cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

🕋 ISLAMIካ🧐

በዚህ ቻናል እንባን ከአይን የሚያፈሱ አፍን በእጅ የሚያስይዙ ጥቅሶች በኢስላማዊ ለዛ የተዋዙ ውብ፣ልብ የሚነኩ፣ የተለያዩ ፅሁፎች እና ስራዎች ይለቀቃሉ:: የአኼራ ማስታወሻ ኢስላማዊ ስነልቦና ለአስተያየት 👇👇👇 @Usman_mustofa ለመቀላቀል/join ለማድረግ 👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/ISLAMIKA_BORN_MUSLIM789

Show more
Advertising posts
1 801
Subscribers
-224 hours
+27 days
+1030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

🍃 ከእሴቶቻችን 🍃 ሰይድና ዑመር(ረዐ) እንዲህ ይላሉ፦    [[ እናንተ ጠላቶቻችሁን በቁጥራችሁ መብዛትና ባላችሁ መሳሪያ አይደለም የምትረቷቸው የምትረቷቸው ባላችሁ ብርቱ ዲን(እምነት) ነው። እናንተ ከጠላቶቻችሁ ጋር በወንጀል ተመሳስላችሁ የቀረባችሁ እንደሆነ ድሉ የጠላቶቻችሁ ነው]] ።
Show all...
ላብ አደር በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 43፥32 ከፊላቸውም ከፊሉን ሠራተኛ አድርጎ ይይዝ ዘንድ ከፊላቸውን ከከፊሉ በላይ በደረጃዎች (በሀብት) አበለጥን፡፡ وَرَفَعْنَا بَعْضَهُمْ فَوْقَ بَعْضٍ دَرَجَاتٍ لِّيَتَّخِذَ بَعْضُهُم بَعْضًا سُخْرِيًّا "አደር" ማለት የዕለት ለዕለት የአኗኗርን ዘይቤን ለማመልከት የሚመጣ ፈሊጣዊ አነጋር እንጂ "አዳር" ከሚለው ቃል የሚሳለጥ አይደለም፥ ለምሳሌ፦ "ሠርቶ አደር" "ወጥቶ አደር" "አርሶ አደር" "አርብቶ አደር" "ወዝ አደር" "ላብ አደር" ሲባል ይህንን ታሳቢ እና ዋቢ ያደረገ ነው። ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ስለ ላብ አደር የሠራተኛን ዋጋ ላቡ ሳይደርቅ ክፈሉ" ብለው ነግረውናል፦ ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 16 ቁጥር 8 ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "የሠራተኛን ዋጋ ላቡ ሳይደርቅ ክፈሉ"።  عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عُمَرَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ أَعْطُوا الأَجِيرَ أَجْرَهُ قَبْلَ أَنْ يَجِفَّ عَرَقُهُ ‏"‏ ‏.‏ አንድ አሠሪ የሠራተኛውን ላብ የማይከፍል ከሆነ አሏህ በትንሣኤ ቀን ከሚጻረራቸው ሦስት ሰዎች አንዱ ይሆናል፦ ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 16 ቁጥር 7 አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "አሏህ እንዲህ ይላል፦ "እኔ በትንሣኤ ቀን የሥስት ሰዎች ተጻራሪ ነኝ፥ እኔ የማንም ተጻራሪ ከሆንኩ በትንሣኤ ቀን አሸንፈዋለሁ። በስሜ ቃል የገባ ከዚያም የሚያታልል ሰው፣ ነጻ ሰው ሸጦ ዋጋውን የሚበላ ሰው እና ሠራተኛ የሚቀጥር እና ተጠቅሞበት ከዚያም ደመወዙን የማይሰጥ ሰው ነው"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ ثَلاَثَةٌ أَنَا خَصْمُهُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ وَمَنْ كُنْتُ خَصْمَهُ خَصَمْتُهُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ رَجُلٌ أَعْطَى بِي ثُمَّ غَدَرَ وَرَجُلٌ بَاعَ حُرًّا فَأَكَلَ ثَمَنَهُ وَرَجُلٌ اسْتَأْجَرَ أَجِيرًا فَاسْتَوْفَى مِنْهُ وَلَمْ يُوفِهِ أَجْرَهُ ‏"‏ ‏.‏ አምላካችን አሏህ በቅርቢቱ ሕይወት ኑሯችንን በመካከላችን አከፋሏል፥ ከፊላቸውም ከፊሉን ሠራተኛ አድርጎ ይይዝ ዘንድ ሀብትን ሰጥቶአል፦ 43፥32 እነርሱ የጌታህን ችሮታ ያከፋፍላሉን? እኛ በቅርቢቱ ሕይወት ኑሯቸውን በመካከላቸው አከፋፍለናል፡፡ ከፊላቸውም ከፊሉን ሠራተኛ አድርጎ ይይዝ ዘንድ ከፊላቸውን ከከፊሉ በላይ በደረጃዎች (በሀብት) አበለጥን፡፡ የጌታህም ጸጋ ገነት ከሚሰበስቡት ሀብት በላጭ ናት፡፡ أَهُمْ يَقْسِمُونَ رَحْمَتَ رَبِّكَ ۚ نَحْنُ قَسَمْنَا بَيْنَهُم مَّعِيشَتَهُمْ فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا ۚ وَرَفَعْنَا بَعْضَهُمْ فَوْقَ بَعْضٍ دَرَجَاتٍ لِّيَتَّخِذَ بَعْضُهُم بَعْضًا سُخْرِيًّا ۗ وَرَحْمَتُ رَبِّكَ خَيْرٌ مِّمَّا يَجْمَعُونَ የአሏህ ገነት ከሚሰበስቡት ሀብት በላጭ ናትና ላብ አደርን በዙልም በመዞለም ጀነት ተነፍጎ አሏህ ከሚጻረረን አሏህን ፈርተን የላብ አደሩን ሐቅ መስጠት ትሩፋት አለው። ዲኒል ኢሥላም የሚያስከብረው ላብ አደርን እንጂ የላብ አደር ቀንን አይደለምና ላብ አደርን እናክብር! አምላካችን አሏህ የሰዎችን ሐቅ ከሚጠብቁ ባሮቹ ያድርገን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Show all...
ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

ወንድም ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!

👍 1
"ቱርኪ ደቡብ አፍሪካ በእስራኤል ላይ በICJ ላይ ባቀረበችው የዘር ማጥፋት ወንጀል ክስ ለመቀላቀል መወሰኗ ተገለፀ ።" … ቱርኪ እስራኤል በፍልስጤም ጋዛ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽማለች በሚል በአለም አቀፍ ፍርድ ቤት ደቡብ አፍሪካ ባቀረበችው ክስ ላይ አጋር እንደምትሆን የቱርኪዬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሃካን ፊዳን ተናግረዋል ። … እ.ኤ.አ. በ2023 መገባደጃ ላይ የቀረበው የICJ ጉዳይ ቴል አቪቭ የዘር ማጥፋት ተግባሯን እንድታቆም እና ለችግረኛው ሰብአዊ እርዳታ መሰጠቱን ለማረጋገጥ እርምጃዎችን እንድትወስድ በጥር ወር ጊዜያዊ ብይን ቢያስተላልፍም እስራኤል አሁንም ተግባራዊ ለማድረግ ፍቃደኛ አልሆነችም። … ኒካራጓ እና ኮሎምቢያ በተመሳሳይ የዘር ማጥፋት ክሱን  ለመቀላቀል ሙከራ ቢያደርጉም ፣ ነገር ግን አለም አቀፉ  ፍርድ ቤት እስካሁን በጥያቄያቸው ላይ ውሳኔ አልሰጠም። … እስራኤል በፍልስጤም ጋዛ ላይ ጭካኔ የተሞላበት ወረራ ከፈጸመች በኋላ ከ34,500 በላይ ፍልስጤማውያን ተገድለዋል፣ አብዛኛዎቹ ሴቶች እና ህጻናት መሆናቸውም ተገልጿል። ©ሀሩን ሚድያ
Show all...
🌿🌹🌿 “አላህ (ሠ.ወ) እንደሚያስፈልግህ ስትዘነጋ፣ ያ አላህ እርዳኝ ብለህ እርሱን እንድትጠራ የሚያደርግ ሁኔታ ውስጥ ያስገባሃል። ያ ደግሞ ለራስህ ጥቅም ነው" ዑመር ሱሌይማን
Show all...
👍 4
♻️ይቅርታ መጠየቅ ማለት ሁልጊዜ ጠፋተኛ ነን ማለት አይደለም ፣ ነገር ግን አንዳንዴ ከዛ ሰው ጋር ያለንን ግኑኝነት እናከብረዋለን ትልቅ ቦታ እንሰጠዋለን ማለት ነው ፣ ♻️አቡ ሀቲም አንዲህ ብሏል ፡ይቅርታ መጠየቅ ጭንቀትን ያነሳል ፣ሀዘንን ያስወግዳል ፣ ቂምን ይከላከላል (ረውደቱል ኡቀላ) ♻️ይቅርታ መጠየቅ ማለት የመልካም አሰተዳደግ መገለጫ እንጂ መዋረድ  አይደለም ፣ ♻️ይቅርታ መጠየቅ ማለት ወደ ሰዎች ልብ የመግቢያ ድልድይ ነው ፣ ♻️ ይቅርታ መጠየቅ መሀይሞች ዘንድ ሽንፈት ፣ አዋቂዎች ዘንድ ደግሞ ድል ነው ♻️ስህተት ግን ሲደጋገም ይቅርታ ፊዝ ይሆናል
Show all...
👍 9
🌹ሐዘንና ደስታ የማይነጣጠሉ ነገሮች ናቸው፡፡ ሁለቱም አብረው ይመጣሉ፡፡ ነገር ግን አንዱ ብቻውን ከጎንህ ሲሆን አንደኛው መኝታ ቤትህ እንደተጋደመ አትርሳ፡፡✨
Show all...
👍 6😁 1
👳‍♂ሼሁ በዳንስ ቤት ክፍል-ስድስት ~ ግን ሼሁ ይሄን ሁሉ የስድብ ውርጅብኝ እና የጠርሙስ ውርወራ ከቁብ ሳይቆጥሩ የተሰበሰበውን ህዝብ ከመጤፍ ሳያስቡ ንግግራቸውን ቀጠሉ:: ሰው ግን ጫጫታውን ስድቡን አሁንም አላቆመም፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ አሿፊዎችና ረባሾች መድከም ሲጀመሩ፡፡ ቀስ በቀስ መድረኩ ፀጥ አለ፡፡ በዚህ ዳንስ ቤት ውስጥ ሼሁን የሚያውቋቸው አንዳንድ ሰዎች ስለነበሩ በየአቅጣጫው እባካችሁ ፀጥ በሉ ሼሁ ምን እንደፈለጉ እስቲ እንስማ የሚሉ ድምፆች እየተበራከቱ መጡና፡፡ ዝምታ በመስፈኑ ሼሁ ተደስተው እላህን አመሰገኑ፡፡ ~ ቀስ በቀስም የአድማጩን ጆሮ መሳብ ጀመሩ፡፡ በጆሮአቸው አድርገው ሼሁ ወደ ልባቸው መስረፅ ያዙ፡፡ ሰዎችም ማድመጣቸውን ቀጠሉ፡፡ ከዚያም መረጋጋት ያዙ፡፡ ህዝቡም ፍርሃት ፍርሃት ይለው ጀመር፤ አንገታቸውንም ደፉ፡፡ ወደ ሼሁ በሙሉ ልባቸው ተጠጉ ከዛች ከሚወዷት በልባቸው ካዘሏት አሸብሻቢ ምትክ የሼሁ ቃላት አሸብሻቢዋን ከልባቸው ውስጥ እየገፉ አስወጧት፡፡ የሼሁ ፍቅር በምትኩ በልባቸው መግባት ጀመረ፡፡ ~ የሷ ፍቅር የስሜትና የአዘቅት ነበር፡፡ሼሁ ፍቅር ግን ንፁህና የተቀደሰ ስለነበር የሷን ፍቅር ገረሰሶ ከልባቸው ውስጥ በማውጣት ካርንቋ ውስጥ እንዳይመለስ አድርጎ ዘፈቀው፡፡ ~ ሼሁ ንግግራቸውን ጨርሰው ለመሄድ ሲነሱ ሰዎችም ዳንስ ቤቱን ለባለቤቱና ለሸይጧን ጥለው ሼሁን ተከትለው ወጡ:: ከዛች እለት ጀምሮ እኔም ከሼሆቹ ተለይቼ አላውቅም፡፡ እዛም የነበሩ ሰዎች አብዛኞቹ ዛሬም ድረስ ከሼሆቹ ተለይተው አያውቁም" አለኝ። ~ "ግን አንተ " "ያን ጊዜ ሼሁ ምን ብለው እንደተናገሩ ትንሽ እንኳ አልያዝክም?” አልኩት:: "እሀ" አለ፡፡ “ምነው?” አልኩት፡፡ "እሳቸው የተናገሩት ንግግር እኮ በጣም በጣም ትልቅ ንግግር ነው፡፡ ልክ ከሰማይ የሚወርድ ንግግር ነበር የሚመስለው:: ~ በአጠቃላይ ሼሁ የሚናገሩት ንግግር በልባችን ላይ እንደውሃ ነበር የተንቆረቆረው። በጠጣነው ቁጥር ጣዕሙ የሚያረካ ዝም ባሉ ቁጥር ጨምሩኝ ጨምሩኘ የሚያሰኝ ንግግር ነበር። ሼሁ በተናገሩ ቁጥር የርኩስ መንፈስ ከውስጣችን እየወጣ ቅዱስ መንፈስ ሲሰርፅብን ይታወቀንና ወደ ንጹህ አየር፤ ወደ አላህ ፍቅር፣ ወደ ጀነት በር፤ ወደዕካታ እና ወደ ዕውነተኛ ደስታ ይዞን ሲበር ይታየን ነበር፡፡" አለኝ:: ከዚያስ በኋላ ሸሁ ምን አሉ ነው የምትለው?” አልኩት፡፡ ክፍል 7 ይቀጥላል...ኢንሻአላህ (ማስታወሻ:- ሸሁ በዳንስ ቤት የተሰኘው ይህ የትርጉም መፅሀፍ በሸኽ አልጠንጣዊ የተፃፈ ሲሆን በ ሀሚድ ጣሂር በአማርኛ ተተርጉሞ 2002 ላይ ነበር ለአንባቢያን የደረሰው። በዚህ አጋጣሚ ፀሀፊውን እና ተርጓሚውን ከልብ እናመሠግናለን ጀዛኩሙሏሁ ኸይረን!) like👍 comment 💬 share @ISLAMIKA_BORN_MUSLIM789
Show all...
👍 6
የፍልስጥኤም ተቀናቃኝ ቡድኖች ሃማስ እና ፋታህ በቤጂንግ ለውይይት መገናኘታቸውን ቻይና አስታወቀች የፍልስጤም ተቀናቃኝ ቡድኖች የሆኑት በቅርቡ በቻይና ዋና ከተማ ተገናኝተው "በፍልስጤም ውስጥ ዕርቅን ለማምጣት ጥልቅ እና ግልጽ ንግግሮች" ማድረጋቸውን የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሊን ጂያን ተናግረዋል። የፍልስጤም ብሔራዊ ነፃ አውጪ ንቅናቄ ሃማስ እና የፋታህ ተወካዮች በቅርቡ በቤጂንግ ከተማ መጥተው ነበር ሲሉ በመግለፅ በውይይቶች ላይ “አዎንታዊ መሻሻሎች” ታይተዋል ብለዋል። ቻይና እና ፍልስጤም ጥንታዊ ጓደኝነት አላቸው ሲሉ ተደምጠዋል። የፍልስጤም አንጃዎችን እርቅን ለማምጣት እና በመነጋገር እና በመመካከር አብሮነትን ለማሳደግ እንደግፋለን፤ ለዚያም በትጋት መስራታችንን እንቀጥላለን ”ሲሉ ጂያን ተናግረዋል። በሌላ በኩል ወንጀልን ማስቆም ለጋስነት አይደለም ሲል ሃማስ አስታውቋል። ሃማስ ይህንን የተናገረው የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ዋና ፀሀፊ አንቶኒ ብሊንከን በጋዛ ግንባር እና በቀጠናው ስላለው ጦርነት ውይይት ለማድረግ ወደ ዮርዳኖስ ከዚያም ወደ እስራኤል እያቀኑ መሆናቸውን ተከትሎ ነው። ብሊንከን ባለፈው ሰኞ እንደተናገሩት የቅርብ ጊዜው የእስራኤል የተኩስ አቁም ሀሳብ “በጣም ለጋስ” የሆነ ቀረቤታ ነው እናም ሃማስ “በፍጥነት” ሊቀበለው ይገባል ብለዋል። ነገር ግን የሃማስ ባለስልጣን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የፍልስጤም ሲቪሎችን በተለይም ህጻናትን እና ሴቶችን የገደሉ ጥቃቶችን በማስቆም ሂደት ውስጥ ምንም ለጋስነት የለም ብለዋል ። የሐማሱ ኦሳማ ሃምዳን እንደተናገረው ጥቃቱ እራሱ ወንጀል ነው ስለዚህ ወንጀልን ስታቆም ከእስራኤል ወገን ለጋስ የሆነ ድርጊት ነው ልትል አትችልም ሲሉ ተደምጧል። © ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 6🕊 5
አትፍረድ አንድ የ24 አመት ወጣት በባቡር እየሄደ በድንገት በመስኮት ወደ ውጭ አይቶ በሀይል ጮኸ... "አባዬ, ተመልከት ዛፎቹ ከኋላችን ይከተሉናል!"አለ አባቱም ፈገግ አለ በአቅራቢያቸው የተቀመጡት ጥንዶችም የ24 ዓመቱን ወጣት የልጅነት ባህሪ በአዘኔታ በመመለከት ላይ ሳሉ በድንገት እንደገና ጮኸ... "አባዬ ፣ ደመናው ከእኛ ጋር እየሮጠ ነው!"አለ ጥንዶቹ ይሄኔ ዝም ብለው መመልከት አልቻሉም ፈጠን ብለው አዛውንቱን... "ለምንድነው ልጅህን ጥሩ ዶክተር ጋር የማትወስደው አሉት?" አዛውንቱም ፈገግ ብለው... "ሆስፒታል ወስጄው ከሆስፒታል እየመጣን ነው ልጄ ከተወለደ ጀምሮ ዓይነ ስውር ነበር ዛሬ ነው የአይኑን ብርሀን ያገኘው." ሁሉን ቻይ የሆነው የአላህ ስጦታዎች በመጠን የማይገለፁ በብር የማይተመኑ ናቸው፣ ችግሩ እኛ ስናጣው ነው ሚገባን فَبِأَيِّ ألاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ © Islamic_Short_Stories
Show all...
👍 12👌 2
ከመጥፎ ሚስትና ከመጥፎ ጎረቤት በአላህ ተጠበቅ።
Show all...