cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

FutureX

The future starts here!

Show more
Advertising posts
8 064
Subscribers
+3124 hours
+1987 days
+71330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የምትችለውን ሁሉ አድርግ! ሁልጊዜም ምርጫህ ህይወትህን ይወስነዋል፤ ዛሬ የምትወስነው እያንዳንዱ ውሳኔ ውጤቱን የሚያሳይህ ነገ ነው። ትምህርት የዚህ አለም መጨረሻ አይደለም! ግን ጊዜህን ሰጥተህ እየተማርክ እስከሆነ ድረስ በደምብ ተማር! የምትችለውን ካደረክ ራስህንና የሚወዱህን ማስደሰት ትችላለህ። የሚገርም ምሽት ተመኘንላችሁ🙏 @Futurexethiopia ለውጥ አሁን ይጀምራል!
Show all...
👍 52👏 6🔥 3🕊 1
የትኛውን ትመርጣለህ? በሰዎች መካከል ትልቁን ልዩነት የሚፈጥረው ለአንድ ተመሳሳይ ነገር የሚመርጡት ምርጫ ነው። ነገን አስበህ አሁን ከለፋህ፤ የፈለከውን ሁሉ ታሳካለህ። አሁን የማይጠቅምህን በማድረግ ጊዜህን ካሳለፍክ ነገ በሌሎች ስኬት ትቀናለህ። ተማሪ ከሆንክ አጥና! ፈተና ከደረሰ ብዙ ጥያቄ ስራ! ራስህን በአይምሮና በስነልቦና ለፈተና አዘጋጀው! ነገ ስታስበው የሚያኮራህን ነገር አሁን ምረጥ። የሚገርም ምሽት ተመኘንላችሁ🙏 FutureX ለውጥ አሁን ይጀምራል!
Show all...
👍 71 13🔥 11
ለፈተና ምን ያህል ተዘጋጀህ? ጊዜያዊ ስሜትህን ተቆጣጠር! አሁኑኑ ልደሰት ማለቱን አቁም! ከጥናት የሚያዘናጉህን ነገሮች እምቢ በል! ሁሉም ከፈተና በኋላ ይደርሳል፤ እንደልብህ ፈታ ትላለህ። አሁን ግን በትኩረት አጥና፣ ብዙ ጥያቄ ስራ። ማትሪክ ማለት ብዙ ጥያቄ የሰራ ተማሪ የሚሰቅለው ፈተና ነው፤ አንተ ምን ያህል እየተዘጋጀህ ነው? የሚገርም ምሽት ተመኘንላችሁ🙏 FutureX ለውጥ አሁን ይጀምራል!
Show all...
100👍 24🔥 9🙏 1
ጥረትን መቀጠል! ራሳችንን ለማሳደግ ከኛ የሚጠበቀውን በየቀኑ በትንሹ እያደረግን ከቀጠልን ሁላችንም ያሰብነው ከፍታ ላይ እንገናኛለን! ትንሽ ጠብታ ልፋት ተጠራቅሞ ተዓምር ይሰራል። እውነተኛ ለውጥ የሚመጣው በሂደት እንጂ በድንገት አይደለም! ስለዚህ ጥረታችንን አናቆምም💪 ልዩ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏 @futurexethiopia ለውጥ አሁን ይጀምራል!
Show all...
👍 67🥰 10 4🕊 1
ፅናት! "አሁን የምነግራችሁን የስኬት ሚስጥር ምንም ነገር አይተካውም። ጉብዝና አይተካውም! የአይምሮ ብስለት አይተካውም! እድለኛ መሆን አይተካውም! በቃ እሱን የሚተካ የለም....ፅናት ይባላል" ይለናል ካልቪን ኮሊጅ የተባለ የአሜሪካ መሪ። በዚህ ምድር የተነሳ የትኛውንም ስኬታማና ታላቅ ሰው ብትመለከቱ ከየትኛውም ችሎታው ይበልጥ ለአላማው ያለው ፅናት የሚፈልግበት አድርሶታል። ምርጥ ውጤት ለማምጣት በየቀኑ በፅናት መዘጋጀት አለብህ! ማራኪ ምሸት ተመኘንላችሁ🙏 @FutureXethiopia ለውጥ አሁን ይጀምራል!
Show all...
👍 100 16👏 10
ከባዱ ችግርህ ካንተ በላይ የሆነ ይመስልሀል እንጂ አንተን ማንበርከክ አይችልም! ከሞት በላይ ምን ከባድ ችግር አለ? አትርሳ ወዳጄ እሱ እንኳን ተሸንፏል እኮ! ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ ድንቅ የትንሳኤ በዓል ተመኘን🙏 @futureXethiopia ለውጥ አሁን ይጀምራል!
Show all...
🥰 65👍 23 11😱 5🤔 3🔥 2
ተዓምር መስራት! ሰው ምንድነው ቢሉ ደጋግሞ ያሰበውን ነው ይባላል፤ ስለዚህ ለማን ብለህ ነው አብዝተህ የጎደለህን ከሰው ያሳነሰህን የምታስበው?! በቃ ተዓምር መስራት እንደምትችል ባንተ ምክንያት መጀመሪያ የራስህ ከዛ የቤተሰቦችህ ህይወት እንደሚቀየር አስብ እሱን እውነት ለማድረግ የምትችለው ጥግ ድረስ ጣር የቀረውን ለፈጣሪ ተወው! ሰናይ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏 @FutureXethiopia የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
Show all...
👍 116 23🤝 8🕊 6🥰 3👏 2
ስንፍናን ማሸነፍ! ሮኬት ወደ ህዋ ሲሄድ አብዛኛውን ጉልበት የሚጨርሰው እስኪነሳ ነው፤ የመሬትን ስበት አሸንፎ በሚገርም ፍጥነት ከፍ ማለት ከጀመረ በኋላ ያንን ፍጥነቱን ማስጠበቅ ቀላል ነው። በህይወትም እንዲ ነው ራስህን ለመለወጥ ስትነሳ መጀመሪያ አካባቢ የሚገጥምህን ስንፍና እና መሰልቸት ካሸነፍከው በቃ የምትፈልገውን ነገር ከማግኘት የሚያቆምህ ነገር የለም! ብሩህ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏 @FutureXethiopia የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
Show all...
👍 96🙏 11🕊 5 3🔥 2
ዳይ ወደ ስራ! ከምታውቃቸው ሰዎች ሁሉ ጠንክረህ የምትለፋው አንተ መሆን አለብህ፤ ዕድለኛ ስለመሆን አታስብ! ተዓምር የምትሰራው በማይቆም ጥረትህ ነው። አሸናፊ መሆን ማለት ጥሩ ስሜት ላይ ባትሆንም እንኳን የጀመርከውን መቀጠል ነው። ጀግና ጥረቱን የማያቆም ነው! ዳይ ማቆም የለም! @Futurexethiopia ለውጥ አሁን ይጀምራል!
Show all...
👍 79 22🥰 7🕊 4🔥 2🙏 2
ራስን መቀየር! የማትቆጣጠራቸው ነገሮች ላይ ጊዜህን ልታጥፋ ስትል ንፋስ ልትጨብጥ እየሞከርክ እንደሆነ አስብ፤ የሰዎችን ፀባይ፣ የሀገርህን ሁኔታ፣ የኑሮ ውድነቱን፣ የአለቃህን ወይ የአሰሪዎችህን ፀባይ መቀየር አትችልም! ግን እንደምትችለው እርግጠኛ የምትሆንበት አንድ ነገር አለ...ራስህን መቀየር ግን ትችላለህ! እመነኝ ወዳጄ አንተ ከተቀየርክ ነገሮች ሁሉ ይቀየራሉ፤ ካንተ የሚጠበቀው ለራሴ ያለሁት ራሴ ነኝ ብሎ ማመን እና የተግባር ሰው መሆን ነው። @futurexethiopia ለውጥ አሁን ይጀምራል!
Show all...
67👍 33🕊 4🥰 3😎 2