cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሳተናው ሚዲያ / Satenaw Media

ትክክለኛ ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ! #Ethiopia #Ethiopianews #Addismereja

Show more
Advertising posts
3 209Subscribers
-324 hours
-157 days
+3730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#world_news ‼️ የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት፣ የሱዳን ተፋላሚ ወገኖች በሰሜን ዳርፉር ግዛት ዋና ከተማ አል-ፋሽር አካባቢ የሚያደርጉትን የውጊያ ዝግጅት እንዲያቆሙ ጠይቋል። በከተማዋ ላይ ስጋት ያንዣበበው፣ ፈጥኖ ደራሹ ኃይል ከተማዋን ለመቆጣጠር ዝግጅት እያደረገ ስለመኾኑ ከተሰማ በኋላ ነው። ከተማዋ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የጦርነቱ ተፈናቃዮች የተጠለሉባት ስትኾን፣ ከድርፉር ግዛቶች እስካኹን በፈጥኖ ደራሹ ኃይል ቁጥጥር ሥር ያልገባች ብቸኛዋ ከተማ ናት። ጸጥታው ምክር ቤት፣ አባል አገራት በሱዳኑ ጦርነት ጣልቃ ከመግባት እንዲቆጠቡም ጥሪ አድርጓል። https://t.me/Satenawmedia1
Show all...
ሳተናው ሚዲያ / Satenaw Media

ትክክለኛ ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ! #Ethiopia #Ethiopianews #Addismereja

👍 1
#Ethiopia ‼️ በትግራይ ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር በዋሉ የራያ እና አላማጣ አካባቢዎች ህይወት ምን ይመስላል? ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ የትግራይ ታጣቂዎች ወደ ራያ እና አላማጣ አካባቢዎች መግባታቸውን ተከትሎ የዳግም ጦርነት ስጋት ደቅኗል። የአማራ ክልል በህወሃት ታጣቂዎች ወረራ ተፈጽሞብኛል ቢልም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳድር ግን ተግሩን እየፈጸሙ ያት የፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት ጠላቶች ናቸው ብሏል። የራያ እና አላማጣ አካባቢ ነዋሪዎች በፌደራል መንግስት “ተከድተናል የሚል ስሜት ውስጥ መግባታቸውን” ተናግረዋል። የትግራይ ታጣቂዎች ከአላማጣ 15 ኪሎ ሜት ራዲያስ ውስጥ ሆነው በየቀኑ ተጨማሪ ሀይል እያስገቡ እንደሆነም ነው ነዋሪዎቹ የሚናገሩት። ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ የትግራይ ታጣቂዎች ወደ ራያ እና አላማጣ አካባቢዎች መግባታቸውን ተከትሎ የዳግም ጦርነት ስጋት ደቅኗል። የአማራ ክልል በህወሃት ታጣቂዎች ወረራ ተፈጽሞብኛል ቢልም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳድር ግን ተግሩን እየፈጸሙ ያት የፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት ጠላቶች ናቸው ብሏል። የራያ እና አላማጣ አካባቢ ነዋሪዎች በፌደራል መንግስት “ተከድተናል የሚል ስሜት ውስጥ መግባታቸውን” ተናግረዋል። የትግራይ ታጣቂዎች ከአላማጣ 15 ኪሎ ሜት ራዲያስ ውስጥ ሆነው በየቀኑ ተጨማሪ ሀይል እያስገቡ እንደሆነም ነው ነዋሪዎቹ የሚናገሩት። https://t.me/Satenawmedia1
Show all...
ሳተናው ሚዲያ / Satenaw Media

ትክክለኛ ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ! #Ethiopia #Ethiopianews #Addismereja

#መንግሥት በሪል ስቴትና በሞተር ተሽከርካሪዎች ዝውውር ላይ ታክስ ለመጣል ማቀዱን ተሰምቷል‼️ የሞተር ተሽከርካሪዎች ዝውውር ታክስ በኹሉም ተሽከርካሪዎች ላይ እንደሚጣል መረዳቱን ዘገባው አመልክቷል። ከታክሶቹ የሚገኘውን ገቢ የመሰብሰብና የመጠቀም ሥልጣን ግን ለክልሎችና ለኹለቱ የከተማ አስተዳደሮች ሳይሰጥ እንደማይቀር ከምንጮች መስማቱን ዘገባው ጠቅሷል።    የሪል ስቴት ንብረት ታክስ የሚጣለው፣ በሪል ስቴት አልሚዎች ወይንስ በሪል ስቴትገዢዎች ላይ ስለመኾን አለመኾኑ ግን በመንግሥት ሰነዶች ላይ አልተገለጠም ተብሏል። "የቴሌግራም ቻናላችንን ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ ያድርጉ"👇👇👇 https://t.me/Satenawmedia1
Show all...
#Monday‼️ ዛሬ ሰኞ ሚያዚያ 21/2016 በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ለ5 ቀናት የሚቆየው ሰሞነ ህማማት ተጀምሯል።እስከ መጭው አርብ ይቆያል።እያንዳንዱ ቀናት የራሳቸው የሆነ የአከባበር ስርዓት አላቸው። መልካም ጊዜ‼ አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ https://t.me/Satenawmedia1
Show all...
#መድፈኞቹ ወሳኝ ድል አሳክተዋል ! በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የሰላሳ አምስተኛ ሳምንት  መርሐ ግብር አርሰናል ከቶተንሀም ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል። የመድፈኞቹን የማሸነፊያ ግቦች ቡካዩ ሳካ ፣ ካይ ሀቨርትዝ እና ሆይበርግ በራሱ ግብ ላይ ሲያስቆጥሩ ለቶተንሀም ሮሜሮ እና ሰን ሁንግ ሚን ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል። አርሰናል በዘንድሮው የውድድር አመት በሊጉ ከየትኛውም ክለብ በበለጠ ሀያ ሶስት ግቦችን ከቆመ ኳስ ማስቆጠር ችለዋል። ቡካዩ ሳካ በዘንድሮው የውድድር አመት በሁሉም ውድድሮች ለአርሰናል ባደረጋቸው ጨዋታዎች በሰላሳ ሶስት ግቦች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ማድረግ ችሏል። የቶተንሀም የፊት መስመር ተጨዋች ሰን ሁንግ ሚን በውድድር አመቱ ያስቆጠራቸውን የሊግ ግቦች አስራ ስድስት ማድረስ ችለዋል። በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ? 1️⃣ አርሰናል :- 80 ነጥብ 5️⃣ ቶተንሀም :- 60 ነጥብ ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ? ሐሙስ - ቼልሲ ከ ቶተንሀም ቅዳሜ - አርሰናል ከ በርንማውዝ Via:tikvahethsport https://t.me/Satenawmedia1
Show all...
👏 1👌 1
#ሳያት ደምሴ ከለዛ ሽልማት መውጣቷን አዘጋጁ ገለፀ ተዋናይት ሳያት ደምሴ ከማንኛውም የሀገር ውስጥ ውድድር ራሷን ማግለሏ የዛሬ 2 ዓመት ገደማ ማሳወቋን ይታወቃል:: ይህንን ተከትሎ የለዛ ሽልማት እስከ አሁን ድረስ እያወዳደራት የነበረ ቢሆንም የእሷን ሀሳብ በማክበር አዘጋጁ ብርሀኑ ድጋፌ በማህበራዊ ገፁ ላይ ይህንን አስፍሯል:: ምርጥ ተዋናይት ምድብ ዕጩዎች 4 ቀርተዋል:: ይህም የሆነው ከአክብሮት ጋር  በሚል ተዋናይት ሳያት ደምሴ ከማንኛውም የአገር ውስጥ ውድድር ራሴን ማግለሌ ይታወቅልኝ ባለችው መሠረት ነው ይህ የሆነው ::  ሃሣቧን እናከብራለን :: 13ኛው የለዛ ሽልማት የመጨረሻ ዙር እጩዎች ድምፅ መስጠት ሚያዚያ 23  ያበቃል! https://t.me/Satenawmedia1
Show all...
🥰 2
#USA ‼️ አሜሪካ ለዓለም ፍጻሜ መሸሸጊያ የሚውል አውሮፕላን እንዲሰራ አዘዘች ይህ የክፉ ቀን መሸሸጊያ አውሮፕላን 13 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ፈጃል ተብሏል። ሴራ ኔቫዳ ኮርፖሬሽን የተሰኘው ተቋም ይህን ግዙፍ አውሮፕላን ለመስራት ተስማምቷል አሜሪካ ለዓለም ፍጻሜ መሸሸጊያ የሚውል አውሮፕላን እንዲሰራ አዘዘች፡፡ የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር አሜሪካ እንደ ኑክሌር አይነት ጦርነት ቢነሳ ከአደጋ መጠበቅ የሚቻልበት አውሮፕላን እንዲሰራ ማዘዟ ተገልጿል፡፡ እንደ ሮይተርስ ዘገባ አሜሪካ በ1970ዎቹ የተሰራ የክፉ ቀን መጠለያ አውሮፕላን የሰራች ሲሆን ይህ አውሮፕላን አርጅቷል በሚል አዲስ ልዩ አውሮፕላን እንዲሰራ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ ለክፉ ቀን ማምለጫ ይሆናል የተባለው ይህ አውሮፕላንም 13 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ይፈጃል የተባለ ሲሆን ሴራ ኔቫዳ ኮርፖሬሽን የተሰኘው ኩባንያ አዲሱን አውሮፕላን እንደሚሰራው በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡ ኢ-4ቢ የተሰኘ ስያሜ ያለው ይህ አዲስ አውሮፕላን አውሮፕላን በፈረንጆቹ 2036 ላይ እንደሚጠናቀቅም ተገልጿል፡፡ የአሜሪካ አየር ሀይል ንብረት የሆነው ይህ ልዩ የክፉ ቀን መሸሸጊያ አውሮፕላን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንትን ጨምሮ ሌሎች ቁልፍ አመራሮች፣ ባለሙያዎች እና ሌሎች እጅግ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች እና ቴክኖሎጂዎችን ይዟል ተብሏል፡፡ እንዲሁም አውሮፕላኑ እንደ ኑክሌር ጦርነት፣ አውዳሚ አደጋዎች እና ሌሎች አስጊ ክስተቶች ቢከሰቱ መሪዎች በዚህ አውሮፕላን ላይ በመሆን ትዕዛዝ እና ውሳኔዎችን እንዲያካሂዱ ያገለግላልም ተብሏል፡፡ የመሰብሰቢያ ቢሮዎች፣ የነዳጅ መሙያዎች እና የተግባቦት መሳሪያዎችም ያሉት ሲሆን አሁን በስራ ላይ ያለው የክፉ ቀን መሸሸጊያ አውሮፕላን ከ2030 በኋላ ከአገልግሎት ውጪ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡ Via:Alain https://t.me/Satenawmedia1
Show all...
👎 2👍 1 1
#Gaza‼️ የጋዛን ፍርስራሽ ለማጽዳት 14 አመታትን ሊፈጅ ይችላል‼️ 🗣ተመድ የእስራኤል እና የሀማስ ጦርነትን ተከትሎ እስራኤል በጋዛ ባደረሰችው ጥቃት ያልፈነዱ መሳሪያዎችን ጨምሮ ፍርስራሾችን ለማጽዳት 14 አመታት ገደማ ሊፈጅ እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ። በጦርነቱ አብዛኞቹ የጋዛ ነዋሪዎች ቤት አልባ እና ተፈናቃይ መሆናቸው ተገልጿል። በጦርነቱ 37 ሚሊዮን ቶን ገደማ ፍርስራሽ መከማቸቱን በተመድ ማይን አክሽን ሰርቪስ (UNMAS) ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ፒህር ሎሀመር በጀኔቫ በሰጡት ጋዜጤዊ መግለጫ ተናግረዋል። በጋዛ ምን ያህል ያልፈነዱ የጦር መሳሪያዎች መኖራቸውን መገመት እንደማይቻልም ባለሙያው ገልጸዋል። ጥቅም ላይ ከሚውሉ ተተኳሾች መካከል 10 በመቶ የሚሆኑት ከተተኮሱ በኋላ እንደማይፈነዱ ከዚህ ቀደም የተሰሩ ጥናቶች ያመላክታሉ ሲል የዘገበው ዘ ጋርዲያን ነው። https://t.me/Satenawmedia1
Show all...
#በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ቦይንግ በወንጀል እንዲከሰስ ጠየቁ! በኢትዮጵያ አየር መንገድ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን ከአምስት ዓመት በፊት ሕይወታቸውን ያጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ለአደጋው መንስዔ የሆነው የአውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ ላይ የወንጀል ክስ እንዲመሠረት የአሜሪካ የፍትህ መሥሪያ ቤትን ጠየቁ።የመንገደኞቹ ቤተሰቦች በዋሽንግተን ከአሜሪካ የፍትህ ባለሥልጣናት ጋር ሚያዝያ 16/ 2016 ዓ.ም በተነጋገሩበት ወቅት የአሜሪካው ኩባንያ ቦይንግ ለፍርድ እንዲቀርብ ጠይቀዋል። የተጎጂዎች ቤተሰቦች እና ተወካይ ጠበቆቻቸው ኩባንያው የሚያመርታቸውን አውሮፕላን ምርቶች ደኅንነት እና ጥራት ለማስጠበቅ ከሦስት ዓመት በፊት ከአሜሪካ የፍትህ ሚኒስቴር ጋር የገባውን የቁጥጥር መርሃ ግብር ጥሷል ብለዋል። የ157 ሰዎችን ሕይወት ከቀጠፈው ከኢትዮጵያው አደጋ በተጨማሪ ለ189 ሰዎች ሕይወት ማለፍ ምክንያት በሆነው የኢንዶኔዥያ አየር መንገድ አደጋ ቤተሰቦቻቸውን ያጡ ቦይንግ በወንጀል እንዲጠየቅ ለፍትህ መሥሪያ ቤቱ ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል። በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው አሰቃቂ በተባለው በቦይንግ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን አደጋዎች የ346 ሰዎች ሕይወት አልፏል።በሁለቱ አውሮፕላን አደጋዎች ሕይወታቸውን ያጡ ቤተሰቦች በቅርቡ ንብረትነቱ የአሜሪካ አላስካ አየር መንገድ የሆነ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን በበረራ ላይ ሳለ መስኮቱ መገንጠሉ ጋር ተያይዞ አሁንም የደኅንነት እና የጥራት ችግር እንዳለበት የሚያሳይ ነው ብለዋል። የአሜሪካ የፍትህ መሥሪያ ቤት በአውሮፕላንን አምራቹ ላይ ካደረገው የረዥም ጊዜ ምርመራ በኋላ ቦይንግ ለ737 ማክስ አውሮፕላኑ ፍቃድ ለማግኘት ሲል ሆን ብሎ የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር ተቆጣጣሪዎችን እንዳሳሰተ ደርሸበታለሁ በሚል “አሜሪካን ለማጭበርበር በማሴር” በሚል ከሦስት ዓመት በፊት ክስ መስርቶበት ነበር። ቦይንግ ቺካጎ በነበረው የፍርድ ሂደት በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ካሳ ለመክፈል ተስማምቶ በምላሹም የአሜሪካ የፍትሕ መሥሪያ ቤት ለአውሮፕላን አምራቹ ከ737 ማክስ ዲዛይን ጉድለት ጋር በተያያዘ በማጭበርበር ሴራ በወንጀል እንዳይከሰስ ከለላ ሰጥቶት ነበር።የአውሮፕላን አምራቹ በአደጋው ለሞቱት ሰዎች ኃላፊነቱን እንደሚወስድ እና ተጠያቂነቱን ተቀብሎ ለአሜሪካ መንግሥት፣ አደጋ ለደረሰባቸው አየር መንገዶች እና ለተጎጂዎች የሚሆን 2.5 ቢሊዮን ዶላር የቅጣት ካሳ ለመክፈል ተስማምቷል። https://t.me/Satenawmedia1
Show all...
ሳተናው ሚዲያ / Satenaw Media

ትክክለኛ ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ! #Ethiopia #Ethiopianews #Addismereja

👎 2👍 1
#ሆሣዕና '' (የዐብይ ጾም 8ኛ ሳምንት) ሆሣዕና ከስምንቱ የዐቢይ ጾም እሁዶች አንዱና የመጨረሻው ሳምንት ተብሎ የሚጠራው ከትንሣዔ ቀድሞ የሚገኝ የሕማማት መግቢያ ዋዜማ ነው። ሆሣዕና ማለት የቃሉ ትርጉም  " እባክህ አሁን አድን " ማለት ነው። ዕለቱ ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ የሚቀድሙትና የሚከተሉት ሕዝብ በተለይም ሽማግሌዎች እና ሕፃናት '' ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ ፣ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው ፤ ሆሣዕና በአርያም '' በማለት በክብር መቀበላቸው የሚታወስበት ነው፡፡  ይህ ዕለት በቤተክርስቲያን ውስጥ ዘንባባ ተይዞ፣ እየተዘመረ እጅግ ልዩ በሆነ ሁኔታ ይታሰባል
Show all...