en
Feedback
islamic📚Post

islamic📚Post

Open in Telegram

አሰላምአለይኩም ያጀመአ በቻናላችን * አስተማሪና አዝናኝ ታሪኮች *የተለያዩ የስነ-ፅሁፍ ዘርፎች * አዳዲስ ነሺዳዎች * ሀዲሶች *ቁም ነገር አስጨባጭ ቂሳዎች * ወቅታዊ መረጃዎች * profile pic etc ........ ለሀሳብ አስተያየት 👇👇👇👇👇 @amunaaaaaa

Show more
215
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
አንድ ወቅት ከዉጪ ሀገር የመጡ እንግዶችን የመቀበል ግዴታ ተጣለብኝ። ይዣቸዉ ስንከራተት ሰንብቼ ድንገት ነዳያን ወደበዙበት ቦታ እግር ጥሎን ሄድን። . የጎዳና ተዳዳሪዎቹ፣ ነዳያኑ ልብሳቸዉን አዉልቀዉ ቅማል ሲገድሉ፤ ቆንጅዬዋ ቀበጧ እንግዳዬ ተመለከተች፤ ለረዥም ሰአት አለቀሰች፤ አዘነች። እኔም ማዘኗ አሳዝኖኝ <እንደምትመለከችው ህዝቡ በድህነት ነው የሚኖረዉ፤ ብታለቅሺ አይፈረድብሽም> አልኳት።ከአፌ ቀበል አድርጋ <እንዴት ነፍሳት ይገላሉ?> አለች። . ከዛች ቅፅበት አንስቶ ያለቀስኩት እኔ ነኝ! https://t.me/Islamicpost2399

...........ፍቅር ብዙ የፍቅር አይነት አለ ። የሁሉም ፍቅር ህመም አለው ። የቁርኣን ፍቅር ሲቀር እርሱ ግን ከሁሉም ይበልጣል ሠላምና እርካታን ይሰጣል ። ቁርኣን የልብ ብርኃን ነው ። አላህ ሆይ ልባችንን በቁርኣን ፍቅር ሙላልን 🤲 🍁 የዕለቱ መልእክቴ........

የሀቂቃ ደስታ ያለው በዲን ነው ማይቋረጥ ማያልቅ ለዛ ያለው ሰኪና ያለው ደስታ በዲን አለ አላህን በመውደድ ለአላህ በመዋረድ ዝቅ በማለት እሱን በመገዛት እፊቱ በማልቀስ ውስጥ አለ ሌላው ፌክ ነው የፎቶ ደስታ ነው የሀቂቃ አደለም ከኋላው ማዘን ያለበት ነው ፀፀት ያለበት ነው ደስታውም ተወጋጅ ነው በትዳር በልጅ በሪዝቅ ሀቂቃ ደስታ የለም ዱንያ ላይ ያለ ነገር ሁሉ ተቀያያሪ ነው ዛሬ ያለ ነገ የለም የሌለው ደሞ ይኖራል የተደገፍነው ነገር ይሸሻል አላህዋን የተጠጋን እንደሆን ግን ዳኢም ደስታ ዳኢም ድጋፍ ማግኘት ነው የሆነ ቀን ምናጣው አደለም በውለታ ሚያዝም አደለም እያመፅነውም ያ አላህ ያልን ቀን በቀልባችን ሰኪናን ደስታን የሚያደርግ አላህ አለን ሀጃ አስጨንቆን መግቢያ አጥተን ነገሩ ውስብስብ ብሎብን ልክ ተናንሰን አላህዋ ጨነቀኝ መውጫ ቀዳዳን አብጅልን ብለን የልባችንን ባንሾካሸኩን ሰከንድ ልባችን እረፍት ያገኛል የሀጃው መሳካት አለመሳካትን ሳንጠብቅ ወዲያው ጣፋጭ የሆነች እርጋታን እናገኛለን ወደሱ መጠጋት መዋደቅን እሱው ይስጠን በፍቅሩ ከሌሎች ነገራት መራቅን ይወፍቀን አልሀምዱሊላሂ ዳኢመን ወአበዳ💚 https://t.me/Islamicpost2399

🌙✨የለሊት አውራዶች ና ጥቅሞቻቸው✨🌒 -----°-----°-----°___°------°-------°------                                      🌟سورة الواقعة🌟 ❝ሁሌ ምሽት ላይ ሱረቱል ዋቂኣን የሚቀራ ሰው ድህነት አይነካውም❞ አሉ። ሠይደልዉጁድﷺ🥰 [ البيهقي] ኢብኑ መስዑድም ሴት ልጆቻቸውን ሁሌ ሱረቱል ዋቂኣህን እንዲቀሩ ያዟቸው ነበር። ✨ሱሩቱ ራህማን፥ ሱረቱል ዋቂዓህ ና ሡረቱል ሀዲድን ሁሌ ምሽት የሚቀራ ከፊርደውሰል ጀነት ሠዎች ይሆናል። 🔅በሌላ ሀዲስ፡ ❝ሱረቱል ዋቂዓህ የሀብት ሹል ናት። ቅሩት ለልጆቻቹም አስተምሯቸው❞። በሌላ ዘገባ ፡ ሴቶቻቹሁንም አስተምሯቸው.. ❝አዒሻን እንድትቀራ አዝዣለሁ❞ አሉ። ሠይደልዉጁድﷺ🥰 [ فضائل القرآن ] #አህሉል_ዊርዲ https://t.me/Islamicpost2399

አለመፍረድ። ትንሽ በእድሜ ከፍ ስንል፣ ትንሽ በሚፈትኑ የህይወት ተሞክሮዎች ስናልፍ፣ ትንሽ በኢማን መጨመርና መቀነስ ውስጥ ስንመላለስ… የምንረዳው እውነታ ነው። በቃ… "ምናልባት" ብለን ማሰብ እንድንችል የሚያደርገን የብስለት ደረጃ ነው። በሆነ መልኩ ዱንያ ያንገላታቻቸውን ሰዎች ስታይ  … "ገንዘብ እንዴት እንደሚሰራ ማያውቁ ሞኝ ድሆች" ብለህ ጭራሽ እንዳታስብ። ጭራሽ። ትዳር ዓለም ያልዘለቀላቸውን ሰዎች ስታይ "የባህሪ ደካሞች፣ ጥሬዎች" ብለህ እንዳትፈርድ። እነርሱ ብቻ የሚያውቁት ብዙ ማታውቀው ነገር አለ። "ምናልባት" የሚያስብልህ። https://t.me/Islamicpost2399

➥የሰው ልጅ፦ ትምህርቴን ስጨርስ አርፋለሁ.. ይላል ስራየን ስጀምር አርፋለሁ... ቤት ሲኖረኝ አርፋለሁ... ትዳር ስመሰርት አርፋለሁ... ልጆች ከወለድኩ በኃላ አርፋለሁ... ልጆቼን ካደረስኩ በኃላ አርፋለሁ .. ልጆቼን ከዳርኩ በኃላ አርፋለሁ... ይላል አንድ ቀን አርፋለሁ እንዳለ አንድ ቀን ያርፋል ሰዎችም ምስኪን እንደለፋ አረፈ ይሉታል። አርፋለሁ ይልና ሳያርፍ ይለፋና ላያርፍ ለፍቶ ያርፋል ሞቶ። አወይ ዱንያ🥺 ያረብ መጨረሻችንን አሳምርልን https://t.me/Islamicpost2399

እየሰገደ ሞተ፣ሱጁድ ላይ እያለ ሞተ፣ፆመኛ ሁኖ ሞተ፣እሄ ነገር በአጋጣሚ የመጣ ወይንም የሚመጣ እንዳይመስልህ፡፡የሰው ልጅ ዱንያ ላይ ሲያበዛው በነበረው ነገር ላይ ነው የሚሞተው፡፡እራሳችንን እንመርምር ምን ላይ ነን?😢 https://t.me/Islamicpost2399

🧡ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1445 የኢድ አል-አድሀ የዓረፋ በዓል በሰላም አደረሳቹሁ! ኢድ ሙባረክ ተቀበለሏህ ወሚና ወሚንኩም ሷሊሀል አዕማል። ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ @Alif_i
+2
🧡ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1445 የኢድ አል-አድሀ የዓረፋ በዓል በሰላም አደረሳቹሁ! ኢድ ሙባረክ ተቀበለሏህ ወሚና ወሚንኩም ሷሊሀል አዕማል።      ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ @Alif_islamic_Posts @Alif_islamic_Posts 

ዒድ ተክቢራ! https://t.melimugenet

photo content

🌙🌙ዒድ ሙባረክ🌙🌙 🌙تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال🌙 🌙እንኳን ለ1445ኛው የዒድ አል_ኣድሃ በዓል በሰላም አደረሳችሁ🌙 በዓሉ የሰላም እና የጤና እንዲሆንላችሁ እየተመኘን አላህ የ10ቱቀን ዙልሂጃ በረካ ከገጠማቸው የአላህ ምርጥ ባሮች ያድርገን ሁሌም በኢማን እና በአፊያ ጠብቆ እንዲያደርሳችሁ አላህን እንለምነዋለን። https://t.me/Islamicpost2399

🌙🌙ዒድ ሙባረክ🌙🌙 🌙تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال🌙 🌙እንኳን ለ1445ኛው የዒድ አል_ኣድሃ በዓል በሰላም አደረሳችሁ🌙 በዓሉ የሰላም እና የጤና እንዲሆንላችሁ እየተመኘን አላህ የ10ቱቀን ዙልሂጃ በረካ ከገጠማቸው የአላህ ምርጥ ባሮች ያድርገን ሁሌም በኢማን እና በአፊያ ጠብቆ እንዲያደርሳችሁ አላህን እንለምነዋለን። https://t.me/Islamicpost2399

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥   ስማኝ ወንድሜ ስሚኝ ውድ እህቴ ✍ አንተ ወንድሜ ስልክ ምትደውለውና መልክት የምትልክላት ለምንድን ነው የእውነት ምትወዳት ከሆነ የቀድሞውን ስህተት ማስተካከል ከፈለክ በቤተሰብ በኩል ሂደህ በሩን አንኳኳ... አላህ እንዳለው ወደ ቤቱ ኑ በበሩ በኩል አለበለዚያ ግኑኝነትህን አቋረጥ የሸይጧንን በር ዝጋው። አንችም እህቴ እንደሚወድሽ ካወቅሽ እንዲያገባሽ ጠይቂው እንዲያገባሽ ስጠይቂው አላስፈላጊ ምክኛቶችን የሚደረገድርልሽ ከሆነ አይወድሽም ማለት ነው። ለሃራም ነገር እያመቻቸሽ መሆኑን አትርሺ። እሽ ብሎ እንደሚያገባሽ ከነገረሽ ጥሩ ባስቸኳይ ወደ ትዳር ግቢ áŒáŠ• ያገባኛልና ብለሽ አላስፈላጊ ግኑኝነት እንዳታገርጊ ሂወትሽን ታበላሽዋለሽ አደራሽን አደራሽን እህቴ በዚህ ምንገድ ስህተት እንዳትሰሪ። ብዙዎች ያገባኛል በሚል ምክንያት ያለ ሂጃብ ፎቶ ይልካሉ ተገናኝተው ይተቃቀፋሉ ይሳሳማሉ ብዙ ድምበር ያለፉ ነገሮችን ያደርጋሉ ዚና ሳይቀር።❗️ ሱብሃላህ ቆይ ከመቼ ወዲህ ነው ሃላል በሃራም መንገድ ተሳክቶ የሚያውቀው።ቢሳካስ እንዴት ነው ደስተኛ መሆን ሚቻለው። በጣም የሚያሳዝነው ያለ ሂጃብ ተገላልጠው ፎቶ ይልኩና በኋላ ከዚህ ሃራም ምንገድ ለመውጣት ሲፈልጉ ከተለየሽኝ ከኔጋ ያለውን የሚስጥር ፎቶ ባደባባይ አወጣዋለሁ ብሎ ያስፈራራታል። ተገናኝተን አብረን ጊዜ ካላሳለፍን በሚዲያ አሰራጨዋለሁ እያለ ያስፈራራታል አስቡት ያኔ ምንም የማታውቀዋ ልጅ ሳትፈልገው ሀራም ነገር ትሰራለች ከአላህ ፊት መዋረድን ረስታ በሰው ዘንድ መዋረድን ትፈራለች። አስቡት በራሷ ፎቶ የማትወጣው መቀመቅ ውስጥ ትገባለች። እና እባካችሁ ተጠንቀቁ እህቶቼ ፎቶ መላላክም ይቅርባችሁ። ወላሂ እህቴ በዚህ መንገድ አልፈሽ ሰላም እሆናለሁ ብለሽ እንዳታስቢ የገቡበትም በጭንቀት ተወጥረው ነው ያሉት ሾል ልሹ መስራት አቅቷቸው። ወላሂ ሂወት ምስቅልቅል ነው ሚያወጣው አግብተሽም ጭንቀቱ አይተውሽም አደራሽን ይሄን መንገድ እንዳትሄጂው። በዚህም መንገድ ላይ ከሆንሽ ተውበት አድርገሽ ወደ አላህ ተመለሽ አንዴ ወንጀል ሰርቻለሁ ማን ያገባኛል ከተበላሸሁ በኃላ ብለሽ እንዳታስቢ ወላሂ ወደ አላህ ከመጣሽ አላህ አይተውሽም በደስታ ነው ሚቀበልሽ።   ከዚህ ውጭም መፍትሄ የለም ሂወትሽም ሚስተካከለው በዚህ መንገድ ብቻ ነው።    እና እህቴ በቶሎ አግባኝ በይው ማግባት ካልቻለ እራቂው  ሌሎች የውሸት ምክኛቶችን የሚያቀርብልሽ  ከሆነ  ባስቸኳይ አቋርጭ የሚፈልግሽ ለግዚያዊ ስሜቱ ማብረጃ ነው ማለት ነው። áˆšá‹ˆá‹ľáˆ˝ ከሆነ ሲያቀርባቸው የነበሩትን የውሸት ምክንያቶች አስተካክሎ ያገባሻል። ንቂ እህቴ  እስከመቼ  ትዘናጊያለሽ ወላሂ በዚህ መንገድ ብዙ ሴቶች እያለቀሱ ነው። በውስጥ መሾመር በዚህ መንገድ የሚያማክሩኝ ሴቶችን ብትሰሙ ወላሂ በጣም ታዝናላችሁ እምባየ ሁሉ ይቀድመኛል። ባለትዳር ሁነው ልጅ ኑሯቸው ከካፊር ጋር ሚማግጡ ሁሉ አጋጥሞኛል አስቡት ይሄን ያክል ድምበር አልፈናል።❗️ በጣም አዘንኩ በሙስሊሙ ሁኔታ። እና ውድ እህቴ ይህ ያለሽበትን ትንሽም ብትሆን ከሃራም ፍቅር ግኑኝነት ካልወጣሽ ነገ አንቺም እንደተራ ነገር አይተሽው ትዳር ላይ ሁነሽም ከዚህ ሃራም ልትገቢበት ትችያለሽ። አላህ ይጠብቀን ለማሰብም ይከብዳል ግን የሸይጧንን መንገድ የምንከተል ከሆነ ሂጃባችንን በስርዓት የማንለብስ ከሆነ በቀላሉ ስለምንከፋፈት ወደዛ ምንገድ የማንገባበት ምክንያት አይኖርም እና ሙስሊሟ እህቴ ሆይ ሂጃብሽን አጥብቀሽ ያዢ። ወላሂ ሂጃብሽ በጣም ነው ሚጠቅምሽ። ቁጥብ ከሆንሽ ማንም እንደፈለገ አይጫወትብሽም ያከብሩሻል። አንተም ወንድሜ ማትወዳት/ማታገባት ከሆነ አትጫወትባት በእህትህ እንዲደርስ የማትፈልገውን በሌሎች ሴቶችም ላይ አታድርግ አላህን ፍራ የምትወዳት ከሆነ አግባት አገባታለሁና ብለህም እሷን ማግኜት እና በስልክ በሚዲያ ጊዜህን ከማጥፋት ተቆጠብ። እና እህቴ ይበቃሻል ከአላህ ጋር ዛሬ ታረቂ ከዚህ በላይ በሀራም መንገድ አትሂጂ ገና እየገባሽ ከሆነም በቶሎ አቋርጪው። ውድ እህቴ አንችኮ በተረጋጋ ሁኔታ ላይ ነበርሽ ለምን ወደዚህ አስቀያሚ የሸይጧን መንገድ ገብተሽ ይችን ውድ ህይወትሽን ታበላሻታለሽ። በዚህ መንገድ ስንገባ መጀመሪያ ደስተኛ የሆን ይመስለናል ግን ወላሂ ጊዜያዊ ደስታ ብቻ ነው። እህቴ በሃራም መንገድ ገብተሽ ይችን አጭር ህይወት በጭንቀትና በጥበት የባሰ አታሳጥሪያ።❗️ በሀራም የተነካካ ነገር መጨረሻው አያምርም ብታገቢም አላህ ለትዳርሽ ጥፍጥና አይሰጥሽም ምክንያቱም አላህን እያስከፋሽ ነው የጀመርሺው እና እህቴ ይሄን የሃራም በር ባስቸኳይ ዝጊው።❗️   መልክቱን ሟር አድርጉት ብዙ እህትና ወንድሞች ተዘፍቀውበት ያለው የሀራም ግንኙነት ነው። ለዚና መስፋፋትም ትልቁ መንስኤ እየሆነ የመጣው ይሄው ቦይ ፍሬንድ ገርል ፍሬንድ ነው(የሃራም ፍቅር)።    አላህ ይጠብቀን አላህ የበለጠ ያውቃል https://t.me/Islamicpost2399

photo content
+3

ሀጅ ሀጅ በመጣ ቁጥር እጅጉኑ የሚገባኝ የሚመድደኝ ሀዲስ አለ። እና ሀጅ ላይ የታዩ ትዕይንቶች የዚህ ሀዲስ መልዕክት ይበልጡኑ እንዲሰርፅ ያደርጉታል ። ኢብራሂም ዐስ ለአላህ ትዕዛዝ ብለው ሀጀራን ሲተዉ ። እሶም ለአላህ ትዕዛዝ እራሶን አሳልፍ ስትሰጠ ። ኢብራሂም ዐስ ልጃቸውን ለማረድ ሲዘገጃጁ ። ኢስማኢል ለመታረዳ ወደ እርዱ ቦታ ሲነዳ ። በአይምሮ ይህን ሁሉ ትዕይንት ተመልከት ። መጨረሻው ልጁ ከእርድ ተረፈ፣ ሀጀር  ሁሉ ነገር የተሞላ ሂወት አገኘች ፣ኢብራሂም ዐስአላህንም ልጃቸውንም ሚስታቸውንም አገኙ። የዚህ ጥቅል ትርጉም የኛ ወለላ ሰይዱና ወሀቢቡና እንዲህ ሲሉ ይጠቅሱታል "ለአላህ ብሎ አንድ ነገር የተወ አላህ ከሱ የተሻለ ነገር ይተካለታል" https://t.me/Islamicpost2399 ✍ዘኪ

ለምን በዙርያህ ያለው ሁናቴ ሲያሳምምህ ብቻ ተሸሽጎ ማልቀስ ይቀናሀል💔😌 ለምን በተራመድነው እርምጃ ሁላ ጌታችንን ማመስገን እንደሚገባ ዘነጋነው🥺 ለምን ላንተ የተሻለ የመሰለህን ግዜ ብቻ  ትጠብቃለህ 😡 الحمد لله 💖الحمد لله 💖 ዛሬን አልፎ ነገን ማየቱ ብቻ ከበቂ በላይ  ነው ወላሂ በኒዓደም ቢጠግብ ከጤናው በላይ የሆነን ነገር ከጌታው አይጠይቅም ነበር🙌 የአላህን ውሳኔ ሁሉ አመስጋኝ ያድርገን🤲 በምንወዳቸው አንፈተን🤲 ይጠብቀን ይጠብቅልን🤲 https://t.me/Islamicpost2399

ፈገግታዬን.... 🥺 ወዲህ ወዲያ ብዬ ተሯሩጬ አይቼ እዚም እዚያም ብዬ ሞቼ ተሟሙቼ ጋራ ተራራውን ወርጄ ወጥቼ አጣሁ ፈገግታዬን አደራ ሰጥቼ በሉ እስኪ ንገሩኝ ቦታውን ምታውቁ ሰልችቶኛል እኔን ቆሜ መጠበቁ ካለበት አድርሱኝ ልሁን ካጠገቡ ፈገግታዬን ስጡኝ ልኑር በአግባቡ የደስታዬን ሚስጥር ልዩ ፈገግታዬን አስውቦ አሳምሮ ሚያቀለው ስራዬን የረሱሌን ፈለግ ሱና መድመቂያዬን አፋልጉኝ ባካችሁ አጣሁ ፈገግታዬን ✍ ሂባ https://t.me/Islamicpost2399

ይሄ መንግስት ሁል ጊዜ ፈተና ትዝ የሚለው የኛ በዐል ሲደርስ ነው አይደል ስሙት እስኪ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ግን ይመችህ ጀግና ነህ ወላሂ

በስኬትህ መካከል እስካለህ ድረስ ድምጽህን ዝቅ አድርግ እና ሰዎች እድገትህን እንዲያዩ ድምጽህን አታሰማ። በጫጫታ ውስጥ ትሰናከላለህና! ስለ ሃሳቡ አብዝቶ የሚናገር ሰው ከሱ ይሰናከላል፤ ስለተከለው ችግኝ ዝም ያለ ሰው ፍሬው ይናገራል።

"ቆሎ ሻጩ" (ኑዕማን ኢድሪስ) በሀብቱ የሚታወቀዉ ቱጃር ሰዉዬ በሀጅ ወቅት አረፋ ተራራ ላይ በአከባቢያቸዉ ዝቅተኛ የኖሮ ደረጃ ኖሮት ቆሎ እየሸጠ የሚተዳደርን ሰዉ ያገኘዋል። በጣም ተደነቀ። በሺዎች የሚቆጠሩ ብሮችን ከስክሶ ለሀጅ የሄደዉ ባለሀብት የደሀዉን ሰዉዬ በቦታዉ መገኘት አስገርሞታል። ወደ'ሹ ጠጋ በማለት ሰላምታ አቀረበለት። ቆሎ ሻጩም ሰላምታዉን መለሰለት። "እንዴት እዚህ ልትገኝ ቻልክ?" በማለት ጥያቄ አቀረበለት። ቆሎ ሻጩ ትንሽ ግራ ተጋባ። አረፋ ተራራ ላይ ለሌላ ጉዳይ እንዳልመጣሁ እያወቀ ሳለ እንዴት ጠየቀኝ ሲል አሰበ። "ያዉ ... ለሐጅ ስነ ስርአት ነዋ አመጣጤ" "ገባኝ ግን ያዉ... በየትኛዉ አቅምህ እዚህ ልትመጣ ቻልክ?.. ማለቴ ቆሎ ቸርቻሪ ሆነህ ሳለ ገንዘቡን ከየት አመጣሃዉ?" በማለት ጠየቀዉ። ቆሎ ሻጩም በተረጋጋ መንፈስ መለሰለት። "እኔ ቆሎ ሻጭ ብሆንም ጌታዬ ግን ቆሎ ሻጭ አይደለም! እዚህ ቦታ ላይ ሆኜ እሱን እንድለምነዉና እንድገዛዉ ስለፈለገ ጌታዬ እንድመጣ ፈቀደ። ይኼዉ ነዉ...." ... ኢላሂ! ለኛም ሀጅን ወፍቀን! ሁሌም ካንተ ከጃይ ነንና!                   አጂብ የአላህ ሾል     https://t.me/Islamicpost2399