cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

🎀ሴት ልጅ በኢስላም ውድ ልእልት ናት 🎀

#🎀የሴት ልጅ ክብሯ በኢስላም የላቀ ደረጃ አላት #🎀እኛ የሰለፊያ ሴቶች ነን #🎀ሀሳብ አስተያየት ካላቹህ #🎀ቻናላችንን ይቀላቀሉ ሸር ያድርጉ #🎀https://t.me/aseelfy #🎀ሀሳብ አስተያየት ካለወት➴➴ @assslfy_bot በሚለው ያድርሱን እንመልሳለን

Show more
Advertising posts
498
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-1330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
السلام عليكم ورحمةالله وبركاته ልዩ ፕሮግራም የዳዕዋ ዘመቻ በራያ ቆቦ ከነገ ጁሙዓ ጠዋት ጀምሮ እስከ እሁድ ምሽት ድረስ የሚደረድ ፕሮግራም ይዘንላችሁ ብቅ ብለናል እንኳን መቅረት ቀርቶ ማርፈድ አይታሰብም !! በአካል ራያ ቆቦ በመሄድ የታደሙ እንግዶቻችን  1, ሼይኽ አህመድ አወቀ 2, ሼይኽ ሙሐመድ አሚን 3, ሼይኽ ሁሴን ዑመር 4, ሼይኽ ሙሐመድ መኪን 5, ሼይኽ ሙሐመድ ገዛል 6, ኡስታዝ አቡ ሙዓዝ 7, ወንድማችን አቡ ዓኢሻ አሏህ ከፈቀደ በኦንላይን ይገባሉ ብለን የምንጠብቃቸው እንግዶቻችን ኡስታዝ ኸድር አህመድ አል ኬሚሴ ሼይኽ አወል አህመድ አል ኬሚሴ https://t.me/+7NxWe_h1CNUwMWY0 https://t.me/+75U-d0sq3IY4MDk0
Show all...
ቅድሚያ ለራሳችን ቦታ መስጠትን እንልመድ ብናስተምርም ትምርታችን ከሰዎች ተቀባይነት የሚኖረው ቅድሚያ ለራሳችን ቦታ ሰተን ተምረን ስናስተምር ነው በመልካም የሚያዘው ተናጋሪው ብዙ ነው ሰዎችን ያመላከተበትን ተግባሪው ግን ትንሽ ነው አላህ ይዘንልን በተለይ እህቶች ራስን ማስቀደም እንልመድ ብዙ ጊዜ የኡስታዞቻችንን አውዶ በመቁረጥ እና ከአንዱ ግሩፕ ወደሌለኛው ግሩፕ ማንሸራሸር የተለያዩ ፁሁፎችን ኮፒ በማድረግ እያሳመሩ በመላክ የተለያዩ ተከታታይ ፁሁፎችን በየቻናሉ ላይ በመፃፍ ሰዎችን ሲጠቅሙ እናያለን አላህ ይጨምርላቸው ጊዜያቸውንም አላህ በበረካ ላይ በረካ ይጨምርላቸው ከነዚህ እህቶች ውስጥ ግን የሚያንሸራሽሩትን አውዶ ግማሹን እንኳን በስረአት የማያዳምጡ አሉ በተከታታይ በሚልኳቸው ፁሁፎች ውስጥ ራሳቸው ቀድመው ምን እንደሚል ያልተረዱ አሉ ሀቂቃ ልክ እንደኔ ብዙዎቻቹ አጋጥሟቹህ ሊሆን ይችላል አንድ ፁሁፍ በብዙ ቻናሎች ላይ ሳየው ያነበብኩት እና የወደድኩት ተከታታይ ፁሁፍ ነበር እናም አንድ ቦታ ትንሽ ተወሰበሰበብኘ እህቴን ፈልጌ እንድታስረዳኘ ስጠይቃት የመለሰችልኘ መልስ እንድህ ነበር ሰዎች በገባቸው ልክ እንድጠቀሙበት እልከዋለሁ እንጀ እኔ በራሴ ተረድቸውም አብቤውም አይደለም አለችኘ ሀሳቧ ጥሩ ሳይሆን አይቀርም ግን ያንን ኮፒ አድርጋ እያሳማመረች በየቻናሉ ሸር ባደረገችበት ራሷ ደጋግማ ብታነበው ተጠቃሚ ሆና ላልገባቸውም በማስረዳት ትጠቅም ነበር ባለ አውዶዋም እህቴ ልክ እንደዚሁ በተለያዩ ቻናሎች አድሚን ተሰቷቹህ የምታገለግሉ እህቶች ቅድሚያ ለራሳቹህ ስጡ አታገልግሉ አይደለም ግን ራሳቹህን አስቀድሙ በተረፈው ጊዜያቹህ እኛን ከጠቀማቹህን በቂ ነው በተናገርኩት ነገር ስህተት ካለብኘ ለመታረም ዝግጁ ነኘ https://t.me/+ZKXkcQYiRdcyMDFk https://t.me/+ZKXkcQYiRdcyMDFk
Show all...
📱 ቀጥታ ስርጭት ሙሓደራህ ▪️የዳዕዋው ርእስ ፦ « ይድረስ ለፋኖ ደጋፊ ሙስሊሞች » 🎙 አብዱረሕማን አቡ ዑሰይሚን ተ ጀ ም ሯ ል https://t.me/abuUseyminabdurehman?livestream=3ad23cfef37a8acce0
Show all...
📗
ከአርሹ በላይ
በዚህ ስራዬ ውስጥ ለነዚህ ሃሰተኞች ሰበብ ላለመስጠት የሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብ ቀርቶ የኢብኑ ተይሚያና የተማሪዎቻቸውን ንግግሮችም _ አላካተትኩም። ከቁርኣንና ከሐዲሥ ባለፈ ቀዳሚ ትኩረቴ ያደረግኩት የአሽዐሪያ አንጃ ከመፈጠሩ በፊት ባለፉት እስከ 300 ሂ. ድረስ በነበሩ ዑለማዎች ላይ ነው። ከዚህ ዘመን በኋላ በመጡ ስመ ገናና ዑለማዎች ሊሞግቱን ለሚሹ ማርከሻ ይሆን ዘንድ ያክል ብቻ ከ300 ሂ. ጀምሬ እስከ 7ኛው ክ/ዘመን 2ኛ አጋማሽ ድረስ ካለፉ ዑለማዎች እያለፍኩ አጣቅሻለሁ። አንባቢ በቀላሉ ይለይ ዘንድ ከየስማቸው ፊት ለፊት በሂጅራው አቆጣጠር የሞቱበትን አመት አስፍሬያለሁ። የቀደምት ዑለማዎችን ንግግር ሳጣቅስ በተቻለኝ መጠን ከዘመነ ኢብኑ ተይሚያ የቀደሙ ጥንታዊ ምንጮች ላይ አተኩሬያለሁ። አንዳንዶቹ ምንጮች ላይ ሊነሱ የሚችሉትን ጥርጣሬ ከወዲሁ ለመግፈፍ ስል በዚያኛው ጎራ በኩል የሚታመኑ ሰዎችን ስራዎች ብዙ ቦታዎች ላይ በተጓዳኝ ወይም በብቸኝነት አስፍሬያለሁ። አልፎ አልፎ የኢብኑ ተይሚያ፣ የኢብኑል ቀይምና የዘሀቢን ኪታቦች በምንጭነት ተጠቅሜያለሁ። ልብ በሉ! ንግግሮቻቸውን እያልኩ አይደለም። በታማኝነት ረገድ ጠላት የመሰከረላቸው እንደመሆናቸው የራሳቸውን አቋም ሳይሆን ለሌሎች ንግግር እንደ ምንጭነት በስሱ ብጠቀማቸው በሰፊው የተጓዝኩበትን አያደፈርስም ብዬ በፅኑ አምናለሁ። መፅሃፉ ውስጥ ያጣቀስኳቸውን ስብእናዎች በተመለከተ “አንቱታን" በወጥነት አልተጠቀምኩም። አንዳንድ ቦታዎች ላይ ሶሐቦችን ጭምር “አንተ” በሚል የገለፅኩባቸው ቦታዎች አሉ፡፡ ለቃላት አጠቃቀሜ የተለየ ትርጓሜ እንዳይሰጠው ነው ይህን የምለው። ይህን መፅሐፍ ከአራት አመት በፊት ነበር ያጠናቀቅኩት። አንድም የማሳተሚያው ገንዘብ ጉዳይ ሲያሳስበኝ አንድም እንደምንም ጨምቄ የገፁን ብዛት ለመቀነስ ሳውጠነጥን በህዳር 2010 ላፕቶፕ ኮምፒተሬ በእጄ ላይ እያለ የመኪና አደጋ ደረሰብኝ። መፅሐፉ ሳይታተም በመቅረቱ በዚያች መኪና ውስጥ ተቀርቅሬ ሞትን ስጠባበቅ በነበርኩባት ግማሽ ሰዓት አካባቢ ቁጭት ሲለበልበኝ ይታወሰኛል የአላህ ፈቃዱ ሆኖ ከነበርኩበት አጣብቂኝ ወጣሁ። ቆይቼም የለቀማ ስራዪን ባስቸኳይ ላጠናቅና ለህትመት ዝግጁ ማድረግ አለብኝ ስል ሌላ ያልታሰበ ዱብ አዳ ገጠመኝ። ኮምፒተሬ ከሙሉ መረጃዎቹ ጋር ጠፋ። መረጃዎቹን መጠባበቂያ ህርድ ዲስክ ላይ አስቀምጬ ስለነበር አልተደናገጥኩም ነበር። ማምቴ ግን ልከ አልነበረም። ባላወቅኩት ምክንያት ከፋይሎቼ ተነጥሎ ይሄኛው ሳይገኝ ቀረ። እራሴን ለቀጣይ አዲስ ስራ በማጭበት ጊዜ ይህ ከስተት መከሰቱ ለአጭር ጊዜም ቢሆን ሞራሌን አቀዘቀዘው። ከህመሜ ገና ስላላገገምኩ በምፈልገው ፍጥነት መስራት ባልችልም “ሆ ብየ እንደገና ጀመርኩት። አጠር ባለ ጊዜ አጠናቀቅኩኝ። ይሁን እንጂ በአቅም ማነስና በስንፍናዬ ምክንያት የህትመት ብርሃን ሳያይ ከሁለት አመት በላይ ከቆየ በኋላ የአላህ ፈቃዱ ሆነና ይሄው በዚህ መልኩ ወጣ። ተቆጥሮ የማይዘለቅ ምስጋና ለጌታዬ ይድረሰው። አንባቢዎቼን ሳስብ መጠኑ ተለጥጦብኛል። ይሄ ጭንቀቴ የመጀመሪያውን ስራዬን አሳጥቶኛል። የሚደንቀው አሁንም ተመሳሳይ መጠን ሆኖ ነው የተጠናቀቀው። አንባቢዎች ሆይ! እኔ ስፅፍ ከደከምኩት በላይ አትደክሙምና ከስሜት ነፃ ሆናችሁ በጥሞናና በትእግስት እንድታነቡት አሳስባለሁ። የምትችሉ ሰዎች ጉዳዩ በአሕባሽ መርዛማ ስብከት የተነሳ ሰፊ ውዥንብርና ጩኸት የበዛበት መሆኑን አውቃችሁ ይህንን ስራ በማሰራጨት ላይ የበኩላችሁን እንድትወጡ አደራ እያልኩ ስለምታደርጉት ሁሉ ቀድሜ አመሰግናለሁ። ዲኑ የሁላችንም ነውና ዲናችንን በመጠበቅ ላይ ሁላችንም በየፊናችን እንረባረብ። መልካም ንባብ........ መፅሀፉ የሌላቹህ እየገዛቹህ https://t.me/+ZKXkcQYiRdcyMDFk https://t.me/+ZKXkcQYiRdcyMDFk
Show all...
የሱና መፅሀፎችን ቃጠሎ አስመልክቶ አጭር መልክት በኡስታዝ ሙሀመድ ሲራጅ https://t.me/OkazHijab
Show all...
የሱና_መፅሀፍችን_ቃጠሎ_በተመለከተ_አጭር_ማብራሪያ_.mp313.27 MB
📗 ከአርሹ በላይ መግቢያ   ክፍል አንድ ❶ ተከታታይ ፁሁፍ ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው። እናመሰግነዋለን። በሱም እንታዛለን። ምህረቱንም እንጠይቀዋለን፡፡ ከነፍሶቻትን ተንኮልና ከክፉ ምግባሮቻችን በአላህ እንጠበቃለን። አላህ ያቀናውን የሚያጠመው የለም። አርሱ ያጠመመውን የሚያቀናው የለም። ከአየውጭ ተጋሪ ከሌለው አላህ በስተቀር እውነተኛ አምላክ እንደሌለ እመስከራለሁ። መሐመድ የአላህ ባሪያውና መልእከተኛው እንደሆኑ እመስክራለሁ። በመቀጠል ከንግግር ሁሉ በላጩ የአላህ ንግግር ነው። ከፍኖት ሁሉ በላጩ የሙሐመድ ፍኖት ነው። ከነገር ሁሉ መጥፎ መጤ ፈሊጦች ናቸው። መጤ ፈሊጦች ሁሉ ከንቱ ፈጠራዎች ናቸው። ክንቱ ፈጠራዎች ሁሉ ወደ እሳት ናቸው። የአላህ ከዐርሹ በላይ መሆን ብዙ አይነት ማስረጃዎች የመጠብት፣ የጥንቱ አበው ትውልዶች የተጓዙበት፤ ሃይማኖቶች በጋራ የሚስተጋቡት፣ የሰው ልጅ ተፈጥሮ የታነፀበት ሐቅ ነው። እውነቱ ከፀሐይ የጎላ፣ ከመስታወት የጠራ፣ ከተራራ የፀና ከመሆኑም ጋር ተወናብደው የሚያወናብዱ መጤ አንጃዎች የተከሰቱት ግን ገና ድሮ ነው። የሃገራችን ሰፊው ህዝበ - ሙስሊም በዚህ ረገድ የእምነት መንጋደድ የለበትም። የአላህን በሰማይ መሆን ለማወቅ አስተማሪ አያሻውም። በአራቱም አቅጣጫ ተጉዘን ከህፃን እስከ አዛውንት ብንጠይቅ ይህን እምነት ሳይናወጥ እናገኘዋለን። ይህ የሆነው ግን በካይ አስተሳሰብ የሚያራምዱ ሃይሎች ሳይኖሩ ቀርተው አይደለም። በአንድ ወይም በሌላ ምክንያት እኩይ አስተሳሰባቸውን ከተቋማት አጥር አውጥተው ወደ ህዝብ የማውረድ ትኩረታቸው ለዜሮ የቀረበ ስለነበረ እንጂ ዛሬ ትላንት አይደለም፡፡ ከአመታት በፊት ጀምሮ በመንግስት ያልተቆጠበ ድጋፍ እየተመሩ ሃይል የተቀላቀለበት ስብከታቸውን ያጧጧፉት አሕባሾች በቀዳሚነት የሚያስተጋቡት መፈከር የአላህን ከሰማያት በላይ መሆን ማስተባበል እንደሆነ የአደባባይ ሚስጥር ነው። ቀደም ብሎ በድብቅ ሲሰጥ የነበረው ስብከት በታጠቀ ኃይል ታጅበው ሀሮማያ ከተማ ላይ ፊሽካውን ከነፉ ወዲህ በከልል ዋና ከተሞች፤ ቀጥሎም በጉልበት በሚነጥቋቸው መስጂዶችና መድረሳዎች አማካኝነት ሰፊ የብዥታ ዘር ዘርተዋል። ቀላል የማይባል ህዝብ ግራ ተጋብቷል። ህዝባችን ቀፎው እንደተነካበት ንብ 'ሆ ብሎ የተነሳባቸው የነ ሃጋይ ኤርሊከን ቡራኬና የመንግስትን ያገጠጠ ጣልቃ ገብነት አይቶ እንጂ የእውነት ጥመታቸውን በውል ተረድቶ፣ ብዥታቸውን ለይቶ አልነበረም። ከርእሱ አሳሳቢነት አንፃር ያለንበት ከባቢ አደጋ ያጠላበት በመሆኑ ችግራችንን በሚመጥን መልኩ የወገናችንን ንቃተ ህሊና ከፍ ለማድረግ ሰፊ ስራ ይጠበቅብናል። ስለሆነም ህዝባችንን ከነዚህ አውዳሚ ከፍሎች እምነቱን ለመጠበቅ ያልተቆጠበ ስራ መስራት ሃላፊነት ከሚሰማው ሙስሊም የሚጠበቅ ሲሆን ጥሩ ውጤት ለማግኘትም ሁለንተናዊ ርብርብ ይጠይቃል   አሕባሾችና መሰሎቻቸው “አላህ ከዐርሽ በላይ ነው" የሚለው እምነት በኢብኑ ተይሚያ ዳብሮ በሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብ የተሰራጨ የ“ወሃቢያ እምነት” አድርገው እንደሚያስቡት ህፃን አዋቂው ዘንድ ይታወቃል በዚህ ስራዬ ውስጥ ለነዚህ ሃሰተኞች ሰበብ ላለመስጠት የሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብ ቀርቶ የኢብኑ ተይሚያና የተማሪዎቻቸውን ንግግሮችም _ አላካተትኩም ይቀጥላል ◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉ https://t.me/+ZKXkcQYiRdcyMDFk https://t.me/+ZKXkcQYiRdcyMDFk
Show all...
ከአርሹ በላይ pdf ኢንሻአላህ ኪታቡን ለማናገኘ በተለይ አውሮፓ ሀገራቶች እንድሁም በከፊል አረብ ሀገራቶች እና በገጠር ለሚሰሩ ወንድሞች pdfን ሙሉውን በቅርቡ አዘጋጀተው ይለቁልናል ይህ ከላይ ያለው ግማሽ ነው እህቶች ከኪታባቸው ቀርፀው የላኩልኘን ለራሴም ለማንበብ እንድመቸኘ ባንድ ሰብሰብ ያደረኳቸው ገፆች ናቸው ሽፋኑን ብቻ ነበር በየፕሮፋይል ላይ ተሰቅሎ የማውቀው ለመጀመሪያ ከመግቢያው ራሱ ሳነበው በጣም ነው የጎጎሁት ኪታቡንማገኘት የምትችሉ ግዙት ተነቦ የማይጠገብ መፅሀፍ ነው ይህ ኪታብ በየቤታችን ሊኖር ይገባል
Show all...
ከአርሹ በላይ PDF_.pdf7.94 MB
መንዙማ እዉነታዉ፣ አደጋዎቹ እና መዘዞቹ የመፅሀፉ ፀሀፊ ኡስታዝ ሳዳት ከማል (አቡ መርየም) ይቀጥላሉ pdfቹ ጠብቁኝ ኪታብ ለሌላቹህ
Show all...
4_5987777674456600062_240403_072101.pdf2.44 MB
አላህን ማወቅ_240403_072748.pdf3.61 MB
አልበያን_ጀምዒያ፣_ሱሪና_የተብዲዕ_ህግጋት_240403_161652.pdf2.05 MB
Tewhide and Shirk_240403_162346.pdf3.04 MB
Photo unavailableShow in Telegram
እነዚህን የሽርክ ማውደሚያ ኪታቦች እና ሌላም የፈለጋቹህ ሳዑድ የትኛውም ቦታ ኡስታዝ አቡ ሙስሊምን ጠይቁት ያመጣል
Show all...
የልጆች ተርቢያ ትኩረት ሊሰጣቸው ከሚገቡ ነገራቶች ትልቁን ቦታ የሚይዘው ነው ልጆች የዱኒያ ጌጦች ለመጨረሻውም አለም ሶደቀቱል ጃሪያ የሁለት ጥንዶች አብሮ ለመዝለቀ ሰበብ የሚሆኑ ቤት አድማቂ ናቸው በልጆቻችን ላይ ትኩረት ካልሰጠን ዱኒያችንንም አኼራችንንም ሊያበላሹብን ይችላሉ ልጆች የሚያድጉት የቤተሰቦቻቸውን ሁኔታ ወርሰው ሲሆን ከነሱ ውስጥ እናት ትልቁን ቦታ ትይዛለች አዎ እናት ናት። በዚህ ጉዳይ አንዳንድ ነገራቶችንአ እንወያያለን ◉◉◉◉ ቻናላችንን ይቀላቀሉ ➴➴➴ https://t.me/+ZKXkcQYiRdcyMDFk
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.