cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking ÂŤAccept allÂť, you agree to the use of cookies.

avatar

𝙥𝙤𝙨𝙞𝙩𝙞𝙫𝙚 𝙫𝙞𝙗𝙚𝙨

𝙬𝙚𝙡𝙘𝙤𝙢𝙚 𝙡𝙖𝙙𝙞𝙚𝙨 & 𝙜𝙚𝙣𝙩𝙡𝙚𝙢𝙚𝙣 #በዚህ_#channel_#አንብቤ_#ደስ_#ካሉኝ_#ውስጥ_#ለእናንተ_#ለማጋራት_#የከፈትኩት_#channel_#ነው & also u will get #wallpapers #beautiful_profile_pictures #motivational_qoutes #stay_positive

Show more
Advertising posts
245Subscribers
No data24 hours
-37 days
+330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ስሌቱ በእጃችሁ ነው! አንድ ሰው እንዳለው፣ “ሕይወታችን 10 በመቶው የሆነብን ነገር ውጤት፣ 90 በመቶው ደግሞ ለዚያ የሰጠነው ምላሽና ዝንባሌያችን ውጤት” መሆኑን አትዘንጉ፡፡ የሚሆንባችሁና የሚሆንላችሁ ነገር ላይ ብቻ ከመጠመድ አእምሯችሁን ትንሽ ፈታ አድርጉትና ለመጥፎውም ሆነ ለጥሩው ሁኔታዎች የምትሰጡት ምላሽ ትክክለኛና ጥበብ የተሞላው እንዲሆን ራሳችሁ ላይ ለመስራት ሞከሩ፡፡  Dr Eyob
Show all...
👍 4
አንድ ወጣት ወታደር ወደ አንድ የተከበረ የጦር ጀነራል  ቤት ይሄዳል :: የጀነራሉ  ቤት ውስጥ ብዙ ዋንጫዎችና ሜዳሊያዎችን ይመለከታል :: ወጣቱም  ጀነራሉን ‘’እንዴት ይሄን ሁሉ ዋንጫዎችና ሜዳሊያዎች ልታገኝ ቻልክ?’’ ብሎ ይጠይቀዋል :: ጀነራሉም ‘’1 ትእዛዝ አዝሃለሁ፣ ያዘዝኩክህን ትእዛዝ ከፈፀምክ የስኬቴን ምስጢር እነግርሃለሁ።’’ ብሎ ይመልሳል።  ወጣቱም  ተስማማ :: ጀነራሉ በብርጭቆ ውሀ ሞልቶ ሰጠውና ‘’ምንም አይነት  የውሃ ጠብታ ጠብ ሳታደርግ  ይህን ተራራ ዞረህ ተመለስ። ውሃው ፈሶ ብርጭቆው ከጎደለ እርምጃ እወስድብሃለሁ። ‘’  አለውና እስከ ጫፍ በውሃ የተሞላውን ብርጭቆ ሰጠው :: ልጁም የተሰጠውን ትእዛዝ ተቀብሎ  እንደተባለው ምንም አይነት ውሃ ሳይንጠባጠብበት ተራራውን ዞሮ መጣ :: ጀነራሉም ትእዛዙ ተፈፅሞ መመለሱን አይቶ ጥያቄ ጠየቀው። ‘’መንገድ ላይ ስትሄድ የሚጣሉ ልጆች ነበሩ።  አይተሀል?’’  አለው።  ልጁም ‘’አላየሁም’’ አለ :: አሁንም ጠየቀው።  ‘’ብዙ ቆነጃጅት  ሴቶች በመንገድህ ላይ ነበሩ።  አይተሀቸዋል? አለው።  ልጁም መልሱ ‘’ አላየሁም’’ የሚል ነበር።  ጀነራሉ ጥያቄውን ቀጠለ።   ‘’በመንገድህ ላይ  ወጣቶች  ሲሰድቡህና ድንጋይ ሲወረውሩብህ ነበር። አይተሀቸዋል?’’  አለው። አሁንም ‘’አላየሁም’’ አለ :: ጀነራሉም እንዲህ አለው:- “አየህ!  እኔም ለዚህ  ክብር የበቃሁት፤ ማንም ሲጠራኝ፣ ሲሰድበኝ፣ ጉዞዬን ሊያስተጓጉል ሲሞክር፣ ወዘተ..  ዞር ብዬ ባለማየቴ ነው። ትኩረቴ  አላማዬን ማሳካት ላይ ብቻ ነበር።’’ በማለት መለሰለት።  የምንፈልገው ነገር ላይ ስናተኩር፣ የማያሳፈልጉን ነገሮች ቦታ አይኖራቸውም!!!
Show all...
👍 5
ራስን ፍለጋ (ጥያቄ ሁለት) የመኖሬ ትርጉም ምንድን ነው? ስለመወለዴና በዚህች አለም ላይ ስለመኖሬ በሚገባ አስቤ ምክንያቱን እስከማገኝ  ድረስ ራሴን ማግኘት አልችልም፡፡ አሁን ያለሁበት ቦታና ሁኔታ ላይ ያለሁት ለምንድን ነው? ለምንድነው የተወለድኩት? ምን አይነት መልካም መዋጮ ለማድረግ ነው እዚህ ምድር ላይ ያለሁት? ከሌሎች ሰዎች ለየት የሚያደርገኝ ነገር ምንድን ነው? ከመውሰድና ከመቀበል ባሻገር ለመስጠትና የሌሎችን ጉድለት ለመሙላት እየኖርኩኝ ነው? ከላይ የተጠቀሱትንና መሰል፣ የመኖርህን ትርጉም እንድታስብ የሚመሩህን ጥያቄዎች ስትጠይቅ ሁሉም ነገር ወዲያውኑ ፍንትው ብሎ በርቶልህ በቶሎ መልስን ማግኘት አለመቻልህ አያስገርመኝም፡፡ ምክንያቱም አብዛኛዎቻችን ተቃኝተን ያደግነው በደመ-ነፍስ ወጥቶ በሚገባ ሕብረተሰብ መካከል ስለሆነ ነው፡፡ ሲነጋ ወጥቶ ሲመሽ ወደቤቱ ከሚመለስ መንጋ የምንሻለው ለምን እንደምንወጣ በሚገባ ወደማወቅ ስንመጣና ማታ ስንገባ ደግሞ የወጣንበትን አላማ በትክክል ግቡን መምታቱን ማሰብ ስንጀምር ነው፡፡ አለዚያ ከመብላትና ከመጠጣት፣ ከመገናኘትና ከመለያየት፣ ከመንጠቅና ከመነጠቅ፣ ከማደንና ከመታደን ያላለፈና ከሌሎቹ ፍጥረታት ያልተለየ ሕይወት ውስጥ ነው ያለነው ማለት ነው፡፡ ራሱን ፈልጎ ለማግኘት የተዘጋጀ ሰው የመኖሩን ትርጉም ለማግኘት ጥያቄን የሚጠይቅ ሰው ነው፡፡ አየህ፣ የመኖርህን ትርጉም ስታገኘው ራስህን የማግኘትን ጎዳና ትጀምራለህ፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ከሚሆንልህ ታምረኛ ነገር አንዱ እርካታህንና ለመኖር ያለህንን ጉጉት “ይህና ያኛው ነገር ቢኖረኝ ኖሮ” ከሚለው ነገር ጋር ማገኛኘትን ታቆምና ባገኘኸው ማንነትህና ልዩ በመሆንህ ተጠምደህ ወደፊት ማየትና መኖር ትጀምራለህ፡፡ ዛሬ ለጊዜው ያለህንና የሌለህን ቁሳቁስ መቁጠር አቁምና ለመኖርህ ትርጉም የሚሰጡህን ነገሮች ማሰብ ጀምር፡፡ ከቻልክ ትናንትና እንደተነጋገርነው የየቀን ማስታወሻ (Diary) ሁለተኛው ገጽ ላይ የመኖህን ትርጉም አስመልክቶ ስታስብ የመጣልህን ሃሳብ ለመጻፍ ሞክር፡፡ ይቀጥላል . . . Dr eyob
Show all...
👍 2
ራስን ፍለጋ (ጥያቄ ሁለት) የመኖሬ ትርጉም ምንድን ነው? ስለመወለዴና በዚህች አለም ላይ ስለመኖሬ በሚገባ አስቤ ምክንያቱን እስከማገኝ  ድረስ ራሴን ማግኘት አልችልም፡፡ አሁን ያለሁበት ቦታና ሁኔታ ላይ ያለሁት ለምንድን ነው? ለምንድነው የተወለድኩት? ምን አይነት መልካም መዋጮ ለማድረግ ነው እዚህ ምድር ላይ ያለሁት? ከሌሎች ሰዎች ለየት የሚያደርገኝ ነገር ምንድን ነው? ከመውሰድና ከመቀበል ባሻገር ለመስጠትና የሌሎችን ጉድለት ለመሙላት እየኖርኩኝ ነው? ከላይ የተጠቀሱትንና መሰል፣ የመኖርህን ትርጉም እንድታስብ የሚመሩህን ጥያቄዎች ስትጠይቅ ሁሉም ነገር ወዲያውኑ ፍንትው ብሎ በርቶልህ በቶሎ መልስን ማግኘት አለመቻልህ አያስገርመኝም፡፡ ምክንያቱም አብዛኛዎቻችን ተቃኝተን ያደግነው በደመ-ነፍስ ወጥቶ በሚገባ ሕብረተሰብ መካከል ስለሆነ ነው፡፡ ሲነጋ ወጥቶ ሲመሽ ወደቤቱ ከሚመለስ መንጋ የምንሻለው ለምን እንደምንወጣ በሚገባ ወደማወቅ ስንመጣና ማታ ስንገባ ደግሞ የወጣንበትን አላማ በትክክል ግቡን መምታቱን ማሰብ ስንጀምር ነው፡፡ አለዚያ ከመብላትና ከመጠጣት፣ ከመገናኘትና ከመለያየት፣ ከመንጠቅና ከመነጠቅ፣ ከማደንና ከመታደን ያላለፈና ከሌሎቹ ፍጥረታት ያልተለየ ሕይወት ውስጥ ነው ያለነው ማለት ነው፡፡ ራሱን ፈልጎ ለማግኘት የተዘጋጀ ሰው የመኖሩን ትርጉም ለማግኘት ጥያቄን የሚጠይቅ ሰው ነው፡፡ አየህ፣ የመኖርህን ትርጉም ስታገኘው ራስህን የማግኘትን ጎዳና ትጀምራለህ፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ከሚሆንልህ ታምረኛ ነገር አንዱ እርካታህንና ለመኖር ያለህንን ጉጉት “ይህና ያኛው ነገር ቢኖረኝ ኖሮ” ከሚለው ነገር ጋር ማገኛኘትን ታቆምና ባገኘኸው ማንነትህና ልዩ በመሆንህ ተጠምደህ ወደፊት ማየትና መኖር ትጀምራለህ፡፡ ዛሬ ለጊዜው ያለህንና የሌለህን ቁሳቁስ መቁጠር አቁምና ለመኖርህ ትርጉም የሚሰጡህን ነገሮች ማሰብ ጀምር፡፡ ከቻልክ ትናንትና እንደተነጋገርነው የየቀን ማስታወሻ (Diary) ሁለተኛው ገጽ ላይ የመኖህን ትርጉም አስመልክቶ ስታስብ የመጣልህን ሃሳብ ለመጻፍ ሞክር፡፡ ይቀጥላል . . .
Show all...
Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

ሕይወትን አትሸራርፏት! “በአንድ ነገር ስኬት አገኘን ማለት የሁሉ ነገር መጨረሻው አይደለም፤ አልተሳካልንም ማለትም የነገሩ ማብቂያ አይደለም፡፡ ዋናው ነገር ለመቀጠል ያለን ቆራጥነት ነው” - Winston Churchill ሕይወትን አትሸራርፏት፡፡ ሕይወትን የምትሸራርፏት አንዱ ቀን ጥሩ ነው፣ ሌላኛው ቀን ደግሞ መጥፎ ነው በማለት ደስታችሁን በዚያ ላይ ስትመሰርቱና አንዱን ቀን በደስታ ስትኖሩትና፣ ሌላኛውን ቀን ደግሞ በስሜት ቀውስ ጭጋግ ውስጥ ሆናችሁ በከንቱ ስታሳልፉት ነው፡፡ ሕይወትን ሳትኖሯት አታምልጣችሁ፡፡ ሕይወትን ሳትኖሯት የምታመልጣችሁ “ትክክለኛው” ቀን እስከሚመጣ ድረስ ሕይወታችሁ ሙሉ እንዳልሆነና እንዳልተሳካላችሁ ስታስቡ ነው፡፡ በሕይወታችሁ የምትከታተሏቸውን ነገሮች ስላገኛችሁ ብቻ “ተሳካልኝ” ብላችሁ እዚያ ጋር ከቆማችሁ ተሳስታችኋል፡፡ ሁል ጊዜ አሁን ከደረሳችሁበት የተሻለ ነገር እንዳለ በማሰብ ወደዚያ ወደላቀው ለመዝለቅ መነሳሳት ይገባችኋል፡፡ ያንን ለማድረግ ደግሞ ቆራጥነትን ይጠይቃል፡፡ በተቃራኒው፣ አንድን በብርቱ ስትፈልጉት የነበረውን ነገር ባለማግኘታችሁ ምክንያት የተሰማችሁን የውድቀት ስሜት የመጨረሻው እጣ ፈንታችሁ እንደሆነ አምናችሁ ከተቀበላችሁ አሁንም ተሳስታችኋል፡፡ ካልተሳካው፣ ካልሆነውና ከተሰናከለው ሁኔታ አልፋችሁ ለመሄድ የቆረጠ ማንነት ማዳበር ይጠበቅባችኋል፡፡ በሌላ አባባል፣ አንድን ስኬት ማስመዝገብ የታሪኩ መጨረሻ አይደለም፤ አሁን ከደረስንበት ስኬት የላቀ ሌላ ደረጃ አለና፡፡ እንዲሁም ውድቀትን ወይም አለመሳካትን መቅመስ የመጨረሻው አይደለም፤ ከማንኛውም ውድቀት በኋላ የጠነከረ ማንነት የማዳበርና እንደገና የመጀመር እድል አለና፡፡ ይህንን አመለካከት ለማዳበር በቅድሚያ ሕይወት በብዙ ውጣውረዶች ያሸበረቀችና ውብ የሆነች መስክ የመሆንዋን እውነታ አምኖ መቀበል የግድ ነው፡፡ Dr eyob
Show all...
👍 2
ራስን ፍለጋ (ጥያቄ አንድ) ማን ነኝ? ይህንን ጥያቄ ከተወለድክበት እለት አንስቶ ካሳለፍካቸው ሁኔታዎችና ታሪኮች በመነሳት ምን ወደመሆን እንደመጣህ ራስህን ለመመልከት ተጠቀምበት፡፡ አወላለድህ፣ አስተዳደግህ፣ ኖሮህና ሳይኖርህ ያደከው፣ ተደርጎልህና ተደርጎብህ ያደከው . . . ተደምሮ ምን ወደመሆን እንደመጣህ ይሰማሃል? ይህንን መለስ ብሎ የራስን ማንነት የመጠየቅና የመገምገም ሂደት በፍጹም እውነተኛነትና ድፍረት ልታደርገው ይገባሃል፡፡ እውነተኛነት የሚያስፈልገው አንዳንድ ማሰብ የማንፈልጋቸው ሁኔታዎች ሊኖሩ ስለሚችሉና በክህደት አለም ውስጥ የመደበቅ ፈተና ውስጥ ልንገባ ስለምንችል ነው፡፡ ድፍረት የሚጠይቀው ደግሞ አንዳንድ ታሪኮቻችንና አሁን ያለንባቸው ሁኔታዎች ስናስባቸው አቅም አሳጪ ሊሆኑ ስለሚችሉ ያንን ለመጋፈጥ ራስን የመሞገት ቁርጠኝነት ስለሚጠይቁ ነው፡፡ ማንኛውም ሰው ቢሆን ሁለንተናውን ተጋፍጦና ከታሪኩ ጋር ተፋጦ፣ እውነቱን አውጥቶና አውርዶ፣ “አሁን የሆንኩትን የሆንኩት ከእነዚህ ሁኔታዎች የተነሳ ነው” በማለት ማሰብ እስከሚጀምር ድረስ መስመር የያዘ የወደፊት አቅጣጫ ውስጥ መግባት ያስቸግረዋል፡፡ የሚያስፈሩኝ ነገሮች የሚያስፈሩኝ ለምንድ ነው? - ማሰብ የማልፈልጋቸው ምእራፎቼን ማሰብ የማልፈልገው ለምንድነው? - ከየትኛው ጤናማ ታሪኬ የተነሳ ነው አሁን ያለኝ መልካም ነገር የበቀለው? - ከየትኛውስ አስቸጋሪ ታሪኬ የተነሳ ነው አሁን ያለኝ ቀውስ የተከሰተው? - ዝንባሌዬዎቼና ልገነባባቸው የምችላቸው ጠንካራ ጎኖቼ ምን ምን ናቸው? - ላርማቸው፣ ላስተካክላቸውና ልቀርፋቸው እንደሚገባኝ የማስባቸው ደካማ ጎኖቼ ምን ምን ናቸው? - ከእነዚህ ልምምዶቼና ታሪኮቼ ውስጥ ተደብቆ ያለውን እውነተኛ ማንነቴን እንዴት ፈልፍዬ ላወጣው እችላለሁ? - ከላይ ካነበብኳቸውና ከመሰል ሂደቶች አንጻር እኔ ማን ነኝ? እስቲ ይህንን ጥያቄ ቀኑን ውለህ ሌሊቱን እደርበትና፡፡ ከቻልክ የየቀን ማስታወሻ (Diary) ለመጻፍ ሞክር፡፡ ይቀጥላል . . . Dr eyob
Show all...
የመኖራችሁና ያለመኖራችሁ ጉዳይ በአንድ ቦታ ወይም ግንኙነት ውስጥ አለመኖራች የሚያጎድለው ነገር ከሌለ፣ መኖራች የሚሞላው ነገር የለም ማለት ነው፡፡ በተቃራኒ ደግሞ በአንድ ቦታ ወይም ግንኙነት ውስጥ መኖራችሁ የሚሞላው ነገር ካለ፣ አለመኖራች የሚያጎድለው ነገር አለ ማለት ነው፡፡ ይህንን ለማወቅ ከፈለካችሁ ደግሞ ሁለት ጥያቄዎችን ጠይቅ፡- 1) መኖሬን የሚያደንቁ ሰዎችና ቦታዎች የትኞቹ ናቸው? 2) አለመኖሬ ምንም እንዳላጎደለባቸው የሚያሳዩኝ ሰዎችና ቦታዎችስ የትኞቹ ናቸው? በሕይወታችሁ እንደቀፈፋችሁ፣ የውስጥ አቅም እንዳጣችሁና ሰላማችሁ እንደተረበሸ እንድትኖሩ ከሚያደርጉህ ልምምዶች መካከል አንዱ ብትኖሩም የማትደነቁበት፣ ባትኖሩ ደግሞ የማትናፈቁበት አካባቢ በግድ የመገኘት ጉዳይ ነው፡፡ ይህንን ልምምድ በሚሰጣችሁ አካባቢ ወይም ጓደኝነት ውስጥ መቆየት በማንነታችሁ ላይ ይህ ነው የማይባል የራስ-በራስ ንቀትን ከማስከተሉም በተጨማሪ ራሳችሁን በመናቅ ሌሎች እንዲንቋችሁና እንዲቆጣጠሯችሁ ፈቃድ እንድትሰጧቸው መንገድን ይጠርጋል፡፡ መኖራችሁ የሚሞላው ነገር፣ አለመኖራችሁ ደግሞ የሚያጎድለው ነገር እንዳለ በማመን በብርቱ የሚፈልጓችሁ ሰዎች እያሉ፣ ብትኖሩም ሆነ ባትኖሩ ምንም የምትሞሉትም ሆነ የምታጎድሉት ነገር እንደሌለ ከሚያስቡና ያንንም ከሚያሳዩህ ሰዎች አካባቢ ጊዜያችሁን አታባክኑ፡፡ በዚህ ምድር ላይ ሁል ጊዜ ተለጣፊ፣ ተንጠልጣይ፣ ለማኝና ተለማማጭ ሆናችሁ ለመኖር አልተፈጠራችሁም፡፡ የራሳችሁ ስፍራ ያላችሁ ሰዎች ናችሁ፡፡ የምትወደዱበት፣ የምትደነቁበትና የምትፈለጉበት ቦታ ያላችሁ ሰዎች ናችሁ፡፡ ዛሬ ከእናንተ ጋር ምንም ግንኙነት ባለማድረግ ውስጥ ምቾት ከሚሰጣቸው ሰዎች ጋር ያላችሁን ግንኙነት እንደገና የምትፈትሹበት ቀን ይሁንላችሁ! ዛሬ መኖራችሁ የማያጓጓቸው፣ አለመኖራችሁ ደግሞ የማይናፍቃቸው ሰዎች ጉዳይ ይታሰብበት! ያን ጊዜ ለራሳችሁ ያላችሁን ክብር ትመልሳላችሁ፡፡ ያን ጊዜ ሰውን መለማመጥ አቁማችሁ ቀና ብላችሁ ከዓላማችሁ አንጻር መኖር ትጀምራላችሁ፡፡ Dr eyob
Show all...
👌 1
📚የሐዘን ምክንያት አትሁን ያለፍክበት የሕይወት መንገድ አስሮ ሊይዝህ አይገባም፤ ነገህን መወሰን የራሳህ ምርጫ ነው፡፡ በሕይወትህ የደስታ ምንጭ መሆን ባትችል እንኳን ለሌሎች የሐዘን ምክንያት አትሁን፡፡ ዝምታ፣ በውስጡ ትልቅ ጩኸት የያዘ የማይጠየቅ ጠያቂ፣ የማይመረመር መርማሪ ነውና ከዙሪያህ ካለ የሰዎች ጫጫታ በላይ የውስጥ ዝምታህን አድምጥ፡፡ በምድር ላይ ምንም ፍጹም ነገር የለምና አንተም ፍጹም ለመሆን አትሞክር ሰዎችም ፍጹም እንዲሆኑ አትጠብቅ ነገር ግን ሁሉን በመልካምነትና በቅን ልቦና አከናውን፡፡ ያለህን ችሎታ፣ አቅም፣ ዕውቀት አንተ ካላከበርከውና ካላወጣኸው ማንም መጥቶ ሊያከብርህና ሊያወጣልህ አይችልም፡፡ ስለዚህ ከተቀምጥክበት ተነሳና ከምኞት ወጥተህ ወደ ተግባር ተሻገር፡፡ በሕይወትህ ትልቅ መከራ፣ ችግር፣ ሀዘን ደርሶ ሊሆን ይችላል፤ "ሰው እንዴት በዚህ ውስጥ ያልፋል" ብለህ አዝነህ፣ ተክዘህ ሊሆንም ይችላል፡፡ በሕይወት ዘመን መዘንጋት የሌለብህ ነገር ቢኖር ተስፋ የሚባል ነገር መኖሩን ነው፡፡  
Show all...
👌 2
"እድሎች" ⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️ ስንጠቀማቸው ሀብቶች ስናባክናቸው ቁጭቶች ይሆናሉ። 💥💥💥💥💥 ሰላም እድል ነው ጤና እድል ነው ሰው እድል ነው ጊዜ እድል ነው አለመመቸት እድል ነው 🌠💸✈️🚘💰 ችግር ለጠየቅነው እድል መንገድ ነው። 🔥🔥🔥🔥 አሁን እድል ነው አሁን አሁን ነው ለእድልህ ማቀድ መዘጋጀት ነው ወደ ተግባር መግባት የመሻት መገለጫ ነው መፅናት የማመን ማሳያ ነው መጨበጥ ውጤት ነው 💸💸💸💸💸 ውጤት የትናንት ውሳኔ ማሳያ ነው። ትናንት አሁን ነበር ትናንት ካልወሰንክ አሁን ወስን አሁን ካልወሰንክ አሁን ትናንት ሲሆን ቁጭት ታጭዳለህ። 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 አሁን ስትወስን ነገህ በፈለግከው ውጤት ይሞላል። 👏👏👏👏 መልካም አሁን መልካም ዛሬ መልካም ነገ 💥💥💥💥💥
Show all...
👌 3👎 1
ራሳችንን ከራሳችን የሚጋርዱ ነገሮች “ራስን ማግኘት” የሚለውን ሃሳብ ከፍልስፍና፣ ከኃይማኖትና ከመሳሰሉት አቅጣጫ መመልከት ይቻላል፡፡ ያንን የማድረጉን ነጻነት ለአንባቢዬ ተወት በማድረግ እዚህ ጋር ለጊዜው ተግባራዊው ገጽታ ላይ በመነጋገር እንቆያለን፡፡ 1. ራስን አለመቀበል ራስን መቀበል ማለት ዘሬን፣ መልኬን፣ ቁመናየን . . . እና የመሳሰሉትን ልቀይራቸው የማልችላቸውን የማንነቴ አካሎች በመቀበል መደላደል ማለት ነው፡፡ እነዚህን ነገሮች ሲታገሉና ሲሸፋፍኑ መኖር ከዋናው ነገር ወደኋላ ይስቀረናል፡ 2. ባለፈው ታሪክ መቆለፍ ያለፈ ታሪክ ማለት ከዛሬ በፊት የነበሩኝን ስኬቶችንና ስህተቶችን የሚያካትት ጉዳይ ነው፡፡ ስኬታማ ነበርኩ፣ ምንም አያስፈልገኝም ካልን፣ እንዲሁም ደግሞ ስህተተኛ ነበርኩ ስለዚህም ለምንም ነገር አልበቃም ብለን ካሰብን ራስን የማግኘት ትክክለኛ እያታችን ይጋረዳል፡፡ 3. ራስን ከሌሎች ጋር ማወዳደር ራስን ከሌሎች ጋር ማወዳደር ማለት ማንነቴን፣ ዓላማዬንና ስኬታማነቴን ሌሎች አቻዎቼ ሆነዋል፣ ደርሰውበታል ብዬ ከማስበው አንጻር መገምገም ማለት ነው፡፡ ይህ ዝንባሌ የራሴ ደረጃና ግብ እንዳይኖረኝ ያግደኛል፡፡    4. የተዛባ የስኬት ልኬት ስኬት ማለት ማንነትን ማወቅና መቀበል፣ ዓላማን መለየትና ለዚያ መኖር፣ ያለንን ነገር ማሳደግና ለሕብረተሰቡ ጥቅም ማዋል ሆኖ ሳለ፣ ስኬትን ከገንዘብ፣ ከእውቀት፣ ከዝና፣ ከስልጣን . . . ጋር ብቻ ማዛመድ ከራስ ጋር የሚያፋታ እይታ ነው፡፡  5. ወቃሽነት ወቃሽነት ማለት በዙሪያችን ለሚሆነው ነገር ሁሉ የሚወቀስ ሰው መፈለግና ኃይለኛ አቋሞችን መያዝና ቃላቶችን መናገር ማለት ነው፡፡ ሰዎችን የመውቀስ ልመዳ የእኛን ሃላፊነት ከመወጣት ይልቅ ወደማሳበብ አዘቅት ውስጥ ያወርደናል፡፡ ከላይ ከተጠቀሱት እንቅፋቶች ራሳችሁን ያገኛችሁበት ነጥብ ላይ ለመስራትና ለማሻሻል ሞክሩ፡፡ . . . ይቀጥላል!
Show all...