️ፈለገ ጥበብ Photography (ፈለገ ጥበብ ፎቶ ማህደር ዘፈለገ ጥበብ ሚዲያ)
Open in Telegram
እንኳን ወደ ፈለገ ጥበብ ሚዲያ የ 🅿🅷🅾🆃🅾🅶🆁🅰🅿🅷 ቻናላችን በደህና መጣቹ። ✔️በፈለገ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤትም ይሁን በተለያዩ ደብራት የሚነሱ ፎቶግራፎችን በዚህ የፈለገ ጥበብ የፎቶ ማህደር ላይ ያኙታል። መልካም ጊዜ 📸📷📹💽
Show more733
Subscribers
No data24 hours
-57 days
-530 days
Posts Archive
ደብረታቦር 2016 ዓ.ም በደብረዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል አብያተክርስቲያናት
በቢሾፍቱ ከተማ በደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል አብያተክርስቲያናት ለ3ቀን የተዘጋጀው ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ በዛሬው ዕለት 2ኛ ቀን ጉባኤ የተከናወነ ሲሆን በነገው ዕለት በሚኖረው የማታ ጉባኤ ላይ ታላላቅ አባቶች መምህራን የፈለገ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤት ዘማሪያን በተገኙበት መርሀግብሩ የሚጠናቀቅ ይሆናል። ጉባኤው ከቀኑ 10 :00 ሰዓት ላይ የሚጀምር ይሆናል።
በነገው ዕለት ጉባኤውን ለመታደም ስንመጣ 1ችቦ ይዘን መገኘታችን እንዳይረሳ።
#ፈለገ_ጥበብ_ሚዲያ
#FTM
ነሀሴ 11/2016 ዓ.ም
https://t.me/felegetibebimage
በፈለገ ጥበብ ሰንበት ት/ቤ የ2016 ዓ.ም የ2ኛ መንፈቀአመት ማጠቃለያ ጠቅላላ ጉባኤ ተደረገ።
በመርሀግብሩ ላይም የደብሩ ስብከተ ወንጌል ምክትል ሰብሳቢ የቢሾፍቱ እና አካባቢው የሰንበት ትምህርት ቤቶች ህብረት ሰብሳቢ እና ምክትል ሰብሳቢ ፣በቢሾፍቱ ወረዳ ማዕከል ማህበረ ቅዱሳን ፀሀፊ እና ሌሎች የሰንበት ት/ቤት አባላት መርሀግብሩን የታደሙ ሲሆን በመርሀግብሩላይም የ2016 ዓ.ም የሂሳብ ሪፓርት፣የ2016 ዓ.ም የስራ አፈፃፀም ሪፓርት ፣የ2017 ዓ.ም እቅድ፣ በስራ እና በተለያዩ ምክንያቶች ከስራ አመራርነት ለተነሱ አባላት በእነሱ ምትክ የሆኑ አባላት በጠቅላላ ጉባኤላይ የመምረጥ እና የተጠባባቂ አካላትን በማዘጋጀት መርሀግብሮች የተከናወኑ ሲሆን በመጨረሻም የሰንበት ት/ቤት ህብረት ሰብሳቢ እና የወረዳ ማዕከል ፀሀፊ መልዕክት እና ብራኬ በመስጠት መርሀግብሩ በፀሎት ተዘግትዋል።
እኛም እንደዚህ አይነት የአንድነት መርሀግብሮች በየጊዜያቱ ይበል ይቀጥል እያልን ምልዕክታችንን እናስተላልፋለን።
#ፈለገ_ጥበብ_ሚዲያ
#FTM
ነሀሴ 6/2016 ዓ.ም
