en
Feedback
LEARN TECH ||ethiopia ®

LEARN TECH ||ethiopia ®

Open in Telegram

We are dedicated to provide tech tips and other tech related information. #join and #share

Show more
1 495
Subscribers
No data24 hours
-107 days
-5530 days
Posts Archive
🗞first ደራሲ እሆናለው ማለቱ ቤተሰቡን አስደነገጠ........ 🗞second የሚፅፋቸው ግጥሞች ፓለቲካ ላይ በማመዘናቸው ምክንያት ከ3 ጊዜ በላይ ዘብጥያ ወረደ....... 🗞Third በእስርቤ
🗞first ደራሲ እሆናለው ማለቱ ቤተሰቡን አስደነገጠ........ 🗞second የሚፅፋቸው ግጥሞች ፓለቲካ ላይ በማመዘናቸው ምክንያት ከ3 ጊዜ በላይ ዘብጥያ ወረደ....... 🗞Third በእስርቤት ውስጥ ሆኖ ዱላና እና የተለያዩ ምቶችን ከቀመሰ በኃላ ተፈታ........ 🗞 forth እስከመቼ ከህይወቴ ግብ ሸሽቼ ብሎ በ38 አመቱ አንድ መፅሐፍ ፃፈ.......... 🗞 final በመላው አለም የሚገኙ በርካታ ሚሊየን አንባቢያን የፃፈውን አንብበው የማይጠግቡለት የዘመናችን ተወዳጅ እና ቁጥር አንድ ደራሲ ሆነ.......... 👤ይሄ ደራሲ ፓውሎ ኮዮልሆ ይባላል።የአልኬሚስቱ እና የሐጅ ጉዞ የተባሉት ድንቅ መፅሐፎች ደራሲ ነው @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom

አልኬሚስቱን በጥቂቱ፦ “አልኬሚስቱ” በፓውሎ ኮህሊኦ በፓርቹጊዝ ቋንቋ የተፃፈ በዓለማችን ታሪክ በብዛት ከተሸጡ መጽሐፍት አንዱ ነው፤ የመጽሐፉ ታሪክ ህልሙን ስለሚከተል አንድ የሳንቲያጎ እረኛ ሲሆን ታሪኩ በዓለማችን ላይ ብዙ ሰዎች ስለህልማቸው እንዲኖሩ አነሳስቷቸዋል፡፡ መጽሐፉ ከ80 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች የተተረጎመ ነው፡፡ ይኸ መጽሐፉ በህይወታችን ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ ስለሚገባን ነገሮች ምሪት ይሰጣል፤ እነኝህ ትምህርቶች በዐስር ነጥቦች ሊቃኙ ይችላሉ ... እንደሚከተለው ቀርበዋል መልካም ንባብ! 1. የአሁን ስጦታን መቀበል፡፡ በታሪኩ ህይወት የአሁን ጥርቅሞች መሆንዋን ያሳየናል፤ አሁንን የዘነጋ ህይወቱን የዘነጋ ነው ይለናል፡፡ ህይወት ቀደም ሲል የኖርነው ወይም ወደፊት ስለምንኖረው አለመሆኑንና በአሁን ላይ የተመሰረተች መሆኗን አጉልቶ | እንድናይ ያደርገናል፡፡ በአሁን ላይ ያተኮረ ሰው ደስታው ወደር እንደሌለው እንዲሁም ባለፈው ጊዜ ውስጥ ላሁን የሚሆን ቦታ እንደሌለ የወደፊቱም ገና የሚመጣ እንጂ | እያመለጠን እንዳልሆነ፣ ስላለፈው መጨነቅና ስለወደፊቱ ተስፋ መቁረጥ የአሁንን ሚዛን እንደሚያከሳ፣ ነገር ግን አሁን ስንል በተረጋገጠው መስክ ላይ መሆናችንና በአሁን ላይ ተነሳሽነቱ ካለን ለአሁን የምንሰጠው ምላሽ ህይወታችንን እንደሚመራው ያሳየናል፡፡ 2. ውሳኔ ማድረግ። አንድ ሰው ለአንድ ዓላማ ውሳኔ ሲያደርግ ህልመኛ ሳይሆን ከነበረበት ከማዕበል ነፃ ክልል ወደሚታገለው ኃይለኛ ዥረት እየገባ መሆኑን ያስገነዝባል፡፡ አንድ መርከብ ማዕበል ፈርቶ በባሕር ዳርቻ ታስሮእንደማይቀመጥና ስሪቱ ለዚያ እንዳልሆነ፣ ይልቁኑ መልህቁን ፈትቶ ማዕበሉን እንደሚገጥም፤ እኛም ለህይወት ዓላማዎች ስንል መልህቃችንን ፈትተን በጉዞውሳኔዎች መመራት እንዳለብን፤ በባህር ዳርቻ ቁጭ ለማለት እንዳልተፈጠርን ይልቁኑ በማዕበሉ ውስጥ ስናልፍ እድፋችን እንደሚጠራና እንደምናበራ ያሳየናል፡፡ 3. ህልማችንን ስንከተል ከሚገጥሙን ችግሮች የበለጠ ፍርሃት የስኬት ደንቃራ ነው፡፡ ፓውሎ፣በማንኛውም ጉዟችን ከሚገጥሙን መከራዎች ይልቅ ከጉዞ ታቅበን የምናሳልፈው የፍራቻ ስቃይ የከፋ መሆኑን ይነግረናል፤ ጉዞን እንድንመርጥም ይገፋፋናል፤ ህልማችንን የሚከተል ልብ ካለን በውስጡ ስቃይ እንደማይኖር፣ ቢኖርም ጣፋጭ ውጤት ያለው መሆኑን ያሳየናል፡፡ ማንኛውም የአዲስ ነገር ፍለጋ ጉዞ ወዳልታወቀ ቦታ የሚደረግ እንደመሆኑ መጠን መልካም አጋጣሚዎች እንዳሉት ሁሉ አደጋዎችም እንዳሉት ይጠቁመናል፤ ይሁንና አስፈሪ ከሚመስል አደጋ ጀርባ ጣፋጭ ሽልማት መኖሩን በማመልከት ህልምን የመከተል ዋጋን ያሳየናል፡፡ 4. እውነት የሆነ ነገር በሙሉ ፅኑ ነው፡፡ ከንፅህና የተገኘ ነገር በሙሉ እንደማይጠፋ፣ የጠፋ ቢመስል እንኳ ጊዜጠብቆ ተመልሶ እንደሚመጣ በታሪኩ ያሳየናል፤ እውነት በጢስ ሊሸፈን እንደማይችልና ሁልጊዜ ፀንቶ እንደሚቆም እንዲሁም ለትክክለኛ ነገሮች መቆም እንዳለብን ይህ ቁመናችንም በጊዜ ብዛት በሚገጥመው ፈተና ማዘመም እንደሌለበት ይመክረናል። 5. አዲስ ነገር ከፈለግን ከምቾት ቀጠናችን መውጣት አለብን፡፡ በየዕለቱ ፀሐይ ወጥታ ስትጠልቅ ስናይና ሁሉም ቀናት ተመሳሳይ መስለው ሲታዩን የተለመደን ነገር ብቻ መምረጥ እንደሌለብን ይጠቁመናል፡፡ ነገሮች ተፈታታኝ ቢመስሉም ብሩኀ ገጽታም እንዳላቸው እንዲሁም ሁለቱን የምትለይ ቀጭን መስመር ያለች ሲሆን በዚህች ድንበር ውስጥ ብዙ መመላለስ እንዳለብን ያሳየናል፤ ይህ ሁኔታም ከምቾት አርቆ እንደሚወስደን ነገር ግንድንበራችንን እያሰፋ አንደሚሄድ፣ ጉዟችን ወደምናይበት አቅጣጫ ከሆነደግሞ የምናየው ነገር ሁሉ በጊዜ እየጠራ እንደሚመጣ በተግባር ያስመለክተናል፡፡ 6. የአንዱ ስኬት ወደሌሎችም ሊተላለፍ የሚችል በጎ ተፅእኖ አለው፡፡ ዛሬ ላይ ከትላንት የተሻልን ለመሆን ስንሰራ፣ ስንጥርና ለውጥ ስናመጣ፤ለውጡ ሌሎችንም የሚነካ ይሆናል፡፡በሂደቱም በዙሪያችን ያሉ ነገሮች በሙሉ የተሻሉ ይሆናሉ፡፡ እድገትና ለውጥ ወደ እውነታ የሚመጣው የራሳችን ስሪት ስንሆን መሆኑን ተፅእኖውም በኛ ላይ ብቻ ተወስኖ እንደማይቀርና ወደ ቤተሰብ፣ ጓደኛና ማኀበረሰብ እንደሚጋባ ለዚያም እንድንተጋ ይመክረናል፡፡ 7. ዓለምን በምንመርጠው መንገድ እንጂ በምትመርጥልን መንገድ ብቻ መጓዝ እንደሌለብን፡፡ የዓለም ሰዎች በሙሉ ዓለምን ለመቀበል ቢመርጡ ኖሮ እጅግ ብዙ የፈጠራውጤቶች ባልተከሰቱ ነበር፤ ዓለም በሰጠችን ብቻ ቢሆን ኖሮ ጨለማነበብርሃን አይገፈፍም፣ አየሩንም ቀዝፈን አንሳፈፍም ነበር፡፡ መልካም ስኬቶችናፈጠራዎች የሚጀምሩት የማይቻሉ መስለው የሚታዩ ነገሮችን በማሰብ ነው፡፡ 8. የራሳችንን ምትክ ስለመፍጠር፤ ወድቆ መነሳት፡፡ የህይወት ሚስጢር ሰባት ጊዜ ለመውደቅ ፈቃደኛ መሆንና በስምንተኛውመነሳት ስለመሆኑ በተግባር ያሳናል፡፡ ምክንያቱም ወደፊት ሊያስጉዘን የሚችለው ትክክለኛ ጥንካሬያችን ያለው ወይም የሚገኘው በስምንተኛው ላይ ነውና፡፡ እንደምሳሌም በታሪክ ውስጥ ከታዩ ታዋቂ ልብ-ወለድ መጽሐፍት ቁጥራቸው የበዛ ውድቅ ከተደረጉ በኋላ የታተሙ መሆናቸውን አሰታውስ። ዋናው ነገር እነዚህ ጸሐፊዎች ፈጽሞ ተስፋ አልቆረጡም፡፡ 9. በጉዟችን ላይ ብቻ ማተኮር፡፡ ሁሉም ሰው ለሌሎች ሰዎች ህይወት እንዴት እንደሚመራ ግልጽ ግንዛቤ ያለው ይመስላል፤ ምክንያቱም ሰዎች ሌሎችን እንዲህ ማድረግ አለባቸው፣ እንዲያ ማድረግ የለባቸውም ሲሉ ይደመጣሉ፤ በሌሎች ላይ ተፅእኖ ማሳደር ቀላል ይመስላል፤ ነገር ግን የሌሎችን ኑሮ እንድንኖር ብንደረግ ይቸግረን ይሆናል፡፡ ከሌሎች ላይ ምክሮችን በመቀበልና በመማር መጓዝ ምንም ስህተት የለበትም፤ ነገር ግን ከፍላጎታችንና ከስሜታችን ጋር መስማማት እንዳለበት ያስታውሰናል፡፡ በራሳችን ላይ ማተኮር ኃይል እንደሚያጎናፅፈን መንገዶችን ያሳየናል፡፡ 10. እርምጃ መውሰድ፡ የመማር መንገዱ አንድ ብቻ ነው፤ ተግባር ነው ይለናል፡፡ ስለአንድ ነገር ዐይናችን እስኪቀላ ልናነብና ልናጠና ወይም ጆሯችን እስኪሰለች ልንሰማ እንችላለን፤ ነገር ግን ሂደቱ ሙሉ የሚሆነው ቀሪው የተግባር ክፍል ላይ እርምጃ ስንወስድ ነው፡፡ @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom

🔴 ርዕስ የታንጉት ሚስጥር የድሮ ምርጥ መፅሐፍ ነው አንብቡት.

✍    #የአምላክ__ደብዳቤ  እንዲህም ሆነ    ከዕለታት 1 ዕለት አንዲት ብቻዋን የምትኖር ሴት ከመኝታዋ ስትነሳ አንድ ፖስታ አልጋዋ አጠገብ ካለ ኮመዲኖ ላይ ተቀመጦ ታገኛለች፡፡ ወዳው ፖስታውን ስትከፍት በውስጡ አጠረ ያለች ደብዳቤ አገኘች፡፡ ደብዳቤው እንዲህ ይነበባል፡፡ "ዛሬ በእንግድነት ለእራት አንቺ ቤት ስለምመጣ ተዘጋጅተሽ ጠብቂኝ፡፡" ከታች ላኪ በሚለው ቦታ " #አምላክ " የሚል ተፅፏል። ሴቲቱ ደነገጠች፡፡ ነገር ግን ከተረጋጋች በኀላ ያላትን ገንዘብ ከዚም ከዛም ለቃቅማ ማታ ለእንግዳ የሚሆን ነገር ለማዘጋጀት የሚረዳትን የሚበላ፣ የሚጠጣ ነገር ለመግዛት ከቤት ወጣች፡፡   ገበያ ውላ ለእራት ግብዣው የሚሆናትን ነገር ገዛዝታ ወደ ቤት ስትመለስ እመንገድ ላይ አንድ ርሀብ ያጎሳቆለው ህፃን ከያዘችው ዳቦ እንድትሰጠው ለመናት፡፡ ዳቦውን የገዛችው ማታ በቤትሽ እንግዳ ነኝ ላላት ፈጣሪ ነው፡፡ እና ለእዚህ ህፃን ከሰጠችው ማታ ለአምላኳ የምታቀርበው ልታጣ ነው ትንሽ ካመነታች በኃላ ለተራበው ልጅ ሰጠችው፡፡ አሁንም ትንሽ እንደተራመደች አንድ በእድሜ የገፉ አባት "ልጄ ተጠማው፤ እባክሽ አትለፊኝ" እያሉ ለመኗት፡፡ አሁን ልቧ ትንሽ ካመነታ በኃላ ለአምላኳ የገዛችውን ለስላሳ ለተጠሙት አባት ሰጠቻቸው፡፡     አሁን የገዛችውን ምግብና መጠጥ ለተቸገሩ ሰጥታ ስለጨረሰችው በቀራት ገንዘብ ትንሽ ነገር ለመግዛት ወደ ሱቅ ስታመራ ሌላ ነዳያን "የዕለት ጉርሴን እባካችሁ" እያሉ ሲለምኑ ተመለከተች፡፡ አሁንም አላስቻላትም እጇ ላይ የቀረችውን ገንዘብ ሰጠቻቸው። በስተመጨረሻ አምላክን ማታ ምን እንደምታበላ፣ እንደምታጠጣ እያሰበች ባዶ እጇን ወደ ቤት ስትመለስ "አንድ በእድሜ የገፉ እናት የለበሱት ልብስ ተቀዳዶ አይደለም ሳይለብሱ በጃንጥላ ውስጥ እንኳን አልፎ የሚያቃጥለው ፀሀይ ቀጥታ ቆዳቸውን እያገኛቸው ሲቃጠሉ ተመለከተች፡፡ ወዲያው የለበሰችውን ሹራብ አውልቃ አለበሰቻቸው። በስተመጨረሻ መሸና ፈጣሪ ከቤቷ መጣ፡፡ ምንም ስላላዘጋጀች ደነገጠች፡፡          "ጌታ ሆይ ይቅርታ ምንም የሚጠጣና የሚበላ አላዘጋጀሁም አለች፡፡" ፈጣሪም በመቀጠል "እንዴ አበላሽኝ፤ አጠጣሽኝ፤ እኮ" አላት፡፡ "እንዴ መች አግኝቼህ ? ነው ያበላውህ? ያጠጣውህ?" አለችው ፈጣሪም "ቀን ስታጠጪ፣ ስታበይ፣ እንዲሁም ስታለብሺ የነበረው እኔን ነው፡፡" አላት፡፡ ብዙዎቻችን ማለትም የየትኛውም ሀይማኖት ተከታይ እንሁን ሀይማኖታችን ለፈጠረንን አምላክ መልካም እንድንሰራ እንደሚያዝ እናምናለን፤ ለእሱ ሁሉን እናረጋለን እንላለን፡፡ ነገር ግን አጠገባችን ያሉትን ርሀብተኞች አንድ ጉርሻ አናጎርስም፤ አንዲት ጉንጭ አናጠጣም፤ አይደለም አዲስ ጠቦንና አርጅቷል አንለብሰውም ያልነውን ብጫቂ ጨርቅ አንሰጥም፡፡ ታዲያ ምኑ ላይ ነው ፈጣሪያችንን መውደዳችን? የቱ ጋር ሀይማኖታችን የሚለውን መፈፀማችን፡፡ ቢገባን ፈጣሪ ተጠምቶ ልናጠጣው የሚገባን ወገናችን ነው፤ ቢገባን ተርቦ ልናበላው የሚገባን ጎረቤታችን ነው፡፡ ፈጣሪ መልካም ልቦናን ይስጠን፡፡         አሜን ሰላማቹ ይብዛልኝ:: ምንጭ፡ ከደራሲያን አለም    @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom

ልምድ ያመጣብን ጦስ (ታደሰ ደምሴ) "ጌታ መጣ" ሲባል፣ መቸም ልምድ ሆኖብን፣ መቸም ባህል ሆኖን ወይራ ዛፍ መዘንጠፍ ዘንባባውን ማንጠፍ ይሔው በቀደም ለት፣ እቺ የኛ ሀገር ከጉድ ገብታ ሳለ ከጉድ የሚያወጣት፣ "አሻጋሪ ጌታ" መጣ ስለተባለ እንደለመደብን፣ አደባባይ ሙሉ በወግ ተሰልፈን ዘንባባ እያነጠፍን ወይራ እየዘነጠፍን በአሸሸ ገዳሜ፣ በእልልታ በሆታ መሲሁን አከበርን😭 ግና ምን ዋጋለው... እንዲያ ባደባባይ፣ ሰግደን አጨብጭበን፣ "ሺ ዓመት ንገስ" ያልነው ተሳስተን እንጂ ለካ አህያውን ነው! ይሔው... አምስት ዓመት ሙሉ፣ የታሰረ አህያ ጫንቃችንን ጋልቦን እሱም አልተፋታን እኛም ጌታ አላየን እንጃልን እንግዲህ ምንእንደሚበጀን 😭😭😭 @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom

ሀዲስ ደራሲ - በዐሉ ግርማ ዘውግ - ልብወለድ የህትመት ዘመን - 1975 ዐ.ል የገፅ ብዛት - 325 ከ book for all ምርጥ 30 ሀገርኛ መፅሀፍት አንዱ ! ይ🀄️ላ🀄️ሉ @OLDBOOKSPDF

✨"ያልሆንከው ነገር ሁሉ ሲከብህ የሆነከውን ያንን ነገር አትርሳ" 🌙አንድ ብርሃን ብሎ እራሱን ሚጠራ ነፍስ ነበር። ብርሀን መሆኑን በደንብ ያቀዋል። ሁሉም ብርሀን ብለው ይጠሩታል። ትንሹ ነብስ እራሱን ብርሀን እንደ ሆነ ይወቅ እንጂ ብርሀን ምን ማረግ እንዳለበት አያቅም። የብርሀን ጥቅሙን አልተረዳም ነበር። ታድያ ይሄ ትንሽ ነብስ ከቃላት በላይ መሆን የሚፈልገውን ነገር ለመራዳት የሚያስችለው ሁኔታ ውስጥ መገኘት ስላልቻለ ምንነቱን ከቃላት በላይ በድርጊት አያውቅም ነበር። ታድያ ይሄን ሁኔታ በመፈለግ በመሻት ይኖር ነበር። !💫 መሻቱ ትልቅ ነበርና ፈጣሪ አንድ ቀን ወደዚህ ትንሽ ነብስ ተጠግቶ " ትንሹ ብርሀን ሆይ መሻትህን አይቼ ተገርምያለው። መሻትህን ለማግኘት ምን ታረጋለህ? " አለው። ትንሹም ነብስ:- "ፈጣሪ ሆይ ሁሉንም አረጋለው" አለው። ፈጣሪም:- " ትንሹ ነብስ ሆይ አከባቢህን እስኪ ተመልከት አለው" አከባቢውን የተመለከተው ትንሹ ነብስ አንድ ትልቅ እውነታን ተረዳ። እከባቢው ሁሉ በብርሀን ነብሳት የተሞላ ነበር። ሁሉም ያበሩ ነበር። ፈጣሪም:- "ትንሹ ነብስ ሆይ ምን አየህ ?" አለው። ትንሹም ነብስ:-"በትልቅ ብርሀናት የተከበብኩ ብርሀን እንደሆንኩ!" አለው። ፈጣሪም:- " መሻትህን ታገኝ ዘንድ ብርሀንም ሚሰራውን ታውቅ ዘንድ የሆነ ምታረገው ነገር አለ" አለው ። " ከነዚህ ብርሀናት ውስጥ አውጥቼ ወደ ጨለማ እልክሀለው" አለው ፈጣሪ ደግሞ። " ጨለማ ምንድነው ፈጣሪ ሆይ?" አለ ትንሹ ነበስ። ፈጣሪም:- "ትንሹ የብርሀን ፀዳል ሆይ ጨለማማ አንት ያልሆንከው ያ ነገር ነው " አለው። 🪐በዚህ ተስማምተው ትንሹ ብርሀን ወደ ጨላማ ግዛት ተላከ። ትንሹም ነበስ ለመጀመርያ ጊዜ ባልሆነው ነገር ሲከበብ ፍርሀትን ተጋፈጠ። በብርሀናት ጥላ ስር ሆኖ የሚያበራው ያ ትንሽ ሻማ ተሸበረ። "አባቴ ሆይ ወዴት አለህ" ብሎ ተጣራ። ፈጣሪም:-  " አይዞህ አለው። እራስህን ለማውቀ ብዙ ጥረሀልና ይኸው እራስህን ምታውቅበትን ሁኔታ አመጣውልህ።" አለው ፈጣሪ። ትንሹ ብርሀንም ግራ ተጋባ። " ፈጣሪ ሆይ ዙርያዬ ሁሉ በጨለማ ተውጧል። እንዴት ይሄ ለኔ ጥሩ ሁኔታ ሊሆን ይችላል?" አለ ትንሹ የብርሀን ወጋገን። "ልጄ ሆይ ያልሆንከው ነገር ሁሉ ሲከብህ ያኔ የሆንከውን ያንን ነገር አስታውስ። ☀️ጨላማ ቢከብህ ጨለማውን ትተተህ ብርሀንህን አስታውስ። ጨለማውን ከመርገም ጨለማው ላይ ብራ። ብርሀን የመሆንህ ቁም ነገር ጨላማ ላይ እንድትበራ ነውና። በብርሀናት ተከብህ ሳለ ያኔ ምን እየሰራህ እንደሆነ አታውቅም። ምክንያቱም ብርሀን ብርሀን ላይ ቢያበራ ምንም የሚፈጠር ነገር የለምና። አሁን ግን የመፈጠርህ ትርጉሙ ብርሀን የመሆንህ ሚስጢር ተገልጦልሀልና ሄደህ በደንብ አብራ።" አለው። (from the book conversation with God) ✨የሁላችንም ጥንካሬ ያለው በተመቻቸው ስፍራ ሳይሆን ሁኔታዎች ፈር ሲለቁ ጨለማ ሲከበንና ህይወት መውጫ የሌላት መስላ ስታስጨንቀን በምንወስነው ውሳኔ ውስጥ ነው። የማንነታችን ትርጉም የሚለካው ነን ብለን የምናስበው ማንነታችን ፈተና ሲገጥመው በምንወስደው እርምጃ ነው። እራሳችንን የፍቅር ጥግ አርገን የምንይ ከሆነ የፍቅር ጥግ መሆናችንን የሚረጋገጠው ጥላቻ ግድ የሚሆንበት ቦታ ላይ የፍቅርን ፀዳል መልቀቅ ስንችል ነው። የይቅርታ ሰው መሆናችን የሚታወቀው ይቅርታ ለማረግ በሚያስቸግርበት ሁኔታ ላይ ይቅር ማለት ስንችል ነው። ✨ምክንያቱም ነን ብለን የምናስበው ሁሉ ያልሆነው ነገር ሲመጣ ይፈተናልና። እናም በምትፈተንበት ሰዓት የምታረገው ትልቁ ነገር ትልቁ መሸጋገርያህ ይሆናል። ☀️ታድያ ፍቅር ስትሆን ጥላቻ መሀል ትሄዳለህ። ህይወት ስትሆን ሞት መሀል ትራመዳለህ። ሰላም ስትሆን ጦርነት መሀል እራስህን ታገኛለህ። ደግ ስትሆን ክፋት ይከብሀል። እና ይሄ ሁሉ የሚሆነው ነኝ ብለህ የምታስበውን ብርሀን ነኝ ብለህ የምታስበውን ፍቅር ነኝ ብለህ የምታስበውን መልካምነት ታረጋግጥ ዘንድ ነው። " እኔ መልካም ሆኜ ሳለው ለምን መከራ በኔ ላይ ፀና" ብለህ ምታዝን ከሆነ አላማውን ስተሀል። ማንም ክፉ የለምና። ሁሉም ደግ ሁሉም ቸር ሁሉም ፍፁም ነውና። ነገር ግን አንዳንዱ ሁኔታው ሲናወጥ ማንነቱ መርሳቱ ነው። ስልጣን ፤ ገንዘብ፤ ረሀብ ፤ ጥጋብ ፤ ድህነት . . . ወዘተ ማንነትን የማስረሳት ችሎታ አላቸውና። ታድያ ሚሰርቅ ስታይ ሌባ ባለመሆንህ እራስህን እንደ ፃዲቅ አትቁጠር። ምክንያቱም የሌባው ቦታ ላይ ብትሆን እራስህ ያንን ነገር ላለማረግህ ምንም ዋስትና የለህምና። ስንቶች በተናገሩ ባወገዙት በጠሉት ነገር እራሳቸው ገብተውበት አይተናልና። 💜ፍጥረት ሁሉ ፍፁም መሆኑን ተረዳ። ፍፁም ያልሆነ ሁኔታ እንጂ ፍፁም ያልሆነ ሰው የለም። ሁሉም ሰው ክፍቶብህ ከታየህ ከመራገም ይልቅ ነኝ ብለህ ምታስበውን መልካምነት ሁን። ጥላቻ ሲከብህ ነኝ ብለህ ምታስበውን ፍቅር ሁን። ይሄን መሆን ካልቻልክ ግን ሁሌም ቢሆን ማንነትህን ሳታውቅ ትኖራለህ። እራስን መካድ የፈጠረን መካድ ነው። ውብ እና ድንቅ ሆነህ ከተፈጠርክ ውብ ና ድንቅ ሆነህ መኖር ብቸኛው አማራጭህ ነው። ውብ ና ድንቅ ሆኖ የተፈጠረው ደግሞ አንተ ብቻ ሳትሆን ሁሉም ነውና መንገዱን የሳተ ሰው ሲጎዳህ ከመርገም ይልቅ ወደ ውብነቱ ወደ መልካምነቱ የሚመለስበትን ብርሀን አብራበት።                       📃የመኖር ጥበብ 💫☀️🌘💫☀️🌘💫☀️?💫☀️🌘      ምንጭ፦EthioHumanity ❤️❤️❤️ @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom

የፍቅር እስከ መቃብር መፅሐፍ ደራሲ ማነው????
Anonymous voting

Select the correct spelling
Anonymous voting

ወታደሩ በማለዳ ተነስቶ ልብሱን እየለባበሰ ነው።የሚፈልጋቸው ትጥቆች፣ስንቁንም ጭምር በሚገባ ተሟልተውለታል።ጠላቱን በሩቅ የማያይበት የጦር ሜዳ መነፅሩን አስቀድሞ ይዟል።ወደ ፍልሚያው ስፍራ ሲደርስ ግን አንዲትም ጥይት ሳይተኩስ ተማረከ። ፍቅርም ይህን ይመስላል፤ለማሸነፍ ሳይሆን፣እጅ ለመስጠት የሚታጠቁበት እና የሚስማሩበት ጦርነት! ከ ያልተንኳኩ በሮች መፅሐፍ ገፅ 43 የተወስደ @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom

Select the correct spelling
Anonymous voting

እስኪ ስለ ደም ዓይነታችን የተወስነ ነገር እንመልከት። ደም የፍጥረት ሁሉ መጀመሪያ ነው። ለመኖራችን ወሳኝ በመሆኑ፣በጤና የመኖራችን ወይም በሽተኛ መሆን፣የአእምሯችን ጥንካሬም ሆነ ድክመት የሚስጥሩ ብቸኛ ቁልፍ የምናገኘው በዚሁ የደማችን ዓይነት ነው። ይኽውም የደም ዓይነታችን ለሰዉነታችን አስፈላጊ የሆነዉን የምግብ ዓይነትና ውጥረትን ለመቋቋም የምንውስደው እርምጃ ይወስናል ምልክት ነው። የደም ዓይነት ከምግብ ጋር ያለው ዝምድና በየጊዜው የሚለዋወጥ ሳይሆን ቋሚ የሆነ ኬሚካላዊ ቅንብር ይዞ ከመፈጠር እስከ ሞት ድረስ አብሮ የሚጓዝ ነው። ለዘመናት ጤናኛ ወይም በሽተኛ የመሆናችን ነገር ምስጢር ከደማችን ዓይነትና የአመጋገብ ዘዴ ጋር መያያዙን ልብ ሳይባል ቆይቷል።የሚያስገርመው ነገር ሰውነታችን ጤና በማይስማበት ጊዜ የምግብ ፍላጎቱን ወደ ማማረጥ እንገባለን፣ ደማችንም በዓይነቱ እንዲቀርብለት ይፈልጋል።እንዲሁም በተጨማሪ ልብ ብለን ካየን የተወሰነ የምግብ አይነት ለአንዳንድ ሰዎች መደበኛ ምግባቸው ሆኖ የስውነታቸውን ክብደት በማስተካከል ጤናማና ንቁ እንደሆኑ ሲረዳቸው፣ ባንፃሩ ይኽው ምግብ እየተመገቡ የስውነታቸው ሚዛን በየጊዜው እየጨመረና የስውነታቸው ቅርጽም እየተበላሸ ድካም የሚስማቸው ብዙ ናቸው። እናም ከላይ ወዳየነው አንድነትና ልዩነት ውስጥ ስንገባ በቂ ግንዛቤ ኖሮን በጥንቃቄ የአመጋገባችንን ዘዴ እንድናስብበት ይረዳናል።የደም ዓይነት ከመጀመሪያው የስው ዘር ጀምሮ ለትውልድ በተፈጥሮ የማያቋርጥ ሰንስለታዊ መስመር ይዞ እየተጓዘ ነዉ አሁን ወደ ምንኖርበት ወቅት የደረሰው።ስለዚህ የደም ዓይነት የማያረጅ የማይወድም የቅድመ ዝርያዎቻችን የማይፋቅ የታሪክ አሻራ መዝገብ ነው። ከ የጤና ምስጢራዊ ቁልፍ መጽሐፍ ገጽ 11 የተወሰደ አዘጋጅ፡-ዶ/ር ፒተር ጀይ.ዲ.አዳሞ ትርጉም፡-ዮናስ ተዛረ @Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom

ሃዋርድ ጋርደነር የተባለ የሥነ-አእምሮ ሊቅና ፈላስፋ «መጥፎ ሰው ጥሩ ባለሙያ ሊሆን አይችልም፤ መጥፎ ባለሙያም ጥሩ ሰው ሊሆን አይችልም።» በማለት እንደጻፈ አንብቤያለሁ። እውነት ነው። የተዋጣለት ባለሙያነትን የሚሸከመው የተስተካከለ ሰብዕና ይፈልጋል። ሰይፍና ሰገባ፣ ጎራዴና አፎት፣ ዳዊትና ማኅደር፣ ፅላትና ታቦት፣ ነፍስና ሥጋ ናቸው። ሙያና ተግባር የሌለው ጥሩ የሚባል ሰው "ጅል" እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም። በሌላ በኩል ብዙ የሚያውቅ፣ ብዙ የተማረ፣ በሙያው የተካነ ቢመስልም ክፉ ሰው ከሆነ ሙያውን አንድም ለግል ጥቅም ማካበቻ፣ ለርካሽ ተወዳጅነት ማፍሪያ፣ አለዚያም ለሰው ልጅ መጥፊያ አውሎት መጨረሻ ክፋቱ ሲገለጥ ሙያውን ያረክሰው እንደሆን እንጂ  አያኮራውም። የመርዝ ጋዝ የተሠራው ክፉ ሰብዕና ባላቸው "ጥሩ" ባለሙያዎች ነበር። ክፉ ሰው መልካም ተግባር ሊወጣው አይችልም። መልካም ተግባር የሚመነጨው ከበጎ ሕሊናና ከንፁሕ ልብ ብቻ ነው። እርግጥ በጎ ሐሳብ ያመነጨ ሁሉ ወደ ተግባር ላይቀየር ይችላል። ነገር ግን የበጎ ተግባር ምንጩ በጎ ሐሳብና ቅን ልብ ናት። ከኩርንችት በለስ፣ ከበለስም ኩርንችት አይለቀምምና። «የሀገራችን የትምህርት ሥርዓት ትልቁ ድክመቱ መልካም ሰብዕና ሳይቀርፅ ጥሩ ባለሙያ ለማፍራት ማሰቡ ነው። እናም ብዙ ባለዲግሪዎች፣ ብዙ ባለ ሰርተፍኬቶች ብናፈራም በተግባር ከማይምነት አልወጣንም። ሰይፉን እንጂ ሰገባውን፣ ጎራዴውን እንጂ አፎቱን አላዘጋጀንም። ያለአፎት የተሳለው ጎራዴ ያገኘውን ሁሉ ሸረካከተና ብዙ ሳይቆይ ዶለዶመ። ዳግም እንዳይሞረድም ደንደስ አውጥቶ ቁጭ አለ። ነፍስ ሠርተን ሥጋ አልነበረውምና ተንሳፎ መሬት ሣይነካ ሰው ሳይሆን መንፈስ ሆኖ ቀረ።» ይለኝ ነበር ዶ/ር ክብረ በዓል። ━ ሚተራሊዮን 117 - 118 @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom

"የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እኔን አምባገነን ይለኛል።አሜሪካም እኔን አምባገነን ትለኛለች።የአውሮፓ ህብረትም እኔን አምባገነን ይለኛል።እነሱ ኢራቅን ከመውረራቸው በፊትም ይሄን ሲሉኝ ነበር። ነገር ግን እግራቸው የኢራቅን መሬት እንደረገጠ መጀመሪያ የተቆጣጠሩት የወርቅና የነዳጅ ማምረቻችንን ነበር።በእርግጠኝነት የምነግራችው በሊቢያም ሆነ በቀሪው አለም ማድረግ የሚፈልጉት ይሄን ብቻ ነው። በእኔ ዘመን የተራበ፣የተጠማ፣መድሀኒት መግዣ አጥቶ የሞተ፣ልጁን ከፍሎ የሚያስተምር፣መኪናና የእርሻ ቦታ፣እንዲሁም የግል ቤት የሌለው ሊቢያዊ የለም።ይሄ አምባገነንነት ከሆነ አዎ እኔ ጋዳፊ የእውነት አምባገነን ነኝ!" የቀድሞ የሊቢያ ፕሬዚዳንት #ሙሀመድ_ጋዳፊ @abyssinianwisdom   @abyssinianwisdom   @abyssinianwisdom

Select the correct spelling
Anonymous voting

ምርጥ 20 የካህሊል ጂብራን አባባሎች 1. ‹‹ ቁንጅና ያለው ፊት ላይ አይደለም፡፡ ቁንጅና በውስጣችን የሚገኝ የልብ ብርሃን ነው፡፡ ›› 2. ‹‹ አዋቂ ሠው ሁለት ልብ አለው፡፡ አንዱ ሲደማበት በሁለተኛው ይታገሳል፡፡ ›› 3. ‹‹ እምነት እውነትነቱን ከማረጋገጥ ባሻገር በልብ ውስጥ የሚገኝ እውቀት ነው፡፡ ›› 4. ‹‹ ኢምንቷ የደግነት ስራ ትልቁን ነገር ለማድረግ ከማሰብ በላይ ዋጋ አላት፡፡ ›› 5. ‹‹ ፍቅር የሚያንቀጠቅጥ ደስታ ነው፡፡ ›› 6. ‹‹ እውነት እርቃኑን በባዶው መራመድ ይችላል፡፡ ውሸት ግን ሁልጊዜ አምሮና ደምቆ መልበስን ይፈልጋል፡፡ ›› 7. ‹‹ ኩሩ መሆን ማለት ከምትፈልገው በታች መውሰድ ማለት ነው፡፡ ›› 8. ‹‹ ፍቅር የመለያያ ሠዓቱ እስኪደርስ ድረስ የራሱን ጥልቀት አይረዳም፡፡ ›› 9. ‹‹ ወንድ ሁለት ሴቶችን ይወዳል፡፡ አንደኛዋ በአዕምሮው የሚስላት ስትሆን ሁለተኛዋ ግን ገና አልተወለደችም፡፡ ›› 10. ‹‹ ልክ እንደ አበባ ሁን፡፡ ፊትህን ወደ ፀሃይ ብርሃን አዙር፡፡ ›› 11. ‹‹ ሐዘንና ደስታ የማይነጣጠሉ ነገሮች ናቸው፡፡ ሁለቱም አብረው ይመጣሉ፡፡ ነገር ግን አንዱ ብቻውን ከጎንህ ሲሆን አንደኛው መኝታ ቤትህ እንደተጋደመ አትርሳ፡፡›› 12. ‹‹ በአንድ ሕይወት ውስጥ ወደ ኋላ እየተመለከቱ መደሠት መቻል ሁለቴ መኖር ማለት ነው፡፡ ›› 13. ‹‹ ፍቅርና ደግነት የድክመትና የተስፋ መቁረጥ ምልክቶች ሳይሆኑ የጥንካሬና የውሳኔ ሠጪነት መገለጫ ናቸው፡፡ 14. ‹‹ ትናንት ለዛሬ ትዝታ ነው፡፡ ነገ ደግሞ የዛሬ ህልም ነው፡፡ ›› 15. ‹‹ ጓደኛህ የፍላጎትህ መልስ ነው፡፡ ›› 16. ‹‹ የሠውን ልጅ ልብና አዕምሮ ለመረዳት እስካሁን ያሳካቸውን አትይ፡፡ ከእሱ ይልቅ ወደፊት ሊያደርጋቸውን የሚመኛቸውን ተመልከት፡፡ ›› 17. ‹‹ የምትወደውን ሠው የፈለገበት ይሄድ ዘንድ ተወው፡፡ ሄዶ ወደአንተ ከተመለሠ ቀድሞውኑ ያንተ ነበር፡፡ ካልተመለሠ ግን ቀድሞውኑም የአንተ አልነበረም፡፡ ›› 18. ‹‹ ልክ ወንዝና ባህር አንድ እንደሆኑት ሁሉ ሕይወትና ሞትም አንድ ናቸው፡፡ 19. ‹‹ ጓደኝነት የሁልጊዜ ጣፋጭ ሃላፊነት እንጂ አጋጣሚ አይደለም፡፡ ›› 20. ‹‹ ፍቅር አልባ ሕይወት አበባ ወይም ፍሬ እንደሌለው ዛፍ ነው፡፡ ›› @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom

Select the correct spelling
Anonymous voting

የአልከሚስቱ (The alchemist) መፅሐፍ ደራሲ ማነዉ??
Anonymous voting

📚ስለጥንታዊ ባህላችን መነሻና አመጣጥ ብዙን ጊዜ በቁጭት ይፅፋሉ።ይቀኛሉ።ይናገራሉ።ጥንታዊ የባህል መነሻችንን ማወቅ ምን ይጠቅመናል? መነሻችንን አለማወቅ፣የመጣንበትን አለማወቅ ባህላዊ ማንነታችንን(Cultural identity) ይገድለዋል።የትናንት መነሻችንን በትክክል ሳናውቅ የነገ መዳረሻችንን በትክክል መቀየስና ማወቅ አንችልም።በአሁኑ ዘመን ህይወታችን ውስጥ ወደፊት የሚያስሮጠንን አጣዳፊ የሆድ ችግር ብቻ እንጂ ከኋላ የሚነዳንን ሀይል ዞር ብለን አናይም።ለማን ጥቅምና ለምን አላማ እንደሚነዳንም አናውቅም።ስለዚህም መድረሻችን በግልጥ አይታየንም። ጥንታዊ ታሪካችንን ረስተን፤ሆዳችንን ብቻ አስቀድመን ዕድገት እያልን ወደ ንቅዘት፣ልማት እያልን ወደ ጥፋት፣መረጋጋት እያልን ወደ ጦርነት፣ፌደራላዊ ክልል እያልን ወደ ዘረኝነት እክል፣ዘላቂ ሰላም እያልን ወደ ጥላቻ ገሃነም የምንገባው መነሻችንንና መድረሻችንን ስለማንገነዘብ ነው። የኢትዮጵያዊነታችንን ማንነት(identity) መነሻ የኦርሞም፣የአማራም፣የትግሬም፣የኑብያም፣የሱማሌም፣የጉራጌም፣የአፋርም፣ወዘተ መሰረታዊ መነሻችን አንድ የካም ዘር መሆኑን አለማወቃችን ነው ትብትብ የማንነት የስነልቦና ቅዥንብር (Crisis of identity) የከተተን።» 📰 ጦቢያ መጽሔት(1990) ✍ ሎሬት ባለቅኔ ፀጋዬ ገብረመድህን @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom

"Educatig the mind without educating the heart is no education at all." "ልብን ሳያስተምሩ አእምሮን ማስተማር በፍፁም ትምህርት አይደለም። “ (አርስቶትል) @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom