тнσυgнт°ραι𝔫тιиg 🎞️
Open in Telegram
2 203
Subscribers
+324 hours
+107 days
+1230 days
Posts Archive
2 203
ብቸኛ ሰው ነህ፤ በትክክልም ብቸኛ ሰው!። የምትወደውን ዘፈን ማንም አልሰማውም፤ ያነበብከውን መፅሐፍ ማንም አላነበበውም። ቆንጆ ነው ብለህ በምታስበው ቀልድ ማንም አይስቅም። ትዝታዎች አሉህ ነገር ግን እነሱ ልክ እንደ ዋሻ ዘመን ገንዘብ ይመስላሉ፤ ዛሬ ዋጋ ቢስና የማይጠቅሙ ናቸው። ምንም እንኳን ለአንተ ጠቃሚ ቢሆንም ለሌሎች ምናቸውም ነው። የድሮ ጓደኞችህ ተራ በተራ ተለይተህዋል ቦታዎች እና ፍላጎቶችህ በጠቅላላ ተቀይረዋል።
አንተ ምርጥ የጉዞ ባለቤት ነህ። አንተ ማለት ሰይፍ ሰሪ ነህ። አንተ ጥሩ የሆንክበትን ነገር ማንም አይፈልገውም፤ በበጎ አይቀበለውም። ምንም እንኳን በአቀባበልህ አንተ የተሻልክ ብትሆንም ቀረቤታህን አያስተናግዱትም። እና አንዳንዴ እንደ ሰው መቼ ይሆን ወደ ንቃተ ህሊና የምመለሰው? ብለህ ታስባለህ፤ የድሮውን ውበት መቼ ይሆን የምትመልሰው?፤ መቼ ነው እንደገና አስፈላጊ የምትሆነው?፤ ያ መቼም አይሆንም!። በስተመጨረሻ ወደ ጨለማው ወንዝ ትሄዳለህ፡፡ ስንቶች ቀድመውህ ተሻግረው ላይመለሱ የገቡበት ወንዝ። ወደ ማዶ ትሻገራለህ ከዛ ሁሉም ይረሳሃል።
―አህመድ ካሊድ ታውፊቅ2 203
🎶🎶🎶. የጀርባ ምስል. 🎶🎶🎶
"መቆም በቆምክበት ቦታ ብቻ ያለውን ዕድል እንድትጠቀም ያደርገሃል ፣ መሄድ ግን የማታውቀውንም ዕድል እንድትሞክር ይረዳሃል። ስትቆም መጀመሪያ ታረጃለህ ፣ ቆይቶም ትበሰብሳለህ። ስትሄድ ግን መጀመሪያ ትደክማለህ ፣ ቀጥሎ ግን ትጠነክራለህ። ባለቀ ትናንት አትታሰር ፣ በተበላ ዛሬ አትወስን ፣ ይልቅ ወደማይታውቀው ነገ ሂድ። ነገ ወዳንተ ሳይመጣብህ አንተ ወደ ነገ ሂድ። አንድ ቦታ ላይ የግድ እንድንቆም ቢፈለግ ኖሮ እግር ሳይሆን እንደ ዛፍ ስር ይኖረን ነበር። የመሄዳችን ዋናው ምክኒያቱ የምንቆይበት ምክኒያት አለመኖሩ ነው።"
Rophnan - ሮፍናን
2 203
ከቤቴ ጓሮ ለአንድ ሰው የሚሆን መቃብር እየቆፈርኩ ነበር። እና በወርቅ ሳንቲሞች የተሞላ አንድ ሣጥን አገኘሁ። ይሄ የፈጠነ ለሚስቴ ልነግራት በቀጥታ ወደ ቤቴ መሮጥ ጀመርኩ። ከዚያም በጓሮ ውስጥ ለምን እንደቆፈርኩ አስታወስኩኝና ተመለስኩ።
2 203
የምንፈልገውን ለማግኘት ብቻ ከመማሰን ያገኘነውን በመውደድና በማመስገን ቀናችንን እናስውብ ፡፡
ከመጸለይሽ በፊት ተመስገን በይ። ስለሁሉም ነገር አመስግኝ...በረከቶችሽን ቁጠሪ! ጠዋት ገና ከእንቅልፍሽ ስትነቂ....አይኖችሽን ስትገልጭ.....አየሩን ስትተነፍሽ <<ተመስገን>> በይ!!!...ሞተሽ ልታድሪ ትችይ ነበርና!!! ደግሞ ከአልጋሽ ወርደሽ መሬት ስትቆሚ…‹‹ተመስገን>> በይ! በሆነ ምክንያት የአልጋ ቁራኛ ሆነሽ ልትቀር ትችይ ነበርና!!! ውለሽ ስትገቢ ተመስገን በይ፣ ብዙዎች እንደወጡ የቀሩ አሉና።
በየትኛውም መንገድህ ላይ አመስግን። ምስጋና ቢስ አንደበቶች ልመናን ሲያሻግሩ ለዛቸውን ያጣሉ!
📃መልካም ቀን📄
📨 ሼር 📈2 203
-ኦሾው #ሱፊዝምአለማወቁን የማያውቅ እሱ ሞኝ ነውና ተወው አለማወቁን የሚያውቅ ብልህ ነው አስተምረው ማወቁን የማያወቅ እሱ ያንቀላፋ ነውና አንቃው ማወቁን የሚያውቅ እሱ ጠቢብ ነውናተከተለው!
2 203
“መስጠም ማለት በውሃ ውስጥ መውደቅ ማለት አይደለም። የትኛውም አሳ በዚህ መንገድ መስጠም የሚለው ነገር አይገልጸውም፤ ነገር ግን በአየር ላይ ይሰጥማል። ስለዚህ የመስጠም ትርጉሙ ያንተ ባልሆነ ቦታ ላይ መውደቅ ነው።”
፦አህመድ ካሊድ ተውፊቅ
2 203
“አንዳንዴ ደህና ነኝ ስል አጥብቆ የሚይዘኝ ሰው ያስፈልገኛል፤ አይኔን እያየ እንዲህ የሚለኝ ‹አይ አይደለህም አውቃለሁ!› ”
―ፓውሎ ኮሄሎ2 203
“ሲቀጥል ዛሬ እነዚህ ሁሉ ስሜት ውስጥ አይደለሁም፡፡ ለመታየት፣ ለመገረም፣ ለመዝናናት እና ሌላውን ለማሳመን ፍላጎት የለኝም። አላማዬ ፍፁም እረፍት ነው። ምንም ነገር አለመፈለግ፣ ምንም አለማወቅ፣ ምንም አለማስተማር፣ ያለምንም ጥልቅ ግንኙነት፣ መተኛት፣ ከዚያም የበለጠ መተኛት..፡፡”
—ቻርልስ ባውዴላይር2 203
ስራ አጥ ቦዘኔ ስትሆን ከእናትህ በላይ ዋነኛ ጠላቶችህ ጎረቤቶች ናቸው። ጥሩ የስራ ገቢ ብሎም በራስህ ላይ የለውጥ መሻሻል ማየት ስትጀምር ከሁሉም በላቀ በቁልምጫና በሽብሸባ የሚጠሩህ እነዚው ጎረቤቶችህ ናቸው።
ቦዘኔ ስትሆን የሰፈር ሰዎችና ጎረቤቶችህ እራስህን እንድጠላ፣ ምንም ጥቅም እንደሌለ እንዲሰማ የሚያደርጉ ጠላቶችህ ይሆናሉ!። አብዛኛውን ወጣት deep anxiety ውስጥ እንዲዘፈቅና እንዳይወጣ የስነ ልቦና ጥቃት ደጋግመው በአፍና በግልምጫ የማድረስ ባህል አላቸው። ማኀበረሰብ የማይከሰስ አረመኔ ወንጀለኛ ነው። እራስህን አድንና አፋቸውን አዘጋጀቸው!።2 203
ምላሽ የመስጠት ጥበብ
የዲዮጋን አባት ድሃ ልብስ ሰፊ ነበረ። እና ዲዮጋን ብዙ ባለሃብቶችና መኳንንቶች በተገኙበት ትልቅ ድግስ ላይ ተገኝቶ ሳለ አንድ አልጋ ወራሽ ልዑል ሊሳለቅበት ፈልጎ እንዲህ አለው፦“አባትህ ልብስ ሰፊ አልነበረም እንዴ?”
ዲዮጋን፦“አዎ”
ልዑሉ፦“ታዲያ ለምንድነው እንደሱ ልብስ ሰፊ ያልሆንከው?”
ዲዮጋን፦“ማለት! የአንተ አባት ብልህና አርቆ አሳቢ ንጉስ አይደለም እንዴ?”
ልዑሉ፦“አዎ”
ዲዮጋን፦“ታድያ ለምንድነው አንተ ቅል እራስ ደደብ የሆንከው?” 😐2 203
“ጥሩ ሰው ነኝ ግን መልአክ አይደለሁም፤ ሃጥያተኛ ነኝ ነገር ግን ሰይጣን አይደለሁም። በትልቅ አለም ውስጥ ከምወደው ሰው ጋር ለመገናኘት የምጥር ትንሽ ልጅ ነኝ፡፡”
―ማሪሊን ሞንሮ
2 203
አብሬው የምጠጣው መላጣው ጀለሴ በጨብሲ ፈረስ ስለ ኤክሱ እያነሳ ሲያለቃቅስ እንዲህ ብዬ አጽናናውት፦“ሴት እና ፀጉርን ካልተንከባከብካቸው ይሸሻሉ፤ አንተ ደግሞ ሁለቱም ሸሽተውሃል..”
አሁን በበደሌ ፈንታ በረኪና እየፈለገ ነው። እኔ ደግሞ ቀላል መንገድ አለ ልሙጡን ባንዲራ ይዘ አስፓልት ውጣ እያልኩት እገኛለሁ። 🤝🏼☹2 203
All the things you wanted to be... then, all the things you wish you never wished for.
It was the delicious itch you go to scratch, then find it is under the skin and can't reach it. So the delicious itch becomes unbearable.
It told you what you most want is what you most can't have... and what you most can't have is what you already had, and lost.
It was the song of all the promises I failed to keep.
2 203
የፈላስፋው ፍሬድሪክ ኒቼን ደብዳቤዎች ያነበበ ሰው በብቸኝነት ስሜት ብዙ እንደተሰቃየ ይገነዘባል። በ1887 ዓ.ም ለጓደኛው ኮቭሪክ እንዲህ ሲል ደብዳቤ ጻፈለት፦
“ልጅ እያለሁ ብቻዬን ነበርኩ ዛሬ ላይ አርባ አራት አመት ሞልቶኝም ብቻዬን ነኝ። የሰው ልጅ ሁሌም እንደናፈቀኝና እንደፈለኩት ነው። እኔ ግን ይሄ ፍለጋ ሁሌም እራሴን ያስገኝልኛል ምንም እንኳን እራሴን ባልናፍቅም። ከእንግዲህ ወዲህ ማንም ወደ እኔ የሚመጣ የለም፤ እኔማ ወደ ሁሉም ሄጄ ነበር ቢሆንም አንድም አላገኘሁም!።”2 203
ሃሩኪ ሙራካሚ የተሰኘው የአረብ ጸሃፊ “Kaf Beach” በተሰኘው ታዋቂ ልብ ወለዱ ውስጥ ከፃፋቸው ምርጥ መስመሮች መካከል፦
“አንዳንድ ሰዎች በህይወታችን ውስጥ ቦታ ሳይኖራቸው ለዘላለም በልባችን ውስጥ ቦታ እንደሚይዙ መቀበል አለብን..።”2 203
“በህይወቴ ውስጥ የተፈጠሩ አስቸጋሪ ጊዜያት በሙላ እስኪያልፉ እየጠበቅኩ ነው። በዋሻ መጨረሻ ስለሚወጣው ብርሃን ተስፋ አደርግ ነበር። ነገር ግን በቃ የኔ ህይወት ይህ ቢሆንስ?። በዋሻው መጨረሻ መቃብር...”
―አህመድ ካሊድ ተውፊቅ
2 203
ኩባዎች አንድ አባባል አላቸው፦
“ወደ ትክክለኛው መንገድ ልትመራኝ እንዳትሞክር፤ ምክንያቱም አንተ ብትሄድበት ኖሮ እዚህ ባላገኘውህ ነበር!።”2 203
“በዚህች ምድር ላይ ሰባ ዓመት ብቻ ትኖራለህ፤ እና ምናልባትም እሱ እድሜ ላይ ሳትደርስ ሞት በድንገት ይወስድሃል። ታዲያ ለምን በሀዘን፣ በህመም፣ ስለ ሰዎች እና ስለወደፊትህ በማሰብ እራስህን ታጠፋለህ?። ለጥቂት አመታት ብዙ ፍለጋ..”
–ዶስቶይቭስኪ2 203
ከዚህ በፊት በሺዎች የሚቆጠር ጊዜ ምግብ በልተሃል ግን አሁንም አንዳንዴ ምላስህን ትነክሳለህ
ከዚህ በፊት በሺዎች ጊዜ ተራምደሃል ግን አሁንም አንዳንዴ እንቅፋት ይመትሃል
ታዲያ ለምንድን ነው አሁንም አንድን ነገር በደጋጋሚ ስላደረከው ብቻ perfect እንድትሆን የምትጠብቀው
ተሳሳትክ ማለት ሰው ነህ ማለት ነው
መውደቅ አዳማዊ ነው ወድቆ መቅረት ነው ኪሳራው🙌