cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Kurulus Osman

Voice of Muslims የሙስሊሞች ድምፅ

Show more
Advertising posts
209
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#ታላቅ_የኸይር_ስራ_ጥሪ 📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣 "ወደ ኸይር ያመላከተ የሰሪውን ያክል ያገኛል።" من دل علی خير فلہ مثل اخر فاعلہ (ረ.ዐ.ሰ) 📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚 🕌 ለረመዳን #10ሺ_ቁርአን ይዘን ወደ #ገጠራማው ጎንደር ( ወልቃይት ጠገዴ) እና አካባቢው ጉዞ እናደርጋለን። 🕌 በአካል ቁርአን መስጠት የምትፈልጉ 🕌 አድራሻችን አዲስ አበባ ቤተል ሳራ ህንፃ 4ተኛ ፎቅ 🕌 በዋትሳፕ ለማናገር 0947939484 #ታላቅ_የኸይር_ስራ_ጥሪ 🕌 ለረመዳን #10ሺ_ቁርአን ይዘን ወደ #ገጠራማው ጎንደር ( ወልቃይት ጠገዴ) እና አካባቢው ጉዞ እናደርጋለን። 🕌 በአካል ቁርአን መስጠት የምትፈልጉ 🕌 አድራሻችን አዲስ አበባ ቤተል ሳራ ህንፃ 4ተኛ ፎቅ 🕌 በዋትሳፕ ለማናገር 0947939484 🕌 በገንዘብ መርዳት የምትፈልጉ 1000183466918 CBE መጠቀም ትችላላችሁ 🕌 ለረመዳን #10ሺ_ቁርአን ይዘን ወደ ገጠራማው ጎንደር ( ወልቃይት ጠገዴ) እና አካባቢው ጉዞ እናደርጋለን። 🕌 በገንዘብ መርዳት የምትፈልጉ 1000183466918 CBE መጠቀም ትችላላችሁ ሙሃመድንጉስ አብዱ 🕌 ለረመዳን #10ሺ_ቁርአን ይዘን ወደ ገጠራማው ጎንደር ( ወልቃይት ጠገዴ) እና አካባቢው ጉዞ እናደርጋለን። ሙሃመድንጉስ አብዱ
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
የስብሰባ ጥሪ! ለ እስላማዊ ተቋማት (ማህበራት፣ ሙአሰሳ፣ ድርጅቶች) በሙሉ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 1207/2012 በተሰጠው ስልጣን መሠረት በስሩ የኢስላማዊ ተቋማት የምዝገባ አገልግሎት እንደሚሰጥ ይደነግጋል። በመሆኑም በኢስላማዊ ተግባር ላይ የተሰማራችሁ ድርጅቶች እና ማህበራት በሙሉ ተሳታፊ የምትሆኑበት በጠቅላይ ምክር ቤቱ በፀደቀው የኢስላማዊ ተቋማት የምዝገባና አገልግሎት መመሪያ ደንብ ዙሪያ የትውውቅ መድረክ ጠቅላይ ምክር ቤቱ አሰናድቷል:: ስለሆነም ጥር 25/ 2015 ዓ.ል ከቀኑ በ8:00 ሰዓት በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት መሠብሠቢያ አዳራሽ ከየድርጅቶቹ እና ከማህበራት የሚወከሉ 3 ሰዎችን በመላክ የውይይቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ጥሪውን ያስተላልፋል። ከኢስላማዊ ሠላምታ ጋር! የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ይከታተሉን | Follow us https://t.me/ethio_mejlis
Show all...
Kurulus Osman

Voice of Muslims የሙስሊሞች ድምፅ

Nega bulteni Endet aderachu Akam Nega_alehu Feyadha aleh wey
Show all...
ክፍል 165 a&b 🔗KURULUS OSMAN🖌 🔅quality HD🔆 📣አማረኛ ትርጉም📣 ➠ፊልምቤት ላላችሁ VIP ቻናላችንን በቅናሽ ይቀላቀሉ👉 @WASE_RECORDS_VVIP 🇪🇹ቻናላችንን ለማግኘት⤵️ @alparslan_buyuk_et
Show all...
Kurulus Osman 165.mp4637.17 MB
ክፍል 162 a&b 🔗KURULUS OSMAN🖌 🔅quality HD🔆 📣አማረኛ ትርጉም📣 ➠ፊልምቤት ላላችሁ VIP ቻናላችንን በቅናሽ ይቀላቀሉ👉 @WASE_RECORDS_VVIP 🇪🇹ቻናላችንን ለማግኘት⤵️ @alparslan_buyuk_et
Show all...
Kurulus Osman 162.avi407.21 MB
Kurulus Osman 163.avi445.91 MB
Kurulus Osman 164.mp4594.92 MB
በመጅሊስ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተይዞ የነበረው የጽዳትና ችግኝ ተከላ መርኃ ግብር መራዘሙን ተቋሙ አስታውቋል።
Show all...
ትክክል ከሰራሁኝ አግዙኝ ፣ ከተሳሳትኩ ደግሞ አቃኑኝ አዲሱ ፕሬዝዳንት ሀጂ ሽኽ ኢብራሂም ቱፋ # Ethiopia | የተረከብነው ሀላፊነት ከባድ ብቻ ሳይሆን የተወሳሰበም ጭምር ነው። ተቀዳሚው ስራችን የኡማውን አንድነት ማስጠበቅ ይሆናል፤ አኩርፈውን የራቁንንም ቢሆን ለማቅረብ የተቻለንን ያህል እንጥራለን። በአላህ ፍቃድ_ ዑለሞችን፣ ነጋዴዎችን፣ወጣቶችን፣ሴቶችን እና የተለያዩ የሙስሊሙ ማህበረሰብ አካላትን ማደራጀት የወደፊት ስራችን ይሆናል። በመጨረሻም ኸሊፋው አቡበከር ሲዲቅ _ ረዲየላሁ ዐንሁ _ ያሉትን እኔም ለመድገም አወዳለሁኝ " ትክክል ከሰራሁኝ አግዙኝ ፣ ከተሳሳትኩ ደግሞ አቃኑኝ " ። ) አዲሱ የመጅሊስ ፕሬዝደንት ሸ/ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ካስተላለፉት መልዕክት/
Show all...
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለቀጣይ 3 ዓመታት የሚመሩ ኃላፊዎች ተመረጡ 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 ከ3ዓመታት በፊት በሚያዚያ 23 ቀን 2011 የቀድሞውን የመጅሊስ የዑለማ ም/ቤትና የሥራ አመራር ቦርድ አባላትን የመረጠውና 300 አባለት ያሉት የሸራተኑ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ሐምሌ 11/2014 ባካሄደው 2ኛ ጉባኤ ለቀጣይ 3 ዓመታት መጅሊስን የሚመሩ አመራሮችን መርጧል። የምርጫ ሂደቱ የተካሄደው 5 የምርጫ አስፈጻሚዎች ተሰይመው በነርሱ መሪነት ሲሆን የየክልል ተወካዮች የሆኑ የጉባኤው ተሳታፊዎች ለየብቻቸው በተለያዩ አዳራሾች ዉስጥ ተሰብስበው ክልሎቻቸውን የሚወክሉ ተወካዮችን ከመረጡ በኋላ የተመራጮችና የመራጮች ዝርዝርን በማስፈር ቃለ ጉባኤው ላይ በመፈረም ነው።በዚሁ መሠረት በአጠቃላይ 30 አባላት ያሉት ጠቅላላ ጉባኤ አባላት ተመርጠዋል። ተመራጮችም በህዝቡ ፊት ለሕዝቡ አንድነት፣ጥቅምና ጉዳዮች በታማኝነት ለመሥራትና ህዝቡ የሚፈልገውን ካልሰሩለት ዉረድ ባላቸው ጊዜ ከስልጣን ለመውረድ ጭምር በሸሪዓ ፍ\ቤት አማካኝነት በአላህ ስም ምለው ቃለ መሀላ ፈጽመዋል። ቀጥሎም 30ዎቹ ተመራጮች ወደ ሌላ አዳራሽ በማቅናት ረጅም ዉይይት ካደረጉ በኋላ ከመካከላቸው 14 አባላት ያሉት ሥራ አስፈጻሚ መርጠዋል።በዚህም መሠረት:- 1. ሸኽ ሃጂ ኢብራሂም ፕሬዚዳንት – ከኦሮሚያ 2. ሸኽ አብዱልከሪም በድረዲን ተ/ም/ፕሬዚደንት – ከደቡብ ክልል 3. ሸኽ አብዱልአዚዝ አብዱልዋሊ- ም/ፕሬዚደንት– ከሶማሌ 4. ሸኽ ሃሚድ ሙሳ ዋና ፀሃፊ – ከአዲስ አበባ(በብሄር አማራ) 5. ሸኽ አብዱልሃሚድ – ከኦሮሚያ 6. ሸኽ እድሪስ አሊ – ከአማራ ክልል 7. ሸኽ መሃመድ አህመድ ያሲን– ከአፋር ክልል 8. ሃጂ ሙስጠፋ ናስር– ከሲዳማ ክልል 9. ሸኽ አልመርዲ አብዱላሂ – ከቤኒሻንጉል ክልል 10. ሸኽ ሁሴን ሃሰን– ከደቡብ ምዕራብ ክልል 11. ሸኽ ዛኪር ኢብራሂም – ከጋምቤላ ክልል 12. ሸኽ መሃመድ አሚን አያሽ – ከሀረሪ ክልል 13. ሸኽ አሚን ኢብሮ– ከድሬደዋ ከተማ 14. ኢንጂነር አንዋር ሙስጠፋ– ከትግራይ ናቸው። ተመራጮቹም በተመደቡበት ሥፍራ በታማኝነት ለመስራት ዳግም ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።ቀጥሎ በተያዘው መርሃ ግብር መሠረት ዛሬውኑ ለተመራጮች የቢሮ ርክክብ ተካሂዷል። የፌደራል መጅሊስ ጠቅላላ ጉባኤ ከ2 ወራት በፊት በአብላጫ ድምጽ አዲስ የሥራ አስፈጻሚ መርጦ እንደነበረ የሚታወስ ሲሆን በጊዜው የመጅሊስ ፕሬዝዳንት ሙፍቲ ሀጅ ዑመር ምርጫውን ህገወጥ ነው።ስልጣኑን አላስረክብም።» ብለው መግለጫ በመስጠታቸውና ረብሻ ለመፍጠር በመንቀሳቀሳቸው ህዝቡ የህግ የበላይነት እንዲከበር ሲጠይቅ ቆይቷል። በመጨረሻም መንግስት በጉዳዩ ላይ አቋም ለመያዝ ተቸግሮ ከቆየ በኋላ ከ2 ሳምንት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትሩና ሌሎች የመንግስት አመራሮች በተገኙበት ከሁለቱም ወገን 25 25 ተወካዮች በተገኙበት ከ3 ዓመታት በፊት ሁለቱንም ወገኖች(26 ዑለሞችንና 7 ቦርድ አባላትን) የመረጠው 300 ተወካዮች ከመላ ሀገሪቱ የተወከሉበት የሸራተኑ ጉባኤ ዳግም ተሰብስቦ «ይመራኛል» ያለውን አካል እንዲመርጥ በተቀመጠው አቅጣጫ መንግስት በጉባኤው ለተመረጠው አካል ህግ እንደሚያስከብር በመግለፅ እስከዚያ የአረፋ በዓልን በጋራ እንዲያከብሩ ለሁለቱ አመራሮች ምክሩን ለግሷል።በዚሁ መሠረትም የእንኳን አደረሳች የአረፋ በዓል መልዕክት በጋራ አስተላልፈዋል። በመንግስት ሚዲዎች ጭምር በተደረገው ጥሪ መሠረት የዛሬው ጉባኤ ከ300 የጉባኤው አባላት መካከል 261ዱ በተገኙበት ተካሂዷል።ሆኖም የአመራር ምርጫ እንደ አዲስ ይደረግ መባሉንና ምርጫው በሸራተኑ ጉባኤ አባላት የሚለውን የተቃወሙ፣የሞቱና ወደ ሀጅ የተጓዙ 39 የሚሆኑ አባላት በጉባኤው ሳይሳተፉ መቅረታቸው ተገልጿል። የጉባኤው አባላት የመረጣቸው የሥራ አስፈፃሚዎች ቢሮ ተረክበው ሥራ ጀምረዋል።በርካታ የጉባኤው ተሳታፊዎች መንግስት ለጉባኤው ስኬትና ጸጥታውን ለማስከበር ላደረገው ሚና እንዲሁም ነገሮች በተደጋጋሚ በሽምግልናና በመግባባት እንዲፈታ ከፍ ባለ ትዕግስት በመጓዝ የዛሬው ስኬት እንዲገኝ ላበረከተው ሚና መንግስት በበርካቶች በስፋት ተመስግኗል። በተለይ ደግሞ እለቱ በሀምሌ ወርና በሀምሌ 11 ቀን መካሄዱ እለቱን ልዩ ያደርገዋል።ምክንያቱም ሀምሌ ወር በዘመነ ኢህአዴግ ለድምፃችን ይሰማ ንቅናቄ መነሻ ሰበብ የሆነው የአሕባሽ ግዳጅ ጠመቃ የተጀመረበት እለት ሀምሌ 6 ቀን 2003፣«የአህባሽ ግዳጅ ጠመቃ ይቁምና መሪዎቻችንን መንግስት ሳይሆን እኛው እንምረጥ» በሚል በአወሊያ ተቃውሞ ሲያደርጉና ለሀምሌ 8 የሰደቃና አንድነት ዝግጅት ሲያደርጉ በአወሊያ ባደሩት ሙስሊሞች ላይ ሌሊት ጥቃት የተፈፀበትና መስዋእትነት የተከፈለበት ሀምሌ 6 ቀን 2004 ነበር። እንዲሁም «እምቢ ለመብቴ» ያሉትን ሙስሊሞችንና ተወካዮችን በሽብር በመወንጀል በይፋ ማሰር የተጀመረበትም ሀምሌ 12 ቀን 2004 ነበር። በተለይ ደግሞ ልክ በዛሬው እለት ሀምሌ 11 ቀን 2006 በሕዝበ ሙስሊሙ ላይ የጥቁር ሽብር ጥቃት የተፈጸመበት እለት ላይ የዛሬው የመጅሊስ ምርጫ መደረጉ እለቱን ታሪካዊ አድርጎታል። ዝግጅቱ በታላቁ የአንዋር መስጊድ ኢማም ሼህ ጠሃ ሙሀመድ ሃሩን አመካኝነት በቁርኣን ተከፍቶ በርሳቸው በዱዓ ተጠናቋል።ሼህ ጠሃ መሀመድ ሃሩንም አዲስ አበባን በመከል ለመጅሊስ ጠቅላላ ጉባኤ ከተነረጡት 30 አባላት አንዱ ሆነው ተመርጠዋል። እኔም እንደ ግለሰብ በመራጭነት፣በተመራጭነት ወይም በአስመራጭነት ሳይሆን ድምጽ መስጠት ከማይችሉት ተዛቢዎች መካከል እንደነበረ ሰው የዛሬው ምርጫ ሁሉም ክልል «ማን ይወክለናል?» በሚል ስሜት በዉይይት አጅግ በሰላማዊ፣ በመግባባትና በምክክር በተሞላበት መልኩ ተወካዮቻቸውን የመረጡበት ታሪካዊ ምርጫ በመሆኑ በመጀመሪያና ከሁሉ በላይ ፈጣሪያችንን አላህን ቀጥሎ ደግሞ መንግስትንና በሂደቱ ስኬት የተሳተፉትን ሁሉ ከልብ አመሰግናለሁ። በዚህ አጋጣሚ ሁላችንም ከአዲሶቹ ተመራጮች ጎን በመቆም ስኬታማ የስራ ጊዜ እንዲኖራቸውና ሕዝበ ሙስሊሙ የሚፈልገውን ሃይማኖታዊና የልማት ጉዳዮችን በመፈጸም ህዝቡን እንዲክሱ ሁላችንም ከጎናቸው በመቆም የየበኩላችንን እንድንወጣ ጥሪዬን አቀርባለሁ። ኡስታዝ አህመዲን ጀበል
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
የመጅሊሱ ቁልፍ ርክክብ በሰላም ተጠናቋል።
Show all...