1 492
Subscribers
-224 hours
-87 days
+1630 days
Posts Archive
መልዕክት ➊
⭐️ በፈተና ጊዜ የሚፈጠርን ጭንቀት ወይም ቴንሽንን ልንቆጣጠር የምንችልባቸው ዘዴዎች!
========================
⭐️ ፈተና የመፈተኛ ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ ነገር ነው::
⭐️ ከፈተና በፊት ይህን አይነቱን ከፍተኛ ውጥረት መቆጣጠር የምንችለበት መንገድ:-
--------------------------------
✅ ፈተና ሲመጣ መጠነኛ ውጥረት እና ጭንቀት ተፈጥሮአዊ እና ሁሉም ተፈታኝ ተማሪ እንደሚያጋጥመው መረዳት።
✅ ለፈተና ስንዘጋጅ አዎንታዊ እና በጎ ሀሳቦችን ማሰብ፡፡
✅ ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ እንጂ የኛ የህይወት ምዕራፍ ማብቂያ ወይም አጠቃላይ ችሎታችንን የሚያመላክት አይደለም ።
✅ ማወቅ ያለብን አንድ ነገር ቢኖር መሳሳትን አለመፍራት እና ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጅ መሆንን ነው ። እንዲሁም አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን።
✅ ከጓደኞቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ፡፡ ይህ ዘዴ ይበልጥ የማስታወስ ብቃታችንን እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያረጋል ። ከዚህም በተጨማሪ የተሳሳትነውን ነገር ድጋሚ እንድንከልስ እና እርማት እንድናረግ ያግዘናል።
✅ የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ መተኛት ። ይህም ጭንቀትን ይቀንስልናል፣ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
◆ በተጨማሪም የአቅማችሁን (የምትችሉትን) ያህል ጥረት አድርጋችኋልና የቀረውን ለአላህ መስጠት (በአላህ ተወኩል ማድረግ)!
➤ አላህ ሁሉንም ነገር እንዲያገራላችሁ ዱዓ (ፀሎት) ማድረግ!!
➤ ከሰዎች (ከጓደኞቻችሁ) ጋር ትንሽም ቢሆን ተጋጭታችሁ ከሆነ፤ ውስጣችሁ ሰላምና ደስታ እንዲሰማችሁ፣ በንፁህ (Fresh) አዕምሮ ፈተና ላይ እንድትቀመጡ እንዲያግዛችሁ፣ ጌታችን አላህ እንዲደሰትባችሁም ጭምር ከጓደኞቻችሁ ጋር ይቅር ተባባሉ። ይቅር መባባል ለልብ ነፃነትን ለአዕምሮ ደግሞ ጤናን ይሰጣልና❗️
▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬
አላህ ይርዳችሁ!
አላህ ለማህበረሰቡ የሚጠቅምና ቤተሰብ የሚያኮራ ውጤት ይስጣችሁ።
አላህ ሰዎች የሚያዝኑቧችሁ ሳይሆን በመልካም ነገራችሁ የሚደሰቱቧችሁ ያድርጋችሁ!
መልዕክት ❷
◆ ፈተና ከጀመርን በኋላ ማድረግ የሚገቡን ነገሮች (ፈተና ላይ እያለን) ❗️
◉ ወደ ፈተና ከመሄዳችን ቀደም ብለን ለፈተና የሚረዱንን መሳሪያዎች እና የመፈተኛ ቁሶችን ማዘጋጀት።
◉ አብዝተን ፈተናን እና የምናመጣውን ነጥብ ስሌት አለመገመት ።
🔰 ፈተና ስንጨርስ የተሳሳትነውን ጥያቄ አብዝቶ ማሰብ እና ሌላ ተማሪ መጠየቅ ጭንቀት ውስጥ ስለሚከተን ከዚህ ይልቅ እረፍት ማድረግ እና ለቀጣይ ፈተና መዘጋጀት ።
◉ በፈተና ጊዜ ድንገተኛ ጭንቀት እና ድንጋጤ ከገጠመን ወዲያው የምንሰራውን ገታ አድርገን በጥልቀት አየር በአፍንጫችን ስበን ወደ ሳንባ እያስገባን መልሰን ማስወጣት ይህንንም እስክንረጋጋ መደጋገም።
ከዚህ በመቀጠል የማረጋጊያ ቃላትን ለራስዎ መንገር::
◉ ፈተና በምንሰራ ጊዜ ግራ ያጋባንን እና እርግጠኛ ያልሆንበትን ጥያቄ በይለፍ ማቆየት እና ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ይህም ጊዜያችንን በአግባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። ነገር ግን ምልክት አድርገን ማለፍ፤
◉ በተመሳሳይ እርግጠኛ ያልሆልንበትን መልስ ላይ ተደናግጠን መሰረዝ እና መደለዝን መቀነስ ይህም ስንደነግጥ እና ስንጨነቅ የምናውቀውን መልስ ትተን ወደ ሌላ መልስ እንድሰጥ ስለሚያረግ መሰረዝና መደለዝን መቀነስ ።
◉ ፈተናውን ወደ ማገባደድ ስንደርስ በይለፍ ያስቀመጥናቸውን ግራ ያጋቡንን ጥያቄዎች ጥቂት አስበንበት መልስ መስጠት ፤ ካልሆነም ደግሞ ብልሀት ተጠቅመን የግመታ መልስ ሰጥተን ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ።
◉ በተደጋጋሚ ሰአት በቃን አልበቃን እያልን አለመጨነቅ።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
➚ ሁሉም ነገር አላህ ከወሰነው ውጭ እንደማይሆን እርግጠኛ መሆንና ፈተና ማለት ለጀነትና ለጀኃነም ማለፊያ ትኬት እንዳልሆነ እርግጠኛ መሆን።
▮ከኛ የሚጠበቀው የአቅማችንን ያህል ማድረግ ሌላውን ለአላህ መተው ነው‼️
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
◉ ወቅቱ የፈተና ወቅት በመሆኑ ተማሪዎች ይህን ማስታወሻ እንዲጠቀሙበት አሳስባለሁ።
🔰 አላህ ይርዳችሁ!
🔰 አላህ ውጤቱን ያማረ ያድርግላችሁ!
🔰 አላህ በናተው ጥረት ብቻ ሰይሆን በሱ (በአላህ) እዝነት መልካም የሆነ ውጤትን ይስጣችሁ!!
▮Source: ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
⭕️ መልዕክቱን ለወንድም እህቶቻችሁ አጋሯቸው።
══════════════
+3
⚽️ በስፖርት ክበብ አዘጋጅነት በየአመቱ ይደረግ የነበረው የሁለተኛው መንፈቀ አመት የወንድ ተማሪዎች የእግር ኳስ ውድድር ለዋንጫ ጨዋታ ለማለፍ በተደረገ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ዛሬ (28/08/2017) ዓ.ም 10:00 ላይ 6ኛA ከ 8ኛA ባደረጉት ጨዋታ 8ኛA 10 ለ 5 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ስፖርት ክበብ
Practical questions
👉Choose the best answer for the given alternatives
1.Which areas of Low insolation Recieved ?
A. At the equator
B. at the poles
C. At the tropics
D. Temperate
2. During the summer season of the Northern hemispher in Ethiopia's ---------
A. Cloudy
B. Rainy
C. Windy
D. Sunny
3. Every part of Ethiopia experience vertical rays of the sun twice in year
A. April&June
B.June& September
C. October& November
D. A&B
4. Which season is experianced in Ethiopia Little Rainfall
A. Summer and winter
B. Autumn and spring
C. Spring and autumn
D. Winter and spring
5. Which one of the following is Correct Combination
A. Woinadga - alpine
B. Kola - Desert
C. Dega - Temperate
D. Bereha - Sub tropical
6. Which one of the ff are Coldest and the highest altitude
A. Bereha
B. Kola
C. Woinadega
D. Wurch
2017E.C Grade 8 General science model Exam #ብዙ ጥያቄዎችን መስራት እንደ ማጥናት ስለሚቁጠር #ጥያቄዎችን በመስራት ለከተማ አቀፍ ፈተና እራሳችሁን ለማዘጋጀት ይጠቅማችዋል!!!!
የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና 1 ወር ያልበለጠ ጊዜ ቀርቶታል።
ይህ ጊዜ ለእናንተ ወርቃማ ስለሆነ ጊዜያቹን በአግባቡ መጠቀም ይኖርባችኋል፡፡
🔹 ያነበባቹትን የምትክልሱበት
🔹 ጥያቄዎችን የምትሰሩበትን
🔹 የሚያዘናጋቹ ነገር የምትቀኑስበት መሆን አለበት፡፡
🔹 ከትምህርታቹ ጋር ግንኙነት የሌላቸውን ሶሻል ሚዲያዎች ቀንሷቸው ወይም ከተቻለ ለጊዜው አጥፏቸው፡፡
🔹 ቤታቹ በአግባቡ ማጥናት ካልቻላቹ በግሩፕ ወይም ላይብረሪ እየሄዳቹ አጥኑ፡፡ በርቱ 🫶ተስፋ እንዳትቆርጡ 🫵 አይዟቹ 💪
