cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Motivation Ytterbium

ቆይ አንዴ አሁን የት ነህ? የምታረገውን ነገር ሁላ እስኪ ለደቂቃዎች አቁም እና የት ነው ያለውት ወዴትስ ነው እየሄድኩ ያለውት ብለህ ራስህን ጠይቅ። መልስ አገኘህ?መልስህስ ምን አመላከተህ? የተለያዩ የምክር አገልግሎቶችን በአካል ወይም በስልክ ለማግኘት 0901160070 telegraminbox @birukyemariyam https://youtube.com/channel/UClz_c_bS9jGG7FAZBKxxliw

Show more
Advertising posts
330
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ህመሙ ጊዚያዊ ነው፡፡ስቃዩ ያልፋል፡፡እንደ መሸ አይቀርም፡፡ጸሐይ ትወጣለች፡፡አዲስ ብሩህ ቀን ይሆናል፡፡ትዕግስት ገንዘባችሁ ይሁን፡፡የተሻለውን ትልቅ ቀን በልባችሁ ተስፋ አድርጉ፡፡ያለማቋረጥ ትጉ፡፡ከችግራችሁ የሚያስመልጣችሁን  ቀዳዳ ሳትሰለቹ ፈልጉ፡፡ከቀን ወደ ቀን በትኝሹም ቢሆን እደጉ፡፡በእርግጠኝነት ዛሬ ከትላንት የተሻለ ነው፡፡ነገ ደግሞ ከዛሬም የሚበልጥ ልዩ ቀን ነው፡፡አይዟችሁ ስቃዩ ወቅታዊ ነው፡፡ሁልጊዜ የምትደሰቱበት ዘመን በቅርብ ይመጣል፡፡ከባዱ ቀላል መሆኑ አይቀርም፡፡ @motivationYb
Show all...
አልጋህ ላይ ተኝተህ አጉል አትጨነቅ፡፡የመኝታ ሰዓት ካለቀ ተነስ፡፡መነሳትህ ካልቀረህ አነሳስህን የጀግና አድርገው፡፡አትንቀራፈፍ፡፡እግርህ ወለሉን ፈጥኖ ይርገጥ፡፡ልብህ ለፈጣሪ ምስጋና ይስጥ፡፡ቀኑን ቀደም ብለህ በወኔ ጀምረው፡፡ እስክትዘጋጅ አትጠብቅ፡፡ --------------- "ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላውቅም!" አትበል፡፡ተነስና just አድርገው፡፡ "ከየት መጀመር እንዳለብኝ አላውቅም!" አትበል፡፡just ጀምረው፡፡ይጠቅመኛል የምትለውን ነገር በጠዋቱ ጀምረው፡፡ያልጀመርከውን ነገር አትጨርሰውም፡፡ስለዚህ አሁን ጀምረው! በወኔ ጀምረው! በእምነት ጀምረው! ጀምርና መንገዱ መንገዱን ይመራሃል፡፡አንዱ ደረጃ ወደ ቀጣዩ ያደርስሃል፡፡እምነት ካለህ? ሁሌም መንገድ አለ፡፡ግን በመጀመርያ ጀምረው፡፡
Show all...
ለሚቀኑ ቀኑ ጨለማ ነው! የሰው ስኬት ልባቸውን የሚያስከፋቸው ሰዎች ተሸናፊ ናቸው፡፡ምድር የሁላችንንም ስኬት  የማስተናገድ አቅም አላት፡፡በእምነት እና በልፋታችን መጠን እኩል እንሸለማለን፡፡በጥበብ እየተመራ ጥሮ እና ግሮ ለሚኖር ሰው የስኬት ደጃፍ ይከፈትለት ዘንድ ግድ ነው፡፡ ---------------- ወንድሜ ሆይ  በከበደ ስኬት የምትቀናው ለምንድን ነው?ስትቃጠል፣ ጨጓራህ ሲጬስ፣ እንቅልፍ ስታጣ ምን ለማግኘት ነው? ከበደ ስኬታማ ሆነ ማለት አንተ ስኬታማ አትሆንም ማለት አይደለም፡፡ ----------- አንተም ሆንክ ከበደ ሁለታችሁም  ስኬታማ መሆን ትችላላችሁ፡፡ሁለታችሁም መደሰት እና መልካም ህይወትን የማጣጣም መብት አላችሁ፡፡የከበደ ህይወት የከበደ ነው፡፡መልካም እንዲገጥመው ተመኝና ወደ ራስህ ህይወት ተመለስ፡፡ትኩረትህን ሙሉ  የራስህ ህይወት ላይ አኑሩ፡፡በምትፈልገው ቦታ ለመሆን የምትፈልገውን ነገር ብቻ አሳድድ፡፡የምትቀና ከሆነ ግን የራስህን ህይወት ትረሳለህ፡፡የሰውን ህይወት ስታሳድ በማትፈልገው ቦታ ትወድቃለህ፡፡አሁን ካለህበት ደረጃ ወደ ታች ትወርዳለህ፡፡ @motivationYb
Show all...
የአእምሮህን ጥርጣሬ የምታደምጥ ከሆነ የልብህን ምኞት አታሳካም፡፡የምታስበውን ሀሳብ ሁሉ አትመን፡፡ምክንያቱም አእምሮህ የአለማችን ውሸታሙ መሳርያ ነው፡፡"ይህ ቢሆንስ? ያ ቢከሰትስ?" እያለ ያልተፈጠሩ የውሸት  ታሪኮችን በውስጥህ ይተርካል፡፡በመጥፎ ሀሳቦች አስሮ በፍርሃት አለንጋ ይገርፍሃል፡፡ካለህበት ቦታ እንደ ዛፍ ቆመህ እንድትቀር ያስገድድሃል፡፡ -------------- ወደፊት ለመስፈንጠር የምትፈልግ ከሆነ  የአእምሮህን መጥፎ ሀሳቦች አትስማቸው፡፡አእምሮ ያልሆኑ ታሪኮችን ሲተርክ  ፈጥነህ በድንጋጤ ምላሽ አትስጥ፡፡እነዚህ just አእምሮ ውስጥ የተፈጠሩ ሀሳቦች ብቻ እንደሆኑ ተገንዘብ፡፡ስትጨነቅ እና ስትከፋ ዙርያ ገባውን ቃኘው፡፡አገሩ አማን ነው፡፡ችግሩ ያለው በውስጥህ ነው፡፡መጥፎ ስሜት እንዲሰማህ የሚያደርገው የአእምሮ መጥፎ ሀሳብ ነው፡፡ -------------- ቁጭ በልና ሰውነትህን ዘና ዘንከት አድርግ፡፡ትኩረትህን ወደ አእምሮህ ከተማ ውሰደው፡፡በዚያ የሚጨፍሩ መጥፎ ሀሳቦችን በጥሩ ሀሳቦች ለውጣቸው፡፡የአእምሮህ መጥፎ ሀሳቦቹ በጥሩ ሀሳቦች  ሲለወጡ መጨነቅ፣ መከፋት፣ መጠራጠር፣ መረበሽና  መጥፎ ስሜቶች በሙሉ ሰውነትህን ፈጥነው  ይለቃሉ፡፡የጥሩ ስሜት ወንዝ በሰውነትህ ይፈሳል፡፡ነፍስ እና መንፈስህ ይታደሳል፡፡ሰላም እና እረፍት ታገኛለህ፡፡ካላመንከኝ አሁን ጥሩ ሀሳብ ማሰብ ጀምርና  የሰውነትህን ስሜት አስተውለው፡፡ @MotivationYb
Show all...
የብዙ ሰው ምርጫ ሁለት  ነው፡፡ማሸነፍ ወይም መሸነፍ፡፡አንተ ግን መሸነፍን ከምርጫ ውስጥ አታስገባው፡፡"ያለኝ አማራጭ ማሸነፍ ወይም መሞት ነው፡፡" ብለህ ራስህ ንገረው፡፡ የማታሸንፍ ከሆነ የሚጠብቅህ ሞት እንደሆነ ተራዳ፡፡የምታሸንፍበትን መንገድ ብቻ አስብ፡፡አሸናፊ የሚያደርግህን ነገር ብቻ አድረግ፡፡ ------------- ጨዋታዋን እንደ ልብ ለመጫወት የጨዋታውን ህግ በመጀመርያ እወቅ፡፡የህይወት ጨዋታን ስትጫወት  አትከላከል፡፡መጫወትህ ካልቀረ እንደ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በርትተህ አጥቃ፡፡የምትፈልገው ውጤት ጤና ሆነ ገንዘብ፣ ትዳር ሆነ የትምህርት ቤት ነጥብ፣ ስራ ሆነ  እውቅና፣ ቤተሰብ መምራት ሆነ ከሱስ መውጣት ስትጫወት አትከላል፡፡የሚከላከሉ ፈሪ ተጫዋቾች ብቻ ናቸው፡፡ፈሪ ሰው ደግሞ አያሽንፍም፡፡ፍርሃትህን ግደለውና በወኔ   አጥቃ፡፡ማሸነፍ ወይም መሞት እያልክ በድፍረት ተጫወት፡፡መሸነፍን ከምርጫ ውስጥ በፍጹም አታስገባ፡፡ @MotivationYb
Show all...
ከአእምሯችሁ ሀሳብ ውጡ፡፡ወደ ስራ ግቡ፡፡ይህ አለም የሚሰራበትን መንገድ ተረዱ፡፡አለም የሚሰራው በስራ ነው፡፡በውስጣችሁ ሀሳብ አመላልሳችሁ  ምንም ካላደረጋችሁ ምንም አትጠቀሙም፡፡አትፍሩ፡፡ምቹ ጊዜ እስኪመጣ አትጠብቁ፡፡just ተነሱና ሀሳባችሁ ላይ እርምጃ ውሰዱ፡፡የአበጠው ይፈንዳ ያሰባችሁትን አድርጉ፡፡ብሳሳት እና ብወድቅ ብላችሁ አትደናገሩ፡፡መሳሳት እና መውደቅ ወሳኝ ነገሮች ናቸው፡፡መሳሳትን ውደዱት፡፡ጥሩ ጥሩ የህይወት አስተማሪ ነው፡፡መውደቀን አትጥሉ ወደ ስኬት የሚመራ መሰላል ነው፡፡ ----------- በህይወት ትልልቅ ሊጎች ስትጫወቱ  የምታሸንፉት በፍርሃት ስትጫወቱ  ሳይሆን በእምነት ስትጫወቱ ነው፡፡ሰው ምን ይለኛልን አትፍሩ፡፡ሰው ምንም ቢል ስሜተ ደንዳና ሆናችሁ  ከሚለው ነገር ለመማር ቁረጡ፡፡የተማሪነት ሞዳችሁን ሁሌም on አድርጋችሁ ከእያንዳንዱ አጋጣሚ እየተማራችሁ ወደፊት ገስግሱ፡፡በስሜት ሳይሆን በእወቀት ተመሩ፡፡ ------------- "አሁን የምሳሳተው ልምድ ስለሌለኝ ነው፡፡ሰው የሚተቸኝ አሁን ባለሁበት ስለሚመለከተኝ ነው፡፡ነገር ግን በስራ ሳድግ እና ስለወጥ ይህ ሁሉ ይቆማል!" እያላችሁ ራሳችሁን አበረታቱ፡፡ጊዜ እየሄደ ነው፡፡አላማችሁን ሳታሳኩ እንዳትሞቱ ተጠንቀቁ፡፡ተነሱ ዛሬ አንድ ብላችሁ ጀምሩ፡፡ @motivationYb
Show all...
የምትዋሹት እውነት ስትናገሩ  ከምታውቋቸው አስር ሰዎች መካከል ዘጠኙ እንደ ሚጠሏችሁ ስለምታውቁ ነው፡፡ -------------- ከሁሉ በይበልጥ የሚጠላው እውነት የሚናገር ሰው ነው፡፡ዋሾ ሰውማ አሽቃብጦ መኖርን ያውቅበታል፡፡ከሁሉም ጋር የመመሳሰል ብቃት ስሳለው በጥሩም በመጥፎም ሰዎች መወደድ ለእሱ ቀላል ነው፡፡ --------------- አለም ውሸትን እንጂ  እውነትን አታበረታታም፡፡ እውነተኛ ሰው  ስትሆኑ  ትጠላላችሁ፣ ትደበደባላችሁ፣ ትታሰራላችሁ፣ ትገለላላችሁ በስተመጨረሻ ግን ነጻ ትወጣላችሁ፡፡ ------------ ውሸታም ስትሆኑ ግን ትወደዳላችሁ፣ ትደነቃላችሁ፣ ትመሰገናላችሁ፣ ትናፈቃላችሁ በስተመጨረሻ ግን የህሊናችሁ እስረኛ ባርያ ትሆናላችሁ፡፡መጀመርያ  ብታገኙም መጨረሻው ላይ በትልቁ ታጣላችሁ፡፡ ------------- ዋሽቶ ከመወደድ  እውነን አውርቶ መጠላት በብዙ የተሻለ ነው፡፡ይህን ሀቅ የሚረዳ ግን ጥቂት ሰው ነው፡፡ብዙ ሰው የሚፈልገው አሁን ላይ የሆነ ነገር ተጠቅሞ መሞትን ነው፡፡ -------------- እናንተ ግን በሰዎች መወደድንም ሆነ መጠላትን አትፈልጉ፡፡እውነትን ብቻ ፈልጉ፡፡መላው  አለም እውነትን ከተቃወመ እናንተ አለምን ተቃወሙ፡፡የሐይማኖት አባቶቻችሁ፣  ውድ ቤተሰቦቻችሁ፣  አስተማሪዎቻችሁ እና የምታደንቋቸው ሰዎች  እውነትን የሚቃወሙ ከሆነ አትደራደሯቸው፡፡እነሱ እውነትን ከተዋጉ እናንተም እነሱን እንደምትዋጉ እውነቱን ይወቁ፡፡ ------------ ምክንያቱም ነጻነት ያለው እውነት ጋር ነው፡፡ሰላም የሚገኘው እውነት ባለበት ነው፡፡ፈጣሪ የሚፈርደው ለእውነት ነው፡፡ @MotivationYb
Show all...
ከማንም አትበልጥም፡፡ከማንም አታንስም፡፡አንተ ልክ እንደ ማንም ሰው ነህ:: ራስህን ከማንም ጋር አታወዳድር፡፡ያንተ ህይወት ያንተ ነው፡፡ስለዚህ በራስህ መንገድ ኑረው፡፡ከሰው ጋር ልወዳድር ካልክ ግን የቱንም ያህል ትልቅ ቦታ ብትደርስም  በማንኛውም መስፈርት ካንተ የሚበልጥ ሰው  ምድር ላይ አይጠፋም፡፡ ---------------- ሁሌም ካንተ የበለጡ ቆንጆ፣  ካንተ የበለጡ ጎበዝ፣ ካንተ የበለጡ ሀብታም፣ ካንተ የበለጡ  ዝነኛ፣ ካንተ የበለጡ ጀግና ወ.ዘ.ተ ሰዎች በምድር ላይ አሉ፡፡ከሰው ጋር ራስህን የምታነጻጽር ከሆነ የህይወት ጥፍጥናውን  ሳይታጣጥም  ትሞታለህ፡፡ራስህን በእነሱ መነጽር እያየህ ህይወትህን ትረግማለህ፡፡ --------------- ህይወት የምትጣፍጠው ከሰው ጋር ስትወዳደር ሳይሆን  በራስህ መንገድ ስትኖር ነው፡፡ -------------- ህይወት ላንተ ምንድን ነው? አለም ላይ ቤተሰቦችህም፣ ጓደኞችህ፣  የምታውቃቸውም የማታውቃቸውም ሰዎች ባይኖሩ የምትኖረው ምን አይነት ህይወት ነው? ከቀን ወደ ቀን በደስታ ተሞልተህ የምትሰራው ስራ የቱ ነው? ሁሌም አብረኸው በትሆን የማትሰለቸው ሰው ማን ነው?ሰው ምን ይለኛል ሳትል ሁልጊዜ የምትለብሰው አለባበስ እንዴት ያለ ነው? የምታወራው  ወሬ ምን ይመስላል? በአጠቃላይ አንተ ፈቅደህ እና ወደህ የምትሆነው ምን አይነተ ሰው ነው? ያን የምትፈልገውን ሰው አሁን ሁነው፡፡ -------------- ሰው ምን ይለኛል ብለህ አትጨነቅ፡፡በሁለቱም ጆሮዎችህ ውስጥ ጥጥ አስገባና መስሚያህን ድፈን፡፡ወይም ደግሞ ትልቁን ኤርፎን ግዛና ጆሮችህን ክደንበት፡፡የልብህን ሙዚቃ ብቻ አድምጥ፡፡ያመንክበትን ነገር ብቻ አድርግ፡፡ላንተ ትክክለኛ ህይወት ማለት ያ ነው፡፡በራስህ መንገድ የራስህን ህይወት ኑረው፡፡ -------------- መወዳደር ካለብህም ከራስህ ጋር ብቻ ተወዳደር፡፡ሁልጊዜ ትላንት ከነበረው አንተ ተሽለህ ለመገኘት ልፋ፡፡ነገ ደግሞ ከዛሬው አንተ በሆነ መልኩ እደግ እንጂ ሰዎችን ባንተ ህይወት አታስገባ፡፡ ------------- ምክንያቱም አንተ እና ሰዎች አንድ ብትሆኑም አንድ አይደላችሁም፡፡ የተወለዳችሁበት ቦታ እና ሰዓት  ይለያያል፣ ያሳደጓችሁ  ሰዎች ይለያያሉ፣ ባንተ ጊዜ የነበረው ፋሽን እና ቴክኖሎጂም ከእነሱ ጋር ሲነጻጸር ልዩ ነው፡፡ባህል እና ሐይማኖትህም ከሰው ጋር አንድ አይደም፡፡የምታስቡበትም መንገድም  ፈጽሞ ለየቅል ነው፡፡ታዲያ ከሰው ጋር መወዳደር ምን ያደርጋል? ወዳጄ  የራስህን አለም ኑር፡፡ ------------- ራስህን ስትሆን ሁሉም ሰው ላይደሰት ይችላል፡፡ሁሉንም  ሰው ለማስደሰት ግን አትጣር፡፡ሰዎችን ሁሉ ለማስደሰት ፈጽሞ  አይቻልም፡፡ሁሉንም ሰው ለማስደሰት የምትደክም ከሆነ ግን  በመጀመርያ የማታስደስተው  ራስህን ነው፡፡ @motivationYb
Show all...
የሚያስጠላ ሁኔታ ውስጥ ካለህ ለምን ታለቃቅሳለህ? ያንተ ጥፋት ነው፡፡የምታለቅሰው ምን ይሁን ብለህ ነው? ደስተኛ ካልሆንክ፣ ሰላም ካልተሰማ፣ ህይወትህ ከተዘበራረቀ፣ ለመኖር ገንዘብ መጠለያ ምግብና ልብስ ካነሰህ  ያንተ ጥፋት ነው፡፡የምታለቅሰው ምን እንዲፈጠር ነው? ለህይወትህ መጥፎ ሁኔታ ካንተ ውጪ ማንንም ተጠያቂ አታድርግ፡፡አናትህ ላይ ሹጉጥ ደቅኖ አንድ ሰው ቢገድልህ የማን ጥፋት ነው? ያንተ ጥፋት ነው፡፡ሽጉጥ ያለበት ቦታ ማን ሂድ አለህ? ሰውየው ካለህበት መጥቶ ከሆነም ሽጉጥ ሲደቀንብህ ማን ዝም ብለህ ተመልከት አለህ? የራስህን መንገድ ተጠቅመህ ራስህን ካላዳንክ ማን እንዲያድነህ ትፈልጋለህ? ያንተው ጥፋት ነው፡፡ ሰዎች ቢከዱህም እና ቢዘርፉህም እነሱ ላይ ጣትህን አትቀሰር፡፡ሀያ አመት ተምረህ ስራ ብታጣ መንግስትና አገሪቱን አትክሰስ፡፡ -------------- ያፈቀርካት ልጅ ወደ ሌላ ሰው ብትኮበልል፣ የወለድካቸው ልጆች ጠላቶችህ  ቢሆኑም  ጥፋቱ ያንተ ነው፡፡አንተ እንደ እርግብ የዋህ እንደ እባብ ብልህ ሁን፡፡በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ከህይወት ለሚቃጣብህ ችግር ምላሽ ለመስጠት ራስህን አዘጋጅ፡፡ብችግርህን ከስር መሰረቱ ለመንቀል የምትፈልግ ከሆነ "የኔ ጥፋት ነው!" በል፡፡ከራስህ ውጪ  ሌላ አካል ላይ ማመካኘት ሐላፊነትህን እንዳትወጣ እንደሚያደርግ እወቅ፡፡ ሙሉ ወኔ የምትፈልግ ከሆነ  ለችግርህ ሙሉ ሐላፊነት ውሰድ፡፡"የኔ ጥፋት ነው!" በልና ሰዎች ላይ ከመፍረድ ነጻ ውጣ፡፡የሚከፈለውን ከፍለህ የተወላገደ ህይወትህን አቃና፡፡ @motivationYb
Show all...
አንድ ውሳኔ ብትወስን አሰልቺ ህይወት መኖር ታቆማለህ፡፡ያቆምከውን ነገር እንደገና ብትጀምርና የጀመርከውን ነገር ብትጨርስ የሆነ ቀን ካሰብክበት ትደርሳለህ፡፡ለራሳህ ትዕዛዝ እየሰጠህ እሱን ብታከብር ትለወጣለህ፡፡ --------------- ስኬት ራስን በራስ እያዘዙ ማድረግ ነው፡፡ያለምንም አዛዥ ላመኑበት ነገር ዋጋ መክፈል ነው፡፡አበረታች በጠፋበት ራስን እያበረታቱ መስራት ነው፡፡ -------------- ስኬት ወደ ውድቀት የሚወስዱ ነገሮችን አለማድረግ ነው፡፡ሐይልና ጊዜን ለተገቢው ስራ ብቻ ማዋል ነው፡፡ --------------- ስኬት መሸለም እና ማግኘት አይደለም፡፡ስኬት ማሸነፍ አይደለም፡፡ህንጻ መገንባት፣ መኪና መግዛት፣ ሀብት ማብዛት፣ ዝናን ማስፋትና ድግሪ መለቃቀም  ስኬት  አይደለም፡፡ ------------- ስኬት መሞከር ነው፡፡ሲወድቁ ፈጥኖ መነሳት ነው፡፡ተስፋ ሳይቆርጡ መጣር ነው፡፡እንደገና ማድረግ ነው፡፡ስኬት ዝም ብሎ መስራት ነው፡፡ ------------- የሚሞክር፣ ወድቆ የሚነሳና  እንደገና የሚያደርግ ሰው አሁን ስኬታማ ነው፡፡ -------------- ሰው ወድቋል የሚባለው በወደቀበት ሲቀር ነው፡፡ከወደቀበት ተነስቶ እንደገና የሚጣጣር  ሰው አልወደቀም፡፡እሱ አሁን ባለበት  ስኬታማ ነው፡፡ምክንያቱም ስኬት መሞከር ነው፡፡እንደገና ማድረግ ነው፡፡ --------------- "አንድ....ሁለት...ሶስት .. አስር ጊዜ ሞክሬ አልተሳካም፡፡ሙከራዬን ያቆምኩት አልሆን ስላለኝ ነው!" የሚል ሰዉ አሳማኝ ቢመስልም አሳማኝ አይደለም፡፡አስር ጊዜ ብቻ መሞከር በቂ አይደለም፡፡ከአስር በላይ የትየለሌ (infinite ) ቁጥሮች አሉ፡፡ተስፋ ሳድቆርጥ ለአስራ አንደኛ ጊዜ፣ ለሀምሳ አንደኛ ጊዜ፣ ለመቶኛ ጊዜ ፣ ለአንድ ሺኛ ጊዜ ..ወ.ዘ.ተ አልሞከረም፡፡ስለዚህ አያሳምንም፡፡የማይሞክርና ያቆመ  ሰው ምን ያገኛል? ምንም፡፡ስለዚህ ይሄ ሰው ስኬታማ አይደለም፡፡ስኬት ከሙከራ ወደ ሙከራ በተስፋ መጓዝ ነው፡፡እንደገና ራስን እያሳደጉ መስራት ነው፡፡ ------------ ስለሆነም ውድ አንባቢ  ምን ትጠብቃለህ? አንድ ሺህ ጊዜ መክረህ ያቆምከው ነገር ካለህ ተነስና  እንደገና ሞክር፡፡አንድ ሺ ጊዜ ማድረግ በቂ አድደለም፡፡ይህ  ትንሽ ቁጥር ነው፡፡ሰኬት ሁልጊዜ ማድረግ ነው፡፡እንደገና መስራት ነው፡፡ተነስና ከአንድ ሺህ በላይ ያሉ ቁጥሮችን ዛሬ ሞክር፡፡ሳታቋርጥ ጣር፡፡ለማቆም ስታስብ ስኬት መሞከር እንደሆ አስታውስ፡፡ማን ያውቃል የአንድ ቀን ሙከራህ ህይወትህን ለዘለዓለም ሊለውጠው ይችላል፡፡ሰነፍ አትሁን ሞክር ወዳጄ፡፡ጥረትህን አታቁም፡፡በርታ ወንድሜወንድሜ።
Show all...