cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

በብሂለ አበው ኩኑ ውሉደ ብርሃን

“የዱሮውን ዘመን አስብ፥ የብዙ ትውልድንም ዓመታት አስተውል፤ አባትህን ጠይቅ፥ ያስታውቅህማል፤ ሽማግሌዎችህን ጠይቅ፥ ይነግሩህማል።” ተብሎ እንደተፃፈ በአባቶች ፍሬ ቃል የብርሀን ልጆች እንሁን!

Show more
Advertising posts
198Subscribers
No data24 hours
-37 days
-630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

“ሕብረ ሐመልሚል ቀይሕ ወጸአድዒድ አርአያ ኰሰኰስ ዘብሩር ተአምርኪ ንጹሕ በአምሳለ ወርቅ ግቡር ተፈጸመ ናሁ ማሕሌተ ጽጌ ሥሙር አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት ወምድር ከመ በሕጽንኪ ያሰምክ ፍቁር” "የሚያብረቀርቅ ቀይና ነጭ ቀለም ያለው አርአያው የብር ዝንጒርጒር ጠቃጠቆ የኾነ ንጹሕ ተአምርሽ በወርቅ አምሳል የተሠራ ነው፤ እነሆ የተወደደ (መልካም) ማሕሌተ ጽጌ ደረሰ ተፈጸመ፤ የሰማይና የምድር ንግሥት ማርያም ሆይ የተወደደ ልጅሽ በጒያሽ (በዕቅፍሽ) እንዲጠጋ (እንዲደገፍ፣ እንዲንተራስ) በርሱ ዐማጽኚ፡፡" አባ ጽጌ ድንግል (ማህሌተ ጽጌ)
Show all...
"እንበለ አውሎጊዮስ ለዳንኤል አመ አርአዮ ስቅለተ፤ ከመ እገሪሁ ሰዐምኪ ወሰአልኪዮ ምሕረተ፤ ለተአምረ ሣህል ወልድኪ በእንተ ፍቅረ ሰብእ ዘሞተ፤ እንዘ ታዘክሪዮ ድንግል ይምሐረኒ ሊተ፤ ከናፍሪሁ ጽጌ አንኂ ስዕመተ።" #አባ_ዳንኤል_ታላቅ_ገድለኛ_ነው ከቅጠል በቀር ሌላ አይመገብም ነበር በዚህ ሁኔታ አርባ ዓመት ከስድስት ወር በአስቄጥስ ገዳም ኖረ ይህም ቅዱስ ስሙ አውሎጊስ የሚባለውን ሰው አየው ይህም አውሎጊስ የወፍጮ ድንጋይን እየወቀረና እየሸጠ ሁል ጊዜ በመጠኑ እየተመገበ ድኆችንና ጦም አዳሪዎችን ይመግባቸዋል የተረፈውንም ፍርፋሪ ለውሾች ይጥላል /ይሰጣል/ ለነገ ብሎ ምንም አያሳድርም ነበር አባ ዳንኤልም ይህን መልካም ሥራ አይቶ በእርሱ ደስ አለው እጅግም አማረው ለአውሎጊስም የዚህን ዓለም ብልጽግና እንዲሰጠውና ለድኆች የሚመጸውተውን እንዲጨምርለት ወደ እግዚአብሔር ለመነ አባ ዳንኤልም ለአውሎጊስ ዋስ ሆነው የሚወቅረውንም ድንጋይ ሲፈነቅል በሸክላ እቃ ውስጥ የተዳፈነ ወርቅን አገኘ ወደ ቊስጥንጥንያ ከተማ ሄዶ የንጉሥ የሠራዊት አለቃ ሆኖ ባገኘው ወርቅ ተሾመበት የሚሠራውንም የቀደመ በጎ ሥራውን ተወ፡፡ #አባ_ዳንኤልም አውሎጊስ በጎ ሥራ መተውን ሰምቶ ወደ እርሱ ሄዶ አረጋገጠ አዘነ ስለ እርሱ እግዚአብሔርን በመለመኑ ተጸጸተ ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለፍርድ እንደመጣ አባ ዳንኤልንም እንዲሰቅሉት /ይሰቅሉት ዘንድ/ የአውሎጊስንም ነፍስ ከእርሱ እንዲሹ አዘዘ፣ በእርሱ ምክንያት ጠፍቷልና። የከበረች እመቤታችን ድንግል ማርያምም የክብር ባለቤት የሆነ ልጅዋ ኢየሱስ ክርስቶስን ስለ አባ ዳንኤል ስግደትን እየሰገደችና እግሮቹን እየሳመች እንደለመነችው በሌሊት አባ ዳንኤል ራእይን አየ በነቃ ጊዜም ደነገጠ አውሎጊስንም ወደ ቀድሞ ሥራው ይመልሰው ዘንድ በጸሎትና በምሕላ በመትጋት ወደ እግዚአብሔር እየለመነ ግብር ገባ /ሱባዔ ያዘ/ ከዚህ በኋላም ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጸለት በፍጥረቱ ላይ በሚያደርገው በእግዚአብሔር ፍርድ ውስጥ ለመግባት በመድፈሩ ገሠጸው በዚያንም ወቅት አውሎጊስን የሾመው ንጉሥ ሞተ ሌላ ንጉሥ ነገሠ በአውሎጊስም ላይ በጠላትነት ተነሥቶ ገንዘቡን ሁሉ ወረሰ ደግሞም ሊገድለው ፈለገው አውሎጊስም ነፍሱን ለማዳን ከንጉሡ ሸሽቶ ወደ አገሩ ሄደ እንደ ቀድሞውም ድንጋይን ይወቅር ጀመረ አባ ዳንኤልም ወደ እርሱ ተመልሶ ስለእርሱ ያየውን ሁሉ ነገረው፡፡ #እመቤታችንም ከመስቀል እንዳዳነችው ነገረውና አደነቀ:: የአውሎጊስና የአባ ዳንኤል የመጨረሻ ሕወታቸው ከዚህ ተገልጿል። አባ ዳንኤል በመጨረሻ ጊዜ የትቢት ሐሳብ ከአደረበት በኋላ ትቢትንና መመካትን የማይወድ እግዚአብሔር ወደ ባሕታዊው ንጉሥ አኖሬዎስ ወስዶ የንጉሡን ትሕትና አሳይቶ ከትቢቱ ተመልሶ ንጉሡ አኖሬዎስና አባ ዳንኤል በአንዲት ቀን በአስቄጥስ ገዳም በክብር ሲያርፉ አውሎጊስና የአውሎጊስ ረዳት ደግሞ በዚያች ዕለት በአንድነት በክብር አርፈዋል፡፡ #ትርጓሜ_ማኅሌተ_ጽጌ @Weldeaman 👈
Show all...
"ሚ ሠናይ ከመፄና ጽጌ ልሑይ፤ በኵሉ ጊዜ ምሒረ ነዳይ፤ በእንተ ኪዳንኪ ድንግል ለበላዔ ሰብእ ጊጉይ፤ ሶበ ዐብየ ኃጢአቱ ክበደ መድሎቱ ለማይ፤ ለተአምርኪ በሰማይ ተገብረ ግናይ።" #የመጀመሪያ_ስሙ_ስምዖን የሚባል ሰው ነበር አንድ ልጅ ብቻ ነበረው እንደ አብርሃም በመልካም ሥራ ጸንቶ ሲኖር ዲያብሎስ በመልካም ሥራው ቀንቶ ልጅህን ሠዋልኝ /እረድልኝ/ ብሎ ልጁን አሳርዶ የልጁን ሥጋ እንዲበላ ካደረገ በኋላ ከዚያች ቀን ጀምሮ በላዔ ሰብእ ተባለ፡፡ ዲያብሎስ ሲያታልለው የነበር እንደ አብርሃም በሶስት እንግዶች አምሳል ወደ ቤቱ ገብቶ ነበር ልጁን ከበላበት ቀን ጀምሮ ፍላጎቱ የሰው ሥጋን መብላት ሆነ በዚህም ሰባ ስምንት ሰዎችን በላ። #ከዚህ_በኋላ በመንገድ አንድ ውሃ የተጠማ ደሀ ሰው በእመቤታችን ስም ውሃን ለመነው በእውነት አሁን የጠራሃት በአማላጅነቷ የምታድን ናት ከሕፃንነቴ ጀምሬ አማላጅነቷን እሰማ ነበር ብሎ ትንሽ ውሃን በተጠማው ሰው እጅ ላይ አፈሰሰለትና ጠጣ ለጉሮሮው እርጥበት እንጂ አላረካውም ከዚህ በኋላ የበላዔ ሰብእ የቀድሞ አእምሮው ተመለሰለት ከዋሻ ገብቶ ስለበደሉ እያለቀሰ ሰውነቱን በረሀብ በፅምዕ እየቀጣ በእህልና በውሃ ሌላም አንዳች ነገርን ሳይቀምስ በእግዚአብሔር ኃይል ሃያ አንድ ቀን ተቀምጦ ሞተ የሲኦል አበጋዞች ነፍሱን ወደ ሲኦል ይወስዷት ዘንድ ከበቧት እመቤታችንም ልጅዋ የሰጣትን ቃልኪዳን እየጠቀሰች ማለት ስምሽን የጠራ ዝክርሽን የዘከረ እምርልሻለሁ አላልከኝምን አለችውና በእመቤታችን አማላጅነት ያች ነፍስ ከሲኦል ወደገነት ለመግባት በቃች፡፡ ለድንግል ማርያም እና ለልጅዋ ለመድኃኔዓለም ምስጋና ይሁን አሜን፡፡ #ትርጓሜ_ማኅሌተ_ጽጌ @Weldeaman 👈
Show all...
👍 2🥰 2
"ምንተኑ ለጽጌከርሥኪ አዐሥዮ፤ እንበይነኪዳንኪ ድንግል ምክንያተድኂን ዘወሀበንዮ፤ ባሕቱ ምስሌኪ ማርያም መጠነ ተክህለኒ አዐብዮ፤ ትእምርተ ፍሥሓየ በእንቲአየ ዘኢይፌጽም ኀልዮ፤ ሰይጣንሰ ይበኪ ርእዮ።" #በገዳም_አገልግሎት ፀንተው የሚኖሩ ሁለት ወንድማማቾች ነበሩ ታላቁ ትንሹን መጽሐፍ የምደግምበት /የማነብበት/ መብራት አምጣልኝ አለው መብራት ሲያመጣ ሰይጣን አጠፋበት ያን ጊዜ ታላቁ ታናሹን ይህ ልል /ፈዛዛ/ ብሎ በጥፊ መታው በዚህ ጊዜ ታናሹ ታግሦ እኔ እንዳጠፋሁት እኔ አመጣለሁ አለ እግዚአብሔር የታናሹን ትግሥት አይቶ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ሰይጣኑን በእሳት አለንጋ ሲገርፈው አደረ ሰይጣንም አይነኩ ሲነኩ ያድራል ሲታወኩ እያለ ሲያለቅስ አድሯልና "ሰይጣንሰ ይበኪ ፤ ሠይጣን ያለቅሳል" አለ፡፡ #ትርጓሜ_ማኅሌተ_ጽጌ @Weldeaman 👈
Show all...
"መልዐ ተአምረኪ ኵሎ መካነ፤ አድባረኒ በሥነ ጽጌሁ ከደነ፤ ማርያም ፍሥሓ ዘትስዕሪ (ዘታረሥዒ) ኀዘነ፤ በከመ አውጻእኪ እምከርሠ እመምኔት ሕፃነ፤ እሞተ ኀጢአት ነፍስየ አውጽኢ ፍጡነ።" #በቀርሜሎስ_ደብር ጠባይዋ ያማረ እግዚአብሔርን የምትፈራ እመቤታችንን የምትወድ ሶፍያ የምትባል የሴቶች ገዳም አስተዳዳሪ ነበረች። በገዳሙ ውስጥ በድንግልና የሚኖሩ ብዙ መነኮሳት አሉ የቀኖናን ሥርዓት ስታስተምራቸውና በጸሎት ጊዜ ስንፍና እንዳይዛቸው ትመክራቸዋለች ስለዚህ ነገር ይጠሏታል። ከሹመቷ የምትሻርበትን ከቤተክርስቲያን የምትባረርበትን ምክንያት ይፈልጉባት ነበር። በዚህች እመምኔት ርኩስ መንፈስ አደረባትና ለገዳሙ ከሚያገለግለው ጎልማሳ ፀነሰች ደናግል እኅቶች በኤጲስቆጶሱ /በአባ ሳዊሮስ/ እንደከሰሷት ተረዳች ወደ ቤተክርስቲያን ሔዳ በእመቤታችን ሥዕል ፊት ቆማ ትሰግድ ጀመር በማሕፀኔ ያለውን የአመፃ ፅንስ ሻሪልኝ እያለች ጸለየች እመቤታችንም ከማህፀኗ ያለውን ሕፃን አውጥታችሁ ፊሊኒክስ ለሚባል ሰው ያሳድገው ዘንድ ስጡት እሱ የወተት ላሞች አሉትና ብላ ሁለት የብርሃን መላእክትን አዘዘች መላእክትም የታዘዙትን ፈጸሙ እመምኔቷም ከእንቅልፏ ብትነቃ የእርግዝና ምልክት ፈጽሞ የሌለባት መሆኑን ተረዳች በዚያ ጊዜ ተደሰተች ከሳሾቿም በቀጠሮው ቀን ቢመረምሯት የእርግዝና ምልክትን አላገኙም ነገር ግን እመምኔቷ እመቤታችን ያደረገችላትን ተአምር ለአባ ሳዊሮስ ነገረችውና ተደንቆ ሕፃኑም ወደገዳም መጥቶ የቤተክርስቲያን ትምህርትን ተምሮ ኤጲስቆጶሱ ከአረፈ በኋላ በእርሱ ፈንታ ሾሙት ባለ ዘመኑ ሁሉ ቤተክርስቲያንን ሲያገለግል ኖረ። #ትርጓሜ_ማኅሌተ_ጽጌ @Weldeaman 👈
Show all...
👍 4