en
Feedback
የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

Open in Telegram
918
Subscribers
No data24 hours
+17 days
+730 days
Posts Archive
ቀን የካቲት 17/2018ዓ.ም የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሳይንስ እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት የ2ኛ ሩብ ዓመት የዜጎች ቻርተር እና የህዝብ ክንፍ መድረክ ዛሬ ማካሄዱን አስታወቀ። ፨፨፨፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨፨፨፨ የፅ/ቤቱ የልማት ዕቅድ ባለ ሙያ ወ/ሮ ሂክማ መሀመድ የ2ኛሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የዜጎች ቻርተር ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል። ተሳታፊዎች ካነሷቸው ሃሳብና አስተያየቶች መካከል የሰው ሃይልንና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ በትኩረት መሰራት እንዳለበት፤ለኢትዮ ኮደር ያለንንግንዛቤ አነስተኛ መሆኑንና ፤ወጣቱ ያገኘው እድል መጠቀም መቻል እንዳለበት ናበተቋማት የተበላሹ ኮምፒዩተሮች፤ፕሪንተር ማሽኖች ተጠግነው ዘላቂ የሆነ ችግር መፍታት መቻል አለባቸው የሚሉት ናቸው። ለተነሱ ሀሳብ አስተያየት ምላሽ ና ማብራሪያ የሰጡት የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ሳ/ኢ/ቴ ፅ/ቤት ሀላፊ ተወካይ አቶአ/መጂድ ዘይኔ በየ ተቋማት የሚጠገኑ ማንኛውም ኢሌክትኒክስ ቼክ ሊስት በማዘጋጀት ክትትል እየተደረገ መሆኑ ገልፀው ጥገና ና እድሳት እየተደረገላቸው እንደሚሂድና በወረዳ ደረጃ ያሉትን ብልሽት የገጠማቸው የኤሌክትሮኒክስ ግብዓቶችን በመጠገን ከፍተኛ የመንግስት ናየህዝብ ሃብት ማዳን የተቻለ መሆኑ አብራርተዋል።ከመሰረታዊ ኮምፒውተር ስልጠና ተቋማት ተደጋጋሚ ተመሳሳይ ሰው ከመላክ ይልቅ እድሉ ያላገኙት የስልጠናው ተካፋይ መሆን ይጠበቅባቸዋል ብለዋል ። በኢትዮ ኮደርስ ያገኘነውን እድል መጠቀም መቻል ያለብን በመሆኑ መዘናጋት ሳይታይ በሁሉም ደረጃ ያለ የህብረተሰብ ክፍል መሰልጠን እንደ ሚገባ ና በተለይ ወጣቱ ትኩረት ሰጥቶ በመሰልጠን ተጠቃሚ እንዲሆኑ  መሰልጠን እንደሚገባቸው ገልፀው በየ ተቋሙ ኢትዮ ኮደርስ ስልጠና መጨረስ አለመጨረሳቸውን ክትትል ይደረጋል ብለዋል።

የካቲት 17/2018 ዓ/ም 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ነፃ ፣ፍትሃዊ፣በሁሉም  ዘንድ ተቀባይነት ያለውና ዲሞክራሲያዊ ለማድረግ እየተሰራ ነው፦ አቶ አለማየሁ ገብረመስቀል ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የጉራጌ ዞን የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ  ጽህፈት ቤት በዞኑ በሁሉም መዋቅሮች የፖለቲካና የአደረጃጀት ስራዎችናን ጨምሮ የምርጫ ምቹነት ሁኔታ መነሻ በማድረግ ያደረገውን የሱፐርቪዥን ስራ ሪፖርት ደጋፊ አመራሮች በተገኙበት በወልቂጤ ከተማ ገምግሟል። የጉራጌ ዞን የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት  ኃላፊ አቶ አለማየሁ ገ/መስቀል እንደገለፁት በዞኑ የፖለቲካና የአደረጃጀት ስራዎች ለማጠናከር የሚያስችል ወጥነት ባለው መልኩ  ስራዎች እየተሰሩ ነው። በዚህም ያሉ ጉድለቶች ለማረም እና ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል ብሎም የህዝቡ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በዞኑ ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በስሩ የሚገኙ ሁሉም መዋቅሮች የብልፅግና ህብረትና በቤተሰብ ደረጃ የሱፐርቪዥን ስራ ተሠርቶ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴያቸው ተገምግሟል ብለዋል። በሱፐርቪዥኑ  የፖለቲካና የአደረጃጀት እንዲሁም የምርጫ ምቹነትን ጨምሮ አዳዲስ የኢንሼቲቭ ስራዎች በተገቢው ምልከታ መደረጉን የገለፁት አቶ አለማየሁ በመንግስትና ህብረተሰብ ተሳትፎ የተሰሩ ማህበራዊ ልማቶች ተሞክሮ ሊሆኑ የሚችሉ መሆኑን አብራርተዋል። አመራሩ በምርጫ ስራዎች ህዝቡ ያለው ግንዛቤ የበለጠ እንዲያሳድግ ሊሰራ ይገባል ያሉት አቶ አለማየሁ ለዚህም በቤተሰብ ደረጃ የሚሰሩ ስራዎች ላይ ትኩረት ማድረግ ያስፈልጋል በማለት አፅንዎት ሰጥተዋል። በቀጣይም የድጋፍና ክትትል ስራዎች አጠናክሮ በመስራት ወደ ብልፅግና የሚደረገው ጉዞ ለማፋጠን በየደረጃዉ የሚገኘው አመራርና አባላት ግንባር ቀደም ሆነው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል። ኃላፊው አክለውም የምርጫ ምቹነት 100% ማሳከት በማለት እየተሰራ ያለው ስራ እንደጅምር አበረታች መሆኑን አመላክተው አሁንም ፓርቲው ያስቀመጣቸውን መሰረታዊ የምርጫ ግቦች ለማሳካት የቅድመ ምርጫ ተግባራት በታቀደላቸው ጊዜ  መፈፀም ያስፈልጋል ብለዋል። የብልፅግና ፓርቲ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ነፃ ፣ፍትሃዊ፣በሁሉም  ዘንድ ተቀባይነት ያለውና ዲሞክራሲያዊ ለማድረግ ከወትሮው በተለየ መልኩ እየሰራ ነው ያሉት ኃላፊው በዞናችንም ይሄንን እውን ለማድረግ የሚያስችል መድላድል እንዳለ በሱፐርቪዥኑ ማረጋገጥ እንደተቻለ አስገንዝበዋል። በጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ናስር ሀሰን በበኩላቸው የፓርቲ ተቋም ግንባታ ስራዎች ከቅንጫፍ ጽ/ቤት ጀምሮ እስከ ቤተሰብ ድረስ ያሉ አደረጃጆቶች ይበልጥ ተጠናክረው በመስራት እየተመዘገቡ ያሉ ለውጦች በዘላቂነት ሊያስቀጥሉ ይገባል ብለዋል ። 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊነት ፣ፍትሀዊነት ነፃ እና ተዓማኒነት እንዲኖረው አየተሰሩ ያሉ ስራዎች ይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል። በሱፐርቪዥን የተለዩ ጠንካራ አፈፃፀሞች ማስቀጠልና ጉድለች ደግሞ ፈጥሮ በማረም የህዝቡ ፖለቲካዊ ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ላይ ይበልጥ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሁሉም መረባረብ ይገባል ብለዋል። በመድረኩ የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፈይሰል ሀሰን፣ የወረዳና ከተማ ደጋፊ አመራሮች ጨምሮ ሌሎችም ተሳትፈዋል።

የካቲት 16/2018 ዓ ም የመንግስት የተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ በማስተካከል ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የ2018 በጀት ዓመት የ2ኛ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀምና የዜጎች ቻርተር  ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ። በሁሉም ተቋማት ለማህበረሰቡ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት የሚሰጥ ሲቪል ሰርቫንት ለመፍጠር በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ  የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፋሪስ ከማል ገልጸዋል። በመድረኩ የጽ/ቤቱ የልማት ና የመልካም አሰተዳደር የቡደን መሪ የሆኑት አቶ ሙስጠፍ ሽፍ አማካኝነት የ2018 ዓ.ም በ2ኛ ሩብ አመት በሴክተሩ የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት  በዝርዝር ቀርቦ  ከባለድርሻ አካላት  ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን በተነሱ ጉዳዮች ምላሽና አስተያየቶች ተሰጥቶባቸዋል። የወረዳው የፐብሊክ ሠርቪስ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፋሪስ ከማል በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ እንደገለፁት የተቋማትን የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ለመፍታትና አገልግሎት አሰጣጡን ሊያረጋግጡ የሚችሉ አሰራሮችን በመዘርጋት እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል። በጽ/ቤቱ በተቋማት የሚነሱ የመልካም አሰተዳደር ችግሮች ፈጣንና ቀልጣፋ ምላሽ በመስጠት የህ/ሰቡ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚሰሩ ተግባራት የህዝብ ክንፉ እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት  ቅንጅታዊ አሰራር ማጠናክር እንደሚገባም ገልጸዋል :: አክለውም አቶ ፋሪስ ከማል ተቋማት የሚቀርቡ አቤቶታና ቅሬታዎች የመፍታት እና ሚፈለጉ መረጃ በወቅቱ ለሚመለከተው  አካል ከማስተላለፍ አንጻር የማስተዋሉ ችግሮች በቀጣይ  ሊታረሙ እንደሚገባ  ተናግረዋል ። በሁሉም ተቋምት ማህበረሰቡ ጥራት ያለው ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በአግባቡ እንዲያገኝ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል ። የአገልግሎት ፈላጊውን የማህበረሰብ ክፍል ፍላጎት ማሟላት የፐብሊክ ሠርቪስ ተቋም ብቻ ሳይሆን ሁሉም ተቋማት እና የሚመለከታቸው አካላት የድርሻቸውን ወስደው በቅንጅት ሊሠሩ እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በውይይት መድረኩ የህዝብ ክንፎች፣ እንዲሁም የሴክተር የልማት እቅድና የሰው ሀብት ባለሙያዎች እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የካቲት 16/2018 ዓ/ም የ3ኛው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ልዩ ልዩ  ስፖርትና የባህል ስፖርት ሻምፒዮና ፌስቲቫል በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በድምቀት እየተካሄደ ይገኛል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ጉራጌ ዞን በብስክሌት እና በጠረጴዛ ቴኒስ አንደኛ በመሆን በድጋሚ ድሉን አስመዝግቧል። የጉራጌ ዞን በሁሉም የስፖርት አይነቶች አበረታች ውጤት እያስመዘገበ ነው። በዚህም ዛሬ ጠዋት ላይ በወልቂጤ አስፋልት ላይ ብርቱ ፉክክርና ትይንት ታይቶበት የነበረው የብስክሌት ውድድር በጉራጌ ዞን የበላይነት ተጠናቋል። በውድድሩ ጉራጌ ዞን 1ኛ ስልጤ ዞን 2ኛ እና ማረቆ 3ኛ ሆኗል። ጉራጌ ዞንና ምስራቅ ጉራጌ ዞንን ያገናኘ የነበረው የፍጻሜው የጠረጴዛ ቴኒስ ጨዋታ በጉራጌ ዞን አሸናፊነት ፍጻሜው አግኝቷል። በተያያዘም ዛሬ 5 ሰአት ላይ በሴቶች እግር ኳስ ጉራጌ ዞን ሀዲያን ዞንን 2ለ1 አሸንፏል። በወንዶች እግር ኳስ ደግሞ ጉራጌ ከሀዲያ ነገ 7 ሰአት ላይ የሚያደርጉት ጨዋት በጉጉት ይጠበቃል። የ3ኛው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስፖርት ሻምፒዮናና ፌስቲቫል በወልቂጤ ከተማ በድምቀት እየተካሄደ ነው።

የሳምንቱ አበይት ዜናዎች የካቲት 15/2018 ዓ.ም 🎤 "ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገር "በሚል መሪ ቃል የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ጽ/ቤት ከወረዳና ቀበሌ ለተወጣጡ የኮሚሽን አባላትና አመራሮች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተሰጠ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 🎤 በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ "በመደራጀት ወደ ተግባራዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት" በሚል መሪ ቃል ወረዳ አቀፍ የሴቶች ልማት ህብረት የንቅናቄ መድረክ በመሃል ከተማ ተካሄደ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 🎤 የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ትምህርት ቤቶች ጽ/ቤት የ6 ወር የትምህርት ቤቶችን ተግባር አፈጻጸም የግምገማ መድረክ ተካሂዷል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 🎤 "ክህሎት መር ስራ ዕድል ፈጠራ ለብልጽግናችን" በሚል መሪ ቃል በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ስራ ዕድል ፈጠራ ምክር ቤት የ7 ወር ስራ አፈፃፀም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተካሄደ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 🎤 ውስን የሆነውን የመንግስት በጀት በአግባቡ በመጠቀም፣በመቆጣጠርና በመከታተል በጀቱ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል በማድረግ የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 🎤 በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አዘጋጅነት የልማት ስራዎች ጉብኝት ተካሄደ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 🎤 የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ንግድና ገብያ ልማት ጽ/ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 🎤 ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!! ለ7ተኛው ዙር ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲ የመወዳደርያ ምልክት የሆነውን" የስንዴ ነዶ" የማስተዋወቅ መርሃ ግብር ተካሄደ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨

ቀን የካቲት 14/2018ዓ.ም የሴቶች ኢኮኖሚያዊ ፣ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎቸው ለማሳደግ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚያስፈልግ ተገለፀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ይህ የተገለፀውበገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ "በመደራጀት ወደ ተግባራዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት" በሚል መሪ ቃል ሴቶች ልማት ህብረት የንቅናቄ መድረክ ባካሄደበት ወቅት ነው። የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሴቶችና ህጻናት ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ፈትያ መህዲ እንደገለፁት ሴቶች በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች ያላቸውን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ የሴቶች ልማት ህብረት  አደረጃጀት ወሳኝ መሆኑ ገልፀው  የሴቶች ልማት ህብረት አደረጃጀት በማጠናከር   በሁሉም ዘርፍ ተጠቃሚ ለማድረግ  ሁሉም የድርሻውን ለመወጣት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል። ሴቶች ተደራጅተው በመቆጠብና  በመረዳዳት ረገድ እየተደረገ ያለው ጥረት ሊበረታታ የሚገባ በመሆኑ በቀጣይም በየአካባቢው ያልተደራጁ  ሴቶች በአደረጃጀት እንዲሳተፋ የማድረግና እና በአደረጃጀቶች ሊታቀፉ ይገባል እንደሚገባ የገለጹት ኃላፊዋ የሴቶች ልማት ህብረት አደረጃጀት ይበልጥ እንዲጠናከር በየቀበሌ የሚገኘው ስትሪንግ ኮሚቴ ተግባሩን ትኩረት ሊሰጡት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል። የገ/ጉ/ወ/ወ/ወ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ የአቅም ግምባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሚፍታ አረቦ በበኩላቸው በየደረጃ ያሉ ባለድርሻ አካላት ሴቶች ለሚፈልጓቸው ማንኛውም ድጋፍ በመጠየቅ እና ውጤታማ መሆን እንደሚጠበቅባቸው ገልፀው ቀጣይ ሀገራዊ ምርጫ ላይ የሴቶች ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ የሴቶችን ችግሮች የመፍታት ፣የመሰብሰብ ፣የመደራጀትና በልማት ስራዎች ላይ ንቁ ተሳታፊ በመሆን ለሀገራችን እድገት ወሳኝ ሚና እንዳላቸው ገልፀው ያለ ሴቶች ተሳትፎ የሚታሰብ ልማት ባለመኖሩ ሴቶች ንቁ ተሳታፊ መሆን እንደሚጠበቅባቸው አስታውሰው ሴቶች በተቀናጀ መልኩ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ መልዕክት አስተላልፈዋል ። የሴቶችን በቁጠባ ባህልን ለማሳደግ የኦሞ ባለሙያ የድጋፍና ክትትል ጉድለት ፣የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆን እንደሚገባ ፤ሴቶች በኢኮኖሚ ላይ ላይ ንቁ ተሳታፊ መሆን እንዳልባቸው ፤የሴቶች ተወካይና ክንፍ አደረጃጀቶችን ጠንክረው መያዝ እንደሚጠበቅባቸው ፤ሴቶችን ማህበርና በሌሎችም ዘርፎች ተሳታፊ መሆን እንደሚገባቸው፣ ጊዜው የፈጠራቸው ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ግምባር ቀደም መሆን እንዳለባቸው ፤በልማት ስራዎች ንቁ ተሳታፊ መሆን እንደሚገባቸው የመድረኩ ተሳታፊዎች  ሀሳባቸውን ገልጸዋል። በመድረኩ የወረዳ አመራሮች፣የቀበሌ ሊቃነመናብርት፣ የሴቶች ተወካይና ሴቶች ክነፍ፣የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች እንዲሁም የቀበሌ ህብረት ስራ አደራጅ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

የካቲት 14/2018 ዓ.ም በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ "በመደራጀት ወደ ተግባራዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት" በሚል መሪ ቃል ወረዳ አቀፍ የሴቶች ልማት ህብረት የንቅናቄ መድረክ በመሃል ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሴቶችና ህጻናት ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ፈትያ መህዲ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ሴቶችን በሁለንተናዊ ዘርፍ ተሳታፊና ተጠቃሚ ማድረግ የተጀመረውን ብልፅግና ለማፋጠን ወሳኝ ነው ብለዋል። የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሴቶች ልማት ህብረትን በሁለንተናዊ መስክ ለማጠናከር እየተሰራ በሚገኘው ስራ የተገኙ ውጤቶችን ይበልጥ ማስፋትና ጉድለቶችን በተቀናጀ መልኩ ለመቅረፍ መረባረብ እንደሚገባ ገልፀዋል። የሴቶችን አደረጃጀቶች በማጠናከር የሴቶች ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት፣በተጠያቂነት እና በኃላፊነት ሊሰራ እንደሚገባ ወ/ሮ ፈትያ  አስገንዝበዋል። በመድረኩ በሴቶች ልማት ህብረት ስራ አደረጃጀት፣ በብድርና ቁጠባ ህብረት ስራ ማህበር ሴቶች እንዲደራጅ ለማድረገ የተዘጋጅ ሰነዶች በጽ/ቤቱ ልማት እቅድ ባለሙያ በሆኑት አቶ ተስፋሁን ሻምበልና መርሻ አስቻለው አማካኝነት ቀርቦ ጥልቀት ያለው ውይይት በማድረግ የተለያዩ አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። በመድረኩ የወረዳ አመራሮች፣የቀበሌ ሊቃነመናብርት፣ የሴቶች ተወካይና ሴቶች ክነፍ፣የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች እንዲሁም የቀበሌ ህብረት ስራ አደራጅ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።