en
Feedback
LEARN TECH ||ethiopia ®

LEARN TECH ||ethiopia ®

Open in Telegram

We are dedicated to provide tech tips and other tech related information. #join and #share

Show more
1 495
Subscribers
No data24 hours
-107 days
-5530 days
Posts Archive
photo content

ለፕሮፋይል የሚሆኑ ገራሚ ገራሚ ፎቶዎችን ለማግኘት ከስር ጆይን ያድርጉ የፈለጉትን አይነት ያገኛሉ ይ🀄️ላ🀄️ሉን!👇
ለፕሮፋይል የሚሆኑ ገራሚ ገራሚ ፎቶዎችን ለማግኘት ከስር ጆይን ያድርጉ የፈለጉትን አይነት ያገኛሉ ይ🀄️ላ🀄️ሉን!👇

የተወለዱበትን ወር በመምረጥ ኮከቦን ይመልከቱ https://t.me/+A4CCZ5VB9DAyMDA0 https://t.me/+A4CCZ5VB9DAyMDA0 Add your channel 💬 @tomi8019
የተወለዱበትን ወር በመምረጥ ኮከቦን ይመልከቱ https://t.me/+A4CCZ5VB9DAyMDA0 https://t.me/+A4CCZ5VB9DAyMDA0 Add your channel 💬 @tomi8019

🎉ለ10ሰው ብቻ የ100 ብር ካርድ ሽልማት እስካሁን 3 ሰው ተሸልሞዋል 7 ሰው ይቀራል ይሸለሙ 👇👇👇👇SEE ALL ሚለው ተጭነው ሪኩዌስት በመላክ ይሸለሙ👇👇👇👇 * 805 *4362891…
🎉ለ10ሰው ብቻ የ100 ብር ካርድ ሽልማት             እስካሁን 3 ሰው ተሸልሞዋል             7 ሰው ይቀራል ይሸለሙ           👇👇👇👇SEE ALL ሚለው ተጭነው ሪኩዌስት በመላክ ይሸለሙ👇👇👇👇              * 805 *4362891…See All

😍Do you want Habeshan?🔞
😍Do you want Habeshan?🔞

ሀሳባችሁን በኮሜንት ግልጹ
ሀሳባችሁን በኮሜንት ግልጹ

ትግረኛ አትችልም "አባቴ ይሙት !>> አለችኝ እየሳቀች። እውይ ጥርሶቿ ታይተው አይጠገቡም። የውበት አምላክ በጥንቃቄ የደረደራቸው የቀይ ባህር ዕንቁዎች ይመስላሉ። << ይህ ጉሮሮ የሚፍቅ ቋንቋ ! መጓጉጥ ነው። አልኳት << እንጥላችሁ ስላልተቆረጠ ይሆናል >> << እሰኪ መቶ በይ >> << ሞቶ >> << እስኪ አንተ በይ >> << አንቴ >>    << አንቺም አማርኛ አትችይም አባቴ ይሙት >> አልኳትና መጠጧን ላመጣላት ሄድኩ። መጠጧን አመጣሁላትና << ሕራይ ትግርኛ ክትምህርኒ እሺ >> ሺ እምበአር ? ጸጋዬ ኃይለማርያም እባላለሁ >> አልኳትና መጠጧን ቀምሼ ሰጠኋት። እውነትም ጥሩ መጠጥ ነው። << በቲቪ አውቅሀለሁ አንተም አማርኛ ታስተምረኛለህ >> አለች ፡ ጠጉሯን እየነሰነሰች ፈገግታዋ ይናፍቃል።       << ማን ብዬ ልጥራሽ ሰሜናዊት ጽብቖቲ ?>> ብዬ ስሟን ጠየኳት ሳቀችና << ፊያሜታ ጊላይ እባላለሁ >> ብላ ስሟን ነገረቺኝ። ስሟ ደንቆኝ ቅንድቤን ከፍና ዝቅ ሳደርግ አይታኝ "ምነው አለች።               << እንግዳ ስም ነው ....>>              << የጣሊያን ስም ነው ....>>             << ምን ማለት ነው ? >>             << ትንሽ ነባልባል ....>> << እውነት አንቺን ከሩቅ መሸሽ ይሻላል >> አልኳት "                 << ለምን አለችኝ >> << ስምን መላክ ያወጣዋል ይባላል። እንደ ስምሽ ከሆንሽ አደገኛ ነው። በትንሽ ነበልባል ተቃጥሎ ማለቅ ደግ አይደለም። እንደ ስምሽ እንዳልሆንሽ ተስፋ አደርጋለሁ አልኳት።                  << ነኝ አባቴ ይሙት >> አለች ስቃ።                    << እንዴት ? >> << በሕፃንነቴ እሳት ነበርኩ። እያቀስኩ ፣ እቃ እየሰበርኩ ፣ ከቤት እየጠፋሁ እናትና አባቴን ሳስቸግራቸው ነበር። ብቻዬን ደግሞ መተኛት አልወድም ነበር። ብቻዬን ካስተኙኝ ሌቱን በሙሉ ሳለቅስ አድራለሁ። ከእነሱም ጋር ተኝቼ እነሱ ሲጫወቱ የሰማሁ እንደሆነ አለቅሳለሁ። ለዚህ ሳይሆን አይቀርም ፊያሜታ የሚል ስም ያወጡልኝ >> በማለት አስረዳችኝ።        << አሁንስ ? ብዬ ጠየኳት >>        << አአሁንም ነባልባል ነኝ። ለምወደው ግን አይደለሁም። ለምወደው ሰው ማርና ወተት ነኝ። ስኳር ነኝ። << እና የምትወጂው ምን አይነት ሰው ይሆን >> << እንደ ድንጋይ የጠጠረ ፣ እንደ ብረት የጋለ ፣ እንደ ስኳር የጣፈጠ ወንድ >> ብላ እንደገና ሳቀች።                  << እውነት ? >> << ቀልዴን ነው። ምስጢሬን አሁን አልነግርህም .... >> << ምናለበት ? >> << ምስጢር ነው >> አለች። << እሺ ራሴ አንድ ቀን እደርስበት ይሆናል። ግን ስምሽን ብትውጪው ጥሩ ነበር .... >>         << ለምን ? >> << የባዕድ ስም ነው። የአሥመራ መንገዶች ፣ ሱቆች ፣ ቡና ቤቶች ፣ ሆቴሎችና ሬስቶራንቶች  ፋብሪካዎች ሳይቀሩ በባዕዳን ስም ነው የሚጠሩት። የጣሊያን ቅሪት ያው የባዕድ አስተሳሰብና አመለካከት ማስከተሉ አይቀርም። በዚህ ክፍለ ሀገር ከፍተኛ የባህል አብዬት ማካሄድ ያስፈልጋል ፣ በእውነት አይመስልሽም አልኳት። << ፊያሜታ ካስጠላህ ፋና በለኝ >> ብላ ዝም አለች። ደራሲ ፦ በዓሉ ግርማ ርዕሰ ፦ ኦሮማይ

photo content

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን በመምሰሌ የደህንነት ስጋት ስላለብኝ ጥበቃ ይደረግልኝ ሲሉ ኑሮዋቸዉን በፑንትላንድ ያደረጉ ግለሰብ ተናገሩ ከወደ ሶማሊያ ፑንትላንድ የተሰማው ዜና ፈገግታን የሚጭር ሆ
+1
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን በመምሰሌ የደህንነት ስጋት ስላለብኝ ጥበቃ ይደረግልኝ ሲሉ ኑሮዋቸዉን በፑንትላንድ ያደረጉ ግለሰብ ተናገሩ ከወደ ሶማሊያ ፑንትላንድ የተሰማው ዜና ፈገግታን የሚጭር ሆኗል። "የኢትዮጵያውን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን በመምሰሌ የደህንነት ስጋት ስላለብኝ ጥበቃ ይደረግልኝ" ያሉት በፑንትላንድ ግዛት የዋኢዮ ወረዳ አስተዳዳሪ ኢሳቅ አህመድ ሀሰን በሶማሊያ ሶሻል ሚዲያዎች የእለቱ ሳቅ የሚጭር መነጋገሪያ ሆኗል። ሰውዬው በሶሻል ሚዲያ ብቅ ብለው በአፍ ሶማሊ ቋንቋ "አብይን ትመስላለህ እያሉ ህይወቴን አደጋ ውስጥ የከተቱብኝ ሰዎች አሉ። እኔ ሳልሆን አብይ ነው እኔን የሚመሰለው። በዚህ ምክንያት ለህይወቴ ሰለሰጋሁ ያለጠባቂ መንቀሳቀስ አቁሜለሁ። በዛ ላይ የአባቱ እና አባቴ ስም አንድ ነው። ወደ ኢትዮጵያ የሄድኩት በመለስ ዘመን ነው አሁን መሄድ ብፈልግም  ለደህንነቴ ስጋት ስላለብኝ ጠባቂ  ያስፈልገኛል።" ብለዋል። በፑንትላንድ ግዛት የዋኢዮ ወረዳ አስተዳዳሪ ይህን መልእክት ያስተላለፉት ለቀልድ ይሁን የምራቸውን ግን የታወቀ ነገር የለም። Via - Somali Fast Info/ሶማሊ ፈጣን መረጃ

«ልጆቿ ራሳቸው ህመምተኞች ሆነዋል።እናም ሁሉም የግሉን ህመም እንጂ አንዱ የአንዱን ህመምና ችግር አያይም።ሁሉም ጥጉን ይዞ ግማሹ የዳነውን ቁስሉን እየቀረፋ፣ግማሹ አዲሱን እያመገለ በየቤቱ ሙሾ ያወርዳል።ተበዳይ ነኝ የሚል እንጂ በዳይ ነኝ የሚል የለም።ሁሉም ተገፋሁ የሚል እንጂ ገፋሁ የሚል የለም።አንዳንዶቹም የአንዱ ቁስል ከሌላው እንደሚበልጥ ትንታኔ በመስጠት ተጠምደዋል።ሁሉም ህመምተኞች፣ሁሉም አልቃሽ በመሆኑ፣ማን ከራሱ አልፎ እቺን ሚስኪን እናቱን ያስታውሳል።»                          📓ሚተራሊዮን                           ✍️ አለማየሁ ዋሴ 📚 @abyssinianwisdom

እስቲ ከላይ ያለውን ግጥም በcomment ግልጹት ስሜታችሁን።

እስቲ ከላይ ለውን ግጥም በcomment ግልጹት ስሜታችሁን።

አፈር ብላ አለችኝ  አሜን ይሁን አልኳት ዘላ ስትነክሰኝ ይቅር ብዬ ሳምኳት ዛሬ ወይም ነገ ብትለወጥ ብዬ እሽሩሩ እያልኩኝ ከጀርባ አዝዬ እንኳን ልትለወጥ ልትራራልኝ ቀርቶ ታሯሩጠኝ ጀመር በእራሴ ቀበቶ              ማነው ባል😕 በ ኪሩቤል አሰፋ @Cher7ub ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! @Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom

የቀድሞው የዙምባቤ ፕሬዚዳንት # ሮበርት ሙጋቤ በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር ፦ "የአፍሪካ የትምህርት ስርዓት አስገራሚ ውጤቶች አሉት ።" ካሉ በኋላ አንደኛ ደረጃ የሚይዙ ቀለሜና ጎበዝ ተማሪዎች ጥሩ ውጤት አምጥተው # ኢንጂነሪንግና # ሜዲሲን እንዲማሩ እድል ያገኛሉ ። ሁለተኛ ደረጃ የሚይዙት ደግሞ # ህግና # ማኔጅመንት ነገር ተምረው አንደኛ ደረጃዎቹን ያስተዳድሯቸዋል ። ዝቅ ብለው በሶስተኛ ደረጃ የሚገኙት ተማሪዎች ደግሞ # ፖለቲካ ውስጥ ይገቡና አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ላይ ያሉትን ከላይ ሆነው ይቆጣጠራሉ ። በትምህርት ውዳቂዎች ደግሞ # ፖሊስና # ወታደር ይሆናሉ ። እነዚህ ደግሞ ፖለቲከኞችን ይቆጣጠራሉ ደስ ያላላቸውን ፖለቲከኛ ደግሞ እስከ መግደል ድረስ ይደርሳሉ ። ከሁሉም ከሁሉም ግን ምርጡ ጭራሽ ክላስም ሆነ ትምህርት ቤትም ገብቶ የማያውቀው ሰው ደግሞ # ነብይና # ጠንቋይ ይሆናል ። ይሄን ደግሞ ሁሉም ይከተሉታል ። ብለው ነበር ። እኛስ በሃገራችን ያየነው ይህንን ነው ወይስ ሌላውን ነው ? ═════════❁✿❁ >>>>>>>>>>>>

🔔የአለማችን ታዋቂ ሰዎች በአንድ ወቅት የተናገሩትን ድንቅ ንግግሮች በጥቂቱ ጀባ ልበላችሁ🤗 🔸"በዝናብ ውስጥ መሄድ እወዳለው ምክንያቱም ሰዎች እኔ ሳለቅስ ሊያዩኝ አይችሉም" 🗣🗣 ቻርሊ ቻፕሊን 🔸"ሲጋራ አላጨስም ነገርግን በኪሴ ክብሪት እይዛለው ምክንያቱም ሀጢያት ልሰራ ባሰብኩ ቁጥር እጄን አቃጥለዋለው ከዛም ለሬሴ እንዲ እለዋለው ይችን መቋቋም ያቃጠህ እንዴትስ የሲኦል እሳትን ትችለዋለህ?" 🗣🗣 መሀመድ አሊ 🔸"ምናብ ከ እውቀት ይበልጣል።እውቀት የተገደበ ነው ነገር ግን ምናብ አለምን ይዞራል"🗣🗣 አልበርት አንስታይን "ጓደኛህ ታማኝ መሆኑን ለማረጋገጥ ለሌላ ጓደኛ እንዲዋሽ ጠይቀው" 🗣🗣 ኔልሰን ማንዴላ 🔸"እኔ በህይወት ካሉት ሰዎች ሁሉ ጠቢብ ነኝ ምክንያቱም አንድ የማውቀው ነገር አለ እሱም ምንም እንደማላውቅ ነው" 🗣🗣 ፕላቶ

እውነት ያበደው ግን ማነው? ስለእውነት የተሟገተው? ማነው ህሊና ቢስ የሆነው? በጠራራ ፀሐይ ፋኖስ አብርቶ እግዚአብሔርን የፈለገው? አይደለም! እሱማ ጤነኛ ነው፡፡ ነገር ግን እብዶች በነገሱበት ሐገር ጤነኛው እንደቀውስ ይቆጠራል፡፡፡ ዘንድሮ መሪው እብድ፣ ተከታዩ እብድ፣ ጳጳሱ እብድ፣ ፓስተሩ እብድ! ኡስታዙ እብድ! ምሁር ተብዬው እብድ! ምዕመኑ እብድ፣ ፖለቲከኛው ቀውስ! ካድሬው ንክ ነው፡፡ ለማህተቡ የቆመ፣ ለእውነት የወገነ፣ ለሐገር የሚያስብ፤ ለተበደሉ የሚሟገት፣ ለምስኪኖች የሚጮህ ጤነኛ ሰው ማግኘት ብርቅ ነው፡፡ የሃይማኖት ድርጅት የበዛበት፤ እምነትና ምግባር ያነሰበት ሐገር ሆነናል

ኒቼ የፈጠረው ገፀባህሪ የዚህ ዓለምን የስብዕና ልሽቀት የሚያሳይ ጥሩ ምሳሌ ነው፡፡ እብድ የተባለው ሰው ይሟገት የነበረው ስለእውነት ነበር፡፡ ሃይማኖት ቢዝነስ ሲሆን፣ ፍትህ ሲጠፋ፣ እኩልነት ሲርቅ፣ አድልኦ ሲበዛ፣ ደሃ-አደጉ ሲበደል፣ ምስኪኑ ሀብት ንብረቱ ተቀምቶ ሲሰደድ፤ ንጹሃን በፖለቲከኞች ቁማርና ሴራ ደማቸው ደመ-ከልብ ሲሆን ሲያይ እንዴት እግዚአብሔር ሞቷል አይል፡፡ የሐገራችን ገበሬም እኮ በ77ቱ ድርቅ ወገን ዘመዶቹን በርሃብ ሲያጣ፣ ከብቶቹ መንምነው ሲሞቱ አይቶ የሚደርስለት ቢያጣ፡- ‹‹አንጋጥጬ ባየው ሰማዩ ቀለለኝ፣ አላህንም ሰፈራ ወሰዱት መሰለኝ፡፡›› ......... ብሏል እኮ፡፡ በርግጥ ይሄ ዘመን ስለእውነት ስትሟገት እብድ የምትባልበት ዘመን ነው፡፡ መታመን፣ ለህሊና መቆም፣ ለምን እንዴት ብሎ መጠየቅ እብድ ያስብላል፡፡

ብዙ ሰው ታላቁን ጀርመናዊ ፈላስፋ ፍሬዲሪክ ኒቼን የሚያስታውሰው ‹‹እግዚአብሔር ሞቷል! (God is dead)›› በሚለው ንግግሩ ነው፡፡ በዚህ አባባሉ ብዙዎች ተከራክረውበታል፣ ተነታርከውበታል፡፡ አ
ብዙ ሰው ታላቁን ጀርመናዊ ፈላስፋ ፍሬዲሪክ ኒቼን የሚያስታውሰው ‹‹እግዚአብሔር ሞቷል! (God is dead)›› በሚለው ንግግሩ ነው፡፡ በዚህ አባባሉ ብዙዎች ተከራክረውበታል፣ ተነታርከውበታል፡፡ አንዳንድ ኢአማኞችም አጠቃላይ ጭብጡን ባለመረዳት ሃይማኖተኞችን ማብሸቂያ አድርገውታል፡፡ ኒቼ ከፃፋቸው አስራአምስት መፅሐፍቶቹ መካከል በዋነኛነት የሚጠቀሱለትና አንባቢው ዓለም ያጨበጨበለት ‹‹Thus Spoke Zarathustra›› እና ‹‹Beyond Good and Evil›› የተባሉት መፅሐፎቹ ሲሆኑ እነዚህን መፃህፍት ከማሳተሙ አስቀድሞ እ.ኤ.አ. በ1882 ዓ.ም. ለመጀመሪያ ህትመት ባበቃው ‹‹The Gay Science›› በተባለው መፅሐፉ ‹‹The Madman›› በሚል ንዑስ ርዕስ ስር በፃፈው የእብድ ሰው ገፀባህሪ ምክንያት ነው ‹‹እግዚአብሔር ሞቷል! (God is dead)›› የሚለን፡፡ ኒቼ በዚህ ገጸባህሪ እንደሚነግረን አንድ እብድ ሰው ወደአንዲት ትንሽ መንደር ሄዶ በጠራራ ፀሃይ ፋኖስ ለኩሶ ‹‹እግዚአብሔርን እፈልጋለሁ (I seek God)›› በማለት በጩኸት መጠየቁን፤ እንዲሁም ‹‹እግዚአብሔር የት ነው ያለው?›› እያለ ህዝቡን ማፋጠጡን በመፅሐፉ ይተርክልናል፡፡ የእብዱን ጥያቄ ግን ማንም የመለሰለት አልነበረም፡፡ ይልቁንስ ይሄን የሰሙ ሁሉ ስቀውበታል፤ አንዳንዱም አላግጠውበታል፡፡ ሰውየው ግን ጩኸቱን ሳያቋርጥ ፊቱ በእንባ እየታጠበ ‹‹እኔ እነግራቹሃለሁ፤ እግዚአብሔርን እኔና እናንተ ገለነዋል፡፡ ሁላችንም ገዳዮቹ ነን፡፡ ‹‹እግዚአብሔር ሞቷል! (God is dead)›› በማለት አማኙ የሰው ልጅ በክፉ ስራው ምክንያት አምላኩን ከህይወቱ ውስጥ ማስወጣቱን በእብዱ ምሳሌ ያስረዳናል፡፡ የኒቼን ጭብጥ ያልተገነዘቡ ጥራዝ ነጠቆች ግን አውዱን ሳይረዱ ቃሏን ብቻ መዝዘው ላልተፈለገ ትርጉም አውለውታል፡፡