en
Feedback
የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

Open in Telegram
918
Subscribers
+124 hours
+27 days
+930 days
Posts Archive
የካቲት 05/2018 ዓ.ም በትምህርት ዘርፋ ያጋጠመንን የውጤት  ስብራት በተቀናጀና በተባበረ መንገድ መጠገን ይገባል ሲሉ የጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ  አቶ ሚፍታ ሁሴን ገለጹ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ለኢንጌ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የአከባቢ ተወላጅ የከተማ ነዋሪዎች ከ350 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ከ600 በላይ የትምህርት መማሪያና ማጣቀሻ መጽሃፍቶች ድጋፍ በዛሬው እለት አድርገዋል። የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን መንግስት ጠንካራ የትምህርት ፖሊሲና ስትራቴጂዎች በመንደፍ ህብረተሠቡን ተወላጅ ባለሃብቱንና ረጂ ድርጅቶችን በማሳተፍ የትምህርት ተቋማትን ከማስፍፍት በተጨማሪ የትምህርት ቁሳቁስ ለማሟላት አጽኖት ሠጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። አቶ ሚፋታ አክለውም ኢንጌ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መማሪያና ማጠቀሻ መጽሃፍትን በማዘጋጀት ያቀረቡትን የአካባቢው ተወላጆችን አመስግነው የተደረገው የመጽሃፍት ድጋፍ የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው በማንሳት በትምህርት ዘርፋ ያጋጠመንን የውጤት  ስብራት በተቀናጀና በተባበረ መንገድ መጠገን እንደሚገባ አስታውቀዋል። የመጽሃፍ ሃብት አሰባሳቢ ኮሚቴ አስተባባሪ የሆኑት ወ/ሮ አምርያ ሰማን ድጋፋን አስመልክተው እንዳሉት ለኢንጌ 2ኛ  ደረጃ ትምህርት ቤቶች በጠቅላላ 600 በላይ የተማሪዎች መማሪያ መፅሀፍ እና አጋዥ መፅሀፍ 350 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ማድረጋቸው ገልፀው በየትምህርት ቤቱ የሚስተዋሉ የመማሪያ መጽሃፍ፣ የመማሪያ ክፍል የጥራትና የግብዓት ችግሮችን ለመፍታት የሚያደርገውን ጥረት እንደ ተወላጅ ህብረተሠቡን ለማገዝ በቀጣይም ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸው ለወላጆችና መምህራን የትምህርት ጉዳይ አደራ የሰጡ ሲሆን ድጋፉ ላይ ለተባበሩ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የወረዳው ትምህርት ቤቶች ጽህፍት ቤት ኃላፊ አቶ አለማየው ኬኔ መንግስት የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ አዲስ ፍኖተ ካርታ ቀርጾ ወደ ተግባር ገብቷል ብለዋል። የመጽሃፍ አቅርቦት ችግሩን ለመፍታት መንግስትና ህብረተሠቡ ተቀራርበው መሰራት በመቻላቸው አሁን ላይ አበረታች የሆኑ ውጤት ማየት እየተቻለ ሲሆን ዛሬ 600 በላይ መጽሃፍ ድጋፍ ያደረጉ ተወላጆችን በትምህርት ሴክተሩ ስም አመስግነው መሠል እገዛዎች መጠናከር ይኖርበታል በለዋል።

የካቲት 05/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ብልፅግና ህብረቶች "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ሀሳብ የአባላት ኮንፈረንስ እና የምርጫ ምልክት ይፋ ማድረጊያ መድረክ ተካሄደ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ሀሳብ የወረዳው ፐብሊክ ሰርቫንት ብልፅግና ህብረት የአባላት ኮንፈረንስ ተካሄደ። የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አ/ረሂም ርዳ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በዛሬው እለት የምናካሄደው  "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ሀሳብ የወረዳው ፐብሊክ ሰርቫንት ብልፅግና ህብረት የአባላት ኮንፈረንስ መድረክ በባለፋት አምስት አመታት በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ህዝቡ የሰጠንን አደራ እና ፓርቲያችን የገባውን ቃል በተግባር በማረጋገጥ በርካታ ስኬቶችን በማስመዝገብ እነሆ  የ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለመወዳደር የመወዳደርያ ምልክት ይፋ በሚደረግበት ወቅት የሚካሄድ በመሆኑ ከሌላ ጊዜ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል። የ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ምልክት የስንዴ ነዶ መሆኑን ጠቀሰው ስንዴ የመደመር መንገዳችን ምሳሌ፣ የአንድነትና የምርታማነት ተምሳሌት ፣ ከተረጂነት የተላቀቅንበት የድል ብሰራታችን ምልክት እና የሉዓላዊነታችን መገለጫ እነደደሆነ አቶ አ/ረሂም ርዳ አክለው ገልጸዋል። በየደረጃው የሚገኙ አመራርና አባላት የፓርቲያችን ብልጽግና የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት የሆነውን የስንዴ ነዶ በተገቢው በመረዳት የግንዛቤ ስራ መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል። የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጠይብ አስፍር "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ሀሳብ ለወረዳው ፐብሊክ ሰርቫንት ብልፅግና ህብረት የአባላት ኮንፈረንስ የተዘጋጃ የውይይት ሰነድ አቅርበዋል። በመድረኩ የብልጽግና ፓርቲ አባላት ኮንፈረንስ መድረክ ላይ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ምልክት ይፋ ተደርጓል።

የካቲት 04/2018 ዓ/ም የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን  ከሼሽት ማዴ- አመቶ መንገድ የዳገት ቆረጣ እና የአፈር ስራዎች ያሉበት ደረጃ  የመስክ ምልከታ አካሄዱ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ እየተገነባ ያለው ከሼሽት ማዴ- አመቶ ቀሪ የስትራክቸር እና የ8 ኪሎ ሜትር የጠጠር ንጣፍ ስራዎች የወረዳው መንግስትና የአካባቢ ተዋላጅ ባለሃብቶች በጋራ የተጀመረ መንገድ ነው። በምልከታወ ወቅት የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን እንደገለጹት መንገድ ለአንድ ህብረተሰብ ሁለንተናዊ ልማት የአንበሳዉን ድርሻ ይጫወታል። ከዚህ ረገድ በዘርፉ በተከናወኑ መጠነ-ሰፊ ስራዎች አበረታች የመንገድ መሰረተ-ልማት ዝርጋታ ማከናወን የተቻለ ቢሆንም በአንጻሩ መንግስት ተደራሽ ባልሆነባቸው የልማት መስኮች ላይ የባለሀብቱ ሚና ቀላል የሚባል እንዳልሆነ ገልጸዋል። ከጎራ አመቶ መንገድ የህብገተሰቡ የረዥም ጊዜ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ የነበረ ሲሆን የወረዳው መንግስት ችግሩን ለመፍታት 19 ሜትር ርዝመት ያለው የሶስት ማዴ ድልድይ በወረዳው በጀት በመመደብ በመገንባት የአካባቢው ተወለጅ ባለሃብቶችን በማሳተፍ የመንገድ ስራዎች እየተገነባ እንደሚገኝ አቶ ሚፍታ አስተውቀዋል። ከሼሽት ማዴ- አመቶ ቀሪ የስትራክቸር እና የ8 ኪሎ ሜትር የጠጠር ንጣፍ ስራዎች የወረዳው መንግስት የአካባቢ ተዋላጅ ባለሃብቶችን በማሳተፍ እየተሰራ መሆኑን በመግለጽ የወረዳው ተወላጆች ከመንግስት ጎን በመሰለፍ የሚከናወኑ ሁለንተናዊ የልማት ስራዎች ለማገዝ እያደረጉት ያለውን ጥረት መንግስት እውቅና የሚሰጠው እንደሚሰጠው ጠቅሰው ለስራው መሳካት መንግስት አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግ ገልጸዋል። በመጨረሻም የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን  ከሼሽት ማዴ- አመቶ መንገድ የዳገት ቆረጣና የአፈር ስራዎች ያሉበት ደረጃ በማየት ማስተካከያ በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ለወረዳው ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት አመራርና ፕሮጀክቱን ለሚከታተሉ ባለሙያዎች አሰደተያየት ሰጥተዋል።

የካቲት 03/2018 ዓ/ም በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በሀደሮ ቀበሌ በበጋ መስኖ የለማ ኩታገጠም የድንች ማሳ በከፊሉ

ብልፅግና ፓርቲ የኢትዮጵያን የተጽዕኖ አድማስ ለማስፋትና የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትጋት ይሠራል የካቲት 3/2018(ወልቂጤ)፦ ብልፅግና ፓርቲ የኢትዮጵያን የተጽዕኖ አድማስ ለማስፋትና የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትጋት እንደሚሠራ በምርጫ ማኒፊስቶው ማረጋገጡን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ገለጹ፡፡ ብልፅግና ፓርቲ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የምርጫ ማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክቱን ይፋ ያደረገ ሲሆን ፓርቲው በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚወከልበት የምርጫ ምልክቱ የስንዴ ነዶ መሆኑን አስታውቋል። አቶ አደም ፋራህ በዚሁ ወቅት፤ ፓርቲው በ"መደመር" እሳቤ በመመራት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ለዘመናት የቆዩ መዋቅራዊ ስብራቶችን በመጠገን፣ ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት ሲሠራ ቆይቷል ብለዋል። ፓርቲው ህዝብን በማሳተፍ፣ በጽናትና ቁርጠኝነት ስኬቶችን ሲያረጋግጥ መቆየቱን ጠቅሰው፤ የህዝብ ይሁንታ በማግኘት በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውጤታማ ጉዞ ማስቀጠል የሚያስችለውን የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ማኒፊስቶ አዘጋጅቶ ይፋ ማድረጉን አስታውቀዋል፡፡ ማኒፌስቶው ብልፅግና ፓርቲ በመደመር እሳቤ በመመራት እስካሁን ያስመዘገባቸውን ስኬቶች፣ ወቅታዊ ሁኔታዎችንና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በዝርዝር የያዘ መሆንን አብራርተዋል። ማኒፌስቷችን ትናንትን ማከምን፣ ዛሬን በአግባቡ መጠቀምንና ነገን መተንበይን ማዕከል ያደረገ ነው ሲሉም አስታውቀዋል። በማኒፌስቶው ትልቅ ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮች መካከል የዲፕሎማሲው ዘርፍ ቀዳሚውን ስፍራ መያዙን ጠቁመው፤ ፓርቲው በቀጣይ አምስት ዓመታት የኢትዮጵያን የተጽዕኖ አድማስ ለማስፋትና የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትጋት እንደሚሰራ በማኒፌስቶው ይፋ መደረጉን ገልጸዋል፡፡ ከጎረቤትና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት፣ ከብሪክስ አባል ሀገራትና ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሰራም በማኒፌስቶው መገለጹን አስታውቀዋል፡፡ እንዲሁም በዓለም አቀፍ የኃይል አሰላለፍ ውስጥ የሚዛናዊነት መርህን በመከተል የኢትዮጵያን ተደማጭነት ይበልጥ ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ ተካትቷል ብለዋል። ብልፅግና ፓርቲ በማኒፌስቶው ይፋ እንዳደረገው፤ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከሀገራቸው ጋር ያላቸውን ትስስር የሚያጠናክሩ አዳዲስ ኢኒሼቲቮችን ተግባራዊ ማድረግና የዜጎችን ክብር ማስጠበቅ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ተመላክቷል፡፡ አባይን በፍትሃዊነት የመጠቀምና አስተማማኝ የባህር በር የማግኘት መብታችንን ለማስከበር የጀመርናቸውን ጥረቶች እንደምናሰፋ በማኒፌስቶው በግልጽ ተቀምጧል ብለዋል፡፡ ለዚህም ሰላማዊ፣ ህጋዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ እና የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረጉ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ በማኒፌስቶው ማካተቱን አረጋግጠዋል። ኢዚአ

የካቲት 03/2018 ዓ/ም የሴቶች ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የሴቶች ውሳኔ ሰጪነትና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት አክሎ ገልጿል። የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ፈትያ መህዲ በ2018 በጀት አመት የሴቶችን የኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሴቶች ልማት ህብረት እንዲደራጁ የተሰራ ሲሆን  19 ሺህ 222 ሴቶች በ640 የሴቶች ልማት ህብረትና 1920 1ለ10  ማደራጀት መቻሉን ገልጸዋል። ባለፉት 6 ወራት በሁሉም ዘርፍ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ በተሰራው ስራ ሴቶች የተሻለ ተጠቃሚ  መሆናቸው ገልጸው በኢኮኖሚው ዘርፍ የሴቶች ተጠቃሚነት ለማሳደግ በልማት ህብረት በማደራጀት ከ7 ሄክታር በላይ መሬት በማልማት ከ50 ኩንታል በላይ ምርት ማግኘት መቻላቸው ገልጸዋል። ሴቶች በተሰማሩበት የስራ ዘርፎች ውጤታማ ለማድረግ የቁጠባቸው ባህላቸውን ለማሳደግ በተሰራው ስራ 12 ሺህ 200 በላይ ሴቶች በማሳተፍ ከ8 ሚሊየን ብር በላይ የተቆጠበ ሲሆን 716 ሺህ ብር በላይ የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል ብለዋል። የሴቶችና ህፃናት ውክልና ከማረጋገጥ አንፃር ሴቶች በአመራር ውሳኔ ሰጭነት ያላቸው ሚና እንዲጎለብት ማድረግ፣የህጻናት ፓርላማ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ በማጠናከር ተጠቃሚ የማድረግ ስራ እንደተሰራ ገልጸው በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደረጉ ፆታዊ ጥቃት፣  አስገድዶ መደፈር እና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ለመከላከል የሚያስችሉ ሰፊ ግንዛቤ በመፍጠር የተለያዩ ጥቃቶችን መከላከል ተችሏል ብለዋል። በማህበራዊ ዘርፍ በጤናው የእናቶች የማህጸን በርና የጡት ጫፍ ካንሰር፣የማህጸን ውልቃትና ፌስቱላ ህክምና ተደርጎላቸው ከበሽታው መዳን ችለዋል፣ በትምህርት ዘርፍ በተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት ላይ ተሳታፊና ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ያሉት ኃላፊዋ አቅመ ደካማ ለሆኑ ሴቶች የመርዳት እና በችግር ውስጥ ያሉ ህፃናት የመማሪያ ቁሳቁስ የማበርከት ስራዎች መሰራቱን ጠቁመዋል። በተጨማሪም ከ2 ሺህ 8 መቶ በላይ ሴቶችን ጊዜና ጉልበት ቆጣቢ ተስማሚ ቴክኖሎጂ ተጠቀሚ እንዲሆኑ በማድረግ ማለትም በሶላር፣በማገዶ ቆጣቢ ምድጃ እና በባዮጋዝ ቴክኖሎጂ ተጠቀሚ የተደረገ ሲሆን 602 ሴቶች በግብርና በማኑፋክቸሪንግ አገልግሎት ዘርፍና  ጊዜያዊ የስራ መስኮች የተፈጠረላቸውና በሂደቱም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርገዋል። በወረዳው በ3ተኛ ዙር ሁሉም ቀበሌዎችን ሞዴል የልማት ህብረት ለመፍጠር  እየተሰራ መሆኑ ጠቁመው በግማሽ አመቱ  በሶስተኛ ዙር 3 ቀበሌዎች የልማት ህብረት የሞዴልነት እውቅና የመስጠት ስራ መሰራቱን አመላክተዋል። በመጨረሻም በግማሽ አመቱ በተቋሙ በሁሉም ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን የገለጽት ኃላፊዋ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፓለቲካዊ   ዘርፎች ላይ ሁለተናዊ ተጠቃሚነትና ተሳታፊነት የበለጠ ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

የካቲት 01/2018 ዓ/ም የጉራጌ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 13ኛ አመት 30ኛ መደበኛ ጉባኤውን የካቲት 03/2018 እንደሚያካሂድ ተገለፀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ኸይሩ መሀመድ  የምክር ቤቱ 4ኛ ዙር 13ኛ አመት 30ኛ መደበኛ ጉባኤውን የካቲት 03/2018 እንደሚካሄድ ገልፀዋል። በጉባኤው የሚቀርቡ አጀንዳዎች  የ4ኛ ዙር 12ኛ አመት 29ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ-ጉባኤ መርምሮ ማጽደቅ እና  የ2018 በጀት አመት የአስፈጻሚ ተቋማት የስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት መገምገም እንደሆነ ዋና አፈጉባኤው ገልፀዋል። በበጀት አመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ለማድረግ የተሰሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች በጥልቀት የሚገመገሙ ሲሆን ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች በመለየት የምክርቤቱ አባላት የቀጣይ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጡ አስገንዝበዋል።