cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

መቂ ቅድመ ግቢ ጉባዔ

✞✟✞

Show more
Advertising posts
241
Subscribers
No data24 hours
+67 days
+630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
ክፍል ፭ ኢየሱስ ክርስቶስ የት ተወለደ? የሕይወት እንጀራ ክርስቶስ በእንጀራ ቤት ተወለደ (ሉቃ. ፪፣፬-፲፭)። ቤተልሔም ማለት የእንጀራ ቤት ማለት ነው። የክርስቶስ መወለድ ድንገት እንደ እንግዳ ደራሽ፣ እንደ ውሃ ፈሳሽ አይደለም። በቅዱሳን ነቢያት የሰውን ሥጋ ተዋሕዶ እንደሚወለድ ትንቢት ሲነገር ነበርና (ኢሳ. ፯፣፲፬)። ከጽድቅ ለተራበው ዓለም መንፈሳዊ ምግብ ይሆን ዘንድ የሕይወት እንጀራ ክርስቶስ በእንጀራ ቤት ተወለደ። ቤተልሔም በእስራኤል ሀገር ያለች የዳዊት ከተማ የነበረች ቦታ ናት። ነቢያቱ፣ ነገሥታቱ ተወልደውባታል። የነቢያት ሀገር ናት። ከነቢያቱ፣ ከነገሥታቱ ግን የሕይወት እንጀራ ሆኖ የተራበውን ዓለም ማጥገብ የቻለ አልነበረም። ወልደ እግዚአብሔር ግን ከድንግል ማርያም ተወልዶ ዘለዓለማዊ ሕይወትን የሚሰጥ የሕይወት እንጀራ ሆነ። ምእመናን ንሥሓ ገብተው፣ ሥጋውን በልተው፣ ደሙን ጠጥተው በእርሱ ሕያዋን ሆነው ይኖራሉ። እርሱም በእነርሱ ይኖራል። © በትረማርያም አበባው የፌስቡክ ገጼ:- Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው። የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።
Show all...
👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
ክፍል ፬ ቃለ እግዚአብሔር ወልድ ዋሕድ በተዋሕዶ ከበረ ዋነኛ ትምህርታችን ነው። ቅዱስ አትናቴዎስ በሃይማኖተ አበው እንደተናገረው ሥጋ መክበሩ ቃል ስለተዋሐደው ነው እንጂ መንፈስ ቅዱስ ክብር ሆኖት አይደለም። ኢየሱስ ክርስቶስ ቃለ እግዚአብሔር ነው። ይህም ማለት ቃለ አብ፣ ቃለ መንፈስ ቅዱስ ነው ማለታችን ነው። በአንድ ህልውና በአንድ ባሕርይ ለሚኖሩ ሦስቱ አካላት ቃላቸው እርሱ ነው። ይህ ቃል ከሰው፣ ከእንስሳት፣ ከመላእክት ቃል (ድምፅ) የተለየ ነው። እነዚህ ቃላት (ድምፆች) ዝርዋን ናቸው እንጂ አካላውያን አይደሉም። ቃለ እግዚአብሔር አአትሪኮን፣ አተርጋዎን፣ ቦርፎሪኮን ከሚባሉት ቃላት የተለየ ቃል ነው። ቅዱሳን ነቢያት ከእግዚአብሔር የሰሙት ድምፅ እንኳ ዝርው ነው። አካላዊ ቃል የሚባለው ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል ነው። ከንባብ (ንግግር) የተለየ አካላዊ ቃል ነው። ይህ ቃል ሥጋ ሆነ። ይህም ማለት ረቂቁ አካለ ቃል ግዙፉን አካለ ሥጋ በተዋሕዶ ገንዘቡ አደረገው ማለታችን ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምድር እየተመላለሰ ሲያስተምር ለሕዝቡ ጆሮ ይሰማ የነበረው ድምፅ ዝርው ስለሆነ አካላዊ አይደለም። ራሱ ክርስቶስ ግን አካላዊ ቃል ነው። እርሱ የተናገረው ንግግር ግን ከእርሱ ከአካላዊ ቃል የተገኘ ንግግር (ንባብ) ነው እንጂ ራሱ ንግግሩ አካላዊ አልነበረም። © መ/ር በትረማርያም አበባው የፌስቡክ ገጼ:- Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው። የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ክፍል ፫ አማኑኤል አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ (እግዚአብሔር ምስሌነ) ማለት ነው። እግዚአብሔር በአካል ከፍጥረቱ ተለይቶ አያውቅም። እርሱ በአካል የሌለበት ቦታ የለምና። በረድኤትም በብሉይ ኪዳን ከቅዱሳን አበው፣ ከቅዱሳን ነቢያትና፣ ከቅዱሳን ነገሥታት ጋር ነበር። ይህኛው "ምስሌነ" ግን አነጋገሩ ከረድኤት የተለየ "ምስሌነ" ነው። በረድኤት ከእኛ ጋር መኖርን ብቻ የሚገልጽ አይደለም። የእኛን ሥጋ ተዋሕዶ ከእኛ ጋር መኖሩንም የሚገልጽ አነጋገር ነው። አማኑኤል የሚለው ስም ስመ ሥጋዌውን የሚገልጽ ስም ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን እንደእኛ ሰው ሆኖ ክሦ፣ ቤዛ ሆኖ አድኖናል። እንግዲህ ምንንም፣ ማንንም አንፈራም። የሚያስፈራን ፍጡር የለም። ምክንያቱም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው። በእምቢታችን ጸንተን፣ በራሳችን ፈቃድ ከእግዚአብሔር ጋር መኖር አንፈልግም ብለን ከሰይጣን ጋር ካልተባበርን በስተቀር እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ስለሆነ በእርሱ ሁሉን አሸንፈን እንኖራለን። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆኖ ነጻነትን መለሰልን፣ ፍጹም መንፈሳዊ ደስታን ሰጠን። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ሁሉ አለን። ኵሉ ብነ እንዘ አልብነ ኵሉ እንዳለ። © በትረማርያም አበባው የፌስቡክ ገጼ:- Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው። የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።
Show all...
👍 1
🥰 3👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ክፍል ፩ _ኢየሱስ_ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሚጠራባቸው ስሞች አንዱ ኢየሱስ ነው። ኢየሱስ ማለት መድኃኒት ማለት ነው። ዓለም በአዳም በደል ምክንያት ታሞ ይኖር ነበር። ዓለምን መፈወስ የቻለ ሰው ደግሞ እስከ ክርስቶስ ልደት ድረስ አልተገኘም ነበር። ስለዚህ ዓለምን ለማዳን ከሦስቱ አካላት አንዱ ወልድ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ፣ ከነፍሷ ነፍስን ነስቶ ተዋሐደ። ዓለምን የማዳን ሥራውም ከማኅፀን በተዋሕዶ ጀመረ። በዓለም ላይ ብዙ መድኃኒቶች ቢኖሩም መድኃኒትነታቸው የጸጋ ማዳን ነው። በባሕርይው አዳኝ የሆነ እግዚአብሔር ነው። እርሱ እግዚአብሔር ሥጋን ተዋሕዶ አድኖናልና ኢየሱስ ተብሏል። ሰውን ያዳነው፣ ወደቀደመ ቦታውም የመለሰው ኢየሱስ ነው። ሌሎች ፍጡራን ቢያድኑ ግን ማዳንን ከክርስቶስ በጸጋ ተቀብለው ነው። ኢየሱስ የሚለው ስም በአማርኛ መድኃኒት፣ መድኃኒ ዓለመ፣ መድኃኔ ዓለም ተብሎ ሊገለጽ ይችላል። የኢየሱስ ስሙ፣ አካሉ፣ ሁለንተናው አዳኝ ነው። ስለሆነም በየጊዜው በየሰዓቱ ከሰይጣን ተንኮል ያድነን ዘንድ ስሙን እንጠራለን። ስለሆነም እንደ ደራሲው ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ሠረፀ እምቤተ ሌዊ፣ ኮሬባዊ መለኮታዊ፣ ቃል ሰማያዊ እምድንግል ተወልደ እንለዋለን። © በትረማርያም አበባው
Show all...
4
Photo unavailableShow in Telegram
ክፍል ፪ ክርስቶስ ክርስቶስ በዕብራይስጥ ማስያስ፣ በዐረብ መሢሕ፣ በግሪክ ክርስቶስ፣ በግእዝ ቅቡዕ ማለት ነው። ቅቡዕ ማለትም የተቀባ ማለት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው የሆነ አምላክ፣ አምላክ የሆነ ሰው ነው። ወልደ እግዚአብሔር ከድንግል ማርያም የነሣውን ሥጋ ሲዋሐድ በአምላክነት አከበረው። ሥጋም ቃልን ስለተዋሐደ ከብረ። ስለዚህም ቅቡዕ ተባለ። ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው መባሉ በሰውነቱ እንደሆነ ሁሉ ቅቡዕ መባሉም በሰውነቱ ነው። በአምላክነቱ ክብርን (ቅብዕን) የሚሻ አይደለምና። ክርስቶስ ለተዋሐደው ሥጋ ክብር የሆነውም ራሱ ቃል ነው። እንጂ የቅባት እምነት አራማጆች እንደሚሉት መንፈስቅዱስ ቅብዕ (ክብር) አልሆነውም። በሥላሴ ዘንድ ቅብዕ፣ ተቀባዒ፣ ቅቡዕ የሚል አካላዊ ግብር የለምና። በማክበር፣ በክብር አንድ ስለሆኑ አብ አከበረው፣ ወልድ አከበረው፣ መንፈስ ቅዱስ አከበረው ቢል አንድ ነው። ለሥጋ ክብር የሆነው በተለየ አካሉ ቃል ነው። ምክንያቱም ሥጋ ቃልን ሆነ እንጂ ልብን ወይም እስትንፋስን አልሆነምና ነው። ሥጋ ከበረ መባሉ እንኳ ቃልን ሆነ ማለት ነውና። ክፍል ፫ ይቀጥላል። © በትረማርያም አበባው
Show all...
4
Show all...
ቅዱስ ቂርቆስ እና ቅድስት ኢየሉጣ

  ሦስት ዓመት እንኳን ሳይሞላው በሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወሩ ታላቅ ሰማዕትነትን የተቀበለው ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ አባቱ ቆዝሞስ (ስምዖን) እናቱ ኢየሉጣ ይባላሉ፡፡ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ በኅዳር 15 ቀን የተወለደ ሲሆን ሀገሩ በታችኛው እስያ ልዩ ስሙ ሀንጌቤን ይባላል፡፡ ዘመኑ ዘመነ ሰማዕታት ነበርና መምለኬ ጣዖት የሆነው ንጉሥ እስክንድሮስ ቅድስት ኢየሉጣን ‹‹ለጣዖቴ ስገጂ›› ብሎ አስገደዳት፡፡ እርሷም ‹‹ሕፃኑ ልጄ መጥቶ ይመስክር›› ብላ ስትናገር ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ተጠራና ተጠየቀ፡፡ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስም ‹‹ለጣዖት አንሰግድም፣ ዘላለማዊ የሆነ የማይሻር አምላክ ስላለ ለእርሱ ነው የምንሰግደው›› ብሎ የአምላኩን ክብር በሕፃን አንደበቱ መሰከረ፡፡ ሕፃኑም ይህንን በመሰከረ ጊዜ ዕድሜው ገና ሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወሩ ነበር፡፡ ነቢዩ ቅዱስ ዳዊትም ‹‹ከልጆችና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ›› ሲል…

Photo unavailableShow in Telegram
ክርስቶስ ማን ነው? √ ቅድመ ዓለም የነበረ የአብ ልጅ ነው። √ ከድንግል ማርያም የተወለደ ፍጹም ሰው ነው። √ ፍጹም አምላክ ነው √ ፍጥረታትን ሁሉ የፈጠረ ነው። √ የአብና የመንፈስ ቅዱስ ቃላቸው ነው። √ አዳምን ለማዳን ሥጋን የተዋሐደ ነው። √ ቤዛችን፣ መድኃኒታችን፣ ጌታችን ነው። √ ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው። √ ክርስቶስ ንጉሠ ነገሥት፣ አምላክ ነው √ ከሁለት አካል አንድ አካል፣ ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ የሆነ ነው። ሰው የሆነ አምላክ፣ አምላክ የሆነ ሰው ነው። አምላክም ሰውም ነው። በቅዱሳት መጻሕፍት ራሱ ስለራሱ የነገረን ይህንና የመሳሰለውን ነው። ሁልጊዜም እኛን ለማዳን ስለኛ ቤዛ ሆኖ በመስቀል የተሰቀለልንን ጌታ እናስበዋለን። መመኪያችን፣ ደስታችን፣ ሕይወታችን እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። © በትረማርያም አበባው
Show all...
👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
ቤተክርስቲያን የተመሠረተችው በክርስቶስ ላይ ነው። ስለሆነም አካሉ ናት። የቤተክርስቲያን አገልግሎት ሁሉ ማዕከሉ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ብዙ ጊዜ የቤተክርስቲያንን ትምህርት ጠንቅቀው ሳያውቁ ትተዋት የሄዱ ሰዎች ማንነቷን ሳያውቁ ሲሳደቡ ይስተዋላል። በማንነቷ ሳይሆን እነርሱ ናት ባሏት ማንነት ይሰድቧታል። ነገር ግን ይህ አይገርምም። አካሏ ክርስቶስ ምንም ጥፋት ሳይኖርበት በአደባባይ ተሰድቧል። በአደባባይ ተሰቅሏልና። ስለዚህ የሌላ እምነት ሰዎች ቤተክርስቲያን ስለኢየሱስ የምታስተምረው ምን እንደሆነ መጀመሪያ ጠይቁ እወቁ። የቤተክርስቲያን አካል፣ የቤተክርስቲያን ሕይወት በመስቀል ተሰቅሎ ያዳነን ኢየሱስ ነው። "እኛስ የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን" ቅዱስ ጳውሎስ
Show all...
🙏 5
Photo unavailableShow in Telegram
የቃናውን ወይን የቃና ሰርገኞች ጠጥተው ጨርሰውታል። ከትውልድ ወደ ትውልድ ሳይተላለፍ በታሪክ ብቻ እንማረዋለን። የቀራንዮውን ወይን ግን እስከ ዕለተ ምጽአት ምእመናን ንሥሓ እየገቡ ይጠጡታል። እርሱም ንጽሐ ሥጋን ንጽሐ ነፍስን ያጎናጽፋቸዋል። ለምእመና ልዩ ቀን (ዕለት ኅሪት) ንሥሓ ገብተው ከዘለዓለማዊው ወይን የሚጠጡበት ቀን ናት። #ዕለት #ኅሪት #ዕለተ #መድኃኒት እስራኤላውያን ከግብፅ የወጡባት ቀን ዕለት ኅሪት ትባላለች። ባሕረ ኤርትራን የተሻጉረባት ቀን ደግሞ ዕለተ መድኃኒት ትባላለች። ጌታ የተፀነሰባት ዕለት ዕለት ኅሪት ትባላለች። የተወለደባት ቀን ደግሞ ዕለተ መድኃኒት ትባላለች። አንድም የተወለደባት ቀን ዕለት ኅሪት ትባላለች። የተሰቀለባት ቀን ዕለተ መድኃኒት ትባላለች። አንድም የተሰቀለባት ቀን ዕለት ኅሪት ትባላለች። ከሙታን የተነሣባት ቀን ዕለተ መድኃኒት ተብላበች። ሰው ንሥሓ የሚገባባት ቀን ዕለት ኅሪት ትባላለች። ሥጋውን ደሙን የሚቀበልባት ቀን ደግሞ ዕለተ መድኃኒት ትባላለች። ዕለት ኅሪት፣ ዕለተ መድኃኒት በንባብ እንጂ በምሥጢር አንድ ናቸው። ጌታ ጥር ፲፩ በውሃ ተጠመቀ። በዕለተ ዐርብ ከጎኑ በፈሰሰው ንጹሕ ውሃ (ማየ ገቦ) ደግሞ እኛ እንድንጠመቅ አደረገን። ጌታ በቃና ዘገሊላ ውሃውን ወደ ወይን ለውጦ ሠርገኞችን አስደሰታቸው። ወይን ያስተፌሥሕ ልበ ሰብእ ማለትኮ ይህ ነው። ወይን ደመ ክርስቶስ ምእመናንን ያስደስታል። በዕለተ ዓርብ ደሙን አፍስሶ አነጻን። ወይን ክርስቶስ እስከ ዕለተ ምጽአት ለሚነሡ ምእመናን መድኃኒት የሚሆን መጠጥን ሰጠን። ስለ ቃና ወይን ስንናገር ንሥሓ ገብተን ዋናውን ወይን ደመ ክርስቶስን መቀበል ይገባናል።
Show all...
🙏 2👍 1🥰 1
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.