cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የሆሳዕና ልጆች ህብረት

ወቅታዊና ተዓማኒነት ያለው መረጃ ምንጭ

Show more
Advertising posts
226
Subscribers
No data24 hours
+87 days
+730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

"አንዱ ሰለ ሁሉ ሞተ" (2ኛ ቆሮ ም 5:14) ለመለው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለቱ መታሰቢያ ዕለት በሰላም አደረሳቹ እየልን.. የሆሳዕና ልጆች ህብረት ከወዲሁ መልካም በዓልን ይመኛል። የሆሳዕና ልጆች ህብረት
Show all...
ክርስቶስ ስለዘላለማዊነት ያስተማረበት የመጨረሻው ምሽት። እውነት እውነት እላችኋለሁ  በእኔ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት ያገኛል የሆሳዕና ልጆች ህብረት
Show all...
👍 2 2
🎴British Council🎴🚩Salary: 71,454.00 ETB per month plus benefits ▪️Job Position - Customer Service and Sales Manager ▪️Education:University Degree or degree-level (level 5 or above) ▪️Find More Details here           💧💧💧💧💧 https://elelanajobs.com/job/british-council-may-1-24/ ▪️Deadline: May 14/24
Show all...
በሻምፒየንስ ሊጉ ግማሽ ፍፃሜ ዶርትመንድና ፓሪስ ሴንት ጀርሜይን ይፋለማሉ #Ethiopia | የጀርመኑ ቦርሺያ ዶርትመንድና የፈረንሳዩ ፓሪስ ሴንት ጀርሜይን በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታቸውን ዛሬ ምሽት ያካሂዳሉ፡፡ ጨዋታው ከምሽቱ 4 ሰዓት በዶርትመንድ ሜዳ ሲገናል ኤዱና ፓርከ የሚካሄድ ሲሆን÷ የመልሱ ጨዋታ ደግሞ በፓሪስ ፓርክ ደ ፕሪንስ የሚካሄድ ይሆናል፡፡ ትናንት ባየርን ሙኒክ እና ሪያል ማድሪድ በአሊያንዝ አሬና ያደረጉት የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡ የባየርን ሙኒክን ግቦች ሌሮይ ሳኔ እና ሀሪ ኬን ሲያስቆጥሩ÷ የሪያል ማድሪድን ግቦች ደግሞ ቪኒሽየስ ጁኒየር ከመረብ አሳርፏል፡፡
Show all...
📖.ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል። 1ኛ ዮሃንስ 2፥17 ✍️,አሁን የምታዩት ነገር ሁሉ እንዲያልፍ ተወስኖበታል፨ ይህ የማያልፍ ለዘላለም የሚኖር የሚመስለው አለም ያልፋል፨ ይህ ብልጭልጩ ነገር ሁሉ አንድ ቀን ያልፋል፨ አለም የምንተማመንበት ዘለቄታዊ ነገር አይደለም፨ አለም ተስፋ የምናደርገው ቋሚ ነገር አይደለም፨ ሰማይና ምደር ስለሚያልፉ የእግዚአብሄር ቃልና የእግዚአብሄርን ቃል የሚያደርጉ ብቻ አያልፉም፨ 📖,ሰማይና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም። ማቴዎስ 24፥35 ✍️,ሰማይና ምድር ያልፋሉ የእግዚአብሄር ቃልና በእግዚአብሄር ቃል የተሰሩ ነገሮች አያልፉም፨ በእግዚአብሄር ቃል ያለተሰሩ ነገሮች ሁሉ ሊለፋባቸው የሚገቡ ቋሚ ነገሮች አይደሉም፨ 📖ለሚጠፋ መብል አትሥሩ፤ ነገር ግን ለዘላለም ሕይወት ለሚኖር መብል የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ሥሩ፤ እርሱን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና። ዮሃንስ 6፥27 አለምና ምኞቱ ያልፋሉ የእግዚአብሄር ቃልና የማይታየው ነገር ሁሉ አያልፍም፨ 📖,የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 4፥17-18 አለምና ምኞቱ ያልፋሉ  በእግዚአብሄር ፈቃድ የተደረገ ነገር ብቻ አያልፍም፨ 📖,በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፥ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይቀልጣል፥ ምድርም በእርስዋም ላይ የተደረገው ሁሉ ይቃጠላል። 2ኛ ጴጥሮስ 3፥10 አለምና ምኞቱ ያልፋሉ በእግዚአብሄር ቃል መሰረት የተገነቡ ስራዎች ብቻ ይፀናሉ፨ 📖,ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፥ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ማንም ግን በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ ቢሆን በብርም በከበረ ድንጋይም በእንጨትም በሣርም ወይም በአገዳ ቢያንጽ፥ የእያንዳንዱ ሥራ ይገለጣል፤ በእሳት ስለሚገለጥ ያ ቀን ያሳያልና፥ የእያንዳንዱም ሥራ እንዴት መሆኑን እሳቱ ይፈትነዋል። ማንም በእርሱ ላይ ያነጸው ሥራ ቢጸናለት ደመወዙን ይቀበላል፤ የማንም ሥራ የተቃጠለበት ቢሆን ይጎዳበታል፥ እርሱ ራሱ ግን ይድናል ነገር ግን በእሳት እንደሚድን ይሆናል። 1ኛ ቆሮንቶስ 3፥11-15 የሆሳዕና ልጆች ህብረት
Show all...
👍 2
#እግዚአብሔር_እየጠበቀ_ያለው_የሞታችን_ቀን_ሳይሆን_የንስሀችን_ቀን_ነው.. #ተስፋ ስትቆርጡ..አጣብቅኝ የሕይወት ፈተና ውስጥ ስትገቡ ሞት ማምለጫ አይደለም፤  ሞት መሸሸገግያ አይደለም፤ ራስን ማጥፋት ማምለጫ አይደለም ለምን ትሞታለህ? #ለምን እራስን ለማጥፋት ታስባለህ? #ጴጥሮስ ኢየሱስ ካደው ድሁዳም ኢየሱስን ሸጠው፡፡ #ጴጥሮስ ተፀፅቶ በንስሀ ወደ ጌታ ስመለስ #ይሁዳ ግን ተፀፅቶ እራሱን አጠፋ #በእርግጠኝነት ይሁዳ ጥፋቱን ካመነ ቦኃላ ራሱን ከማጥፋት ይልቅ ንስሀ ቢገባ ኖሮ መስቀል ላይ ተሰቅሎ እንኳን የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ያለው የምህረቱ ጌታ ይቅር ይለው ነበር #ይሁዳ ግን ዕድሉን አልተጠቀመም #ይሁዳ ሕይወቱ አጣብቅኝ ሁኔታ ውስጥ ስትገባ በንስሀ ከመመለስ ይልቅ ራሱን ማጥፋት ምርጫው አድርጎታል፡፡ #ዛሬ በሃጥያት ወድቃችሁ ሊሆን ይችላል፤ ከባድ የሕይወት ማዕበል ውስጥ ገብታችሁ ሊሆን ይችላል ዛሬም እግዚአብሔር እናንተ መፈለጋችሁን አላቆመም፤ መመለሳችሁን ወደ እርሱ መቅረባችሁ ይጠብቃል፡፡ #በሕይወታችሁ ከባድና አጣብቅኝ ፈተና ውስጥ ስትገቡ መሸሸገግያችሁ ወደ ጌታ ይሁን #እርሱን በድላችሁ ከሆነም እንኳን እንደ ጴጥሮስ መሸሸግያችሁን እርሱን ብቻ አድርጉ፡፡ #ዳዊትን እግዚአብሔር የልቤ ሰው ያለው ሃጥያትን ስለማይሰራ አይደለም በሃጥያት ስወድቅም፤ ስሳሳትም መሸሸጊያውን ወደ እግዚአብሔር ብቻ ስለሚያደርግ ነው፡፡ እግዚአብሔር እየጠበቀ ያለው የሞታችን ቀን ሳይሆን የንስሀችን ቀን ነው ወደ  እርሱ የምንቀርበበት ጊዜ ነው እየጠበቀ ያለው ወደ እርሱ ለመቅረብም ወደ እርሱ ለመመለስም ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው እንመለስ፡፡ ኢየሱስ ከዘላለም ሞት ያድናል የሆሳዕና ልጆች ህብረት
Show all...
👍 1
በዓለም አቀፍ ደረጃ ያጋጠሙ ችግሮች ኢትዮጵያ በቅርቡ የተቀላቀለችውን ብሪክስን አዋልዷል-አቶ አህመድ ሺዴ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያጋጠሙ ችግሮች ኢትዮጵያ በቅርቡ የተቀላቀለችውን ብሪክስን ማዋለዱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ገለጹ። በተለይም የአፍሪካ መቀመጫ የሆነችው እና አፍሪካን እርስ በእርስ በማገናኘት ረገድ በአፍሪካ ቀዳሚ የሆነችው ኢትዮጵያ ብሪክስን መቀለቀሏ ለድርጅቱ ተጨማሪ አቅም መፍጠሩን በአለም ኢኮኖሚ ፎረም ላይ አብራርተዋል። ለዚህም የአፍሪካ ኩራት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለአፍሪካ እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ አንስተዋል። በብሪክስ የታቀፉ ሀገራት የውጭ ኢንቨስትመንትን በመሳብ፣ በቴክኖሎጂ ትብብር፣ በንግድ እንዲሁም በአቅም ግንባታ ረገድ በርካታ ሥራዎችን በጋራ ማከናወን ይችላሉም ብለዋል። ኢትዮጵያ የአለም ሰላምን በተመለከተ ከዚህ ቀደም ለረጅም ጊዜ የምታራምደውን "ሰላምን በዘላቂ ውይይት መፍታት" የሚለውን ነው ያሉት አቶ አህመድ ሺዴ አሁን በዩክሬን፣ በጋዛ፣ በሱዳን እንዲሁም በሌሎች የአለማችን ክፍሎች ያሉ ግጭቶች በሰላማዊ ውይይት መፍታት እንደሚገባ አሳስበዋል። በአንዱ የአለማችን ክፍል የሚከሰት የሰላም መደፍረስ፤ በሁለም የአለም ክፍል ላይ ይብዛም ይነስም ተጽዕኖ እንዳለው ነው ያነሱት። ለዚህም የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት፤ የሸቀጦችን ዋጋ በማናር ረገድ ኢትዮጵያን ጨምሮ የአለማችን ሀገራት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማሳደሩን ለአብነት አንስተዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት ለአካባቢያዊ እና ቀጠናዊ ሰላም እየተጫወተ ያለው ሚና፤ ከሀገሪቱ ፖሊሲ የተቀዳ መሆኑን ለአለም ኢኮኖሚ ፎረም ታዳሚያን አብራርተዋል። የሆሳዕና ልጆች ህብረት
Show all...
መኪናችንን ሊጎዱ የሚችሉ 3 የዳሽ ቦርድ ማስጠንቀቂያ ምልክቶች ፔጃችንን እንደዚህ አይነት ከመኪና ጋር የተገናኙ ወሳኝ ወሳኝ መረጃዎችን ስለሚለቅ ፔጃችንን ላይክ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ 1 ሞተር ላይ ከፍተኛ ሙቀት መኖሩን የሚያሳይ የዳሽ ቦርድ ማስጠንቀቂያ ምልክት 2. የሞተር ዘይት ግፊት መቀነሱን የሚያሳይ የዳሽ ቦርድ ማስጠንቀቂያ ምልክት 3.ባትሪ ቻርጅ እያደረገ አለመሆኑ የሚያሳይ የዳሽ ቦርድ ማስጠንቀቂያ ምልክት የሆሳዕና ልጆች ህብረት
Show all...
👍 1
መኪናችንን ሊጎዱ የሚችሉ 3 የዳሽ ቦርድ ማስጠንቀቂያ ምልክቶች ፔጃችንን እንደዚህ አይነት ከመኪና ጋር የተገናኙ ወሳኝ ወሳኝ መረጃዎችን ስለሚለቅ ፔጃችንን ላይክ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ 1 ሞተር ላይ ከፍተኛ ሙቀት መኖሩን የሚያሳይ የዳሽ ቦርድ ማስጠንቀቂያ ምልክት 2. የሞተር ዘይት ግፊት መቀነሱን የሚያሳይ የዳሽ ቦርድ ማስጠንቀቂያ ምልክት 3.ባትሪ ቻርጅ እያደረገ አለመሆኑ የሚያሳይ የዳሽ ቦርድ ማስጠንቀቂያ ምልክት የሆሳዕና ልጆች ህብረት
Show all...
👎 1
ሚያዝያ 23/2016 ዓ.ም ሆሳዕና የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካሞች ማዕድ አጋሩ። የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ አካላት ከ1 መቶ ሺ ብር በላይ  የሚገመት ድጋፍ በማሰባሰብ የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ50 ሰዎች የተለያዩ ድጋፎችን አበርክቷል። በድጋፉ መርሃ ግብር የተገኙት የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሀብታሙ አበበ ዩኒቨርስቲው በማህበረሰብ አገልግሎት ለአካባቢው ነዋሪዎች የተለያዩ ድጋፎችን እንደሚያደረግ ተናግረው። በበዓላት አቅመ ደካሞችን ለማገዝ  የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ ገንዘብ በማሰባሰብ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው በዓልን በደስታ በቤታቸው እንዲያከብሩ ካላቸው በመቆረስ መልካም ተግባር በየጊዘው እንደሚፈጽሙ ገልፀዋል። ሁሉም በየተሰማራበት ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ካለው ላይ ማካፈልን ባህል ማድረግ  እንደሚገባ የገለፁት ፕሬዝዳንቱ። ዩኒቨርስቲው በቀጣይ የተለያዩ ችግር ፈች ፕሮጀክቶች በመቅረጽ  ድጋፍ ከተደረገላቸው መስራት የሚችሉ ሴቶችን በመለየት በዘላቂነት ራሳቸውን  እንዲችሉ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክተር ዳይሬክተር ወ/ሮ አስቴር አዋኖ  የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከግቢው ማህበረሰብ እና ከሌሎች የህበረተሰብ ክፍሎች ገንዘብ በማሰባሰብ ደጋፊ  ለሌላቸው ሰዎች ማዕድ ማጋራታቸውን ገልፀውልናል። ዳይሬክቶሬቱ በእናቶች ህፃናትና ወጣቶች ተጠቃሚነት ላይ በትኩረት እንደሚሰራ በዚህም ከተቋሙ ሰራተኞች ወራዊ መዋጮዎች በመሰብሰብ እና በበዓላት ደግሞ ህብረተሰቡን በማሳተፍ ተጨማሪ ገንዘብ በማሰባሰብ ለአቅመ ደካማ እናቶች ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ በዓላትን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካሞች ማዕድ እንደሚያጋራ የተናገሩት በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ የህዝብ ግንኙነትና አለም አቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ገዴ በኢድ በዓልም ለሙስሊም ወገኖቻችን ዩኒቨርሲቲው ማዕድ ማጋራቱን ገልፀውልናል። ዩኒቨርሰቲው ከመማር ማስተማር በተጓዳኝ በማህበረሰብ አገልግሎት የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ፣ የትምህት ቤት ግንባታና ቁሳቁስ ድጋፍ ፣ በመንገድ መሠረተ ልማት ፣ የተለያዩ የእንስሳትና ሰብል ምርጥ ዘር በማባዛት ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግና በሌሎች በርካታ አገልግሎቶች ህብረተሰቡን እንደሚያገለግል በመግለጽ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ከተለያዩ ግለሰቦች ገንዘብ በማሰባሰብ በዛሬው ዕለት ከ1 መቶ ሺ ብር በላይ በማሰባሰብ ለ50 ሰዎች የፋሲካን በዓል ምክንያት በማድረግ የዱቄት ፣ ዘይት ፣ ሽንኩርት ፣ የእንቁላልና የብርድ ልብስ ድጋፍ ማድረጉን ነግረውናል። ድጋፉን ያሰባሰቡት የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ እንደተናገሩት ለወገን ደራሽ ወገን በመሆኑ ሳይተፋቸው እናቶች በበዓል በባዶ ቤት እንዳያሳልፉ ከፕሬዝዳንቱ ጀምሮ ሁሉንም በማሳተፍ አቅም በፈቀደ ይህን ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረው ደግነት ለራስ በመሆኑ ሁሉም ጎረቤቱን በበዓላት እንዲያይ መልዕክት አስተላልፈዋል። ድጋፍ የተደረገላቸው የአካባቢው ነዋሪዎች በዓልን በደስታ እንዲያሳልፉ ዩኒቨርስቲው ላበረከተላቸው ስጦታ አመስግነዋል።ዘገባው የሀዲያ ዞን መ/ኮ/ጉ/መምሪያ ነው።
Show all...