cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Kidi Poem

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
178
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የልቤን ስብራት ባንተ አንዳልጠግናት የኔ ማትሆንበት ምክንያቱ ብዙ ነው 😔
Show all...
.....እነሆ ዘነበ..... ግጠም ግጠም አለኝ ፥ አመሌ ተነሳ ዳሩ ምን ያረጋል... 'ሚፃፍ ሀሳብ አጣሁ ፥ ውሃ የሚያነሳ! እንግዲህ አዝናለሁ ... ለብዕር ረሃቤ ፥ ነገር ልበላ ነው🙊 የዛሬ ሶስት አመት ... እሁድ እለት ምሽት ... ያደርሽው ከማን ነው?? ------------//------------- Joined https://t.me/kidipome00
Show all...
የዜግነት ቀብር (በላይ በቀለ ወያ) 👉አብረን እንዘምር . . የዜግነት ቀብር፣ በኢትዮጵያችን በዝቶ ታየ ግፍ ጥላቻ ፣ ዳር እስከዳር ጎልቶ ለበቀል ለበደል ፣ ለህዝቦች ባርነት በአረመኔዎች እጅ ፣ ታርደናል በአንድነት መሠረተ በቀል፣ ፍቅር እያዘመረን ህዝቦች ነን በሴራ፣ ጅምላ የሚቀብረን ድርቅ የርሀብ መድረክ፣ ጦርነት ማያጣት የተፈጥሮ ገብያ፣ ሒያጅ መጪው ሚሸጣት እንጠብቅሻለን፣ ሞተን በየተራ ኢትዮጵያችን ኑሪ፣ እኛ ለአንቺ እንፍራ! ➕ ቀ ላ🀄️ ል➘➘➘ https://t.me/kidipome00 ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ✍በላይ በቀለ ወያ
Show all...

"እንቁላሉ ስንት ስንት ነው?" ስትል ጠየቀቻቸው… "አንዱ እንቁላል 4 ብር ነው " ልጄ በማለት መለሱ፣ እማማ… "አምስቱን እንቁላል በ10 ብር ልወሰደው?…" ስትል ደግማ ጠየቀቻቸው "አይጎዳኝም ብለሽ ነው ልጄ?"…በማለት ደከም ባለ ድምፅ መለሱላት… "ከፈለጉ ይሽጡ፣ ካልፈለጉ ግን በቃ መሄዴ ነው…" አለች፣ ጠንከር ባለ ድምፅ… እማማ ትንሽ አሰቡና ቀና ብለው አይተዋት… "እስካሁን ምንም አልሸጥኩም፣ ባያዋጣኝም እንደ መጀመሪያ ገድ ልቁጠረውና ልሽጥልሽ፣ የፈለግሺውን ያህል እንቁላል በፈለግሺው ዋጋ ውሰጂ…" ሲሉ በደከመ ድምፅ ተናገሩ… #ዘንቢሏን አውጥታ 5 እንቁላል መርጣ አስገባች፣ ከበርካታ 100 ብሮች መካከል ነጠላ 10 ብር አውጥታ ወርውራላቸው እየተጣደፈች የሚያምረው ዘመናዊ መኪናዋ ውስጥ ገባች…የአሸናፊነት ስሜት ተሰምቷታል… … #ከጓደኛዋ ጋር ወደ አንድ ዘመናዊ ሬስቶራንት ገብተው የሚፈልጉትን አዘዙ…ትንሽ በልተው ብዙ አተረፉ። ተዝናኑ። ሂሳቡ ሲመጣ ቢሉ ላይ 1420 ብር ይላል ። ከቦርሳዋ ውስጥ 1500 ብር አውጥታ ሰጠች ። መልሱን ለሪስቶራንቱ ባለቤት ቲፕ እንዲሆነው ነግራው ወጥተው ሄዱ… … ይህ ድርጊት ለሬስቶራንቱ ባለቤት አዲስ አይደለም፣ ለእንቁላል ሻጮ ግን አስደንጋጭና ልብ ሰባሪ ነው… … #ጥያቄው ይህ ነው… ※ከድሆችና ከምስኪኖች የሆነ ነገር ስንገዛ የበላይነታችንን (ጉልበታችንን) ለማሳየት የምንጥረው ለምንድን ነው? የእኛን እርዳታ ለማይፈልጉትስ ቸር ሆነን ለመታየት ለምን እንፈልጋለን? … #አንድ ጊዜ ከታች የተፃፈውን ማንበቤ ትዝ ይለኛል… 🧔‍♂አባቴ ብዙ ጊዜ መንገድ ላይ የተለያዩ ነገሮችን ከሚሸጡ ሰዎች ከጠየቁት ዋጋ አስበልጦ በመክፈል እቃዎችን ይገዛ ነበር። ብዙ ጊዜ የሚገዛቸው ነገሮች የማይጠቀምባቸው ቁሳቁሶች ነበሩ። ቢሆንም ከተገቢው ዋጋቸው ጨመር አድርጎ ነበር የሚገዛቸው። አንድ ጊዜ አባቴን እነዚህን የማይጠቀምባቸውን ነገሮች ለምን ከዋጋቸው በላይ አስበልጦ እንደሚገዛቸው ጠየኩት። እንዲህ ሲል መለሰልኝ… "ልጄ …ይህ ማለት የሰዎችን ክብር ሳይነኩ ቸርነት ማድረግ ማለት ነው…" አስተውለነው ይሆን? ትርጉሙን? SHARE https://t.me/kidipome00
Show all...

textuan sitay fegeg malet kejemerk block adrgat baba https://t.me/kidipome00
Show all...
ቅለት ይመዘናል ሹራብ አይሉት ነገር አልቆ የነተበ ሱሪውም አድጎበት እርሱ ላይ የጠበበ አንጥልጥሉ የወጣ ነጠላ የተጫማ የፊት ወዙን ያጣ መልኩም የገረጣ በጎዳናው መኃል ሚዛን ሚዛን ይላል በተራበ አይኑ ተመዛኝ ይቃኛል። በልቶ ያግበሰበሰው ኑሮ የመጠጠው እኩል ተሰልፎ ሊመዘን ይነጉዳል ከአንድ ብሩ ጋር ሀገሬው ደግ አይደል¡ መቶ ሺህ ሚያወጣ ንቀት ይለግሳል። ሚስጥሩ ሳይገባው ልመዘን የሚልም ክብደቴን ለካኝ ሲል በሚዛን ብቆምም በመዛኙ አይኖች ንቀትን በማየት ይለካል ቅለትም፤ የተራበው መዛኝ በልቶ ለማደር ሲል መናቁ ስያቆስለው አንጀቱ ብቃጠል በአንድ ብር ብቻ ዋጋውን ሳይጨምር የክብደት ተለኪን ቅለት ይመዝናል። Joined https://t.me/kidipome00
Show all...
አሸዋው የማን ነው? አለቱስ የእግዜር? ቤት ስሩ ለማለት ምንድን እንዲህ ማሴር? ፨ «...አለቱ አይበገር ቢገፋ፣ ላይፈርስ ሚያለፋ፣ ፨ «...አሸዋ እፍፍ ናት፣ ብንን ናት፣ የነፋስ ድል እራት፣ በእርሷ ታዛ ስታድር፣ “መፍረስን ግን ፍራት”! ታዲያ ተናናነቀኝ በቀኝ መልስና ጥያቄ፣ ይገለጣል ቢሉኝ፣ መገላለጥ ሆነ፣ ማደሪያዬን ፍቄ! «...አለት ነኝ አልነቃነቅም ብል አፌን ሞልቼ፣ ፈራሽ ነኝ ለንፋስ ብል ግፊት ሸሽቼ፣ ነፍሴን ምን ሊጠቅማት? መኖሯን ነው የቀማት! ከአለት ካ'ሸዋ አልተሰራም ቤቴ.. ከምን? ለሚሉኝ ግን ለመመለስ ፈራው፣ አሸዋውስ ነበር ከቤቴ የተሰራዉ ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! https://t.me/kidipome00 https://t.me/kidipome00
Show all...

#ርዕስ_አልባ_ግጥም . . አንድም መሃል ኗሪ ቆላም ሁኑ ደጋ፣ ሚስጥራት ከታቢ ወይ ሁኑ ወሉ ጋ። . . ብቻ................ የድሃ እንባ ያዘለ የደም ዶፍ እስኪጥል፣ ነፍሳት የቀጠፈ ህይወት እስኪቀጥል። . . በአርምሞ ኑሩ እንጂ ምንም አትበሉ፣ ይልቅ ምድር ትልማ ችግኙን ትከሉ። ✍ ዓቢይ ( @abiye12 ) ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! https://t.me/kidipome00
Show all...
#ርዕስ_አልባ_ግጥም . . አንድም መሃል ኗሪ ቆላም ሁኑ ደጋ፣ ሚስጥራት ከታቢ ወይ ሁኑ ወሉ ጋ። . . ብቻ................ የድሃ እንባ ያዘለ የደም ዶፍ እስኪጥል፣ ነፍሳት የቀጠፈ ህይወት እስኪቀጥል። . . በአርምሞ ኑሩ እንጂ ምንም አትበሉ፣ ይልቅ ምድር ትልማ ችግኙን ትከሉ። ✍ ዓቢይ ( @abiye12 ) ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19
Show all...
0.52 KB