en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe 👈

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

Open in Telegram
925
Subscribers
No data24 hours
+67 days
+1130 days
Posts Archive
ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም የሴቶችና ህጻናትን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ማገዝ እንደሚጠበቅባቸው የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ጽ/ቤቱ ይህንን ያስታወቀው የ2018 ዓ/ም 3ኛ ዙር በሴቶች ልማት ህብረት ላይ ሞዴል ቀበሌ በመፍጠር ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ለመስራት የሚያስችል የውይይት መድረክ በዛሬው ዕለት ባካሄደበት ወቅት ነው። በዚሁ ጊዜም የወረዳው የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ሚፍታ አረቦ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የሴቶችና ህጻናትን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እኩል ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸውን በማረጋገጥ በልዩነት በ3ቱ ቀበሌዎች ማለትም በዘሬ፣ ሰፋቶ ቀርሳ እና ቦኔ ቀበሌዎች ላይ በግብርና፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በስራ ዕድል ፈጠራ፣ በቁጠባና ብድር አቅርቦትን ጨምሮ በሌሎች መስኮች ሞዴል የሴቶች ልማት ህብረት በመፍጠር ተሞክሮውን በሁሉም ቀበሌዎች ማስፍት የመድረኩ አብይ አላማ ስለመሆኑ አብራርተዋል። የወረዳዉ ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ፈቲያ መህዲ የ2017 ዓ/ም የሴቶች ልማት ህብረት ዕቅድ አፈጻጸም እና የሴቶች ልማት ህብረት አሰራር ማኑዋል የግብ ስምምነት ሰነድ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል። በውይይቱም የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያ በሁሉም ቀበሌዎች መሟላት እንደሚገባው፣ የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ያነሱት ተሳታፊዎቹ የቀበሌ ስትሪንግ ኮሚቴን ከማጠናከር ረገድ ተጨማሪ ስራዎችን መስራት እንደሚያስፈልግና ቀበሌ ላይ አንድ ባለሙያ ሁሉንም ያማከለ ተግባር ማከናወን እንዳለበት ተሳታፊዎች አንስተዋል። የወረዳዉ ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ፈቲያ መህዲ ለተነሱ ሃሳብና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል። በምላሻቸው እንዳሉት ከመድረክ በግብዓትነት የተነሱ ሃሳቦችን በመውሰድ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተደርጎ እንደሚሰራ ገልጸዋል። አያይዘውም የሴቶችና ህጻናት ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ማገዝ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል። መድረኩን የመሩት አቶ ሚፍታ አረቦ በበኩላቸው በሴቶች ልማት ህብረት በኩል ጊዜውን ያማከለ ውይይት መደረግ እንዳለበት ጠቅሰው የብልጽግና መንግስት የቀበሌ ስትሪንግ ኮሚቴን በማጠናከር የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸውን በሚፈለገው ደረጃ ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ አብራርተዋል። እቶ ሚፍታ አከለውም በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻዎች ተቀናጅቶ በመስራት የአደረጃጀቶች ሚና አንድ ምእራፍ ወደ ፊት ከፍ ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል። ዘገባው የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነው።

ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም "የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅ የመንግሥት ኃላፊነት ብቻ ተደርጎ መወሰድ የለበትም።" የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ መንግሥት ብሔራዊ ጥቅም እንዲከበር ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅ የመንግሥት ኃላፊነት ብቻ ተደርጎ መወሰድ የለበትም ብለዋል። የብሔራዊ ጥቅምን ማስጠበቅ ስልጣን ይዞ ሀገርን የሚመራ ፓርቲ ወይም መንግሥት ሳይሆን ዘመን ተሻጋሪ የዜጎች ዋና አጀንዳ መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በማሳደግ ብሔራዊ ጥቅምና ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን እንዳታስከብር ባዕዳን ወራሪዎች ለዘመናት ችግር ሲፈጥሩ መቆየታቸውን አንስተው በተለያዩ ወቅቶችም የዓባይን ምንጭ ለመያዝ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር አስታውሰዋል። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያዊያን በአንድነትና በጋራ ትግል የጠላቶችን ሴራ በማክሸፍ ዓባይን በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ለብሔራዊ ጥቅም ማዋል እንደቻሉ ተናግረዋል። ዜጎች በሀገር ጉዳይ ያለ ምንም ልዩነት አብረው መቆማቸው ለብሔራዊ ጥቅም መከበር ዓይነተኛ ተምሳሌት እንደሆነም አውስተዋል። በቀደሙ መንግሥታት ከብሔራዊ ጥቅም ይልቅ የቡድን ጥቅሞችን ማስቀደም ሀገሪቱን ወደ ኋላ እንደጎተታት ጠቅሰው÷ አሁን ላይ መንግሥት የሀገሪቱ ብሔራዊ ጥቅም እንዲከበር ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል። በዚህም የባሕር በርን ጉዳይ ከታሪክ፣ ከህግና ከመልከዓ ምድራዊ አቀማመጥ በመነሳት የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ መንግሥት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ዜጎች ሊደግፉትና የሚጠበቅባቸውን ሊያበረክቱ እንደሚገባም አጽንዖት መስጠታቸውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል ።

ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም የሴቶችን የማሀበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ግንዛቤ በማሳደግ ሁለንተናዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሴቶች ክንፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ጽህፈት ቤቱ “ሚዲያ ለላቀ ልማት፣ ለወረዳችን ከፍታና ለዘላቂ ሰላም የሴቶች ሚና” በሚል በሚል የሴቶች ክንፍ የውይይት መድረክ ዛሬ አካሂዶ ውሏል። መድረኩን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የወረዳው የሴቶች ጽ/ቤት ክንፍ ኃላፊ ወ/ሮ ሪሃና ሃሺም በአሁኑ ዘመን ማሀበራዊ ሚዲያ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ሁነኛ መሳሪያ በመሆኑ አንድ የጋራ ማህበረሰብ ለመገንባት ብሎም በአባላት ዘንድ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ለመፍጠር ዋነኛው የመግባቢያ መሳሪያ ነው ያሉ ሲሆን በማህበራዊ ሚዲያ ምንነት፣ ተግዳሮቶች፣ ጥቅሞችና አጠቃቀም እንዲሁም ስነ-ልቦናዊ ጥቃቶችን መከላከል እንደሚቻልና ማህበራዊ ሚዲያን እንዴት ልማት ማዋል እንደሚቻል ለሴቶች ግንዛቤ ማስጨበጥ የመድረኩ ዋና አላማ መሆኑን ገልጸዋል። ወ/ሮ ሪሃና ሃሺም “ሚዲያ ለላቀ ልማት ለወረዳችን ከፍታና ለዘላቂ ሰላም የሴቶች ሚና” በሚል ለመድረኩ የተዘጋጀ ሰነድ አቅርበዋል። ከሚዲያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የሴቶች ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት፣ ሴቶች በወረዳው የተሰሩ ስራዎችን በሚዲያ በማጀብ የተጣለባቸውን ሀላፍትና በተገቢው መወጣት እንደሚገባቸው፣ የሚዲያ አጠቃቀም ከነጠላ ትርክት ወደ ገዢ ትርክት የሚያጸና መሆን እንደሚገባው ያነሱት ተሳታፊዎቹ መንግስት እያከናወናቸው ያሉ የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች በሚዲያ በማጀብ ለተቀረው ህብረተሰብ ማሳወቅ እንደሚገባ ተሳታፊዎች ካነሷቸዉ ሃሳብና አስተያየቶች መካከል በዋናነት ተጠቃሾች ናቸው። መድረኩን የመሩት የወረዳው ሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሪሃና ሃሽም ለተነሱ ጥያቄና አስተያየቶች ምላሽ የሰጡ ሲሆን ሴቶች ያሉትን የሚዲያ አማራጮች በመጠቀም መንግስት እያከናወናቸው ያሉ ልማታዊ ስራዎች በሚዲያ በማጀብ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ጠቅሰው ሴቶች የሚዲያ ተሳትፏቸውን በማሳደግ ከወረዳ ጀምሯ በመንግስት ኮሚኒኬሽን፣ በፓርቲ እና በሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት የሚለቀቁ መረጃዎችን ሼር፣ ኮሜንትና ላይክ በማድረግ ሃላፍትናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኃላፊ ወ/ሮ ፈትያ አ/ዋሂድ በበኩላቸው ሴቶች የጥላቻ አስተሳሰቦችን ባለመከተል መልካም ስራዎችን ማስፍትና ተደራሽነት ማሳደግ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል። አክለውም የስልጠናው ዓላማ ሴቶች ከማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ በቂ ግንዛቤ ኖሯቸው የተዛቡና አፍራሽ አስተሳሰቦችን በትግል ለማስተካከል አይነተኛ ተዋናይ ለማድረግ የሚያስችል ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል።

ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም ወጣቶች ሚዲያን ለበጎ አላማ በማዋል ለተጀመረው ሁለንተናዊ እድገትና ልማት የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንደሚገባቸው በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ገለጸ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ይህ የተገለጸው በወረዳው በዛሬው ዕለት"ሚድያ ለወረዳችን ከፍታና ለላቀ እምርታ"በሚል መሪ ቃል ከተለያዩ የወጣት አደረጃጀቶች ጋር በሠላምና ልማት ዙሪያ የተዘጋጀ የምክክር መድረክ በተካሄደበት ወቅት ነው። ለውይይት የተዘጋጀውን ሠነድ የወረዳው ወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ም/ኃላፊ የሆኑት አቶ አለማር ሀቢብ ያቀረቡ ሲሆን ጥልቀት ያለው ውይይት ተካሄዷበታል። በመደረኩ የተገኙት የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊና የመንግስት ረዳት ተጠሪ የሆኑት አቶ ሚፍታ አረቦ ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ አላማ በመጠቀም የወጣቱን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ ገልጸው ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የህዝቦች አንድነትና የአብሮነት አስተሳሰብ እንዲጎለብት በቅንጅት መስራት ይገባል ብለዋል። በሚዲያ የሚለቀቁ የተዛቡ መረጃዎችን በመመከት ትክክለኛውን መረጃ ለህዝቡ በማድረስ ወጣቶች የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡም አሳስበዋል። የውስጥ ሠላማችንን ለማረጋገጥና የወረዳችንን ከመስፈንጠር ወደ ላቀ እመርታ ለማሸጋገር የሚናከናወናቸው ብርቱ ጥረቶች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አቶ ሚፍታ አክለው ገልጸዋል። የወረዳው የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አ/ፈታ አማን በበኩላቸው መረጃ ለማህበረሰቡ የጀርባ አጥንት መሆኑን ጠቅሠው የትናንቱን እውነት ከዛሬው ኩነት ጋር በማጋመድ ለቀጣዩ ትውልድ የማቆየት ልዩ አቅም እንዳለውም አመላክተው ህብረተሰቡ በተለይም ወጣት አጠቃቀሙን ሚዛናዊና ምክንያታዊ ሊያደርግ እንደሚገባ ገልጸዋል። ሚዲያን ለልማት፣ ለሠላም፣ለወንድማማችነት፣ ለዴሞክራሲ ባህል ግንባታ እንዲሁም ለበጎ ተፅዕኖዎች መጠቀም እንደሚገባ አሳስበዋል። አንዳንድ የውይይት መድረኩ ተሳታፊዎች እንዳሉት በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጩ ሀሰተኛ ዘገባዎች ለህብረተሰቡ የሚያደርሱት አሉታዊ ተፅዕኖዎችን በመረዳት ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን እና ልማትን ለማፋጠን የወጣቱ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በትኩረት እንደሚንቀሳቀሱ ተናግረዋል። የሚከሰቱ ችግሮችን በመፍታት እንዲሁም አብሮነት፤ ወንድማማችነት እና ህብረ-ብሄራዊ አንድነት እንዲፀና የማስቻል ኃላፊነት እንዳለባቸውም ገልጸዋል።

ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ የጊጬ ዲምቱ ቀበሌ ተወላጅ ባለሃብቶች አማካኝነት የጎራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስፋፊያ ግንባታ ተጠናክሮ መቀጠሉን የወረዳው ትምህት ቤቶች ጽ/ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ አዲሱ ማስፋፊያ ግንባታ 2 ብሎክ 8 መማሪያ ክፍሎች ያከተተ ሲሆን በተጨማሪም ነባር 3 መማሪያ ክፍሎች አሻዋ ግርፍ እና ሌሾ የተለያዩ የውስጥ ቁሳቁስ የማሟላት ስራ እየተሰራ ነው። አጠቃላይ ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በፍጥነት እየተገነባ መሆኑን የወረዳው ትምህርት ቤቶች ጽ/ቤት አክሎ ገልጿል። የወረዳችን ባለሃብቶች በአካባቢያቸው እያደረጉ ያለውን ተሳትፎ በሁሉም ዘርፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገልጿል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የመኸር ምርት አሰባሰብ ወቅታዊ ሁኔታ በምስል:

የሳምንቱ አበይት ዜናዎች ጥቅምት 23/2018 ዓ.ም 👉🏼‎ “International call Organization” የተሰኘው ግብረ-ሰናይ ድርጅት በገ/ጉ/ወ/ወረዳ ገሬኖ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ከ10 ሚሊዮን 600 ሺህ ብር በላይ በሆነ ወጪ ለሚያስገነባው የትምህርት ፕሮጀክት ከወረዳው ት/ቤቶች ጽ/ቤት እና ፋይናንስ ጽ/ቤት አመራሮች ጋር የውል ስምምነት ተፈራረሙ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ፅህፈት ቤት የከተሞች ልማትና ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ አስተወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎በጉራጌ ዞን ገ/ጉ/ወ/ወረዳ በ2017 ዓ/ም የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከ78 ሺህ 70 በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማስጠቀም ህዝብና መንግስት ሊያወጣ ይችል የነበረውን 44 ሚሊዮን 568 ሺህ 395 ብር ማዳን መቻሉን የወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎የትምህርት ስብራትን ለመሻገር የሚደረገውን ርብርብ በየደረጃው የሚገኙ አካላት ማገዝ እንደሚጠበቅባቸው የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ትምህርት ቤቶች ፅ/ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት በወረዳው ያለውን ፀጋ አሟጠ በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የአርሶ አደሮችን ኑሮ ለማሻሻል በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ ገለጸ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨፨ 👉🏼‎በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ "አንድም እናት በደም እጦት ምክንያት መሞት የለባትም! በሚል መሪ ቃል የደም ልገሳ እለት ተካሄደ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨

ጥቅምት 23/2018 ዓ.ም የጤና መዋቅሮች የአልጋ አጎበር ስርጭት ተደራሽነትን ከማስፋት ባሻገር አጠቃቀም ላይ በልዩ ትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ የክልሉ ጤና ቢሮ አሳሰበ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በዚህ አመት 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን የአልጋ አጎበር በማሰራጨት ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ከወባ ለመጠበቅ እየተሰራ መሆኑንም ቢሮው አስታውቋል። ቢሮው በዛሬው እለት ይፋዊ የአልጋ አጎበር ስርጭት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በሆሳዕና አካሂዷል። በየደረጃው ያሉ የጤና መዋቅሮች የአልጋ አጎበር ስርጭት ተደራሽነትን ከማስፋት ባሻገር በማህበረሰቡ የአጎበር አጠቃቀም ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን መቅረፍ ልዩ ትኩረት አድርገው ሊሰሩ እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮዽያ ክልል ጤና ቢሮ አሳስቧል። የወባ በሽታ የማህበረሰብ የጤና ችግር ወደማይሆንበት ደረጃ ለማድረስ ግብ ተቀምጦ እየተሰራ መሆኑንም በዚሁ ወቅት አስታውቋል ። በቢሮው የበሽታ መከላከልና ጤና ማጎልበት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፍስሃ ለመዕጎ እንደገለጹት በየአመቱ ለሚከሰተው የወባ በሽታ ከአጎበር አቅርቦት ክፍተት ባሻገር ከስርጭት በሗላ በማህበረሰቡ ዘንድ የሚታዩ የአጠቃቀም ጉድለቶች ከፍተኛ ሚና አላቸው። በተለይም በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት አለመጠቀም፣ አጎበሩን ለሌላ አገልግሎት ማዋልና ጥቅም ላይ አለማዋል ችግሮች እንደሚስተዋሉ ገልጸዋል ። እነዚህን ችግሮች መቅረፍ ህብረተሰቡን ከወባ ለመከላከል ከፍተኛ ሚና እንዳለው ያነሱት አቶ ፍስሃ የጤና መዋቅሮችም ሆነ አጠቃላይ ህዝቡ በእነዚህ ችግሮች መቅረፍ ላይ በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል። ከክልሉ አጠቃላይ አካባቢ ውስጥ 83 ከመቶ የሚሆነው ለወባ ተጋላጭ መሆኑን የገለጹት አቶ ፍስሃ በዚህ አካባቢ ውስጥ ኗሪ የሆነውን ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ታሳቢ ያደረገ የአልጋ አጎበር ስርጭት ንቅናቄ በይፋ መጀመሩን አስታውቀዋል ። ከዚህ ቀደም ብሎም በተለይ ተጋላጭ በሆኑ 6 ወረዳዎች ሲሰራጭ መቆየቱንም ገልጸዋል ። የአጎበር ተደራሽነትን በማጠናከር፣ የኬሚካል ርጭት በማካሄድና የመራቢያ አካባቢዎችን በማፅዳት የወባ ትንኝ ስርጭትን ከመግታትና ከማስቆም ጎን ለጎን ህክምናና የመድሃኒት ግብኣት አቅርቦት ላይ ትኩረት መደረግ እንዳለበትም ተናግረዋል ። የአልጋ አጎበር ስርጭቱ በ18 ወረዳዎች የሚካሄድ ሲሆን በዚህ አመት 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን አጎበር በማሰራጨት ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ከወባ ለመጠበቅ እየተሰራ መሆኑንም አቶ ፍስሃ አስታውቀዋል። እስከ ባለው ሂደት 600ሺ የሚሆን አጎበር ወደ ማዕከል የገባ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 210ሺ የሚሆነው መሰራጨቱን ተናግረዋል ። የወባ ስጋት ያለባቸው አካባቢዎች የጤና ሃላፊዎች እንደገለጹት ባለፈው አመት የታየው የወባ ስርጭት ጫና በዚህ አመት እንዳይደገም የትንኝ መራቢያ አካባቢዎችን የማጽዳትና የህብረተሰቡን በህብረተሰቡ ዘንድ የሚታየውን የአልጋ አጎበር አጠቃቀም ክፍተት ለመቅረፍ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል ። መረጃው የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው።