላቁ ነጃሺ ዜሮ ዜሮ (00) መንደር አጭር ማብራሪያ (Grand Al Najashi 00 Village Project) 📎የፖሮጀክቱ ሰያሜ ፡ የታላቁ ነጃሺ 00 መንደር 📎 የሚሰራበት ቦታ፦ ትግራይ ክልል፣ ውቅሮ ነጃሺ 📎የዜሮ ዜሮ [00] መጠሪያ ሃሳብ የሸክ ሃጂ ኢበራሂም ቱፋ ሲሆን የታሪኩ መነሻና መገኛ ስፍራ (ትግራይ፣ ነጃሺ) ያመላክታል። ®የዚህ ፕሮጀከት የበላይ መሪ ሸክ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ (የኢትዮጵያ እሰልምና ጉዳይች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት) የፕሮጀክቱ አጋር ተቋማት። ©የትግራይ ክልል እሰልምና ጉዳዮች ጠቅላይ መክርቤት ©የአልነጃሺ መልሶ ግንባታና ልማት ኢኒሼቲቭ( Al-Nejashi Reconstruction and Development initiative (ARDI) የፖሮጅክቱ ዓላማ 📎በኢትዮጵያ ብሎም የአለም ትልቁ የሙሰሊሞች የታሪክ ቅርሰ የሆነው፤ ለሙሰሊሞች በከባዱ ፈተና ወቅት ከለላ(መጠጊያ) የሆኑት ንጉስ ነጃሺ መካነ ቀርስ አሻራ ያለበት ቦታ በትግራይ ክልል በነጋሺ ከተማ ክብራቸውና ታሪካችው የሚመጥን አለም አቀፍ የቱሪሰት መዳረሻ ቦታ አንዲሆን ሁሉም አቀፍ መንደር (ቪሌጅ) ለመገንባት ያለም ነወ፡፡ የሚገነበው መንደር Educational, health and Development facilities የሚያካትት ሲሆን በውስጡ የተለያዩ ንኡስ ፕሮጀክቶች የሚኖሩት ሲሆን በዋናነት:- 📌መስጂድ እና መድረሳ 📌ሙዚየም 📌ሐላል ሆቴል እና ሎጅ 📌የስፖርት ማዘውተሪያዎች 📌ኢስላሚክ የጥናትና ምርምር ተቋም 📌የቴከኒከና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች 📌ሆስፒታል እና ሌሎች Mohammedawel Hagos
Show all...
👍 1
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.