en
Feedback
ዳዊት ጌታቸው።(እይታ)

ዳዊት ጌታቸው።(እይታ)

Open in Telegram

ፍቅር!ሰላም!ግጥም!እይታ! sad! ለ አስተያየት @addemiinilik

Show more
452
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
ደልቶኝ ይመስላል ወይ ተኝቼ ማልነቃው?? ኑሮዬን ሽሽት ነው!! @yefkrgtmdawit ዳዊት ጌታቸው

ሠብረናቸው ለማሩን!! @yefkrgtmdawit
ሠብረናቸው ለማሩን!! @yefkrgtmdawit

ማሳሰቢያ ይህ ግጥም ምንም አይነት አሉታዊ ስብከት የለውም

እኔ ዛፉ.... ያማረለት ቅርንጫፉ አንቺ ቆራጭ.... ያማረልሽ የእጅሽ ምላጭ ከፍሬዬ ጓጓሽ መዝገን ገዘገዝሽው ምስኪን ስሬን 🩸 በዚ አልበቃሽ... ወጣሽብኝ ተንጠልጥለሽ.... ጎድቶኝ ኖሮ መገዝገዜ ተገነደስኩ ከ ገዛ ወንዜ 😭 .....አብረን ወደቅን...🍁 @yefkrgtmdawit @addemiinilik ዳዊት ጌታቸው

ብዙዎቻችን የምንከተለው #ዲያቆን_ሄኖክ_ሀይሌ ሰሞኑን ባጋራው ፅሁፍ እየሩሳሌም ሄዶ እንደነበር ገልፁአል።በዛም ሳለ አንድ የ ስእል መሣያ ቤት ያየው ምስል እጅግ አስገርሞታል....በ አንገቱ የ እሾህ አክሊል ያጠለቀ እና በእጅጉን ያዘነ በግ ምስል ነው።ይህን ምስል ባየው ቅፅበት ጭንቅላቱ ውስጥ የመጣለት ኢሳያስ 53 ነበር....እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።ተጨነቀ ተሠቃየም በሸላቾቹ ፊት ዝም እንደሚል በግ እንዲሁ አፉን አልከፈተም" የሚለው ቃል ነው። ስለዚህ በ @addemiinilik የምትመለከቱት ምስል ትርጓሜ ከዚህ የመጣ ነው!!ለ መምህር ረጅም እድሜ!!!!!

መልካም ልደት ላንቺ አመትሽ ሲነጉድ በ እጥፍ ለምትሞቺ መርዶሽን በደስታ እርጅናን በፌሽታ ጡረታን በእርካታ ለምትቀበይ.... ከ ሻማሽ ጋር አብሮ ውበትሽ ቀለጠ ነገ..ክራንች እንጂ ላንቺ ምኑን ሰጠ?! መጉበጥ አዘናግቶ ጀርባሽ ለይ ሲቀመጥ እንዳትይዥው ሆኖ ልጅነትሽ ሲሮጥ አትሳቂ....አልቅሺ!! መልካም ልደት ለኔ እድሜዬ ሲጨምር ለሚከዳኝ ወኔ!! በቁሜ ሙሾዬን በ ህይወት ሳጥኔን ⚰ መርጬ ለጨረስኩ😭 ተወንጭፎ ሳየው እድሜዬ እንደ ባቡር ጉሮሮዬ አይተፋም ከ ሙሾ በስተቀር ልደቶች ሲያረጁ ብዙ ተደጋግመው ሽፋናቸው ድግስ ውስጣቸው ከፈን ነው!!!!!! @addemiinilik @yefkrgtmwdait ዳዊት ጌታቸው

ሰሞኑን በግል ፕሮፋይሌ ለይ ያደረኩት ምስል እንዳልገባችሁ ነግራችሁኛል ዛሬ አብራራዋለው!!

...ከ እጄ ተሸርፋ የወደቀችውን ለውዝ ተሸክሞ ሊሄድ የሚጣጣረው ጉንዳን ይሄኔ አቤት ደስታው..... "ቤቴ ወስጄ 4 ወር ሸራርፌ እበላዋለው፣ሩብ ለውዝ አይታ ልቧ የማይደነግጥ የጉንዳን ኮረዳ የትኛዋ ናት?! ብቻ እንደምንም ከ ጉድጓዴ ላድርሰው!"የሚል መሰለኝ!! ማን ያውቃል ደግሞ እኔን እንደ ጉንዳኑ የሚያየኝ አምላክ መርካቶን የሚያክል ለውዝ ሸርፎ ሊሰጠኝ እንደሆነ???!! @addemiiniilik @yefkrgtmdawit

መፅሀፈ ፓምፋሎን...የ ፓምፋሎን የመጨረሻው አልበም በቅርብ ቀን በጉጉት እየጠበቅነው ነው😘
መፅሀፈ ፓምፋሎን...የ ፓምፋሎን የመጨረሻው አልበም በቅርብ ቀን በጉጉት እየጠበቅነው ነው😘

ሞተች ያሉኝ ቀን ሳቅ አመለጠኝ አውቃለሁ እና እንዳሳተችኝ! እኔ ጣዲቁን የ እግዜር ባሪያ ለ አፌ ዝማሬ ለ እጄ መቋሚያ ብዬ ነበረ አኗኗሬማ!! ዛሬ ሞታ እሰማይ ቤት... በዛ ጥርሷ ስትስቅለት... አንዱ መልአክ ፈዞ አያት። እያሳየችው የ እጇን ካቴና አገባሀለው ናፍታኝ ና!! አለችው መሠል.... አሁን ገነት ናት😂 comment @addemiinilik @yefkrgtmdawit ዳዊት ጌታቸው

ለመጥፋቴ ይቅርታ እየጠየቅሁ....የጠፋሁበትን ለመቀጣት በርከት ያሉ ግጥሞች ፅፌ ጨርሻለሁ!!!ከ ነገምሽት ጀምሮ የናንተው ናቸው!! ድርጅቱ😂

ዒድ ሙባረክ‼
ዒድ ሙባረክ‼

ጂጂን ለማምጣት ሲጣጣሩ ሳይ ደስ አለኝ!!

"ለሁሉም ግዜ አለው"አለ የስጋ ቤቱ ባለቤት 2 ወር የተዘጋ ስጋ ቤቱን እያፀዳ!! @yefkrgtmdawit @addemiinilik

@yefkrgtmdawit share ለ ወዳጆቻችሁ

አየሽው በአናቴ ለይ እያፏጨ ያለውን ነገር ጥይት ነው ወፍ አይደለም!!...እይው እዛ ማዶ የሚበራውን ደግሞ! ደመራ እንዳይመስልሽ የ አንዱ ባላገር ጎጆ ጋይቶበት ነው!! የገዛ ስንዴአችንን ሽጠን ነው መድፉን የገዛነው እኮ😂...ትላንት ፈንድቃ ያየሻት አበባ ዛሬ ማታ በርታ ተመልከቻት መለኮት ወርዶባት አይደለም!ነዳ ነው!!....ከ ሁሉም ቦታ የሚነሳውን ጭስ እይው የ በአል ኩበት ጭስ እንዳይመስልሽ ከተዳፈነ ሰፈር የተነሳ ነው!!ቀጣዩዋን 2 ደቂቃ ሚሆነው ስለማይታወቅ እቀፊኝ😭😭..... @yefkrgtmdawit @addemiinilik ዳዊት ጌታቸው✍️✍️✍️

ፀልዩ

ከ እሱ ጋር ያሳለፍሽውን ግዜ እንዴት ትገልጭዋለሽ?አልኳት ረጅም ደቂቃ ዝም ብላ አሰበች።አይኖቿ ውስጥ ከ አቅሟ በላይ ትዝታ እንዳለባት አነበብኩ። ለጠየኳት ጥያቄ መልስ ሳትሰጠኝ አጠገቧ ያለውን ክብሪት አንስታ..."እይ"አለችኝ...አንድ የክብሪት እንጨት ለኮሰች ወዲያው ሽታው አፍንጫዬን ወጋው...የክብሪቱ እንጨት ቀስ እያለ እየነደደ ይወርዳል።የነደደው ጠቁሮ ጎበጠ ያልነደደው ተራውን ጠብቆ ይቃጠላል።ጣቷ አካባቢ ሲደርስ ነበልባሏን በጣቶቿ አፍና አጠፋቻት። ከእሱ ጋር ያሳለፍኩት ግዜ ልክ እንዲህ ነበር አለችኝ። አይኗ እንባ ሊተፋ እየተዘጋጀ።አስረጂኝ በሚል አየዋት....ልክ እንደዚህ አጭር ደስ የሚል ሙቀት ያለው ህይወቴን ያበራ አይነት ግዜ አሳለፍኩ ከ እሱ ጋር ግን ብዙ አልቆየም ተለየኝ፤ሄደ።ሲሄድ የተሰማኝ ደግሞ ነበልባሉን ይዞ የመቃጠሉን አይነት ነው፤ያማል። አለችኝ እንባ ከ ግራ አይኗ እየዘነበ።አሳዘነችኝ።ያማል ዴቭ የምሬን ነው አለች በነበልባሉ የበለዙ ጣቶቿን እያሳየችኝ።መሄዱ ነበር የገረማት እና ያሳመማት እኔ ግን እንዴት ሞቷል ብዬ እንደማረዳት ግራ ገብቶኝ ነበር...... @addemiinilik ዳዊት ጌታቸው ወደፊት ከማሳትመው መፅሀፌ የተወሰደ ነው ከወደዳቹት react አድርጉት።አመሰግናለው @yefkrgtmdawit