cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን

"በተማርከው እና በተረዳኸው ነገር ፀንተ ኑር"

Show more
Advertising posts
341
Subscribers
+224 hours
+67 days
+3230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

“ የታረደው በግ ኃይልና ባለ ጠግነት ጥበብም ብርታትም ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል ” ራእይ 5፥12 ታርደሃልና ❤ የእግዚአብሔር ልጅ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው የኾነው የራቅነውን ሊያቀርበን ፣ የተጣላነውን ሊያስታርቀን ፣ ከመርገም ከፍዳ ዋጅቶ ከኃጢአት አንጽቶ ሊቀድሰን ፣ በወርቀ ደሙ ቤዛ ኾኖ የራሱ ገንዘብ ሊያደርገን ነው።ይኽም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍጹም ፍቅሩን ለኃጢአት ያለውን ፍጹም ጥላቻ የሚያረጋግጥልን ዕውነት ነው። በብሉይ ኪዳን ዘመን የሰው ልጅ በኃጢአት ምክንያት ከእግዚአብሔር ተለይቶ ፤ ከጸጋውም ርቆ በእግረ አጋንንት እየተረገጠ ፤ በነፍስና በሥጋ ደዌ ተይዞ በሲኦልና በጨለማ ታስሮ ፤ እረኛ እንደሌላቸው በጎች ሲቅበዘበዝ እግዚአብሔር አምላካችን ፈጽሞ የሚተው አምላክ ስላልኾነ ለጊዜያዊ ኃጢአት ሥርየት እና ዕርቅ ፣ለአፍአዊ ምሕረት ፣ ለሥጋ ደዌ ፈውስ የሚኾኑ እንስሳት ስለ ሰዎች ፈንታ እንዲሰዉ አድርጓል።ለመሥዋዕት ከሚቀርቡ እንስሳት መካከልም አንዱና ዋንኛው የመሥዋዕቱ በግ ነው። ስለ ሰው ልጆች ፈንታ ለኃጢአት ሥርየትና ይቅርታ ይሰዉ የነበሩ በጎች ንጽሕናቸው በሰው ዘንድ የተመሰከረላቸው ነውር የሌለባቸው አውራ የኾኑ ለመሥዋዕት ይቀርባሉ (ዘጸ 29 ፣ ዘሌ 6 ኦሪት ዘጸአትና ዘሌዋውያን ታሪኮች ላይ በዝርዝር ተጽፏል) ። እነዚኽ በጎች አንዳች በደል ሳይኖርባቸው ለበደለኛው ሰው መሥዋዕት ሊኾኑ አፋቸውን ሳይከፍቱ ወደሚታረዱበት ስፍራ ይጓዙ ነበር ። ከሌሎች እንስሳት ጋር ሲሰዉም አያስቸግሩም ደማቸውም ተረጭቶ ጊዜያዊ የኃጢአትና የበደል ሥርየት ያስገኙ ይሄ የመሥዋዕት አገልግሎት ጌታ ኢየሱስ እስከ ሚሰቀል ድረስ የቆየ ነበር።ነገር ግን የእንስሳቱ መሥዋዕትነት ዘለዓለማዊ የኾነውን ሞት ፣ ኃጢአት ፣ እርግማንና ጥል አስወግዶ ከእግዚአብሔር ጋር አስታርቆ ገነትን የሚያስከፍት አልነበረም። ምክንያቱም እንስሳቱ ሟች ፈራሽ በስባሽ ሞትን ድል መንሳት የማይችሉ ፤ የበደለኛውን ሰው ባሕርይ ያልተላበሱ ስለኾኑ ነው። በዚህም ምክንያት የበደለኛውን ሰው ባሕርይ የተላበሰ ፣ ኃጢአት የሌለበት ፣ ሞትን ሽሮ ድል የሚነሳ ንጹሕ በግ አስፈለገ ።ለዚህም እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ለማዳን ካለው ድንቅ ፍቅርና ፍላጎት የተነሳ በብሉይ ኪዳን ዘመን በተለያየ ምሳሌና ትንቢት ስለ ድል ነሺው በግ ገለጠ በይስሐቅ ፈንታ የታረደ በግ አዘጋጀ (ዘፍ 22) በኢሳይያስ ስለ ሚታረደው በግ ትንቢት አናገረ (ኢሳ 54) እስራኤላውያን ከሞተ በኩር የዳኑበትን የታረደውን በግ ገለጠ(ዘጸ 12) ። ትንቢት የተነገረለት ምሳሌ የተመሰለለት በሕዝብ ዘንድ ንጽሕናው የተመሰከረለት አማናዊው በግ ኢየሱስ ክርስቶስ የበደለኛውን ሰው ሥጋ ፣ ደምና ነፍስ ነስቶ ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ተወልዶ ፍጹም አምላክ ሲኾን ፍጹም ሰው ኾኖ ተወለደ(ዕብ 4:15 ፣ 2ቆሮ 5:21 ፣ ሉቃ 2:7 ፣ ዮሐ 1:1-14) ። ይሕ በግ ኾኖ የተወለደው የዓለም ጌታና መድኅን ድውያነ ሥጋን በተአምራት ድውያነ ነፍስን በትምሕርት እየፈወሰ የመንግስቱን ወንጌል እየሰበከ መንግስቱን በመመስረት ተመላለሰ ጊዜው ሲደርስ በ33 ዓመት ከሶስት ወሩ እንደ በግነቱ ሊታረድ እንደ ቤዛነቱ ሊሰዋ እንደ መሥዋዕትነቱ ሊቀርብ በሮማውያንና በአይኹድ እጅ በግፍ ተይዞ እንደሚታረድ በግ ድምጹን ሳያሰማ እየሰደቡት ፣ እያላገዱበት ፣ እያሾፋበት ፣ እየገረፋትና እያዳፋት የሚሠዋበትን መስቀል አሸክመው የሾሕ አክሊል ደፍተው የደም እንባ እያላበው እየተሰቃየ በችንካር ቸንክረው እንደ ብራና ወጥረው የወንበዴዎች አለቃ ብለው በወንበዴዎች መካከል ከከተማ ውጭ በቀራንዮ በጎለጎታ ሰቀሉት ። ስቃዮ ግርፋቱ እትራቱ እና እስራቱ ኹሉ ለእኛ የተደረገ የኾነ ነው ።ለዘመናት በዲያብሎስ ሲረገጥ ፣ ሲገረፍ ፣ ሲሰቃይና ሲንገላታ የኖረውን የሰው ልጅ ነጻ ሊያወጣ ካሳ ሊኾን ተገረፈ ፣ ተሰቃየ ፣ ተንገላታ ፣ ተረገጠ መከራን ተቀበለ ። ኹሉ በእጁ ኹሉ በደጁ የኾነው ጌታ ሊቃነ መላዕክት መላዕክት ፣ የሚታዮ የማይታዮ ፣ የሚዳሰሱ የማይዳሰሱ ፍጥረታት የሚገዙለት ጌታ ምድራውያን የኾኑ ሰዎች መከራ አጸኑበት በተከለከለ ሕግ ሽረው ገርፈው ሰቀሉት።በመከራው መከራችንን ፤ በሥቃዮ ሥቃያችንን ፤ በግርፋቱ ግርፋታችንን ፤ በሞቱ ሞታችንን አራቀ ። የማይሞተው ጌታ በበግነቱ ሞተ(ተሰዋ) ሞቶ ፈርሶ በስብሶ ግን አልቀረም በሞቱ ሞትን ሽሮ በኩረ ትንሳኤ ኾኖ ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ (1ቆሮ 15) የብሉይ ኪዳን መሥዋዕቶች (እንሳት) ያልቻሉትን ፣ ነቢያት ያቃታቸውን ሞት ድል ነሳ። ለዚህም ነው መነሻ ባደረግነው የራዕይ ክፍል ላይ ሞቶ ያልቀረውን ጌታ ኢየሱስ ማሕተሙን የሚፈታ ድል ነሺ ጠፍቶ ሳለ “ከሽማግሌዎቹም አንዱ፦ አታልቅስ፤ እነሆ፥ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል አለኝ።”ራእይ 5፥5 ሲል የገለጠው ። የሞት ማሕተማችን ተፈትቶ ድል ነሺው ጌታ ከሞት እና ከሲኦል በላይ ኾኖ በድል አስከተለን ከእንግዲኽ መሸነፍ የለም ፤ ከእንግዲኽ መውደቅ የለም ፤ ከእንግዲኽ መርገም ፍዳ እና ጠብ የለም የጠቡን ግድግዳ በሥጋው በሞቱ በኩል ሽሮ እግዚአብሔርን አባ ብለን የምንጠራበትን የልጅነት መንፈስ አቀዳጅቶናል። ስለዚህም ለታረደው ጌታ ኢየሱስ በረከት ምስጋና ፣ ውዳሴ ፣ አምልኮ ፣ እልልታ ፣ ሽብሻቦ ፣ ግርግርታ ፣ ስግደትና መገዛት ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ይገባዋል ።ታርዷልና ፣ ዋጅቶናልና ፣ ቤዛ ኾኖናልና ፣ ሞትን ሽሮ ገነትን ከፍቶልናልና ፣ ሊቀ ካህናት ኾኖ ታርቆ አስታርቆናልና ፣ መሥዋዕት ኾኖ ከዘለአለማዊ ኃጢአትና በደል በደሙ አጥቦናልና የኛ ጌታ ኢየሱስ ንጉሳችን ክርስቶስ አዳኛችን አማኑኤል በረከትና ምስጋና ይገባዋል። አዳኛችን ኢየሱስ ቤዛችን ክርስቶስ ታርደሃልና ክብር ምስጋና ውዳሴና አምልኮ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ለአንተ ይኹን አሜን ❤! http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780 ቻናሉን ተቀላቅለው ኦርቶዶክሳዊ ወንጌል ይማሩ! ዲያቆን ሸዋፈራው ይቆየን
Show all...
🤔ክርስቶስ ሰው መሆኑ ፍጡር መሆኑን ያሳያልን🕶❓❓❓ ሙስሊም🗣🗣ሰው ፍጡር ነው። ኢየሱስ ደግሞ ሰው ነው። ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ ፉጡር ነው። አምላክ አደለም።🙆‍♂ 🙄 ከመጽሐፍ ቅዱስ ክርስቶስ ፍጡር የተባለበት ቦታ የለም።፥ ክርስቶስ ሰው ተብሎ የተጠራባቸውን ስፍራዎች በመጥቀስ ብቻ ፍጡር ነው አምላክ አደለም ለማለት ይሞክራሉ 🙆‍♂ መልስ 👇 👉ፍጡር _(ማለት ካለመኖር ወደ መኖር የመጣ ነገር ማለት ነው)። አንድ ነገር በህልውና ያልነበረበት ጊዜ ካለና በሆነ ጊዜና ወቅት ላይ ወደ ህልውና (existence) ከመጣ፥ ያ ነገር ፍጡር ይባላል)☘ መጽሐፍ ቅዱስም ፍጡር ማለት ቀድሞ በህልውና ያልነበረ ማለት እንደሆነ ያስተምራል ፈቃዱን ታደርግ ዘንድ በትእዛዙም ጸንተህ ትኖር ዘንድ ፍርዱንም ትፈራ ዘንድ ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ የፈጠረህ እግዚአብሔር አይደለምን (መቃ7÷2) ምድርን በመሠረትሁ ጊዜ አንተ ወዴት #ነበርህ? (መጽሐፈ ኢዮብ 38:4) " እርሱም። ለብዙ አሕዛብ አባት አደረግሁህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ለሙታን ሕይወት በሚሰጥ #የሌለውንም እንዳለ አድርጎ በሚጠራ ባመነበት በአምላክ ፊት የሁላችን አባት ነው።" (ወደ ሮሜ ሰዎች 4:17) ስለዚህ አንድ ነገር ፍጡር ሊባል የሚችለው፤ ካለመኖር ወደመኖር መምጣቱ ሲረጋገጥ ብቻ ነው።😊 በሆነች ጊዜ እና ቅጽበት ላይ ወደ ህልውና መምጣቱ እስካልተረጋገጠ ድረስ ፍጡር ነው የሚያስብል ምንም ነገር የለም👍 ✝ የፍጡርን ትርጉም በዚህ መልኩ ካየን ዘንድ ወደ ክርስቶስ እንምጣ። ክርስቶስ ሰው የተባለው ለምንድነው❓❓ ክርስቶስ ሰው የተባለው ፍጡር ስለሆነ አይደለም። ክርስቶስ ሰው የተባለው ስለተሰገወ (incarnate) ስለሆነ ነው። ስጋዌ (incarnation) ማለት ቀድሞ ሰው ያልነበረ ነገር በሆነ ጊዜና ወቅት ላይ ሰው ሲሆን ማለት ነው🫡 🫵አስተውሉ! አንድ አካል ተሰገወ ማለት፥ ያ ነገር ሰው ከመሆኑ በፊት በህልውና ነበር ማለት ነው። ሰው ሲሆን አይደለም የእርሱ ህልውና የጀመረው፥ ቀድሞውንም በህልውና ነበር🫶 👉ክርስቶስ ሰው የተባለው ስለተሰገወ እንጂ ካለመኖር ወደ መኖር ስለመጣ አይደለም👈 👇👇👇👇👇👇👇 ✝ከሥጋ የተነሣ ስለ ደከመ ለሕግ ያልተቻለውን፥ እግዚአብሔር የገዛ #ልጁን በኃጢአተኛ #ሥጋ_ምሳሌ በኃጢአትም ምክንያት ልኮ አድርጎአልና፤" (ወደ ሮሜ ሰዎች 8:3) ነገር ግን፥ #የመድኀኒታችን_የእግዚአብሔር ቸርነትና ሰውን መውደዱ #በተገለጠ ጊዜ፥ (ቲቶ3÷4) "✝  #ቃልም #ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን።" (የዮሐንስ ወንጌል 1:14) ✝" እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ #በሥጋና_በደም እንዲሁ #ተካፈለ።" (ወደ ዕብራውያን 2:14-15) ✝" ነገር ግን የባሪያን #መልክ #ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥" (ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2:7) ኢየሱስ ፍጡር ነው ለማለት ካለመኖር ወደ መኖር መምጣቱን የሚያሳይ ማስረጃ ማምጣት የግድ ይሆናል። ሰው ተብሏልና ፍጡር ነው የሚለው ትርክት ማስረጃ የሌለው ስሁት አመክንዮ ነውና ✝ መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስ በቅድመ ስጋዌ ዘመኑ ዘላለማዊው እግዚአብሔር መሆኑን በግልጽ ያስተምራል 1. " እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው። የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት #ሁሉ በፊት በኵር ነው። ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል።" (ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1:15-16) ✝ በዚህ ስፍራ ክርስቶስ ፍጥረትን ሁሉ የፈጠረ ፈጣሪ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ይናገራል። #ሁሉን ፈጠረ ማለት ፍጡር የተባለ ነገር ሁሉ (ቀድሞም በህልውና ያልነበረ፥ በሆነ ጊዜ ላይ ወደ ህልውና የመጣ) ሁሉ በእርሱ ነው የተፈጠረው ማለት ነው። ይህ ደግሞ እሱን ከፍጥረት ውጪ ያደርገዋል። ምክንያቱም ፍጥረትን ሁሉ እሱ ፈጥሮ፥ እሱ ራሱ ፍጡር ነው ከተባለ ራሱን ፈጥሯል ማለት ሊሆን ነው። ይህ ደግሞ ኢ-አመክንዮአዊ ነው። ስለዚህ ክርስቶስ ፍጡር አይደለም ማለት ነው ✝2. “እርሱ የእግዚአብሔር ክብር ነጸብራቅና የባሕርዩ #ትክክለኛ_ምሳሌ ሆኖ፣ በኀያል ቃሉ ሁሉን ደግፎ ይዞአል፤ የኀጢአት መንጻት ካስገኘ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ።”   — ዕብራውያን 1፥3 (አዲሱ መ.ት) ✝በዚህ ስፍራ ወልድ የአብ ባህሪ ትክክለኛ ምሳሌ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። "ትክክለኛ ምሳሌ" የሚለው የግሪክ ቃል karakteir የሚል ሲሆን "exact imprint: exact representation" ማለት ነው። ማለትም የአንድ ነገር ቁጭ አምሳያ ማለት ነው። ያ ነገር የሆነውን በሙሉ አንድም እንኳ ሳይሸረፍ፥ ሳይቀነስ የሆነ ማለት ነው መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረን፥ አብ በባህሪው ዘላለማዊ ነው። (ሮሜ 1:20) ማለትም አብ በባህርይው ፍጡር አይደለም። ይህ ማለት የእርሱ ባህርይ ትክክለኛ ምሳሌ የሆነው ወልድም፥ ፍጡር አይደለም ማለት ነው   ✝የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር፥የሚቤዥም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦እኔ ፊተኛ ነኝ፥እኔም ኋለኛ ነኝ ከእኔ ሌላም አምላክ የለም። (ኢሳ 44÷6)👈 ይህ አተራረክ ክርስቶስ ከመወለዱ በፊት ለእግዚአብሔር ዘለአለማዊነት የሚናገር  ካለመኖር ወደመኖር እንዳልመጣ ዘለዓለማዊ አምላክነትን የሚተረክ ነዉ እሄ አተራረክ 👇ለኢየሱስ ሲዉልበት እናያለን ✝አልፋና ዖሜጋ፥ፊተኛውና ኋለኛው፥መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ። ራዕ22÷13       በዚህ ስፍራ ክርስቶስ ከመወለዱ በፊት  በህልዉና ዘለዓለማዊ አምላክ እንደነበረ እናያለን እንዲሁም ካለመኖር ወደ መኖር እንዳልመጣ እናዉቅበታለን። ✝3. “ኢየሱስም፣ “እውነት እላችኋለሁ፤ አብርሃም ከመወለዱ በፊት እኔ፣ እኔ ነኝ” አላቸው።”   — ዮሐንስ 8፥58 (አዲሱ መ.ት) ✝ በዚህም ስፍራ ጌታ ኢየሱስ አብርሃም ሳይወለድ በፊት እሱ እንደነበር ሲናገር እንመለከታለን። "ሳይወለድ" የሚለው የግሪክ ቃል "genesthai" ሲሆን "ወደ ህልውና መምጣት" ማለት ነው። "እኔ ነኝ" የሚለው ቃል ደግም "eigo emi" ሲሆን በimperfect tense ነው የገባው ይህ ቃል "የክርስቶስ ህልውና የጀመረው በድንግል ማርያም ማህጸን ነው" የሚለውን ሀሰት ከማፈራረስ ባሻገር የክርስቶስን ዘላለማዊነት የሚያጸና ነው። ምክንያቱም ጌታ፥ እያነጻጸረ ያለው የአብርሃምን ካለመኖር ወደ መኖር መምጣት ከእሱ ጅማሬ አልባነት ጋር ነው። አብርሃም ሳይወለድ እርሱ ነው። ይህ አተራረርክ በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር ሲተረክበት የነበረው አተራረክ ነው። (መዝ 90:2)“ተራሮች ሳይወለዱ፥ ምድርም ዓለምም ሳይሠሩ፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ አንተ ነህ።”   — መዝሙር 90፥2             👇👇👇 ማጠቃልያ ክርስቶስ ሰው የተባለው ስለተሰገው እንጂ ወደ ህልውና ስለመጣ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረው፥ መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው ዘላለማዊ ነው። ሰው መባሉ ፍጡር መሆኑን አያሳይም። http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780
Show all...

🕊 ✞   የሰኔ ፳፫ [ 23 ]   ✞ ✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞ ❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖ ❖ ሰኔ  ፳፫ [ 23 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 🕊 † ቅዱስ ሰሎሞን ንጉሠ እሥራኤል †  🕊 መፍቀሬ ጥበብ : ¤ ጠቢበ ጠቢባን: ¤ ንጉሠ እሥራኤል: ¤ ነቢየ ጽድቅ: ¤ መስተሣልም [ ሰላማዊ ]  . . . እየተባለ የሚጠራው ቅዱስ ሰሎሞን የታላቁ ነቢይና ንጉሥ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊትና የቅድስት ቤርሳቤህ [ቤትስባ] ልጅ ነው:: ከ ፫ [3] ሺ ዓመታት በፊት የተወለደው ቅዱስ ሰሎሞን እስከ ፲፪ [12] ዓመቱ ድረስ በቤተ መንግሥት ከአባቱ ጋር አድጉዋል:: ቅዱስ ዳዊት ፸ [70] ዘመን በሞላው ጊዜ የአካሉን መድከም አይቶ አዶንያስ በጉልበት እነግሣለሁ ቢልም አልተሳካለትም:: እግዚአብሔር ሰሎሞንን መርጧልና ገና በ፲፪ [12] ዓመቱ ነገሠ:: ልበ አምላክ አባቱ ዳዊት ነፍሱ ከሥጋው ከመለየቷ በፊት መከረው:: "ልጄ ሆይ ! ልብህን ስጠኝ:: ፈጣሪህንም አምልክ" አለው:: ቅዱስ ሰሎሞን እንደ ነገሠ በገባዖን ለእግዚአብሔር መስዋዕትን አቀረበ:: ጌታም ተገልጾ "ምን ትፈልጋለህ?" አለው:: ሰሎሞንም ልክ እንደ አባቱ ማስተዋልን: ልቡናን ለመነ:: በዚህም ጌታ ደስ ስለተሰኘ "አልቦ እምቅድሜከ: ወአልቦ እምድኅሬከ - ከአንተም በፊት: ከአንተም በኋላ እንዳንተ ያለ ጠቢብና ባለጠጋ ሰው የለም: አይኖርም" ብሎት ተሠወረ:: ቅዱስ ሰሎሞን ለ፵ [40] ዓመታት በእሥራኤል ላይ ነገሠ:: ግሩም በሆነ ፍትሑ: በልዩ ጥበቡ ዓለም ተገዛለት:: እግዚአብሔር የመረጣት የእኛዋ ንግስተ ሳባ /አዜብ/ማክዳም ትፈትነው ዘንድ ሒዳ ምኒልክን [እብነ መለክን] ጸነሰች:: በኋላም ታቦተ ጽዮንና ሥርዓተ ኦሪት መጣልን:: ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን ድንግል ማርያም ከእነሱ ዘር እንደምትወለድ ነግሮት ነበርና ያበጀሁ መስሎት ሴቶችን አብዝቶ ነበር:: ነገር ግን :- ¤ አንደኛ ሰው [ሥጋ ለባሽ] ነውና: ¤ ሁለተኛ ደግሞ ከብዙ ሴቶች መካከል ከአንዷ እመ ብርሃን ትገኛለች መስሎት ነበር:: ነገሩ መንገድ ስቶበት ከአሕዛብ [ከፈርዖን ልጅ] ጋር በመወዳጀቱ ለጣዖት አሰገደችው:: እግዚአብሔር እጅግ አዘነ:: በራዕይ ተገልጦ "ስለ ወዳጄ ስለ ዳዊት ስል በአንተ ላይ ክፉን አላደርግም" አለው:: ታላቁ ነቢይ ሰሎሞን ይህንን ሲሰማ ወደ ልቡ ተመለሰ:: ማቅ ለብሶ: አመድ ነስንሶ በፍጹም ልቡ አለቀሰ:: ንስሃ ገባ:: መፍቀሬ ንስሃ ጌታችንም ንስሃውን ተቀበለው:: የይቅርታው መገለጫም ተወዳዳሪ የሌላቸውን ፭ [5] መጻሕፍት ገለጠለት:: ተናገራቸው:: ጻፋቸው:: እሊሕም :- ፩. መጽሐፈ ጥበብ ፪. መጽሐፈ ተግሣጽ ፫. መጽሐፈ መክብብ ፬. መጽሐፈ ምሳሌ ፭. መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ናቸው:: ቅዱስ ሰሎሞን ልዩ የሆነውን ቤተ መቅደስ በመስራቱም ይደነቃል:: ደጉ ንጉሥ: ጠቢብና ነቢይ ሰሎሞን በዚህች ዕለት በ፶፪ [52] ዓመቱ ዐርፎ ወደ ፈጣሪው ሔዷል:: 🕊       †   አባ ኖብ    †       🕊 ዳግመኛ በዚህ ቀን ታላቁ ሰማዕት አባ ኖብ አርፏል:: በዚሕ ስም የሚጠሩ ብዙ ቅዱሳን ቢኖሩም ዋናው ይኼው ቅዱስ ነው:: አባ ኖብ እንደ ገዳማውያን በበርሃ የተጋደለ: እንደ ሊቃውንት መጻሕፍትን ያመሰጠረ: በተለይ ደግሞ በዘመነ ሰማዕታት ጭንቅ ጭንቅ መከራዎችን የተቀበለ አባት ነው:: ስለ ገድሉ ብዛት "ኃያል ሰማዕት": አንገቱን ስላልተቆረጠም "ሰማዕት ዘእንበለ ደም" ይባላል:: ዘመነ ሰማዕታትን ካለፉ ፸፪ [72] ቱ ከዋክብትም አንዱ ነው:: ከመፍቀሬ ጥበብ ቅዱስ ሰሎሞን: ከኃያሉ ሰማዕት አባ ኖብ በረከትን አምላካችን ይክፈለን:: 🕊 [  †  ሰኔ ፳፫ [ 23 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   ] ፩. ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን [ንጉሠ እሥራኤል] ፪. ቅዱስ አባ ኖብ [ሰማዕት ወጻድቅ] ፫. ቅዱሳን መርቆሬዎስ: ፊልዾስና ቶማስ [ሰማዕታት] [     †  ወርኃዊ በዓላት    ] ፩ ፡ ቅዱስ ዳዊት ልበ አምላክ ፪ ፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት ፫ ፡ ቅዱስ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ ፬ ፡ አባ ሳሙኤል ፭ ፡ አባ ስምዖን ፮ ፡ አባ ገብርኤል ፯ ፡ ቅዱስ ዳንኤል ነቢይ " የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ:: ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታት ሳይደርሱ: ፀሐይ: ጨረቃና ከዋክብትም ሳይጨልሙ . . . አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ: ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ:: ሰባኪው :- "ከንቱ: ከንቱ: ሁሉ ከንቱ ነው" ይላል::" [መክ.፲፪፥፩-፱]  (12:1-9) † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር †          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖 http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780
Show all...
                       †                          [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]   🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒                [  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ] [   ሳምንታዊ መርሐ-ግብር   ] 🕊                            ❝ የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው ፤ ነፍስን ይመልሳል ፤ የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው ፤ ሕፃናትን ጠቢባን ያደርጋል። የእግዚአብሔር ሥርዓት ቅን ነው ፥ ልብንም ደስ ያሰኛል ፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው ፥ ዓይንንም ያበራል። ❞ [ መዝ . ፲፱ ፥ ፯  ] ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ [ ❝ የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው ! ❞  ]                [   ክፍል - ፲ -  ]           💖   ድንቅ ትምህርት  💖 [ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ] ❝ የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። ❞ [ ምሳ.፩፥፴፫ ]          †              †               † ▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬                        👇 http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780
Show all...
†                 🔔               † [ ፈጣሪ ይቅር ይበላቸው። የሚያደርጉትን አያውቁም ! ] 🔔 " ከሁሉ አስቀድመው ወጣቱን ትውልድ ዒላማ አድርገዋልታሪካዊ እውነታዎችን ማጥፋቱን ተያይዘውታል ፤ ሩሲያዊ ባሕላችንን እያጠቁ ይገኛል ፤ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናችንን እንዲሁ ፤ ሌሎች የሩሲያ የሃይማኖት ተቋማትንም እንደዚሁ ፤ የገዛ ሕዝባቸው ላይ እያደረጉት ያለውን ነገር ልብ ብላችሁ ተመልከቱ። ቤተሰባዊ ተቋምን እያፈረሱ ይገኛሉ ፤ ባሕላዊና ታሪካዊ ማንነታቸውን እያጠፉ ይገኛል። የሃይማኖት ቄሶች ሳይቀሩ ተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ [ ሰዶማዊ ርኩሰትን ] እንዲያስፈጽሙ እየተገደዱ ይገኛል። ... ማለት የምፈልገው ግን ምናልባት ቅዱሳት መጻሕፍትን ማየት ሳይኖርባቸው አይቀርም። በማንኛውም ነባር ሃይማኖቶች ያሉ ቅዱሳት መጻሕፍትን የተመለከትን እንደሆነ ቤተሰብ በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት ብቻ እንደሚመሰረት ያስተምሩናል። ግና እነዚህ ቅዱሳት መጻሕፍት ዛሬ በምዕራቡ ዓለም ቦታ እያጡ ይገኛል። የአንግሊካን ቤተክርስቲያን አሁን ላይ ገለልተኛ ጾታ የሚባል መደብ እየተቀበለች ይገኛል። ምን ማለት ይቻላል ፈጣሪ ይቅር ይበላቸው። የሚያደርጉትን አያውቁም። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በምዕራቡ ዓለም ከመንፈሳዊ ዓለም ጋር ያላቸው ግንኙነት እየሞተ እንደሆነ ያምናሉ። ሰዎቹ እያበዱ ነው። መታከም የሚችል አይመስልም። ግን ይሄ ሁሉ የነሱ ችግር ነው። እኛ ግን ልጆቻችንን ከዚህ ሁሉ ነገር መጠበቅ አለብን። ደግሞም በሚገባ እንጠብቃለን። ልጆቻችንን ከጥፋት እንጠብቃለን ! " [  ቭላድሚር ፑቲን በዓመታዊው የምክር ቤት ንግግር ላይ የሰዶም እርኩሰት ባለቤቶች የሆኑትን ምዕራባውያንን በተመለከተ ከተናገሩት  ]       †              †              † ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780
Show all...
🕊  💖  ▬▬   †    ▬▬  💖  🕊   [  🕊  መዝሙረ ተዋሕዶ   🕊  ]              [  ኦርቶዶክሳዊ የተቀደሰ ያሬዳዊ ዝማሬ ሰዓት  ] [ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ] 🕊 በስመ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙር ንጹሕና የተቀደሰ ነው ፥ ለእግዚአብሔር ምስጋናና ልመና የሚቀርብበት ፣ ይቅርታና ምሕረት የሚጠየቅበት ፣ ሰውን ሳይሆን እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት የሚዘጋጅ ንጹሕ መስዋዕት ነው ፥ በአበው ጸሎት ይዘጋጃል ፥ ከስጋዊና ከደማዊ ሀሳብ የራቀ ነው ፥ ልቦናን ወደ ንስሐ ይጠራል ፥ ከኃጢአትና ከክፉ ሥራ የመለየት ኃይል አለው ፥ ክፉ መንፈስን ከሰው ልብ ያርቃል ፥ መረጋጋትን ልቦናን ዘልቆ የሚሰማ ውስጣዊ ሰላምን ይሰጣል ፥ በአሚነ ሥላሴ ያጸናል ፥ የክርስቶስን የባህርይ አምላክነትና መሐሪነት ይመሰክራል ፥ የእመቤታችንን ፍቅር በልቦና ያሳድራል ፥ በእናትነቷና በምልጃዋ እንድንታመን ያደርጋል ፥ በቅዱሳን ጸሎትና በቃል ኪዳናቸው ያጸናናል ፥ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን እናውቅ ዘንድ መንገድ ይመራናል ፥ ፈሪሐ  እግዚአብሔርንና ፍቅረ እግዚአብሔርን ያጎናጽፈናል፡፡ ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ ተወዳጆችሆይ ፦ በተቀደሰ ሰማያዊ ያሬዳዊ ዜማ ነብሳችንን እናስጊጣት፡፡ ከደጋጎቹ አባቶቻችን ጋር ከዓለም ርኩሰት በተለየ የተቀደሰ ዝማሬ አምላካችን እግዚአብሔርን እናመሥግን፡፡ ለስጋዊ ጆሮዎች ከሚመች ከረከሰ የተሃድሶ የኑፋቄ እርሾ ልቦናችንን እንጠብቅ፡፡ ገንዘብን ስለመውደድ ከሆነ ከሥጋዊ ሥራ ፈጽሞ እንለይ፡፡ 🍒 [ ❝  ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች ፤ በኃጥኣን ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ ፥ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ። ❞  ] {   መዝ . ፹፬ ፥ ፲   }   †                       †                       † 💖                    🕊                    💖 http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780
Show all...
🕯🍂🕯🍂🕯🍂🕯🍂🕯🍂🕯🍂🕯🍂🕯 ⛪️✍ስሙ #ዑራኤል_የሚባል መልአክ ወደ እኔ የተላከ ይህ #መልአክ_መለሰልኝ"።            ( #መፅሐፈ_ሱቱኤል.ምዕራፍ ፪÷፩) #እንኳን_አደረሳቹሁ_የእምየ_ተዋሕዶ_ልጆች        (፳፪🕯)  #ቅዱስ_ዑራኤል  አባቴ #ዑራኤል የሚለው ስም “#ዑር” እና “#ኤል” ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ነው። ዑራኤል ማለት ትርጉሙ #የብርሃን ጌታ”፣ #የአምላክ ብርሃን” ማለት ነው። ቅዱስ ዑራኤል #ከ7ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን #ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ #በመብረቅና #በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልአክ ነው።     ⛪️🦋  #ቅዱስ_ኡራኤል 🕯🍂 እመቤቴ ማሪያም #ኢትዮጵያን ስትዞር፣ ኡራኤል ሱርያል ስትረዳት ነበር፣ ለእኛም ድረስልን በቸገረን ነገር። በነጎድጓድና #በመባርቅት ላይ፣ የተሾምከው መልአክ ችግራችንን እይ።    ሱርያል ኡራኤል ብለን #የምንጠራው፤    አዛኝ ርኽሩህ መልአክ ሥምህ መልክት አለው፣    ሁሉም ሰው ይረዳው ትርጉሙ እውነት ነው፣    "ዐለቴ #እግዚአብሔር እግዚአብሔር ብርሃን ነዉ"። ኡራኤል ሆይ እርዳን ብዙ ነው ፈተናው፣ ጥንካሬን ስጠን ጨለማውን አብራው።    እንደገና እንዲጽፍ #ብሉይ ኪዳን እዝራ፣    ሚስጥረ ሰማይን ለሄኖክ ያበራ፣    ለአዳም #የድህነትን ዜና የነገረዉ፣    ዮሴፍን ብርታት ሰጥቶ ከብእሲት ጲጥፋራ ያዳነዉ፣    ኡራኤል ነውና የኛንም ይጎብኘው። #ለጊዮርጊስ ዘጋስጫ ጽዋህ ልቦና ተገልጦ ያጠጣው፣ በእለተ ስቅለት #በብርሃን ፅዋው፣ የጌታን ደም ወስዶ በዓለም ላይ የረጨው፤ የሚያረጋጋ መልአክ ቅዱስ ዑራኤል ነዉ ።    ጠንክረን #እንጸልይ ምህረት እንድናገኝ፣    ኡራኤል ይድረስልን ውስጣችንን ይጎብኝ።   ለዚህ ቅዱስ #እለት ያደረሰን አምላክ፣ የእግዚአብሔር ስሙ ዘልአለም #ይባረክ።    🌿 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 😘🦋   ✳️ብርሃናዊው መልአክ ቅዱስ ዑራኤል ለሀገራችን #የብርሃን_ሻማ ያልብስልን ለእኛም ለህዝቦቹ ሰላም ፍቅር አንድነቱን ያድለን         ለንስሓ   #ሞት_ያብቃን          🤲           🤲           🤲 #አሜን......... 🧡 ......... #አሜን               ⊹ #አሜን🙏³ 🍂🕯🍂🕯🍂🕯🍂🕯🍂🕯🍂🕯🍂🕯🍂 http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780
Show all...
➯ወደ ንጉሡ ከተማም በደረሱ ጊዜ ወደ ንጉሡ ከመግባታቸው በፊት በውኃ ያጥቧቸውና አዳዲስ ልብሶችን ያለብሷቸው ጀመሩ እንዲሁም ለሁሉ አደረጉ ቅዱስ አባ ኖብ ግን አልታጠበም ልብሱንም አልለወጠም። ➯ወደ ንጉሡም በገቡ ጊዜ ከእነርሱ ቡራኬ ተቀበለ ቁስላቸውንም ሳመ እጅግም አከበራቸው ብዙ ገንዘብም ሰጣቸው እነርሱ ግን ለቤተ ክርስቲያን ከሚሆን ንዋየ ቅድሳት በቀር ምንም ምን አልተቀበሉም ከዚህም በኋላ ሰላምታ ሰጥቶ ወደየሀገራቸው በሰላም አሰናበታቸው። አባ ኖብም ወደ ቦታው ተመልሶ አረፈና ወደ ወደደው ክርስቶስ ሔደ። ➯ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። #ስንክሳር ሰኔ 23 ቀን http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780
Show all...
➯ያቺ ሁለተኛዋ ሴትም አይደለም ይህ ደኅነኛው የኔ ልጅ ነው እንጂ ያንቺ ልጅ አይደለም ያንቺስ የሞተው ነው አለች። በንጉሡም ፊት እንዲህ ተባባሉ።............➯ንጉሡም ሰይፍን አምጡ ደኅነኛውንም ልጅ ከሁለት ቆርጣችሁ እኵሌታውን ለዚች እኵሌታውን ለዚያች ስጡ አለ። ስለ ልጅዋ ማሕፀኗ ታውኳልና ልጅዋ ደኅና የሆነ ያቺ ሴት መልሳ ንጉሡን ጌታዬ አይደለም መግደልስ አትግደሉት ደኅነኛውን ልጅ ለሷ ስጧት አለችው ያቺ ሴት ግን አካፍሉን እንጂ ለእኔም ለእሷም አይሁን አለች። ➯ንጉሡም መግደልስ አትግደሉት እሱን ለእሷ ስጧት ላለችው ለዚች ሴት ደኅነኛውን ሕፃን ስጧት እርስዋ እናቱ ናትና አለ። እስራኤልም ሁሉ ንጉሡ የፈረደውን ይህን ፍርድ ሰምተው ቅን ፍርድን ይፈርድ ዘንድ የእግዚአብሔር ጥበቡ በሱ ላይ እንዳለ አይተዋልና በንጉሡ ፊት ፈሩ። ➯ከዚህም በኋላ የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ከወጡ አራት መቶ ሰማንያ አራት ዘመን በሆነ ጊዜ ሰሎሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ በአራተኛው ዓመት በሁለተኛው ወር የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሊያንፅ ጀመረ። ➯በዐሥራ አንደኛውም ዘመነ መንግሥቱ ወሩ ባዕድ በሚባል በስምንተኛው ወር ቤቱንና ሥርዓቱን ሁሉ ፈጸመ በሰባት ዓመትም ውስጥ ሠራው የራሱንም ቤት በዐሥራ ሦስት ዓመት ሠርቶ ጨረሰ። ከዚህ በኋላ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤትና የራሱን ቤት በሃያ ዘመን ሠርቶ በጨረሰ ጊዜ የእግዚአብሔርን ታቦተ ሕግ ከዳዊት ከተማ ከጽዮን ያመጣት ዘንድ ያን ጊዜ የእስራኤልን ሽማግሌዎችና የነገድ አለቆች የአባቶቻቸውንም ቤት አለቆች ሁሉ በኢየሩሳሌም ሰበሰባቸው። ➯የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎሞን በሰባተኛው ወር በጥቅምት ተሰበሰቡ። የእስራኤልም ሽማግሌዎች ሁሉ መጡ ካህናቱም ታቦትዋንና የምስክሩን ድንኳን በምስክሩ ድንኳን ውስጥ ያለ ንዋየ ቅድሳቱንም ሁሉ ተሸከሙ። ንጉሡና እስራኤል ሁሉ በታቦትዋ ፊት ሥፍር ቍጥር የሌላቸው በጎችና ላሞችን ይሠዉ ነበር። ካህናቱም ታቦቷን ከኪሩቤል ክንፎች በታች በቤቱ ውስጥ ወዳለው ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ቦታዋ አገቧት። ➯ኪሩቤል በታቦትዋ ቦታ ላይ ክንፋቸውን ጋርደዋልና ኪሩቤልም በስተላይ በኩል በቅድስተ ቅዱሳን ላይ ታቦትዋን ጋርደዋት ነበር። ከቅድስተ ቅዱሳንም ጋራ የተያያዙ ነበሩ። ቅዱሳን ኪሩቤል ከፍ ብለው ከቅድስተ ቅዱሳኑ አንጻር ላይ ሁነው ያያሉ በውጭ ግን አይታይም ነበር። ከግብጽ አገር በወጡ ጊዜ እግዚአብሔር ከእስራኤል ልጆች ጋራ ቃል ኪዳን ከገባባቸው ሙሴም በዚያ በኮሬብ ከአኖራቸው ከሁለቱ ጽላቶች በቀር በታቦቱ ውስጥ ሌላ አልነበረም። ➯ከዚህ በኋላ ካህናቱ ከቤተ መቅደስ በወጡ ጊዜ ቤተ መቅደሱን ሁሉ ብርሃን መላው። የእግዚአብሔር ብርሃን በማደሪያው ቤተ መቅደስ መልቷልና ከብርሃኑ መገለጥ የተነሣ ካህናቱ ሥራቸውን መሥራትና ከፊቱ መቆም ተሳናቸው። ➯ያን ጊዜ ሰሎሞን እግዚአብሔር በደመና ውስጥ እኖራለሁ ብሏል። እኔም ለዘላለም የምትኖርበት ማደሪያህ ቤተ መቅደስን በእውነት ሠራሁልህ አለ። ንጉሡም ፊቱን መልሶ የእስራኤልን ጉባኤ ሁሉ መረቃቸው ወደ እግዚአብሔርም ረዥም ጸሎትን ጸለየ። ሰሎሞንም ይህን ሁሉ ልመና ወደ እግዚአብሔር ለምኖ በጨረሰ ጊዜ በጉልበቱ ተንበርክኮ ከሰገደበት እጆቹንም ከዘረጋበት ከመሠዊያው ፊት ተነሣ። ➯ቆሞም የእስራኤልን ማኅበር እንደተናገረው ሁሉ ለወገኖቹ ለእስራኤል ዕረፍትን የሰጣቸው እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን ብሎ በታላቅ ቃል መረቃቸው። ከዚህ በኋላ ንጉሡና የእስራኤል ልጆች ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት መሥዋዕትን ሠዉ። ➯ንጉሡ ሰሎሞንም ለእግዚአብሔር ስለ ሰላም መሥዋዕት የሠዋቸው ሃያ ሁለት ሽህ ላሞችና አንድ መቶ ሃያ ሽህ በጎች ናቸው ንጉሡ ሰሎሞንና የእስራኤል ልጆች ሁሉ ያንጊዜ ለእግዚአብሔር ማደሪያ ለቤተ መቅደስ ቅዳሴ ቤት አደረጉ። ➯ቀድሞ በገባዖን እንደታየው ዳግመኛ እግዚአብሔር ለሰሎሞን ታየው በፊቴ የለመንኸኝ ልመናህንና ጸሎትህን ሰማሁ። እንደ ልመናህም ሁሉ አደረግሁልህ ስሜ በዚያ ለዘላለሙ ጸንቶ ይኖር ዘንድ የሠራኸውንም ቤተ መቅደስ አከበርሁት ልቡናዬም ዐይኖቼም በዘመኑ ሁሉ በዚያ ጸንተው ይኖራሉ አለው። ሰሎሞንም አርባ ዘመን ነገሠ ከመንገሡም በፊት ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖረ መላ ዕድሜውም ሃምሳ ሁለት ዓመት ነበር በሰላም አረፈ። ➯ይህም ጥበብ የተሰጠው ንጉሥ ሰሎሞን ጥቅም ያላቸው ብዙዎች መጻሕፍትን ደርሶአል። እሊህም ትንቢትና ትምህርት ያለባቸው ምሳሌዎችና መኃልዮች ናቸው።#ቅዱስ_አባ_ኖብ (ስንክሳር) ➯በዚህችም ቀን ደግሞ በክብር ባለቤት ክርስቶስ የታመነ አባ ኖብ አረፈ። ይህም ቅዱስ መነኰስ በላይኛው ግብጽ ከሚገኙ ገዳማት በአንዱ ገዳም ውስጥ የሚጋደል ጽሙድ ነበር። ➯ዲዮቅልጥያኖስም ብዙዎች ሰማዕታትን ሊአሠቃይና ደማቸውን ሊያፈስስ በጀመረ ጊዜ በአንዲት ቀን ሰማንያ ሰማዕታትን አቅርቦ ደማቸውን አፈሰሰ። በዚያን ጊዜ አባ ኖብን አስታወሱት የእንዴናው ገዥ ወደሆነው ወደ አርያኖስ አቀረቡት። እርሱም ለአማልክት ዕጠን ሠዋ ይህንንም የምንኵስና ልብስ ከላይህ አውጥተህ ጣል አለው። ➯አባ ኖብም ይህ ሥራ ከቶ ከእኔ ዘንድ አይደረግም የክብር ባለቤት ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስንም አልተውም የረከሱ ጣዖታትንም አላመልክም አለ። መኰንኑም በየራሱ በሆነ ሥቃይ እጅግ አሠቃየው ያም አባ ኖብ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ኃይል ታግሦ ተቀበለ። ➯ከዚህም በኋላ ወደ አምስቱ አህጉር ሰደደው በዚያም በጉድጓድ ውስጥ ጣሉት በውስጡም ጌታችን ከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስን አጥፍቶ ደግ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስን እስከሾመው ድረስ ሰባት ዓመት ኖረ። ➯ቈስጠንጢኖስም በነገሠ ጊዜ ክብር ይግባውና ስለ ክርስቶስ የታሠሩትን ሁሉ ፈትተው ወደርሱ እንዲአቀርቧቸውና ከእርሳቸው እንዲባረክ ወደ አገሮች ሁሉ ደብዳቤዎችን ላከ። ለመልእክተኞችም እንዲህ አላቸው ሁሉንም ወደ እኔ ማድረስ ካልተቻላችሁ እጆቻቸውን በራሴ ላይ ጭነው ይባርኩኝ ዘንድ ክብር ያላቸውን ታላላቆችንና መምህራኑን አምጡአቸው። ➯ከእነርሱም ውስጥ የታወቁ አህናህ ከተባለ አገር አባ ዘካርያስ ከፍዩም መክሲሞስ ከሀገረ ድኂን አጋብዮስ ከሀገረ በላኦስ አባ ኖብ ናቸው የንጉሥ መልእክተኞችም በየአገሮች ሁሉ እየዞሩ የታሠሩ ቅዱሳንን ከእሥር ያወጡአቸው ነበር እነርሱም ደስ ይላቸው ነበር የተመሰገነ እግዚአብሔርንም ያመሰግኑት ነበር ይዘምሩለትም ነበር። ➯የንጉሥ መልእክተኛም አባ ኖብን ከአምስቱ አገሮች ፈልጎ የአገሩ አንጻር ወደ ሆነች ወደ ሀገረ በሰላ ወሰደው። በዚያም የብረት ልብስ ለብሶ ተቀምጦ ነበር የንጉሡ መልእከተኛም አገኘውና ከእርሱ ጋራ ወሰደው ወደ እንዴናውም እስከ ደረሱ በመርከብ ተሳፈሩ ክርስቲያኖችም ተሰበሰቡ ከውስጣቸውም አራት ኤጲስቆጶሳት ነበሩ አባ ኖብንም ያለ ውዴታው ቅስና ሾሙትና የቊርባን ቅዳሴን ቀደሰ። ➯በቅዳሴውም ፍጻሜ ቅድሳት ለቅዱሳን ብሎ ጮኸ ይህም ማለት ንጹሕና ቅዱስ የሆነ ከሥጋው ከደሙ ይቀበል ማለት ነው በዚያን ጊዜም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በመሠዊያው ላይ ተቀምጦ ንስሐ የገቡትን ኃጢአታቸውን ይቅር ሲላቸው አየው ሥጋውንና ደሙንም ከአቀበላቸው በኋላ ወደ ንጉሡ ለመሔድ ተዘጋጁ ቍጥራቸውም ሰባ ሁለት ነበር ሠላሳ ሰባት ሠረገላም አዘጋጅተውላቸው እየአንዳንዳቸው በሠረገላው ተቀመጡ። ➯በአለፉም ጊዜ የደናግል ገዳማት ካሉበት ደረሱ ደናግሉም ወጥተው ተቀበሏቸው ቍጥራቸው ሰባት መቶ ነበር ከእነርሱ ጋራም እስከሚሰበሰቡ በቅዱሳን ፊት ይዘምሩ ነበር።
Show all...
#ዝክረ_ቅዱሳን_ሰኔ_23/፳፫ (ስንክሳር) እንኳን በእስራኤል ሁሉ ላይ ለነገሠ ለዳዊት ልጅ #ለጠቢቡ_ሰሎሞን ለዕረፍቱ መታሰቢያ፣ በክብር ባለቤት ክርስቶስ ለታመነ #ለአባ_ኖብ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። "በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።" #ነቢየ_ጽድቅ_ቅዱስ_ሰሎሞን (ንጉሠ እሥራኤል) ➯የዚህ የሰሎሞንም የእናቱ ስም ቤርሳቤህ ነው ዳዊትም ሕግ ተላልፎ ከእሷ ጋራ ስለ መበደሉ ባሏንም ስለ ማስገደሉ ጌታ በገሠጸው ጊዜ ንስሓ ገብቶ መሪር ልቅሶን አለቀሰ ጌታም ንጹሕ ስለሆነ ንስሓው ይቅር አለው። ከዚህም በኋላ በእግዚአብሔር ፈቃድ እርሷን አገባትና ሰሎሞንን ወለደችው ንጉሥ ዳዊትም ከእርሱ በኋላ ልጅዋ ሰሎሞን እንዲነግሥና በዙፋኑ ላይ እንዲቀመጥ ቃል ገባላት። ➯እንዲህም ሆነ ሰሎሞን ዐሥራ ሁለት ዓመት በሆነው ጊዜ አዶንያስ እነግሣለሁ ብሎ ተነሣ ምክሩም ሁሉ ከሶርህያ ልጅ ከኢዮአብና ከካህኑ አብያታር ጋር ሆነ። እነርሱም አዶንያስን ተከትለው ረዱት። አዶንያስም በሮጌል ምድር ምንጭ አጠገብ ባለ በኤልቲ ዘዘኤልቲ ላይ ፍየሎችን በጎችንና ላሞችን አርዶ የንጉሥ አሽከሮች የሆኑ የይሁዳ አርበኞችን ሁሉና የንጉሡን ልጆች ወንድሞቹን ሁሉ ጠራ። ➯ከዚህም በኋላ አዶንያስ ይህን እንዳደረገ ለቤርሳቤህ በነገሩዋት ጊዜ ወደ ንጉሥ አዳራሽ ውስጥ ገብታ ለንጉሡ ሰገደች ንጉሥ ዳዊትም ምን ሆንሽ አላት። ጌታዬ ንጉሥ ሆይ ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል በዙፋኔም ላይ ይቀመጣል ብለህ ለእኔ ለባርያህ በፈጣሪህ በእግዚአብሔር ስም አንተ ማልክልኝ እነሆ ዛሬ አዶንያስ ነገሠ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ አንተ ግን አላወቅህም አለችው። ➯ከንጉሥም ጋራ ገና ስትነጋገር ነቢዩ ናታን መጣ ለንጉሡም ናታን መጣ ብለው ነገሩት። ወደ ንጉሡም ገባ በምድር ላይም በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደ። ነቢዩ ናታንም ከእኔ ቀጥሎ አዶንያስ ይንገሥ በዙፋኔም ላይ ይቀመጥ ያልክ አንተ ነህን ዛሬ ወርዶ በጎችንና ብዙ ፍየሎችን አርዶ የሠራዊቱ አለቆችንና የንጉሥ አሽክሮችን ሁሉ ካህኑ አብያታርንም ጠርቷልና በፊቱም ይበላሉ ይጠጣሉ አንዶንያስ ሽህ ዓመት ያንግሥህ ይሉታል አለው። ➯ዳዊትም መልሶ ቤርሳቤህን ጥርዋት አለና ጠሩዋት ገብታም በንጉሡ ፊት ቆመች። በእግዚአብሔር ፊት እንደማልኩልሽ አሁንም በዚች ቀን እንደዚሁ እንዳደርግ ሰውነቴን ከመከራዬ ሁሉ ያዳናት የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሕያው ነው ብሎ ማለ። ቤርሳቤህም አንገቷን ደፍታ በግምባርዋ በመሬት ወድቃ ለንጉሡ ሰገደች ጌታዬ ንጉሥ ዳዊት ለዘላለም ኑር አለች። ➯ንጉሥ ዳዊትም የዮዳሄ ልጅ ብንያስንና ካህኑ ሳዶቅን ነቢዩ ናታንንም ግራዝማቹንና ቀኝ አዝማቹን ጥሩልኝ አለ። ንጉሡም ከእናንተ ጋራ የጌታችሁ አሽከሮችን ይዛችሁ ልጄ ሰሎሞንን በበቅሎዬ ላይ አስቀምጣችሁ ወደ ግዮን አውርዱት። በዚያም ነቢዩ ናታንና ካህኑ ሳዶቅ ቀብታችሁ በእስራኤል ላይ አንግሡት አላቸው። ➯ቀንደ መለከት ንፉ ሰሎሞን ሺህ ዓመት ያንግሥህ በሉ። ተከትላችሁትም ውጡ ገብቶም በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ እርሱም ስለ እኔ ፈንታ ይንገሥ በሁለቱ ነገድና በዐሥሩ ነገድ ይነግሥ ዘንድ እኔ አዝዣለሁ። ካህኑ ሳዶቅም ከድንኳኑ ቀርነ ቅብዑን ወስዶ ሰሎሞንን ቀባው ቀንደ መለከትንም ነፉ ሕዝቡም ሁሉ ሰሎሞን ሺህ ዓመት ያንግሥህ አሉ ሕዝቡም ሁሉ ተከትለውት ወጡ ከበሮም መቱ ታላቅ ደስታም አደረጉ ከድምፃቸውም የተነሣ ምድሪቱ ተናወጸች። ➯ሰሎሞንም በመንግሥት ዙፋን ተቀመጠ። የንጉሡም አሽከሮች ጌታቸው ንጉሡ ዳዊትን ሊአመሰግኑ ገቡ። እግዚአብሔር የሰሎሞንን ስም ከስምህ ይልቅ መልካም ያድርገው ዙፋኑንም ከዙፋንህ ይልቅ የበለጠ ያድርገው አሉት። ንጉሡም በዐልጋው ሆኖ ሰገደ። እንዲህም አለ ዐይኖቼ ሲያዩ በዙፋኔ ላይ የሚቀመጥ ልጅን ለኔ ለባርያው ዛሬ የሰጠ የእስራኤል ፈጣሪ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን አለ። ዳዊትም የሚሞትበት ወራት በደረሰ ጊዜ ልጁ ሰሎሞንን እንዲህ ሲል አዘዘው። እኔ ሰው ሁሉ በሚሔድበት በሞት ጐዳና እሔዳለሁ አንተ ግን ጽና ብልህ ሰውም ሁን። ➯በሕጉ ጸንተህ ትኖር ዘንድ የፈጣሪህ የእግዚአብሔርን ትእዛዙን ጠብቅ እኔ እንዳዘዝሁህ እንዴት እንደምታደርግ ታውቅ ዘንድ በሙሴ ሕግ የተጻፈውን ትእዛዙንና ሕጉን ፍርዱንም ጠብቅ ልጆችህ ሕጌን ቢጠብቁ በፊቴም በፍጹም ልቡናቸው በፍጹም ሰውነታቸው በዕውነት ጸንተው ቢኖሩ ከእስራኤል ዙፋን ላይ ሰው አይጠፋብህም ብሎ እግዚአብሔር ለእኔ የነገረኝ ቃሉን ያጸና ዘንድ ጠብቅ ብሎ አዘዘው። ➯ዳግመኛም በኢዮአብና በሳሚ ወልደ ጌራ ላይ በቀል እንዲአደርግ አዘዘው እነርሱ እጅግ የከፉና ብዙ ክፋት የሠሩ ነበሩና። ከዳዊት ዕረፍትም በኋላ ሰሎሞን በዚያ መሥዋዕትን ይሠዋ ዘንድ ተነሥቶ ወደ ገባዖን ሔደ ገባዖን ፈጽማ ትሰፋ ነበርና ሰሎሞንም በገባዖን በዚያው መሠዊያ ውስጥ ሽህ መሥዋዕትን ሠዋ። እግዚአብሔርም ለሰሎሞን በሌሊት በሕልም ተገለጠለት ለአንተ እሰጥህ ዘንድ ልብህ ያሰበውን ልመናን ለምን አለው። ➯ሰሎሞንም በቅንነትና በእውነት በንጹሕ ልቡናም ከአንተ ጋራ በፊትህ ጸንቶ እንደኖረ ከአባቴ ከዳዊት ጋራ ታላቅ ቸርነትን አድርገሃል በዚችም ቀን ልጁን በዙፋኑ ላይ ታስቀምጠው ዘንድ ይህን ታላቁን ቸርነት አጽንተህለታል አለው። አሁንም አቤቱ አንተ ፈጣሪዬ ስለ አባቴ ስለ ዳዊት ፈንታ እኔን ባሪያህን አነገሥኸኝ እኔም መግቢያዬንና መውጫዬን የማላውቅ ታናሽ ብላቴና ነኝ። ➯እኔ ባሪያህ ግን የማይቈጠር ብዙ ሕዝብ በሆነ በመረጥከው ወገንህ መካከል አለሁ። ለዚህ ለብዙ ወገንህ መፍረድ የሚችል የለምና ሰምቶ ለወገኖችህ በእውነት ፍርድን ይፈርድ ዘንድ ከክፉ ነገርም ለይቶ በጎውን ነገር ያውቅ ዘንድ ለባሪያህ ዕውቀትን ስጠው። ሰሎሞን ይህንን ነገር ለምኖታልና ይህ ነገር እግዚአብሔርን በፊቱ ደስ አሰኘው። እግዚአብሔርም ይህንን ነገር ከእኔ ለምነሃልና ለአንተም ብዙ ዘመንንና ባለጸግነትን አልለመንህምና ጠላቶችህንም አጥፋልኝ ብለህ አልለመንህምና ነገር ግን ፍርድ መስማትን ታውቅ ዘንድ ለምነሃልና እነሆ እንዳልህ አደረግሁልህ። ➯እነሆ ከአንተ አስቀድሞ እንዳልነበረ ከአንተም በኋላ እንዳንተ ያለ እንዳይነሣ አድርጌ ብልህና አስተዋይ ልቡናን ሰጠሁህ። ሰው በመንግሥቱ እንዳንተ እንዳልሆነ አድርጌ ያልለመንኸኝን ባለጠግነትንና ክብርንም በዘመንህ ሁሉ እሰጥሃለሁ አለው። ➯ሰሎሞንም ከእንቅልፉ በነቃ ጊዜ እውነተኛ ሕልም እንደ ሆነ ዐወቀ ተነሥቶም ወደ ኢየሩሳሌም ሔደ በጽዮንም በእግዚአብሔር ታቦተ ሕግ አንጻር ባለ በመሠዊያው ፊት ቆሞ የሰላም መሥዋዕትን አቀረበ ለሰዎቹና ለሱም ታላቅ ግብዣ አደረገ። ➯በዚያን ጊዜም ሁለት አመንዝራ ሴቶች ወደ ንጉሡ መጥተው በፊቱ ቆሙ አንዲቱም ሴት ጌታዬ ስማኝ እኔና ይህች ሴት በአንድ ቤት እንኖራለን በአንድ ቦታም ወለድን እኔ በወለድሁ በሦስተኛው ቀን ይህች ሴት ወለደች በአንድነትም እንኖራለን በዚያም ቤት ከሁለታችን በቀር ከኛ ጋራ ማንም አልነበረም። በላዩ ላይ ተጭናዋለችና የዚያች ሴት ልጅ በሌሊት ሞተ። ➯በሌሊት እኩሌታም ተነሥታ ተኝቼ ሳለሁ ልጄን ከአጠገቤ ወስዳ በብብቷ አስተኛችው። የሞተውን ልጅዋንም በአጠገቤ አስተኛችው። ልጄን አጠባ ዘንድ በጧት በነቃሁ ጊዜም ያንን የሞተ ልጅ አገኘሁ በነጋም ጊዜ አየሁት እነሆ የወለድሁት ልጄ አይደለም አለች።
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.