cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

አዳኙ የየትምህርት እና የመረጃ ሚዲያ

መረጃ በፍጹም አይናቅም አይደንቅም

Show more
Advertising posts
672
Subscribers
-124 hours
No data7 days
-2430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ አደረሳችሁ። በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረውን የትንሳኤን በዓል በክርስትና እምት ዘንድ ከሁሉም ከዓሎች በበለጠ ሁኔታ የሚከበር ሲሆን ይህንንም ቀን በጉጉት እየጠበቁ ለ55 ቀናት በጾም ቆይተው የሚቀበሉት በዓል ነው።ከዚህ ወቅት በእያንዳንዱ እሁድ እና በተለይም ከእለተ ኦሳህና እስከ ትንሳኤ ድረስ እንደ ቲያትር እያንዳዱ ስረዓት በትዕይን የሚናወንበት ጊዜ ነው።ታዲያ ይኸን ሁሉ ስዓት ሲፈጽሙ ቆይተው ለትንሳኤ እለት ሲደርሱ በታላቅ ድምቀት እና ደስታ ያከብሩታል።ስለዚህም ለመላው ለክርስትና እምት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ2016 የትንሳኤ በዓል እንኳን አደረሳችሁ። የትንሳኤ በዓልን ስናከብር ከሌላው ጊዜ በለጠ ሁኔታ አቅመ ደካሞችን የምንረዳበት ፣ ተካፍለን የምንበላበት ፣ አብረን የምደሰትበት እና የታመሙትን የምንጠይቅበት ፣ ዕርስ በዕርሳችን የምንከባበርበት እና የምንደጋገፍበት ሊሆንም ይገባል። መልካም የትንሳኤ በዓል ይሁንልን ሚያዝያ 27/2016 አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ https://t.me/AdanguMidia
Show all...
የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል)ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ።    የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሐምሌ 3-5 ለማህበራዊ ሳይንስ ሐምሌ 9-11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል።     በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 30-ሐምሌ 01/2016 ዓ/ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ሐምሌ 6-7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናል።     ስለሆነም ተፈታኞች እና የሚመለከታቸው ሁሉ ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ተብሏል። አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ https://t.me/AdanguMidia
Show all...
በአዲስ አበባ በዛሬዉ እለት ባጋጠመ የጎርፍ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት አልፏል #NEWS  | በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ንጋት ላይ በቦሌ ክ/ከተማ በወረዳ 11 ወረገኑ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የጣለዉን ዝናብ ተከትሎ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታዉቋል። የከተማ አስተዳደሩ ማስተር ፕላናቸዉን ያልተከተሉ የወንዝ ዳርቻ ግንባታዎች ህብረተሰቡን ለጎርፍ አደጋ እንደሚያጋልጡ በጥናት በመለየት ይህንን የአደጋ ስጋትና ተጋላጭነት በመሠረታዊነት የሚፈታ ፕላኑን የጠበቀ ዘላቂ የመፍትሄ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አስታዉቋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ በደረሰው በዚህ ድንገተኛ አደጋ ምክንያት ህይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል::በመሆኑም ተመሳሳይ አደጋዎች እንዳያጋጥሙ ህብረተሰቡ ከከተማ አስተዳደሩና ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልእክቶችን ተግባራዊ እንዲያደርግ አሳስቧል:: ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎት በ939 ህብረተሰቡ ፈጥኖ እንዲያሳዉቅ ጥሪ ቀርቧል፡፡ Via: ዳጉ ጆርናል አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ https://t.me/AdanguMidia
Show all...
ኢራቃዊያን ተመሳሳይ ፆታን አውግዘዋል።ኢራቅ ውስጥ ለግብረ ሰዶማዊነት ቦታ የለም ብለዋል። የኢራቅ ፓርላማ የግብረ ሰዶናዊነት / የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ተግባርን ከ10 እስከ 15 ዓመት በሚደርስ እስር የሚቀጣ አዲስ ሕግ አርቅቋል። በአዲሱ ሕግ ጾታቸውን የቀየሩ ሰዎች ከ1 እስከ 3 ዓመት እርስ ቤት ይወረወራሉ። እንዲሁም፦ ✔ግብረ ሰዶማዊነት / የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የሚያበረታቱ፣ የሚያስተዋውቁ፤ ✔ሴተኛ አዳሪነትን የሚያራምዱ ✔ጾታ ለመቀየር ቀዶ ህክምና ሚያደርጉ ዶክተሮች ✔ሆን ብለው ልክ #እንደ_ሴት_የሚሆኑ ወንዶች እና " በሚስት መለዋወጥ " ላይ የተሠማሩ ሰዎች እስራት ይጠብቃቸዋል ፤ ዘብጥያም ይወርዳሉ። የኢራቅ ፓርላማ ተጠባባቂ አፈጉባኤ ሞህሰን አል-ማንዳላዊ  " ይህ አዲስ ሕግ የህብረተሰቡን የሞራል / የግብረገብ / የስነምግባር መዋቅር ለመጠበቅ ያለመ ነው " ብለዋል። "በኢራቅ ውስጥ ለግብረ ሰዶማዊነት ቦታ የለም " ያሉት አል-ማንዳላዊ " ይህ የኢራቅ ምድር የነቢያት፣ የንፁህ ኢማሞች ፣ የጻድቃን እንዲሁም ቅዱሳን ምድር ነው " ነው ሲሉ ተናግረዋል። አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ https://t.me/AdanguMidia ማስታወቂያና ጥቆማ 👇መቀበያ https://t.me/premerja
Show all...
በተወሰኑ ሰዓታት ውስጥ የፈረሰው የጋዛን ፍርስራሽ ለማጽዳት 14 አመታትን ሊፈጅ ይችላል ሲል ተመድ አስታወቀ የእስራኤል እና የሀማስ ጦርነትን ተከትሎ እስራኤል በጋዛ ባደረሰችው ጥቃት ያልፈነዱ መሳሪያዎችን ጨምሮ ፍርስራሾችን ለማጽዳት 14 አመታት ገደማ ሊፈጅ እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ። በጦርነቱ አብዛኞቹ የጋዛ ነዋሪዎች ቤት አልባ እና ተፈናቃይ መሆናቸው ተገልጿል። በጦርነቱ 37 ሚሊዮን ቶን ገደማ ፍርስራሽ መከማቸቱን በተመድ ማይን አክሽን ሰርቪስ (UNMAS) ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ፒህር ሎሀመር በጀኔቫ በሰጡት ጋዜጤዊ መግለጫ ተናግረዋል። በጋዛ ምን ያህል ያልፈነዱ የጦር መሳሪያዎች መኖራቸውን መገመት እንደማይቻልም ባለሙያው ገልጸዋል። ጥቅም ላይ ከሚውሉ ተተኳሾች መካከል 10 በመቶ የሚሆኑት ከተተኮሱ በኋላ እንደማይፈነዱ ከዚህ ቀደም የተሰሩ ጥናቶች ያመላክታሉ ሲል የዘገበው ዘ ጋርዲያን ነው። አያችሁ በተወሰኑ ሰዓታት ውስጥ የምናጠፋው ጥፍቶች ምን ያህል ጊዜ ወስደን እንደምንሰራቸው። መጀመሪያ ብዙ አመታት ለፍተን ሰርተን በተወሰኑ ሰዓታት ውስጥ እናጣቸዋለን፤ ስንቱስ አደጋላይ ወድቋል?እባካችሁ እናስተውል አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ https://t.me/AdanguMidia
Show all...
ጅሩ… አንድ ሰንጋ 650 ሽህ ብር ተጠርቷል።ሌላው 550 ሽህ ጥሪ ተሰምቷል። በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እነዋሬ ከተማ አስተዳደር በአመት አንድ ጊዜ የሚውለው የሆሳዕና ገበያ ዘንድሮም የተለየ ነገር ታይቶበታል። ይህ በምስሉ ላይ የሚታየው ሰንጋ 650 ሽህ ብር ተጠርቷል ።የሰንጋው ባለቤት ወጣት ሚጥዬ ታደለ ይባላል።650 ሽህ ብር የተጠራው የጅሩ ሰንጋ ገና አልተሸጠም። ሌላው በዚሁ ገበያ የሞረትና ጅሩ ወረዳ የማንጉዶ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ አበበ በፍቃዱ  ለ1 አመት ያክል እንደ ልጄ ስንከባከበው ነበር ያሉትን ሰንጋ በ550 ሽህ ብር ሲሉ ጠርተዋል ሲል የከተማ አስተዳደሩ ሚዲያ አስነብቧል።የሁለቱም ሽያጭ ገና አልተፈፀመም።
Show all...
በአዲስ አበባ ት/ጽፈት ቤት  በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በወረዳ12 ት/ጽፈት ቤት ስር የሚገኘው የመንግስት ት/ቤት የሆነው የብስራት ቅድመ አንደኛ፣1ኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ሚያዚያ 18/2016ዓ.ም ቅድመ-አንደኛ ደረጃ አዲሱ ስረዓተ ትምህርት ትግበራ፤ እቅድ አዘገጃጄ፣የምዘናና ክትትል፣ ሮስተር አስራርና አጠቃቀም ዙሪያ ለመምህራን ሱፐር ቫይዘሮች በተገኙበት የደጃ/ገነሜ ቅድመ-አንደኛ፣1ኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት መምህር በሆኑት በመ/ር መኩሪያ ታምሩ ስልጠና ተሰጠ።በስልጠናው ላይም የአዲሱን ስረዓተ ትምህርት አተገባበር፤እቅድ አዘገጃጄት፣የምዘናና ክትትል፣ሮስተር አስራርና አጠቃቀም ላይ የተሻለ እውቀትን ለመጨበት ተችሏል። የብስራት ቅድመ አንደኛ የልጆችን እውቀት ጊዜው በሚፈቅደውና በማንኛውም ሁኔታ ተወዳዳሪ ና ነገ የተሻለ ዜጋ ሆነው እንዲወጡ የሚሰራ ነው።ለዚህም ነው መምህራኑ የሚሰሩት ግልጽ ሆኖላቸው እንዲሰሩ በስልጠና ስለምናምን ስልጠናውን ያዘጋጀነው።በስልጠናው ላይ የቅድመ-አንደኛ አስተባባሪ የሆነችው ወ/ሮ ድንቅነሽ መምህራን ስልጣናው ላይ በአዲሱ ስረዓተ ትምህርት ዙሪያ እንዲሁም በትምህርት አስጣጡ እና በፎርም ዙሪያ በጣም ግልጽ የሆነ ስልጠና መስጠቱን ገልጻ በመጨረሻም ክትትልና ድጋፍ የሚደርጉላቸውን የወረዳውን ሱፐርቫይዘርና የትምህርት ቤቱን ዋና ርዕሰ መምህር የሆኑትን ቶፊቅ ሙሰማ፣ምክትል ርዕሰ መምህራንና የደጃ/ገነሜ ቅድመ-አንደኛ፣1ኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ላደረጉት ቀና ትብብር በት/ቤቱ ስም በጣም አመስግናለች።በመጨረሻው የወረዳው ሱፐር ቫይዘሮች በአዲሱ ስረዓተ ትምህርት ዙሪ እንዴት መስራት እንዳለብን ገለጻ ተደርጓል። ሚያዝያ 18/2016 ምንጭ  የብስራት ቅድመ አንደኛ፣1ኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት መረጃ በፍጥነት ለማግኘት በቴሌግራም 👇 https://t.me/premerja
Show all...
👍 1
በአዲስ አበባ ት/ጽፈት ቤት  በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በወረዳ12 ት/ጽፈት ቤት ስር የሚገኘው የመንግስት ት/ቤት የሆነው የብስራት ቅድመ አንደኛ፣1ኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ሚያዚያ 18/2016ዓ.ም ቅድመ-አንደኛ ደረጃ አዲሱ ስረዓተ ትምህርት ትግበራ፤ እቅድ አዘገጃጄ፣የምዘናና ክትትል፣ ሮስተር አስራርና አጠቃቀም ዙሪያ ለመምህራን ሱፐር ቫይዘሮች በተገኙበት የደጃ/ገነሜ ቅድመ-አንደኛ፣1ኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት መምህር በሆኑት በመ/ር መኩሪያ ታምሩ ስልጠና ተሰጠ።በስልጠናው ላይም የአዲሱን ስረዓተ ትምህርት አተገባበር፤እቅድ አዘገጃጄት፣የምዘናና ክትትል፣ሮስተር አስራርና አጠቃቀም ላይ የተሻለ እውቀትን ለመጨበት ተችሏል። የብስራት ቅድመ እንደኛ የልጆችን እውቀት ጊዜ በሚፈቅደውና በማንኛውም ዘንድ ተወዳዳሪ ነገ የተሻለ ዜጋ ሆነው እንዲወጡ የሚሰራ ነው።ለዚህም ነው መምህራኑ የሚሰሩት ግልጽ ሆኖላቸው እንዲሰሩ በስልጠና ስለምናምን ስልጠናውን ያዘጋጀንው።በስልጠናው ላይ የቅድመ-አንደኛ አስተባባሪ የሆነችው ወ/ሮ ድንቅነሽ መምህርራን ስልጣናው ላይ በአዲሱ ስረዓተ ትምህርት ዙሪያ እንዲሁም በትምህርት አስጣጡ እና በፎርም ዙሪያ በጣም ግልጽ የሆነ ስልጠና መስጠቱን ገልጻ በመጨረሻም ክትትልና ድጋፍ የሚደርጉላቸውን የወረዳውን ሱፐርቫይዘርና የትምህርት ቤቱን ዋና ርዕሰ መምህር የሆኑትን ቶፊቅ ሙሰማ፣ምክትል ርዕሰ መምህራንና የደጃ/ገነሜ ቅድመ-አንደኛ፣1ኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ላደረጉት ቀና ትብብር በት/ቤቱ ስም በጣም አመስግናለች። በመጨረሻው የወረዳው ሱፐር ቫይዘሮች በአዲሱ ስረዓተ ትምህርት ዙሪ እንዴት መስራት እንዳለብን ገለጻ ተደርጓል። ሚያዝያ 18/2016 ምንጭ የብስራት ቅድመ አንደኛ፣1ኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት መረጃ በፍጥነት ለማግኘት በቴሌግራም 👇👇 https://t.me/premerja
Show all...
አርሰናል ቼልሲን እንደጉድ ሲሸምነው አምሽቷል!    የአርቴታ ወጣት ሰራዊት ለሰማያዊዎቹ ርህራሄ ሳያስመለክቱ ደቁሰዋቸዋል!    መድፈኞቹ ወደ ዋንጫው መመልከቱን አላቆሙም!    5-0 ጣፍጭ ድል አስመስግበዋል    አርሰናል የሊጉን መሪነት አጠናክሩዋል
Show all...
👍 1