en
Feedback
ዳዊት ጌታቸው።(እይታ)

ዳዊት ጌታቸው።(እይታ)

Open in Telegram

ፍቅር!ሰላም!ግጥም!እይታ! sad! ለ አስተያየት @addemiinilik

Show more
452
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
ሀገሩ ሸውኸኛ ዳኛው ነገር ሰሚ እኛስ እንሄዳለን ይብላኝ ለከራሚ!!! እሱቤ

Leave አታርጉ

She is mine!!!!

የጀግናውን ሱሪ ሰፊ አበላሽቶበት መንገደኛው ሁሉ ጉልበቱን አየበት። ወይ መናናቅ

አስር ሰዎች እያንዳንዳችን አስር ጓዶቻችንን ወደ ቻናሉ ብናመጣ ሒሳብ አላውቅም ግን ብቻ መአት እንሆናለን

ልዠ ሆይ (በእውቀቱ ስዩም) ትናንት በቀበና ወንዝ ዳር ስራመድ አንድ ከየካ ተራራ ላይ አቅጣጫ የመጡ ጠቢብ አዛውንት አስቆሙኝ ፤ እና የሚከተለውን ለቀቁብኝ፤ “ ልዠ ሆይ! መስከረም ማለት ተፈጥሮ ከጸጋዎቹዋ ሁሉ የክት የክቱን መርጣ የምታቀርብበት ወር ነው፤ ላይንህ አሪፍ ህብረቀለም፤ ላፍንጫህ መልካም መአዛ፥ ለጆሮህ ቆንጆ ጣእመ ዜማ መርኣ ትለግስሀለች! በዚህች አለም ውስጥ ለጥቂት ጊዜም ቢሆን እንድትኖር ስለተፈቀደልህ የምታመሰግንበት ወር መስከረም ነው! ማንነው የማመሰግነው አትበል ? አላህን፥ እግዜርን፥ ዋቃዮን፥ እመቤት ተፈጥሮን ፥ እናትህን ፥ ቆሌህን ፥ ሊሆን ይችላል፤ እንደ መሬት ታጋሽ ፥ እንደ ገበሬ ውለታ አስታዋሽ ሁን! ገበሬ ወረተኛ አይደለም” አትኩራ ገብስ ጎመን ባወጣው ነፍስ ይላል” ገብስ ስለደረሰለት የጎመንን ውለታ አያጣጥልም፤ መስከረም የፈንጠዝያ ወር ነው፤ ሰርተህ ባይሞላልህ ተበድረህ ፥ ተመጽውተህ ያቅምህን ያክል ደግስ ፤ የቻልከውን ያህል አካፍል ! ብላ አብላ! ህዝብ ለህዝብ ሳይሆን ብርጭቆን ከብርጭቆን ማጋጨት ተማር! መጠነኛ ስካር በራስህ ላይ አፋፍም! መስከረም ፤ የሚለው ቃል ስ "መስከርያ" ከሚለው ቃል እንደመነጨ ከቶ አትዘንጋ! ፍቅረኛህን ወይም እማወራህን አውዳመቱን አስተካከህ የከበረ ስጦታ ስጣት! ቤት ባትገዛላት ቤት የሚመታ ግጥም ጻፍላት ! በስስት ሳማት! በልዩ ፈሊጥ እቀፋት ፤ ከምኝታ ፈሊጦች ውስጥ” የእንግላል “ የተባለው ፈሊጥ ለአዘቦት ቀን ብቻ የሚያገለግል መሆኑን አትርሳ ፤ በአውዳመት እና ለክብረበአለት ቀናት ግን ፥ እንደ “ ወስፌ ጥምዝ” “ ምሳር ባንገቴ “ “አሞራ ገፍገፍ ፥ ጫንቃ ሰበር” አይነት ፐዚኖችን መጠቀም ተፈቅዷል፤ ይህንን ሁሌም በልቦናህ መዝገብ አስቀምጠው! ምርጥ የምትለውን ስጥ፤ ኮሚክ ከሆንክ ከባለጌ ወንበራችን ላይ ገፍትሮ የሚጥለንን ቀልድ ልቀቅብን! ዘፋኝ ከሆንክ ወፍ ብቻ ሳይሆን ኮከብ እሚያረግፍ ዘፈን ልቀቅብን ! የቲክቶ ተሳዳቢ ከሆንክ የቸኩ የተሰለቹ ስድቦችን ትተህ ሌላ አምጣ፤ ለምሳሌ፥ ሰገጤ፥ እከካም! ቆማጣ፥ ግማታም፥ ከብት ወዘተረፈ አይነት ስድቦች ከበቂ በላይ ጥቅም ላይ ውለዋል፤ ባዲሱ አመት ብትደግማቸው ስሜት አይሰጡም ! ስድብ ሲደጋገም ቁልምጫ ይመስላል፤ ባዲሱ አመት አባቶቻችን ሲጠቀሙባቸው የነበሩትን አንጋፋ ስድቦችን አድሰህ ተጠቀምባቸው ! ለምሳሌ፥ “ደንደሳም፥” ቅንዳሻም” “ “ ስብድብድ ፥” ዞፍ” እና “ ኩስለመናም “ የመሳሰሉ አጥንት ሰባሪ ስድቦች ከፈለግህ በተመጣጠነ ዋጋ ከኔ መውሰድ ትችላለህ! በተቻለህ መጠን በጎ አድርግ ፤ ተፈለጥ! አልፎ አልፎም አውቀህ ተበለጥ! ያም ሆኖ፥ የሙሉ ጊዜ ጣድቅ ለመሆን አትጋጋጥ! ተሳሳት፤ ያነተ መሳሳት ለፕሮፌሽናል መካሪዎች ፥ ኑዛዜ ተቀባዮች፥ ንስሀ ሰጪዎች፥ ተቺዎች፤ ከሳሾች፥ አሜተኞች ስራ እንደሚፈጥርላቸው አትርሳ!

ከተጋቡ ስድስት ወራቸው ነው እና ይህኛው እንቁጣጣሽ ደግሞ የመጀመሪያው የጋራ በአላቸው ነው።እሱ ያረደውን በግ ግንድ ለይ አንጠልጥሎ ይገፋል።እሷ የምታጨሰው እጣን ሰማይ ውስጥ ያለች መልአክ አስመስሏታል።ከምትቆላው ቡና ልታሸትተው ይዛ ተነስታ መአዛውን ስትጋብዘው ለመጀመሪያ ግዜ አባወራነት ተሰማው።አሽትቶ እንደጨረሰ ግንባሯን ሳማት።ያኔ ነበር ቆንጆ እማወራ እንደሆነች የገባት።ቡና እያፈላች ሰርቃ ታየዋለች።ስጋውን እየገፈፈ በየመሀሉ ይጠቅሳታል።የጠዋቱ ፀሀይ ወርቃማ ጨረሩን የለቀቀበት ግቢአቸው አምሮበታል። ቡናው ደርሷል ና ስትለው የመጀመሪያ የበአል አቦሏን ሊያጣጥም ተቀምጦ አይናን ማየት ጀመረ......ፉት!! መልካም በአል!!!!

አመቱን ብቻ ሳይሆን እኛንም አዲስ ያርገን

መካድ እና መካድ ሲነበቡ ሁለቱም ተመሳሳይ ናቸው።አንደኛውን ጠበቅ አርገን ያነበብነው እንደሆነ ግን በሰዎች መታለል መረሳት የሚለውን ፍቺ ይሰጠናል።ክህደትም ለ ከሀዲው እንዲ ጠበቅ አርጎ ካላሰበበት ሰው ለይ ያደረሰው ጫና በቀላሉ አይገባውም ባይ ነኝ!!አመሰግናለው!!! @dawitview ዳዊት ጌታቸው

የህዳሴ ግድብ 4ኛ ዙር ሞልቶ ሊፈስ ከጫፍ መድረሱን ወዳጆቼ በምስል አስደግፈው አድርሰውኛል።መልካም ነገሩ ከዘመን መለወጫ ጋር ገጥሟል። https://t.me/wasulife/24069 ❤️🙏❤️🙏❤️🙏❤️🙏❤️🙏❤️🙏

አንድ አመት ሞላው😱

ብትጠጊው ግዜ ይህ ወመኔ ልቤ በምኞት ሲላጋ ጥላሽ ቢያርፍበት እንደ ቅቤ ረጋ ለወፍ የሳር ጎጆ ለቀንድ አውጣ ዛጎል ጎርፍ እንደሚያላጋው የብሳና ቅጠል ህይወቴ ሲባክን ደርሰሽ አስጠለልሽው ገዝተሽ መንፈሴን ልቦና ሸለምሽው ቁምነገር ሸምነሽ በልኬ ሰፋሽው። ክንዴን ብትይዥው የልቤ ደረሰ በገዛ ደምስሬ ወንድነት ፈሰሰ በየትኛው ፅድቄ አንቺን ለኔ ሰጠ ያቀፍሽው ጀርባዬ ላባ አቆጠቆጠ ፀደኩኝ... መነነነነንንኩኝ.... አንቺን ስለያዝኩኝ....😘😘😘😘 ለ:-ፈረንሳዊቷ ወጣት ዳዊት ጌታቸው @dawitview

አሪፍ ግጥሞች እየመጡ ነው

ጅል ያሬድ

soulmate 😘😘😘

አቡሽ ዘለቀ!! 💪