ግጥም
Open in Telegram
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post ADMIN 👉 @Big_jor
Show more5 369
Subscribers
+1024 hours
+627 days
+20430 days
Posts Archive
5 370
#ሁሉም_ጥቅም_አይቶ
ሰውንስ አየሁት በወረት ሲመታ
የማትቀያየር አንተ ብቻ ጌታ
ሰው የተደገፉ በተራ ሲወድቁ
ወጀቡን አለፉት አንተን ያጠበቁ
ሁሉም ጥቅም አይቶ ሲወድ ሲጠላ
አንተ ግን ክርስቶስ ሁልጊዜም ነህ ጥላ
ስንቱን ቀርበን አየን ፈተናን ወደቀ
የድንግል ልጅ ብቻ ቃሉን የጠበቀ
ሲኖረን አብረውን ስናጣ የጣሉን
ወረት ሲያንጓልለው አይተነዋል ሰውን
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 370
መኖር በሰው ፍቃድ ሆነና ዘንድሮ
ማስተዋል ተሳነን ልባችን ታውሮ።
ጌታ የሰጠውን ፍጡር ከነጠቀ
አትጠራጠሩ ይህ ዘመን አለቀ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 370
#የጌታ_ደብዳቤ
የድሮ ሰው ደጉ
በ…30…ዲናር
ጌታዉን ካስማማ
ምንኛ ይከፋል
ያሁኑ ሠዉማ
ስለዚህ አትምጣ
ለምፅዓት ቀኑ
ዲናር እንዳይመስልህ
ዶላር ነው ያሁኑ
ይቅር በለኝ አምላክ
አይሁንብኝ ድፍረት
እንዳስቀመጥከው ነው
"ሠው" የሚሉት ፍጥረት
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
#መልካም_ምሽት_አይላቭዪ_React_ምታደርጉ 🫶
5 370
#በጎች_ተጠንቀቁ
በቀበሮ መንጋ በግ እያስጠበቁ
ተበልተው ተበልተው በየተራ አለቁ
እረኛ ባሉት ነው ሁሉም የሚጠቁ
በቀበሮ ዘመን በጎች ተጠንቀቁ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 370
#ማንነት_ሲምታታ
የራስ ምስል ገዝፎ በሌላ ገጽታ
ጠላት ይመስለዋል ማንነት ሲምታታ
ከነበረው እውነት ገዝፎ ሲቀርብ ሀሰት
የራስ ጥላ ሳይቀር ከመሰለው ጠላት
ሳይሻል አይቀርም ከራስ ጋር መታረቅ
ሸንጎ ከመሰብሰብ ሌላን ለማስታረቅ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 370
Repost from ዝባዝንኬ thought🗽
I really felt it when አስቴር አወቀ said "በል እራሴን በለኝ እንካ ዘነዘና" cause, boy do i wish to be caved with a ዘነዘና in my head🚶🏾
5 370
በአህያ ሞት አዝኖ ጅብ ለቅሶ ቢቀመጥ
ለማመቻቸት ነው ሲመሽ ለመለወጥ
በግ ጠፋብኝ አትበል ለቀበሮ መንጋ
ይልቅ ለአምላክ ንገር ወርዷል ለፍለጋ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 370
እንቅልፍ ያጡ ዓይኖቼ ማረፍን የፈሩ
በሀሳብ ነበልባል በቅዠት ያደሩ
በመስታወት መስኮት ሳያቸው ሲነጋ
እጅግ አሳዘኑኝ ለከፈሉት ዋጋ!!!
እረፍት ነፍጊያቸው በሽህ ሀሳብ ስሌት
በማይጠቅም እህ በማይነጋው እውነት
አሳርን እያዩ ማረፍ ሲናፍቁ
ደፍርሰው ያዩኛል አድረው ሲጨነቁ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 370
ተመስገን ማለት ነው ዛሬ ያደረሰን
ስንቱን ክፉ ዓመታት ሰላም ያሻገረን
በማመስገን ትግስት ሆዳችን ባይሰፋ
ያሳለፍነው ፍዳ ከዚህም በከፋ!!!
ይመስገን ፈጣሪ ብዙ ዓመት አልፈናል
የጊዜውስ መክፋት ቀን በቀን ይጥላል።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
#መልካም_ምሽት_አይላቭዪ_React_ምታደርጉ 🫶
