en
Feedback
ቃ ላ ት | 𝚀 𝚊 𝚕 𝚊 𝚝

ቃ ላ ት | 𝚀 𝚊 𝚕 𝚊 𝚝

Open in Telegram

ኪናዊ መጽሔት

Show more
3 105
Subscribers
No data24 hours
+27 days
+1230 days
Posts Archive
እነሆ ቃላት ፲፫ | 13 | Words | ኪናዊ መጽሔት እርማት ፦ ፩፫ የሚለው በ ፲፫ ይነበብ። https://t.me/Words2014 . . ለአስተያየታችሁ :‑ words5102@gmail.com

0f11061a3c61e00906c70d5d0d698d26.jpg0.60 KB

📜  ሰላም! ሰላም! እንደምን አላችሁ ? የቃላት መጽሔት ቀጣይ ክፍል ወይም ❝ ቃላት 13❞  በቀናት ውስጥ ወደ እናንተ ይደርሳል። ......... ቻናሉን ለመቀላቀል :- https://t.me/Words2014 ለአስተያየታችሁ :- words5102@gmail.com እናመሰግናለን!!

እነሆ ቃላት 12 | Words | ኪናዊ መጽሔት ልዩ እትም https://t.me/Words2014 . . ለአስተያየታችሁ :‑ words5102@gmail.com

ቃላት 12 | Words | ኪናዊ መጽሔት በጣም በቅርቡ ፥ በልዩ እትም። https://t.me/Words2014 . . ለአስተያየታችሁ :‑ words5102@gmail.com
ቃላት 12 | Words | ኪናዊ መጽሔት በጣም በቅርቡ ፥ በልዩ እትም። https://t.me/Words2014 . . ለአስተያየታችሁ :‑ words5102@gmail.com

— ማንነት — የዚህኛው የቃላት ፖድካስት ቆይታ ከመጽሐፍ በምግባር ሲራጅ “እየዳነ ሄደ” እና በመስፍን ወንደሰን “ሸሙኔ” ግብዣ ይጀምራል። ርእሰ ጉዳዩንም በ“ማንነት” ጉዳይ ላይ አድርጓል። ማንነት
— ማንነት — የዚህኛው የቃላት ፖድካስት ቆይታ ከመጽሐፍ በምግባር ሲራጅ “እየዳነ ሄደ” እና በመስፍን ወንደሰን “ሸሙኔ” ግብዣ ይጀምራል። ርእሰ ጉዳዩንም በ“ማንነት” ጉዳይ ላይ አድርጓል። ማንነት በፍልስፍናዊ፣ በሥነ ልቦናዊ እና በፖለቲካዊ መድረኮች እጅግ አነጋጋሪና አከራካሪ ጭብጥ ነው። ቃላት ፖድካስት በማንነት ትርጉም፣ በማንነት ሥሪት፣ በማንነት ተፈጥሯዊ ባሕርዪ፣ በማንነት አውንታዊ እሴቶች እና በማንነት ቀውስ ዙሪያ በሚነሡ ሃሳቦች ላይ የግል ምልከታ አዘል ውይይት አድርጓል። ተጋበዙ! — Identity — We discussed issues regarding identity in this session, We have put forward our subjective takes on its multitudes. We chose a mild dive into this heated conception to properly address its controversial attributes as its a much debated subject on the realm of politics and other practical social spheres. As lightly as we could we had a bit nuanced approach to it as to get into the heart of the matter inorder to avoid its wasteful counter subterfuges which its traders employ on whole new scale for their own futile ends. As a whole we tackled it in a low key playfulness and on a human scale. Stay tuned! https://youtu.be/T3Bnr6miPb4?si=WHNGs2FBfplygQLM

— የመዝናኛው ዓለምና የንባብ ባሕል — የዚህኛው የቃላት ፖድካስት ቆይታ ከመጽሐፍ በዓለማየሁ ገላጋይ ሕይወትና ሥራዎች ላይ ያተኮረውን “መልክአ ዓለማየሁ” ከፊልም “The zone of Interest”
— የመዝናኛው ዓለምና የንባብ ባሕል — የዚህኛው የቃላት ፖድካስት ቆይታ ከመጽሐፍ በዓለማየሁ ገላጋይ ሕይወትና ሥራዎች ላይ ያተኮረውን “መልክአ ዓለማየሁ” ከፊልም “The zone of Interest”ን በመጠቆም ይጀምራል። በይዘቱም የኢንተርኔትና ማኅበራዊ ሚዲያ መተግበሪያዎች በንባብ ላይ ያሳረፉትን በጎና አሉታዊ ተጽዕኖዎች ይዳስሳል። አንድን መጽሐፍን በትረካ በመስማት (ኦዲዮ ቡክ)፣ በሶፍት ኮፒ እንዲሁም በሀርድ ኮፒ በማንበብ መሀል ያለውን ልዩነት ይዳስሳል። እንዲሁም ባለንበት ፈጣን ዓለምና የመዝናኛ ዘመን ንባብን እንዴት ማስኬድ ይቻላል፣ የንባብና የመጽሐፍ የወደፊት ዕጣ-ፈንታስ ምንድነው የሚለውን ከግል ልምምዳችን አንጻር ተወያይተናል። https://youtu.be/LEQMzzDwMAo?si=WYg8KvwbgHywMTSV

ቃ ላ ት - 11.pdf26.30 MB

📜  ሰላም! እንደምን አላችሁ ? የቃላት መጽሔት ቀጣይ ክፍል ወይም ❝ ቃላት 11❞  በቀናት ውስጥ ወደ እናንተ ይደርሳል። ......... ቻናሉን ለመቀላቀል :- https://t.me/Words2014 ለአስተያየታችሁ :- words5102@gmail.com እናመሰግናለን!!

From antiquity to our recent era there has always been a manifold friction between society and the individual. Where does those delicate boundaries which mark their divergence manifest and what common ground does they share. Whats the basic issue beyond those delicate boundaries which mark their divergence manifest and what common ground do they share. Whats the basic issue beyond the conflict & convergence of those two. We had took a moment of reflection on a conceptually limited sense of the terms in this episode. our cinema and book recommendations have been included as usual, stay tuned! https://youtu.be/lMAk0k1V7cs?si=lujmHQG5rgmU0CHk

Qalat Podcast Episode 13 Description:- "Art for Art's sake" is a second half of 19th century European phenomenon which lasted for a half century and ended at the dawn of 20th century leaving its profound mark on every aspect of modernism. From Modern art to our era of postmodernism this artistic movement has imprinted a paradigmatic shift in every way we perceive the whole business of art today. In this episode We have discussed what art meant & its implications, capabilities and various manifestations in our collective human affairs. Is art purposeless? Does it have an assigned social utility? What truly is the ultimate goal of the artist? And other related issues have been raised in this session. Our friend Dawit berhanu has joined us as usual. Stay tuned! https://youtu.be/-hYAFoGJAVM?si=UTm81rDstOMIUdqC

ከዚህ በፊት የቃላት ፖድካስት በሰዋሰው መተግበሪያና በyoutube የድምጽ ስርጭት ሲያደርግ ቆይቷል። አኹን ደግሞ በመጀመሪያው የምስል (video) ስርጭት ከደራሲ ያዕቆብ ብርሃኑ ጋር በሥራዎቹና በተ
ከዚህ በፊት የቃላት ፖድካስት በሰዋሰው መተግበሪያና በyoutube የድምጽ ስርጭት ሲያደርግ ቆይቷል። አኹን ደግሞ በመጀመሪያው የምስል (video) ስርጭት ከደራሲ ያዕቆብ ብርሃኑ ጋር በሥራዎቹና በተያያዥ ኪናዊ ጉዳዮች ላይ ተጨዋውተናል። ያዕቆብ ቀደም ብሎ አምስት መጻሕፍት ያበረከተልን ሲኾን፣ በዚህ ቆይታ አጠቃላይ ከኾነ ግላዊ ምልከታ ጀምሮ የሥነ-ጽሑፍ ጉዞውን ያስቃኘናል። ብዙ ነገሮች የተነሡበትን ይህንን ቆይታ ከሥር ያለውን ሊንክ ተከትላችኹ ትመለከቱት ዘንድ ስንጋብዝ፣ እግረ-መንገዳችኹን የሰዋሰው ፖድካስት ኔትወርክን የዩቱብ አድራሻ ሰብስክራይብ በማድረግ ቀጣይ ፕሮግራሞችን እንድትታደሙ በማስታወስ ጭምር ነው። https://youtu.be/SKi7mFCfLng?si=GEZjrF83fVyq90lw

ዘመናችን በወል የታመምንበት ነው። ስብራታችን፣ ውድቀትና መከራችን እንደ ትውልድ በለጋው እድሜያችን ልክ የተሰፋ አይመስልም። የዘመን ተጋሪያችን ወጣቱ ደራሲ እሱባለው አበራ ያለንበትን ምስቅልቅል አው
ዘመናችን በወል የታመምንበት ነው። ስብራታችን፣ ውድቀትና መከራችን እንደ ትውልድ በለጋው እድሜያችን ልክ የተሰፋ አይመስልም። የዘመን ተጋሪያችን ወጣቱ ደራሲ እሱባለው አበራ ያለንበትን ምስቅልቅል አውድ ሊፈክር የምናብ ጸጋን ለብሶ በቃል ኪነት የኖረውን ሕይወት ወርድና ቁመት መትሮ እንደ ግለሰብ፣ እንደ ማኅበረሰብና እንደ ሀገር የጠራ ምስላችን እንዲህ ያለ ነው ሊለን መጥቷል። ሙከራው ፍፁም ኪናዊ ነው። የምርመራ ቀስቱ ውጫዊ ብቻ ሳይሆን ወደ ውስጥም ነው። ጥቁምታው ወደ 'እነርሱ!' ብቻ ሳይሆን ወደ 'እኛም!' ጭምር ነው። ተጠየቁ ላንተና ላንቺ ብቻ ሳይሆን ለእኔም ነው። ኀሠሣው ከቤተሰብ፣ ማኅበረሰብና ሀገር አውድ ቢነሣም የተሰፋው በሰው ልክ ነው። እሱባለው “ፀሓይ ከጨለማዬ ምን አለሽ?” ብሎ በሰየመው ሁለተኛው ወጥ የልብ ወለድ ሥራው (novel) የማኅበረሰብን ነገረ ሰብዕ፤ ቅስም ሰባሪ ቁልቁል ጉዟችንን፤ ሳይጠና የተሰበረን፣ ሳያብብ የተቀጨን ትውልድ አራራይ ሥነ ጽሑፍ ባስታጠቀው ኪናዊ ማጥለያና ከሀገሩ ሊቅ ሙዚቃዊ ድርሰት ባለመደው አዲስ የጽሑፍ ቅርጽ አሽቶ የበሽታችንን ልብ አልቆ ነግሯል። ከበኩር ሥራው “ትዝታሽን ፡ ለእኔ ፥ ትዝታዬ ፡ ለአንቺ” በተለየ አዲስ ሙከራን ይዞ የመጣበት የተዋበ ድርሳን ነውና ቃላት መጽሔት ለባልንጀራችን እሱባለው እንኳን ለዳግም ህትመት በቃህ እያልን መጽሐፉ ነገ ዕለተ ረቡዕ ለንባብ ስለሚበቃ ለቃላት መጽሔትና ፖድካስት ቤተሰቦች በተገኘበት እንዲነበብ ጋብዘናል።

Episode - 10| ተማህልሏዊነት | Mysticism - ተማህልሏዊነት (mysticism) ምንድር ነው? የዚህ መንፈሳዊ ልምምድ ቀጠናዊ(ምስራቅ-ምዕራብ) እና ፍልስፍናዊ (theistic,monisti
Episode - 10| ተማህልሏዊነት | Mysticism - ተማህልሏዊነት (mysticism) ምንድር ነው? የዚህ መንፈሳዊ ልምምድ ቀጠናዊ(ምስራቅ-ምዕራብ) እና ፍልስፍናዊ (theistic,monistic,naturalistic) መልኮች እንዴት ያሉ ናቸው? ልምምዱን በግል እንዴት እንረዳዋለን? ተማህልሏዊነት ከጥንታዊ ባህሎች እስከ ዘመናዊው አውድ ምን ይመስላል? በሀይማኖት፣ በፍልስፍና፣ በስነልቦና እና በኪናዊ ስራዎች(በስነ-ግጥም፣ ስነ-ፅሁፍ፣ ሙዚቃ) ውስጥ እንዴት ያለ አንደምታ አለው? እንደ አንድ ሰዋዊ ልምምድ ለዘወትር ህይወታችን ዋጋው ምንድር ነው? ይህ ረቂቅ መንፈሳዊ የሀሰሳ መንገድ ዛሬ ቁሳዊነቱ አይሎ በተገለጠው ዘመናዊ የተጨባጭነት አለም ውስጥ እንዴት ያለ ሚና ይኖረዋል? እና መሰል ሀሳቦች የተነሱበት የቃላት ፖድካስት 10ኛው ኤፒሶድ በሰዋሰው መተግበሪያ በነፃ ተለቋል። በዚህኛው ጭውውት አንድ እንግዳ ነበረን፤ ዮሴፍ ይድነቃቸው ይባላል። መምህር ነው። ግጥሞችንም ይፅፋል። ለመካከለኛው ምስራቅ ገጣሚያንና ላነሳነው ርዕሰ ጉዳይ የነፍስ ቅርበት ስላለው ጥሩ ጊዜ ነበረን። ያድምጡን። Mysticism is a doctrine of an immediate spiritual intuition of truths believed to transcend our ordinary understanding. Our Mystic experiences which range from commonplace contemplative rituals to the sophisticated altered state of consciousness ecstasies share a common deep & ultimate human longing for the abstract immaterial conceptions. We had dealt with everything mystical, stay tuned!

Episode - 9| ራስን ማጥፋት | suicide | ስር የሰደደ ማህበራዊ ክስተት ከሆነ የሰነበተው የራስን ማጥፋት ዋና መንስኤዎች ምንድር ናቸው? ራስን ማጥፋት (suicide) ከጥንት እስከ ዛሬ
Episode - 9| ራስን ማጥፋት | suicide | ስር የሰደደ ማህበራዊ ክስተት ከሆነ የሰነበተው የራስን ማጥፋት ዋና መንስኤዎች ምንድር ናቸው? ራስን ማጥፋት (suicide) ከጥንት እስከ ዛሬ ምን መልክ ነበረው? ሊብራሉ የምዕራቡ አለም እንደሚያምነው ግለሰባዊ መብት ነው ወይስ ወግ አጥባቂው ከፊሉ የምስራቁ አለም በማህበራዊ ውሎቹ እንደሚፈርጀው ወንጀል ነው? ራስን ማጥፋት በሀይማኖታዊ፣ ፍልስፍናዊ፣ ማህበረሰባዊ፣ ኪናዊና ሰዋዊ ማንፀሪያዎች ልኬት እንዴት ይመዘናል? እንደ አንድ ማህበራዊ ክስተት መፍትሄ ያስፈልገዋል? ከሆነ እንዴት ያለ? እኚህና መሰል ሀሳቦች የተነሱበት የቃላት 9ኛ ኤፒሶድ በሰዋሰው መተግበሪያ ላይ ተለቋል። መደበኛ የመፅሐፍ፣ ሙዚቃና ፊልም ጥቆማዎችም ተካተዋል። እንደተለመደው ወዳጃችን ዳዊት ብርሀኑ ከኛ ጋር ቆይታ አድርጓል። ይከታተሉ። :- As a widely undertaken human phenomenon, suicide marks our existential predicament in the light of consequential social, cultural & economical dysfunctions which manifest in the gloomy collective arena of life. From mental and emotional turbulence to complex socioeconomic deadlocks which pose as its major causes to individual's existential subjective demands how do we approach it personally? How is it perceived in our social context? and other demanding issues with in these regard have been raised in this session. Stay tuned!

Qalat Podcast Episode - 8 | Education | ትምህርት Episode description :- With Dr. Eguale G/yohannes's book "የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ" as o
Qalat Podcast Episode - 8 | Education | ትምህርት Episode description :- With Dr. Eguale G/yohannes's book "የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ" as our guiding reference we have dived deep into multifaceted pros & cons of the so called modern education ranging from our national encounter with its historic emergence to its worldwide implications in this episode. We have dealt with Eguale's seminal work on the subject to enumerate its historical evolution here and abroad, its earnest intentions as a social precursor of culture & how it manifested in all the fundamental aspects of human civilization. What is education basically? How do we grasp the very concept of it? What is its genuine purpose? Where does our national modern education stand in the light of thorough evaluation? Is there an Ethiopian methodology for education? These and many other questions have been tackled in this session. Our friend Dawit Birhanu has joined us as usual, stay tuned! 👇 https://shorturl.at/azNX7 #sewasewmultimedia #sewasew_podcasts_network

🔍 በተለያየ ምክንያት የቃላት ፖድካስትን በሰዋሰው መተግበሪያ ለማድመጥ ዕድል ያላገኛችሁ፤ አሁን በ “Sewasew Podcasts Network” የዩቲዩብ ቻናል በኩል የቃላት ፖድካስት ዝግጅቶችን ከመጀመሪያው ክፍል ጀምሮ በቀላሉ መስማት ትችላላችሁ፦ የመጀመሪያው ክፍል የቃላት ፖድካስት ዝግጅት እነሆ፦ https://youtu.be/AtI1WhsVoZU?si=o40wpJYVZsLcFlVV መልካም ቆይታ!

📻 ቃላት ፖድካስት 🎬 ክፍል 7 🎧 በሰዋሰው መተግበሪያ ላይ በነፃ ያድምጡ። ርእሰ ጉዳይ:— የፈጠራ ሥነ-ጽሑፍ (ልብ ወለድ) ለምን እናነባለን? በዚህኛው የቃላት ፖድካስት ክፍል ርእሰ ጉዳያችንን
📻 ቃላት ፖድካስት 🎬 ክፍል 7 🎧 በሰዋሰው መተግበሪያ ላይ በነፃ ያድምጡ። ርእሰ ጉዳይ:— የፈጠራ ሥነ-ጽሑፍ (ልብ ወለድ) ለምን እናነባለን? በዚህኛው የቃላት ፖድካስት ክፍል ርእሰ ጉዳያችንን በልብ ወለድ ንባብ አስፈላጊነት እንዲሁም፦ - ኢትዮጵያዊ የሚባል ሥነ-ጽሑፍ አለ ወይ ? - አንድን ሥነ-ጽሑፍ ኢትዮጵያዊ የሚያደርገው ምንድነው ? - ከሥነ-ጽሑፍ የሚጠበቅ ሚና አለ? ካለስ ምንድነው? በሚሉና በሌሎችም ተያያዥ ጉዳዮች ላይ አድርገናል። በዚህኛው የቃላት ፖድካስት ሄኖክ በቀለ፣ መርሐጽዮን ጌታቸው፣ እሱባለው አበራ እና ዳዊት ብርሃኑ ቆይታ አድርገናል። ተጋበዙ! አስተያየቶቻችሁን words5102@gmail.com ላይ አድርሱን።

📻 ቃላት ፖድካስት 🎬 ክፍል 6 🎧 በሰዋሰው መተግበሪያ ላይ ያድምጡ። ርእሰ ጉዳይ:— አነቃቂ ንግግር በዚህኛው የቃላት ፖድካስት ክፍል ርእሰ ጉዳያችንን አነቃቂ ንግግርና ተናጋሪዎች ላይ አድርገና
📻 ቃላት ፖድካስት 🎬 ክፍል 6 🎧 በሰዋሰው መተግበሪያ ላይ ያድምጡ። ርእሰ ጉዳይ:— አነቃቂ ንግግር በዚህኛው የቃላት ፖድካስት ክፍል ርእሰ ጉዳያችንን አነቃቂ ንግግርና ተናጋሪዎች ላይ አድርገናል። በዚህኛው የቃላት ፖድካስት ሄኖክ በቀለ፣ መርሐጽዮን ጌታቸው፣ እሱባለው አበራ እና ዳዊት ብርሃኑ ቆይታ አድርገናል። ተጋበዙ!

ቃ ላ ት - 10.pdf21.87 MB