cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Amen zehabesha-official(አሜን ዘሀበሻ)

በዚህ ቻናል ወቅታዊ እና ፈጣን መረጃወችን ያገኛሉ❗❗ ትክክለኛው እና ብቸኛው አሜንዘሀበሻ ቻናል ይሄ ብቻ ነው።ይህን ቻናሌን ለሌሎች ሰወች ሸር አድርጉ። ሀሳብ፣አስተያየት፣ጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከስር ባለው ሊንክ ይፃፉልን 👇👇👇 htttp//t.me//Amloven htttp//t.me//Amloven Telegram bot👇👇👇 @amezehabeshaofficialbot

Show more
Advertising posts
804
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-2330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በጋምቤላ ክልል ግንቦት 3/2016 በኢታንግ ወረዳ ማኮት ቀበሌ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ የጀመረው  ግጭት እስካሁን 7 ስውች ሲገደሉ 11 ስዎች ቆስለው ጋምቤላ ሆስፒታል ገብተዋል። 3 የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት መገደላቸውን ተከትሎ አሁን ግጭቱ ከሯል ብለዋሌ። የክልሉ መንግስትም ሁኔታወችን ከማየት የዘለለ ምንም አይነት ስራ እየስራ አይደለም ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል(አዩዘሀበሻ)። =================== For more upcoming news Join now and invite to others👇👇👇 https://t.me/amenzehabeshaofficial https://t.me/amenzehabeshaofficial
Show all...
😢 1
ትናንት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በአንፆኪያ ገምዛ ወረዳ እና በኦሮሞ ብሄርሰብ ልዩ ዞን ጋር በሚዋስንበት ቦታ በአንፆኪያ በ08 ቀበሌ እና በኦሮሞ ብሄርሰብ በአርጡማ ፉርሲ በሚዋስኑ ቀበሌ ልዩ ስሙ ፌጮ በሚባል ቦታ ለስአታት የዘለቀ ውጊያ እንደነበር የአዩዘሀበሻ ምንጮች ገለፁ። በዚህ ግጭት ከአንፆኪያ በኩል  አምስት ሰው ሞቷል 3ሰው ቆስሏል ብለዋል፣ከኦሮሞ ብሄርሰብ በኩል ያለው ጉዳት በውል ባይታወቅም ጉዳት ሳይደርስ አይቀርም ብለዋል። አሁን ተኩሱ ቆሟል ብለዋል። በዚህ አካባቢ በተደጋጋሚ የሚፈጠሩ ግጭቶች በየጊዜው በርካታ የሰው እየጠፋ ይገኛል[አዩዘሀበሻ]። =================== For more upcoming news Join now and invite to others👇👇👇 https://t.me/amenzehabeshaofficial https://t.me/amenzehabeshaofficial
Show all...
👍 3
ባህር ዳር‼ በአማራ ክልል ርዕሰመዲና በበባህር ዳር ከተማ በአባይ ወንዝ ላይ የተገነባው ድልድይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት በዚህ ሰዓት የምረቃ ስነስርዓቱ እየተከናወነ ነው። ድልድዩ 380 ሜ ገደማ ርዝመት እና ወደ ጎን 43 ሜ ርዝመት ያለው ሲሆን ድልድዩ ከሚሰጠው የትራንስፖርት አገልግሎት ባሻገር ለባህርዳር ከተማ ተጨማሪ ውበትን ያጎናፀፈ ሆኗል(አዩዘሀበሻ)። =================== For more upcoming news Join now and invite to others👇👇👇 https://t.me/amenzehabeshaofficial https://t.me/amenzehabeshaofficial
Show all...
👍 4
በራያ ኦፍላ ኮረም እንዲሁም በራያ አላማጣ ወረዳ የትግራይ ታጣቂዎች ወደ አካባቢው መንቀሳቀሳቸውን ተከትሎ በእነዚህ አካባቢዎች ትምህርት ከተቋረጠ ሳምንታት ተቆጥረዋል። አሁን ላይ የደረሰኝ መረጃ እንደሚያሳየው የ12ኛ ተፈታኝ የሆኑ ተማሪዎች ወልዲያ ዩኒቨርስቲ ገብተው ቀሪውን ትምህታቸወን እንዲያጠናቀቁ ሊደረግ መሆኑን የአዩዘበሀሻ ምንጮች ገልፀዋል(አዩዘሀበሻ)። =================== For more upcoming news Join now and invite to others👇👇👇 https://t.me/amenzehabeshaofficial https://t.me/amenzehabeshaofficial
Show all...
በዚህ መርሐግብር መሰረት ተዘጋጁ‼ የ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና መርሐግብር ይፋ ሆኗል፡፡ መርሐግብሩ ከትግራይ ክልል ውጪ በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱም የከተማ አስተዳደሮች በወረቀት እና በበይነ መረብ ፈተናውን ለሚወስዱ ተፈታኞች እንደሚያገለግል የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል። የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና:— ✔ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም ለማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ✔ከሐምሌ 9-11/2016 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ይሰጣል። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት =================== For more upcoming news Join now and invite to others👇👇👇 https://t.me/amenzehabeshaofficial https://t.me/amenzehabeshaofficial
Show all...
በቁጥጥር መዋሉ እየተነገረ ነው‼️ የፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር( ሞንጀሪኖ) ወንድም ቢሊየነሩ አቶ ዳዊት ገብረእግዚአብሔር በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በኢንተርፖል ቁጥጥር ስር መዋሉ እየተነገረ ሲሆን በቅርቡ ለኢትዮጵያ ተላልፎ እንደሚሰጥም ተነግሯል[አዩዘሀበሻ]። ====================== For more upcoming news Join now and invite to others👇👇👇 https://t.me/amenzehabeshaofficial https://t.me/amenzehabeshaofficial
Show all...
ራያ‼️ በአማራና በትግራይ ክልል መካከል የማንነት ጥያቄ ከሚነሳባቸው ቦታዎች አንዱ በሆነው አላማጣ ወረዳ በዛሬው እለት 03/09/2016 የህወሓት አመራሮች በራያ አላማጣ ከተማ ገረጀሌ ቀበሌ የሆስፒታሉን ሰራተኞች ስብሰባ በመጥራት ከሰኞ ጀምረው የተቋረጠውን የሆስፒታል ስራ እንዲጀምሩና እነሱም በቅርቡ ወረዳውን ሙሉ በሙሉ ተረክበው እንደሚያስተዳድሩ ኦረንቴሽን ሰጥተው የውሎ አበል 600 ብር ለእያንዳንዳቸው ሰጥተው ልከዋቸዋል ብለዋል። ሰራተኞቹ ከዚህ በፊት በመከላከያና በፌደራል አመራሮች ስራ እንዲጀምሩ ቢታዘዙ አንሰራም ያሉ ናቸው።በዚህ ስብሰባ አብዛኛው ከፍተኛ ባለሙያዎች እና ሌሎች ሰራተኞች ያልተገኙ ሲሆኑ ህወሃት በድብቅ መድባ በመረጃነት ሲያገለግሏት የነበሩ አካላት ናቸው በስብሰባው ላይ የተገኙት ሲሉ የአየዘሀበሻ የውስጥ ምንጮች ገልፀዋል። ስብሰባውን በተመለከተ የወቅቱ ኮማንድ ፖስት አመራሮች መረጃው ቢኖራቸውም ለመበተን የተሰራ ስራ የለም ሲሉ ነዉ የአዩዘሀበሻ ምንጮች የገለፁት። ከሳምንታት በፊት የህወሓት ታጣቂዎች በራያ አላማጣ ወረዳ ትንኮሳ በመጀመራቸው ምክንያት በርካታ የአላማጣ ነዋሪዎች ተፈናቅለው በቆቦ ከተማ ይገኛሉ[አዩዘበሀሻ]። ====================== For more upcoming news Join now and invite to others👇👇👇 https://t.me/amenzehabeshaofficial https://t.me/amenzehabeshaofficial
Show all...
ባህር ዳር‼ በባህር ዳር ከተማ በአባይ ወንዝ ላይ የተገነባው ድልድይ መጠናቀቁ ተሰምቷል። ✔ድልድዩ 380 ሜትር ርዝማኔ አለው፡፡ የጎን ስፋቱም 43 ሜትር ሲሆን በግራና በቀኝ በአንድ ጊዜ 6 ተሽርካሪዎች ማስተናገድ ይችላል። ✔5ሜትር የእግረኛ መሄጃ የተሰራለት ሲሆን በሁለቱም አቅጣጫ ለብስክሌት ተጠቃሚዎች የሚሆን መስመርን ያካተተም ነው። ✔ድልድዩ 65,683 ኪሜ የሚሸፍነው፤ ከግብፅ ተነስቶ፤ በሱዳን በማቋረጥ ኬንያ እና ታንዛንያን አልፎ እስከ ደቡብ አፍሪካ የሚያገናኘው የኔትዎርክ መንገድ አካልም ነው። ✔ቀድሞ የነበረው ድልድይ ከ60 ዓመታት በላይ ለማህረሰቡ የትራንስፖርት ማመላለሻ መንገድ በመሆን ሲያገለግል ቆይቶ ለአዲሱ ቦታውን የሚያስረክብም ይሆናል። ✔ግንባታው በአንድ ቢሊዮን አራት መቶ ሰላሣ ሰባት ሚሊዮን  ብር  የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ወጪው ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግስት የተሸፈነ ነው። ====================== For more upcoming news Join now and invite to others👇👇👇 https://t.me/amenzehabeshaofficial https://t.me/amenzehabeshaofficial
Show all...
👏 1
በትግራይ 81 በመቶ ወጣት ስራ-አጥ ነው፣ 89  በመቶ ወጣቶች ትዳር መመስረት አንፈልግም ብለዋል‼️ ለሁለት ዓመታት በጦርነት ውስጥ የነበረችው ትግራይ በጦርነቱ ማግስት ከገጠሟት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች አንዱ የወጣቶች በገፍ ክልሉን እየለቀቁ መሰደድ ነው። በትግራይ ስደት ከጦርነቱ በፊትም የነበረ ቢሆንም ከጦርነቱ በኋላ ግን እጅግ አስደንጋጭ በሆነ መልኩ እንደጨመረ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አሥተዳደር የወጣቶች ቢሮ ኃላፊ ሓይሽ ሱባጋድስ  ለዋዜማ ተናግረዋል። እድሜያቸው ከ 15 እስከ 18 የሚሆኑ ታዳጊዎች ትምሕርታቸውን አቋርጠው ከአገር እየወጡ እንደሆነ፣ አብዛኞቹ በየመን እና ሳውዲ አረቢያ እስር ቤት ወስጥ ቀሪዎቹ ደግሞ በሕገ ወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች እጅ እንዳሉና በርካታ ወጣቶችም በመንገድ ላይ እና በበረሃ እየሞቱ እንደሆነ መረጃዎች ይደርሱናል ሲሉ ኃላፊው ተናግረዋል። ከወራት በፊት የመንን አቋርጠው ወደ ሳውዲ አረቢያ ሊገቡ ሲሉ በሳውዲ ድንበር ጠባቂዎች ከተገደሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንና፣ ጅቡቲ ላይ በጀልባ መስጠም አደጋ ሕይወታቸውን ካጡት መካክል፣ አብዛኞቹ የትግራይ ተወላጅ ወጣቶች መሆናቸውን ኃላፊው ለዋዜማ አረጋግጠዋል። ይህ አስደንጋጭ ክስተት እየታየ እንኳን በቀሪዎቹ ወጣቶች ላይ የመሰደድ ፍላጎት ሲቀንስ አለመታየቱ በትግራይ ክልል ያለው ችግር ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ያሳያል ይላሉ ሓይሽ። እንደ አይ ኦ ኤም ያሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት የሚያወጡት መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በዚህ ውቅት እንደ አገር ያለው የስደት ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን የሚያሳይ ሲሆን ፣ በትግራይ ያለው ግን ከዚያ የተለየና ለመቆጣጠርም አዳጋች የሆነ ነው። ትግራይ ውስጥ ባሉ የተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ከ 500 ሺሕ በላይ ተፈናቃይ ወጣቶች አሉ፣ በመጠለያ ጣቢያው በቂ ሰብዓዊ ድጋፍ ባለመኖሩና ምንም አይነት ለነገ የሚሉት ተስፋ የሚታያቸው ባለመሆኑ ወጣቶቹ ስደትን ቀዳሚ ምርጫቸው አድርገዋል ብለዋል። እንደ ኃላፊው ገለጻ ወጣቶቹ በብዛት እየተሰደዱ ያሉት ከምሥራቅ እና ደቡብዊ ዞኖች፣ከሰሜን ምዕራብ እና ሰሜናዊ የትግራይ አካባቢዎች፣ከመቀሌ ከተማ እና አካባቢዋ በተወሰነ መልኩ እንደሆነ ኃላፊው ሓይሽ ተናግረዋል። ዳግም ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ስጋት እንዲሁም የሕገ ወጥ ደላሎች ማታለያ ለመሰደዳቸው ሌላው ምክንያት እንደሆነ ሓይሽ ያስረዳሉ። ዋዜማ በዚሁ ጉዳይ ላይ የትግራይ ክልል ወጣቶች ማኅበርን ያነጋገረች ሲሆን ማኅበሩ በክልሉ ያለው ሥራ አጥነት ያስከተለው የወጣቶች ስደት እጅግ አስከፊ ሁኔታ ላይ ደርሷል ሲል ገልጿል። የክልሉ ወጣቶች ማኅበር ሥራ አስኪያጅ ሠናይ ከሓሳይ ለዋዜማ እንደተናገሩት ማኅበሩ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር በመተባበር በ 10 ወርዳዎች፣ በ 30 ቀበሌዎችና በ1 ሺህ 200 መቶ ወጣቶች ላይ ፈጣን የዳሰሳ ጥናት ማድረጉን ገልጸዋል። የጥናቱም ፍለጋ ከጦርነቱ በኋላ የወጣቱ መተዳደሪያ ምንድነው?፣ትምሕርት ጤና እና ሌሎች ማኅበራዊ አገልግሎቶችን ከማግኘት አንጻር ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል የሚሉ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን ያካተተ እንደሆነ ለዋዜማ አስረድተዋል። ከላይ የተጠቀሱት አገልግሎቶች ባለመኖራቸውና በክልሉ አሁን ባለው ሁኔታ ምንም የሚጨበጥ ተስፋ ባለመኖሩ ምክንያት ካሉት ወጣቶች መካከል ግማሽ ያህሉ የመሰደድ ሃሳብ ያላቸው እንደሆኑ በተደረገው ጥናት መሰረት ማረጋገጣቸውን ጠቁመዋል። ጥናቱ እንደሚያመለክትው በዚህ ወቅት ትግራይ ውስጥ ካሉ ወጣቶች መካከል 81 በመቶ የሚሆኑት ሥራ አጥ መሆናቸውን የገለጹት ሥራ አስኪያጁ እነዚህ ወጣቶች አብዛኞቹ ከጦርነቱ በፊት የራሳቸው ተቋም የነበራቸው፣ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ፣ መልካም የሚባል ሕይወት ሲመሩ የነበሩ መሆናቸውና ከጦርነቱ በኋላ ግን ያላቸውን ጥሪት ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ያጡ ናቸው ሲሉ። ከትምህርት ፍላጎት ጋር ተያይዞ በወጣቶቹ ላይ በተደረገው ጥናት ካሉት ወጣቶች መካከል 78 በመቶ የሚሆኑት ምንም አይነት የመማር ፍላጎት የሌላቸው ናቸው የሚሉት የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ ለዚህም እንደ ምክንያት የሚያቀርቡት በጦርነቱ ምክንያት ቤተሰቦቻቸን ያላቸውን ነገር በሙሉ ስላጡ እኛን የሚያስተምሩበት አቅም የላቸውም የሚል እንደሆነ አብራርተዋል። ከሥራ ፈጠራ አንጻር፣ 31 በመቶ የሚሆኑት የራሳችን ሥራ ፈጥረን እንሰራለን የሚሉ እንደሆኑ 29 በመቶዎቹ ደግሞ በተለያዩ መንግሥታዊና የግል ተቋማት ተቀጥረን መስራት አለብን የሚል ሃሳብ ያላቸው፣ ቀሪዎቹ ግን የመሰደድ ፍላጎት ያላቸው ናቸው ብለዋል ከነዚህ የመሰድድ ፍላጎት ካላቸው ውስጥ 53 በመቶዎቹ እድሜያቸው ከ 26 እስከ 35 ባለው መካከል የሚገኝ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ ግን ከ 15 እስከ 25 ባለው መካከል እንደሚገኙ ጠቁመዋል። ከቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ጋር ተያይዞ በክልሉ ካሉ ወጣቶች 78 በመቶ የሚሆኑት ምንም አይነት የበይነ መረብ አገልግሎት እንደማያገኙ 97 በመቶ የሚሆኑት የኮምፒዩተር አገልግሎት፣ 29 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ የስልክ አገልግሎት የሌላቸው መሆናቸውን ገልጸዋል። በዚህም ምክንያት ሥራ ለመፈለግና የሚወጡ የሥራ እድሎችን እንዲሁም ማስታወቂያዎችን ለማየት አስቻይ ሁኔታ የላቸውም በማለት ተናግረዋል። ከማኅበራዊ ሕይወታቸው ጋር ተያይዞ 89 በመቶ የሚሆኑት የትግራይ ተወላጅ ወጣቶች ትዳር የመያዝ፣ ኃላፊነት የመውሰድና ቤተሰብ የመመስረት ፍላጎት እንደሌላቸው ባደረጉት ጥናት ማረጋገጣቸውን ተናገረዋል። በሌላ በኩል ትግራይ ከጦርነቱ መገባደድ በኋላ የዝናብ እጥረት ያስከተለው ድርቅ፣ የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝና ሌሎች ተያያዥ ችግሮች ተደማምረው የደቀቀው ምጣኔ ሀብቷ ለወጣቱ መሰደድ ሌላው ምክንያት ነው ብለዋል። ዋዜማም በሕገወጥ መንገደ ተሰደው በሳውዲ አረቢያ እስር ቤቶች ውስጥ የሚገኙትን የትግራይ ተወላጅ ወጣቶች በስልክ አነጋግራለች። ሕሉፍ ዓባይ ተወልዶ ያደገው በሽረ እንዳ ሥላሴ ከተማ ገባር ሽረ በተባለ አካባቢ እንደሆነ ለዋዜማ የገለጸ ሲሆን፣ በዚያም የሚተዳደረው በብረት ብየዳ ሥራ እንደነበር፣ በጦርነቱ ምክንያት ግን ያለው ሃብት ንብረት በሙሉ እንደወደመትና ባዶ እጁን እንደቀረ ይናገራል። ባለትዳርና የአንድ ልጅ አባት መሆኑን የሚገልጸው ሕሉፍ የሚያደርገው ቢጠፋው የራሱንንና የቤተሰቡን ሕይወት ለማሰንበት በሕገ ወጥ መንገድ መሰደድን መምረጡን ገልጿል። ሕሉፍ ያሰበውና የሆነው ለየቅል እንደሆነበትና በሳውዲ አረቢያ የጸጥታ ኃይሎች ተይዞ በእስር ቤት ውስጥ አስቸጋሪ ሕይወት መግፋት ከጀመረ አምስት ወራት መቆጠራቸውን አስረድቷል። ሌላኛው ከውቅሮ ከተማ ተሰዶ እንደወጣና ትምህርቱን ከአስራ አንደኛ ክፍል እንዳቋረጠ የሚናገረው ሀበን ተስፋይ ቤተሰቦቹ ሊያስተምሩት አቅማቸው ባለመፍቀዱ ስደትን መምረጡን ገልጿል። በእስር ቤቶቹ ውስጥ በተመሳሳይ ሁኔታ ተሰደው የወጡ በሺህዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጅ ወጣቶች መኖራቸውን ዋዜማ በእስር ቤቱ ወስጥ ካሉ ሰዎች ማረጋገጥ ችላለች። ዋዜማ በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገረቻቸው የክልሉ ወጣቶች ቢሮና የወጣቶች ማኅበር ወጣቶቹን ከስደት ለመታደግ በፌዴራል መንግስቱም ይሁን በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር በኩል እየተደረገ ያለው ጥረት እጅግ አነስተኛ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ዋዜማ ====================== For more upcoming news Join now and invite to others👇👇👇 https://t.me/amenzehabeshaofficial https://t.me/amenzehabeshaofficial
Show all...
ከባድ የተኩስ ልውውጥ‼️ ዛሬ በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን አነደድ ወረዳ ጃማ ታዳጊ ቀበሌ ላይ ከጠዋቱ 12:30 ጀምሮ በፋኖ ሀይሎች እና በመከላከያ ሰራዊት መካከል ከባድ የተኩስ ልውውጥ እየተካሄደ መሆኑን ነዋሪዎቹ ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል። በተኩሱ ምክንያት ነዋሪዎቹ ከቤት መውጣት አልተቻለም ብለዋል። 👉ከዚህ በተጨማሪ በደቡብ ወሎ ተሁለደሬ ወረዳ ሚግራ ቀበሌ ከባድ የተኩስ ልውውጥ አለ ብለዋል። ====================== For more upcoming news Join now and invite to others👇👇👇 https://t.me/amenzehabeshaofficial https://t.me/amenzehabeshaofficial
Show all...
👍 1