cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ማለዳ ዜና MALEDA ZENA🇪🇹🌍

ለአዳዲስ ወቅታዊና እውነተኛ መረጃዎች ምርጫዎ ማለዳ ዜና ይሁን ሰብስክራይብ በማድረግ ይቀላቀሉ ለተጨማሪ መረጃዎች የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ እናመሠግናለን 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 http://www.youtube.com/c/ShimeMedia ለሃሳብ አስተያየት👉👇👇 @Group_assistant_free_move_bot ይጠቀሙ

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
179
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ዋልያዎቹ ጣፋጭ ሶስት ነጥብ አሳክተዋል ለኮቲዲቯሩ የአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ ከግብጽ ጋር እየተጫወተ ያለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታውን 2:0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። በማላዊ ሜዳ ሁለተኛ የምድብ ጨዋታቸውን ከግብጽ ጋር ያካሄዱት ዋልያዎቹ በዳዋ ሁቴሳ እና ሽመልስ በቀለ ጎሎች ማሸነፍ ችለዋል። ጎሎቹን ዳዋ ሁቴሳ 21ኛው ደቂቃ እና ሽመልስ በቀለ በ40ኛው ደቂቃ አስቆጥረዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታውን በማላዊ አቻው 2:1 በሆነ ውጤት መሸነፉ ይታወሳል። እንኳን ደስ አላችሁ፣ አለን💚💛❤️
Show all...
አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሾሙ ********************** አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ ከሰኔ 01 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው መሾማቸውን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አስታወቀ። አምባሳደሩ ሰኔ 01 ቀን 2014 ዓ.ም ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው እስከተሾሙበት ድረስ በአፍሪካ ኅብረት የኢትዮጵያ ቋሚ መልክተኛ ሆነው በማገልገል ላይ እንደነበሩ ተገልጿል። #EBC
Show all...
#AddisAbaba | የታሪፍ ማማሻያ ሊደረግ ነው። የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የሚዲ-ባስ እና ሚኒ-ባስ ተሸከርካሪዎች የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ ሊደረግ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል። በመዲናዋ ለህብረተሰቡ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የሚዲ-ባስና ሚኒ-ባስ ተሽከርካሪዎች #አዲስ_የትራንስፖርት_ታሪፍ ማሻሻያ ነገ እለተ ማክሰኞ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ለሚዲያ ተቋማት ይፋ ይደረጋል ተብሏል። የታሪፍ ማሻሻያው ከሰኔ 1 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ እንደሆነ ተገጿል። ህብረተሰቡ ከሰኔ 1 ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆነውን ትክክለኛ ታሪፍ አውቆ በመክፈልና ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉ አሽከርካሪዎችን በማጋለጥ በኩል ጥቆማ በመስጠት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ጥሪ አቅርቧል።
Show all...
#Update #ችሎት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እና ጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬ የ10 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ በፍርድ ቤት ተፈቀደላቸው። የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝና ሰለሞን ሹምዬ እያንዳንዳቸው የ10 ሺ ብር ዋስትና በማስያዝ ከእስር እንዲለቀቁ ትዕዛዝ ሰጠ። ፍርድ ቤቱ ፤ ፖሊስ በጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ እና በመስከረም አበራ ላይ እያደረገው ለሚገኘው ምርመራ ተጨማሪ ስድስት ቀናት ፈቅዷል። የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ትዕዛዙን ያስተላለፈው ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 30 ነው። ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር @tikvahethiopia
Show all...
“ሮሃ ሚዲያ” የተሰኘው የዩቲዩብ መገናኛ ብዙኃን መስራች እና ባለቤት መዓዛ መሐመድ በአስር ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንድትለቀቅ በፍርድ ቤት ተወሰነላት። የመዓዛን የዋስትና ጥያቄ ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 30 የፈቀደው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው። መዓዛ ከጓደኛዋ መኖሪያ ቤት በፖሊስ የተያዘችው ከአስር ቀናት በፊት ግንቦት 20፤ 2014 ነበር። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር) #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
#newsalert አሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሐመርን ለአፍሪካ ቀንድ አገራት አዲሱ ልዩ መልዕክተኛዋ አድርጎ መሾሟን አስታውቃለች። ይህንን ዛሬ በትዊተር ገጻቸው ይፋ ያደረጉት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን ናቸው። ማይክ ሐመር ላለፉት ስድስት ወራት በቀጠናው የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩትን አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድን ይተካሉ። አሜሪካ ከዓመት በፊት ለአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ከሾመች ወዲህ አምባሳደር ማይክ ከአምባሳደር ፉልትማን እና ከአምባሳደር ሳተርፊልድ ቀጥለው ሦስተኛው ልዩ መልዕክተኛ ይሆናሉ። ተሰናባቹ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ በአሜሪካው ራይስ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የቤከር ፐብሊክ ፖሊሲ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል። [ዋዜማ ራዲዮ]
Show all...
#ምክር_ለወዳጅ❗️ ይህን ፅሁፍ ማንበብ 100 መፅሐፍት የማንበብ ያህል ነው። 🖋 በወጣትነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ ውጣ፤ ሁሉንም ካላየሁ አላምንም አትበል። ሰምቶ ማመን፣ ከተጎዱት መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ። የሰማንያ ዓመት ዕውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ ዓመት መኖር የለብህም። ሰማንያ ዓመት ከኖሩት በትሕትና መጠየቅ ይገባሃል። 🖋 ምክርን ብትሰማ በነጻ ትማራለህ። ምክርን አልሰማ ብትል ግን በዋጋ እንደምትማር እወቀው! በዋጋ መማር ግን አድካሚ ደግሞም የሚያስመርር ነው። ብልህ ከሆንክ በሰው ከደረሰው ትማራለህ፤ ሞኝ ከሆንህ ግን በራስህ ሲደርስ ትማራለህ። 🖋 የታየህን አሳይ፣ ያልታየህን አጥራው። በደንብ ያልተረዳኸውን አታስተምረው። ያልቀመስከውን ለሰው አትጋብዝ። የሰማኸውን ሁሉ አትመን። ያየኸውን ሁሉ ስጡኝ፣ የተናገርከውን ሁሉ ፈፅሙ አትበል። የሰጠኽውን እርሳ እንጂ አታውራ። ፍፃሜውን ሳታይ ምስጋና አታብዛ። ቀኑ ሳይመሽ ቀኑ ጥሩ ነው አትበል። 🖋 ዓይንህ የፊቱን ቢያይ፤ ልብህ የኋላውን ያስብ። ነገ ላይ እንድትደርስ፤ የትናንቱን አትርሳ። የምትሄድበት እናዳይጠፋህ የመጣህበትን አትዘንጋ። 🖋 የአባቶችህን መልካም ሥራ አብነት አድርግ። ካሳለፉት ሕይወት ተማር እንጂ አወዳሽና ወቃሽ አትሁን። ሌሎች መሆን ያለባቸውን ስታውቅ አንተ መሆን ያለብህ እንዳይጠፋህ ተጠንቀቅ። ደግሞም አንተም በታሪክ ፊት መሆንህን እወቀው። 🖋 ክፋት አይሙቅህ፣ መልካም ነገርም ብርድ ብርድ አይበልህ። ለክፋት አቅም ካለህ ለበጎ ነገርም አቅም አለህና ተግባርህ የምርጫ ውጤት ነውና አስብበት። 🖋 ገንዘብ የሚመልሰው የገንዘብን ጥያቄ ብቻ ነውና ሁሉንም ነገር ገንዘብ ያስገኝልኛል ብለህ አታስብ። ላለው አትሩጥ፣ ምጽዋትህና ተግባርህ በአቅምህ መጠን ይሁን እንጂ ከአቅምህ አትነስ። ድሃም ሆነህ ተበድረህ ስጦታ አትስጥ። በጣም ካልቸገረህ ለቅንጦት አትበደር። ያንተን ድርሻ ከጨረስህ ያልተጨረሰ የሌሎችን ድርሻ ፈፅምላቸው። 🖋 ለሀብታም አትሳቅ፣ የደሀ ጉልበት አይለፍብህ፣ ያለ ሰው ሰው አልሆንክምና ሰው አትጥላ፣ የወጣህበትን መሰላል አትገፍትር፣ ለመውረድም ያስፈልግሃልና፣ ያየኽውን ሴት ሁሉ የመውደድ ጠባይህ ካለቀቀህ ትዳር አትያዝ፣ ካልጋበዙህ በቀር አማካሪ አትሁን፣ ባልጠሩህ ሥፍራ አቤት አትበል፣ ካልሾሙህ መሪ አትሁን፣ ጉድለት በሌለበት ቦታ ጊዜህን አታባክን፣ የሰው ፊት ጥገኛ ሁነህ ሲስቁልህ የምትስቅ ሲቆጡህ የምታለቅስ አትሁን፣ ነገርህን በልክ፣ ቃልህን በጣዕም፣ ድምፅህን በዝግታ ፈፅመው። 🖋 እውር እንዳይሉህ ያልታየኽን አያለሁ አትበል። ጨካኝ እንዳይሉህ ያልተሰማህን ጩኸት እሰማለሁ አትበል። ንፉግ እንዳይሉህ ያለ አቅምህ እረዳለሁ አትበል። ነገር አይገባውም እንዳይሉህ ያልገባህን እንደገባህ አድርገህ አትለፍ። አንድ በጎ ዕውቀት ሳትጨብጥ የዋልክበትን ቀን እንደ ኖርክበት አትቁጠረው፣ ስለዚህ መፅሐፍትን አንብብ፣ አዋቂዎችን ጠይቅ፣ ሁሉን ሳትንቅ ስማ። 🖋 ሥልጣን ሲሰጥህ መሪ እንጂ አለቃ አትሁን፤ ከፊት እየቀደምህ አስከትል እንጂ ከኋላ ሆነህ አትቅደም። 🖋 በዓላማ ኑር፤ እንቅፋቶች የሚያጸኑህ እንጂ ተግባርህን የሚያስተውህ አይሁኑ። ሕይወት ትምህርት ቤት መሆኑና ባለማወቅ ብዙ ትህምርቶች እንዳያመልጡህ ተጠንቀቅ። 🖋 የመከራ ቀን ወዳጆችህን አትርሳ፤ የዛሬ ሰው ብቻ አትሁን። ምንጩን ያላወቅነው ከማህበራዊ ሚዲያ የተወሰደ *
Show all...