LEARN TECH ||ethiopia ®
Open in Telegram
We are dedicated to provide tech tips and other tech related information. #join and #share
Show more1 495
Subscribers
No data24 hours
-107 days
-5530 days
Posts Archive
chemistry የሚመቻችሁ እና ስለ chemistry የበለጠ ማወቅ የምትሹ ከሆናችሁ እነዚህን ድረገጾች ጋብዘናችኋል።
https://www.compoundchem.com/ ከእለትተለት ኑሯችን ጋር የተገናኙ የchemistry ዕውቀቶችን መቅሰም ያስችላችኋል። ለምሳሌ ሽንኩርት ስንከትፍ ለምንድን ነው የሚያቃጥለን...
https://www.chemguide.co.uk/ ስለ chemistry በርካታ መረጃዎችን የያዘ ድረገፅ ሲሆን በሚሰጠው ማብራሪያ ይበልጥ ይታወቃል።
https://www.wolframalpha.com/examples/science-and-technology/chemistry የchemistry ጥያቄዎችን ከመስራት በተጨማሪ በረካታ ምሳሌዎች ስላሉት ለፈተና ያዘጋጃችኋል።
https://molview.org/ molecular structures በ3D አለያም በ2D መመልከት የሚያስችላችሁ ድረገፅ ነው።
https://molview.org/ ከመፅሀፍት ጀምሮ የተለያዩ chemistry ነክ መረጃዎችን የምናገኝበት ድረገፅ ነው። የchemistry Wikipedia ብንለው ማጋነን አይሆንብንም።
Repost from KiNFiSH Farms
Better Auth featured on Forbes - https://www.forbes.com/sites/dariashunina/2025/06/09/the-most-promising-startups-from-the-first-ever-yc-spring-batch/
ኤሎን ማስክ $424 ቢልዮን አካባቢ ሀብት እንዳለው መረጃዎች ያመለክታሉ:: አገር ካልሆነ በስተቀር በግለሰብ ደረጃ የሚፎካከረው የለም::
ይሁንና ትዊተርን (የአሁኑ Xን) በ $44 ቢሊዮን ዶላር ሲገዛ ይሄን ያህል ገንዘብ በካሽ አልነበረውም፤ ይሄን ያህል ገንዘብ በካሽ (ተቀማጭ) የሚኖራቸው ጥቂት አገራት ብቻ ናቸው።
በመሆኑም ኩባንያውን (ቴስላ) እንደ ዋስትና በማስያዝ በባንክ ብድር ነበር የግዥ ገንዘቡን የከፈለው። በአሁኑ ወቅት ከሞገደኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጋር በፈጠረው ሰጣ ገባ የቴስላ አክሲዮን ዋጋ እየቀነሰ ይገኛል። ይህም ከባንክ በወሰደው 44 ቢሊዮን ብድር ቀጥተኛ ተጽዕኖ ማሳደር ጀምሯል። የቴስላ ዋጋ በቀነሰ ቁጥር #በኤሎን_መስክ ላይ የሚገጥመው ጫና ይጨምራል።
ለዚህም ነው ሰሞኑን በፎክስ ኒውስ ላይ ቀርቦ ለማልቀስ ተቃርቦ ከእንባው ጋር ሲታገል የነበረው።
እናም “የዓለም ቁጥር 1 ሀብታም” መሆን ገንዘብ ላይ እንደመዋኘት ማለት አይደለም። ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውን ንብረቶች እንደ ዋስትና መጠቀም ትችላለህ ማለት ነው። ችግሩ የሚጀምረው እነዚያ ንብረቶች ዋጋቸውን ሲቀንስ/ሲያጡ ነው። ለዚህም ነው የምድራችን ሀብታሙ ሰው በጣም ከባድ ጊዜ እያሳለፈ ያለው።
እናም አንዳአንዴ በጣም ሀብታሞች ከድሆች የከፉ ችግሮች ያጋጥሟቸዋል:: ለዚህም ነው "ሀብታም ሰዎች ሀብታም ችግሮች አሏቸው" የሚባለው። Rich People Have Rich Problems❗😥
https://t.me/learn_tech16
https://t.me/learn_tech16
እንኳን ለ1446ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ
መልካም በዓል
https://t.me/learn_tech16
https://t.me/learn_tech16
+1
በAI ዘርፍ ተስፋ እና ስጋትን ይበልጥ ያጫረው Veo 3 . . . ዝግጁ ነን ?
ግዙፉ የአለማችን የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጎግል Veo 3 የተሰኘ ቪዲዮ የሚሰራ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ከሰሞኑ ከለቀቀ በኋላ ትልቅ መነጋገሪያ ሆኗል።
የቴክኖሎጂ ኩባንያው አዲስ ያስተዋወቀው Veo-3 በራሱ ቪዲዮ ሰርቶ ድምፅን ከቪዲዮው ጋር የሚያዋህድ ሲሆን ከዚህ በፊት ከነበሩት በጥራት ከፍ ያለ ነው።
መተግበሪያው ከOPEN AI ምርት ከሆነው sora ለየት የሚያደርገው በሰዎች መካከል የሚደረጉትን ንግግሮች እውነት እስኪመስል ድረስ ድምፅና ምስልን በማቀናበር ማቅረቡ ነው።
ይህ የጎግል አዲሱ ቴክኖሎጂ የተሰሩ ቪዲዮዎች ( ከላይ እንዳለው አይነት) ከእውነተኛ ቪዲዮች ለመለየት በሚያዳግት ደረጃ የቀረቡ ሲሆን የቋንቋ አማራጩም ከዚህ ቀደም ከነበሩት እጅጉን የሚሻል ነው።
አሁን ላይ መተግበሪያውን ለመጠቀም የ249.9 ዶላር ወርሃዊ ክፍያ ያስፈልጋል ተብሏል።
በርካታ በVeo 3 የተሰሩ ቪዲዮዎች ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲለቀቁ አብዛኛው ሰው ከእውነተኛ ቪዲዮዎች ለመለየት ሲቸገር ተስተውሏል።
ቴክኖሎጂው ይፋ በሆነ በጥቂት ቀናት በአማርኛ ቋንቋ ተሰርተው የተለቀቁ ቪዲዮዎችን እንኳን ብንመለከት በቀላሉ ለመለየት አስቸጋሪ ሆኗል። ከዚህ ቀደም ድምጽ ላይ የነበሩ ክፍተቶች በአጭር ጊዜ ተሻሽለው ቀርበዋል። (ቪዲዮ ከላይ ተያይዟል)
ጎግል በተጨማሪ Flow የተሰኘ የተለያዩ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መተግበሪያዎችን ያካተተ እና ፊልም ሰሪዎች በፈለጉት መንገድ ፊልማቸውን እንዲሰሩ የሚያግዝ የፊልም መስሪያ መተግበሪያንም ይፋ ሲያደርግ በዘርፉ ስጋትንም ተስፋንም ይዞ መምጣቱ ተነግሯል።
ተጠቃሚዎች በVeo 3 መስራት የሚፈልጉትን ነገር በፅሁፍ እንደሚያስገቡ የተነገረ ሲሆን መተግበሪያው ከተሰጠው ፅሁፍ በመነሳት እውነተኛ የሚመስል ቪዲዮን ከሰራ በኋላ ትክክለኛ የሚመስሉ ድምፆችን በመጨመር ለተጠቃሚዎች ያቀርባል።
ተጠቃሚዎች የቀረበላቸውን ቪዲዮ ካዩ በኋላ FLOW የተሰኘውን ሌላ የጎግል መተግበሪያ በመጠቀም የካሜራ አንግል እና የገፀ ባህሪያትን እንቅስቃሴ መቀየር ይችላሉ ተብሏል።
ወጪን ከመቀነስ አንፃር በ500 ሺህ ዶላር ሊሰራ የሚችልን የመድሃኒት ማስታወቂያ በVEO 3 ከ500 ዶላር ባነሰ ገንዘብ በአንድ ቀን ውስጥ መሰራቱም ተነግሯል።
አንዳንድ ሰዎች ፈጠራን ይቀንሳል የሚል ሃሳባቸውን እያንፀባረቁ ሲገኙ የተመልካቹ እውነተኛ ቪዲዮ አለመሆናቸውን ለመለየት መቸገር ሌላ ፈተና ነው ተብሏል።
እናንተስ በዚህ ጉዳይ ምን ትላላችሁ ? ለዚህ ቴክኖሎጂ ዝግጁ ነን ?
Source: CNBC, AXIOS
Video Credit : Ehud Ai Studio
#AI #Google #Gemini
@TikvahethMagazine
ለኤ.አይ ሰመር ካምፕ 2025 የክረምት ስልጠና ፈላጊ ታዳጊዎች የምዝገባ ጥሪ
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከሐምሌ 1፣ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ2 ወራት የሚቆይ የኤ.አይ ሰመር ካምፕ የስልጠና መርሓ ግብር በአዲስ አበባ አዘጋጅቷል፡፡
የመመዝገቢያ ቀናት
👉 ከግንቦት 21፣ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት
አመልካቾች ተከታዩን ሊንክ በመጠቀም መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
👉 https://forms.gle/yFThcRq3bSMcFEKU6
Repost from Ethio University 🇪🇹
ለኤ.አይ ሰመር ካምፕ 2025 የክረምት ስልጠና ፈላጊ ታዳጊዎች የምዝገባ ጥሪ
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከሐምሌ 1፣ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ2 ወራት የሚቆይ የኤ.አይ ሰመር ካምፕ የስልጠና መርሓ ግብር በአዲስ አበባ አዘጋጅቷል፡፡
የመመዝገቢያ ቀናት
👉 ከግንቦት 21፣ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት
አመልካቾች ተከታዩን ሊንክ በመጠቀም መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
👉 https://forms.gle/yFThcRq3bSMcFEKU6
🔥 This summer, Telegram users will gain access to the best AI technology on the market. Elon Musk and I have agreed to a 1-year partnership to bring xAI’s chatbot Grok to our billion+ users and integrate it across all Telegram apps 🤝
💪 This also strengthens Telegram’s financial position: we will receive $300M in cash and equity from xAI, plus 50% of the revenue from xAI subscriptions sold via Telegram 💰
Telegram + Grok = ❤️📈🏆
#ጥቆማ
5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢንሼቲቭ ነፃ ስልጠናን ለመከታተል ይመዝገቡ።
ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርትፍኬት ማግኘት የሚያስችልዎትን ስልጠና ባሉበት ሆነው ይውሰዱ።
የስልጠና ዘርፎች፦
► ዌብ ፕሮግራሚንግ
► አንድሮይድ ማበልፀግ
► ዳታ ሳይንስ
► አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ፋንዳሜንታልስ
ለመመዝገብ 👇
https://www.ethiocoders.et/
በተሰጠው ስምንት ሳምንት ስልጠናውን ሲያጠናቅቁ፥ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ይበረከትልዎታል።
@tikvahuniversity
Websites You NEED As a Frontend Developer
1. UIverse
→ Free HTML, CSS, and Tailwind UI components
→ Buttons, cards, loaders, toggles — modern and ready to use
🔗 uiverse.io
2. HyperUI
→ Tailwind CSS components built for real projects
→ Alerts, navbars, modals, dashboards – fully responsive
🔗 hyperui.dev
3. CodePen
→ Playground for testing HTML, CSS, and JavaScript
→ Get UI inspiration, learn animations, and explore real code
🔗 codepen.io
4. Color Hunt
→ Curated, trendy color palettes by designers
→ Click and copy hex codes, build beautiful UIs fast
🔗 colorhunt.co
5. Collect UI
→ Daily UI inspiration from real designers
→ Sign-up forms, pricing pages, dashboards, and more
🔗 collectui.com
@edemy251
#telegram_tip
የስልካችሁ contact list ውስጥ ያሉ ሰዎች ቴሌግራም አካውንት ሲከፍቱ እንትና joined telegram እያለ ሜሴጅ እየገባ ካሰለቻችሁ እንዴት እንደምታስተካክሉት አነሆ፦
በመጀመሪያ ወደ telegram settings ከሄድን በኋላ notification and sounds የሚለውን በመንካትና ትንሽ ወደታች ዝቅ አድርገን የምናገኘውን contact join telegram የሚለውን off ወይም disable ማድረግ። ተገላገላችሁ።
©bighabesha_softwares
በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የታገዘ የአጥንትና መገጣጠሚያ ችግሮችን ማወቅ የሚያስችል ተለባሽ (ዊረብል) ቴክኖሎጂ ይፋ ሆነ፡፡
ቴክኖሎጂዉ ከ20 በላይ ሴንሰሮች በተገጠሙለት ስማርት የጫማ ሶል አማካኝነት የሚሰራ ነዉ፡፡ በኦሀዮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች የተሰራውና በፀሐይ ኃይል የሚሰራዉ ይህ የጫማ ሶል የግለሰቡን እርምጃ ወደ ኤሌክትሪክ ሲግናል ይቀይራል። በመቀጠልም ከቁሱ ጋር ግንኙነት ወዳለዉ ስልክ ወይም ኮምፒዩተር ሲግናሉን ያስተላልፋል። ኮምፒዩተሩ አስቀድሞ በሰለጠነዉ የማሽን ማስተማር ስልተቀመር መሰረት የተሰጠውን ሲግናል ተንትኖ የምርመራ ዉጤቱን ይገልጻል።
ዋሽንግተን ፖስት ባወጣዉ ዘገባ ቁሶቹ የግለሰቦችን እንቅስቃሴ መሰረት በማድረግ የጤና ሁኔታን መከታተል አስችለዋል።
ዊረብል ቴክኖሎጂ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን የሚጠቀሙ ስማርት ቁሶችን የሚያመለክት ሲሆኑ የሚለበሱና ከሰዉነት ጋር ንክኪ ያላቸዉ ናቸዉ። ስማርት ሰዓቶች፣ቀለበቶች፣ ጫማዎች፣ ልብሶች እና ጌጣጌጦች ዊረብል ቴክኖሎጂ ዉስጥ ይካተታሉ።
ቴክኖሎጂዉ አትሌቶች እና ሌሎች ግለሰቦች አስከፊ የሆነ የጤና ጉዳት ከማስተናገዳቸዉ በፊት ጥንቃቄ ማድረግ እንዲችሉ ቅድመ ማስጠንቀቂያዎችን ይሰጣል፡፡
ድረ ገጽ | ፌስቡክ | ኤክስ | ዩቲዩብ | ቲክቶክ | ሊንክድኢን | ኢንስታግራም
#ጥቆማ
#NationalEthioCyberTalentSummerCamp2025
" ስልጠናው የሚሰጠው በነፃ ነው። ምዝገባ ከተጀመረ ጀምሮ ከ1 ሺህ 7 መቶ በላይ ተመዝግበዋል " - የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በ2017 ዓ.ም በሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ሰመር ካምፕ በ4ኛ ዙር ለማሰልጠን ምዝገባ ከጀመረበት ጀምሮ እስከ ግንቦት 5 ድረስ 1,725 ሰዎች መመዝገባቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
ስልጠናው በነጻ እንደሚሰጥ ገልጾ በባለፈው ዓመት በነበረው ጥሪ 6141 ታዳጋዊች መመዝገብ መቻሉንና የምልመላ ሂደቱን አልፈው መሳተፍ ከቻሉት 300 ሰልጣኞች ውስጥ 237ቱ መመረቃቸውንና ወደ ዘርፉ መግባታቸው አስታውሷል።
አሁን በ4ኛው ዙር የስልጠና መርሃ ግብር መሳተፍ የሚችሉት በተወሰ መልኩ አቅምና ታለንት ያላቸው ከተለያዩ ተቋማት ሰርተፍኬት ያላቸው እና በተቋሙ የሚደረጉላቸውን ቃለ መጠይቅ ማለፍ የሚችሉ መሆን እንዳለባቸው በአስተዳደሩ የሳይበር ልህቀት ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ቢሻው በየነ አስረድተዋል።
ዳይሬክተሩ አቶ ቢሻው በየነ በዝርዝር ምን አሉ ?
" በሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ሰመር ካምፕ የተወሰነ አቅም ወይም ታለንት ያላቸው ሰዋችን ቻሌንጅ በመስጠት አቅማቸውን እንዲያሰፉ ነው የሚደረገው።
እድሜው ከ11 ዓመት በላይ የሆነ ማንኛውም ሰው መመዝገብ ይችላል፣ እየሞከረ ያለም እና በእድሜ ትልቅ የሆነ ሰው ካለ እንቀበላለን።
ተመዝጋቢዎች ሶፍትዌር ኢንጅነሪንግ፣ ኮምፒውተር ሳይንስ እና በመሳሰሉት ላይ እየሞከሩ የነበሩ እና በነፃ ስልጠና ከሚሰጡ አካላት ስልጠና የወሰዱ እና ሰርተፍኬታቸውን አደራጅተው ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
በኦንላይን ስትመዘገቡም የግድ ያማረ እንግሊዘኛ አይጠበቅም፣ ነገር ግን በምትችሉት ቋንቋ በገባችሁ ልክ አቅማችሁን እና ፍላጎታችሁን መግለፅ ይጠበቅባችኋል።
ነገር ግን ምንም ታለንት የሌለውን ሰው ወይም ከዜሮ መጀመር ለሚፈልጉ ይህ ምዝገባ አይሆናቸውም። "
የሳይበር ልህቀት ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ቢሻው፥ በሳይበር ደህንነት፣ በዴቨሎፕመንት፣ በኢምቤድድ ሲስተም እና በኤሮስፔስ ላይ ሉዩ ተሰጥኦ እና ፍላጎት ያላቸው በዚህ https://talent.insa.gov.et መመዝገብ እንደሚቻል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
