cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Loza Health Jobs

ያገለግላሉ የህክምና ማሽኖችን እንገዛለን እንሸጣለን፥የህክምና ባለሙያዎችን ለግል ጤና ተቋማት አገናኝ ህጋዊ ፈቃድ ያለው ኤጀንሲ፤ድርጅቶችን ብዙ ሺ ተከታይ ባለን በ3ቱም የቴሌግራም ቻናሎቻችን ማስታወቂያ እንሰራለን፤ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ከመንግስትና ከግል ተቋማት የሚወጡ የስራ ቅጥር ማስታወቂያዎችን በቻናላችን እናጋራለን፤ትኩስና ወቅታዊ የጤና መረጃዎችን እናጋራለን 0917171781/0918706464

Show more
Advertising posts
5 035
Subscribers
+724 hours
+337 days
+3530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ __ የጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ Medicine, Nursing, Health Officer, Anesthesia, Pharmacy, Medical Laboratory Technology, Midwifery, Dental Medicine, Medical Radiology Technology, Environmental Health, Psychiatric Nursing, Pediatrics Nursing እና Emergency & Critical Care Nursing ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ ለተመዘገባችሁ የጤና ባለሙያዎች በሙሉ 1. ፈተናው በግንቦት 15 እና 16/2016 ዓ.ም በኮምፒውተር የሚሰጥ ሲሆን የፈተናው ፕሮግራም እንደሚከተለው ይሆናል፡- • Pharmacy, Public Health, Midwifery, Medical Laboratory Science......15/09/2016 ዓ.ም • Nursing, Medicine, Dental Medicine, Paediatric Nursing, Psychiatric Nursing, Emergency & Critical Care Nursing, Medical Radiology Technology, Anaesthesia and Environmental Health ----------16/09/2016 ዓ.ም 2. ሁሉም ተመዛኞች በግንቦት 14/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ በ 3፡00 ሰዓት በመፈተኛ ጣቢያ በመገኘት ስለፈተናው አሰጣጥ ቅድመ ገለጻ (orientation) መከታተል፣ የኮምፒውተር ቅድመ ፈተና መለማመጃ ጥያቄዎችን መስራት፤ ወደ ፈተና የሚያስገባውን Username and Password ማወቅ፣ የመፈተኛ ክፍላችሁን መለየት ይኖርባችኋል። 3. በፈተናው ዕለት ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ (የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፍቃድ ወይም ሌላ በግልጽ የሚታይ ህጋዊ መታወቂያ)፣ የፈተና መስሪያ ግብዓቶች (እርሳስ፣ ላጲስ፣ መቅረጫ) እና ስትመዘገቡ ሲስተሙ የሰጣችሁን ስሊኘ ይዛችሁ መገኘት ይኖርባችኋል፣ 4. ከላይ ከተጠቀሱት ነገሮች ውጪ ምንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ (ስልክ፣ የእጅ ሰዓት፣ መነጽር (የተረጋገጠ የዕይታ ችግር ከሌለ በስተቀር)፣ ቦርሳ እና ሌሎች እቃዎች፣ ምንም አይነት ማጣቀሻዎች እንዲሁም ባዶ ወረቀቶች፣ ምግብ ወይም መጠጥ (የተረጋገጠ የጤና ችግር ከሌለ በስተቀር) ይዞ መግባት አይፈቀድም፣ 5. በፈተናው ወቅት ተመዛኞች በሁለቱም ክፍለ ጊዜ (ጠዋት እና ከሰዓት በኋላ) አቴንዳንስ ላይ በአግባቡ መፈረም ይኖርባቸዋል፣ 6. የመፈተኛ ጣቢያ ኦንላይን በመረጣችሁት መሰረት ስም ዝርዝራችሁን ከዚህ በታች ያለውን ሊንኩን በመጫን መመልከት ይኖርባችኃል፡፡ (Link: https://drive.google.com/.../1e329fbEYG...) ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0118275936 መደወል እንዲሁም በ moh.gov.et ላይ EHPLE የሚለው ውስጥ በመግባት ማግኘት ይቻላል፡፡ ማሳሰቢያ፤ • በምዝገባ ወቅት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሶሻል ሳይንስ ካምፓስ የተመዘገባችሁ ፈተናው ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አምስት ኪሎ የቴክኖሎጂ ካምፓስ የተዛወረ እንዲሁም ባህርዳር ዩኒቨርስቲ ፔዳ ካምፓስ የተመዘገባችሁ ፈተናው ወደ ባህርዳር ዩኒቨርስቲ ፖሊ ካምፓስ መዛወሩን እናሳውቃለን • ማንኛውም ተመዛኝ ወደ ፈተና ጣቢያ ሲመጣ ሲስተሙ የሚሰጠውን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No)፤ የQR CODE እንዲሁም የተመዘገበበትን ተቋም (Exam Center) የያዘ ወረቀት /ስሊፕ/ print አድርጎ ካልያዘ ፈተናውን መውሰድ የማይችል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡ #MoH
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሊመረቅ ነው መጋቢት 29/2007 ዓ/ም የመሠረት ድንጋይ የተጣለለት አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የፊታችን ሰኔ 01/2016 ዓ/ም ተመርቆ ወደ አገልግሎት ሊገባ ቀጠሮ ተይዞለታል፡፡ ሆስፒታሉ 600 የሕሙማን አልጋዎችን እና የተለያዩ ዘመናዊ የመመርመሪያና የሕክምና ቁሳቁሶችን የሚይዝ ሲሆን ከፍ ያሉ ሕክምናዎችን ለማግኘት ወደተለያዩ ከተሞች የሚደረጉ ጉዞዎችን፣ ተጨማሪ ወጪዎችንና እንግልትን በማስቀረት ረገድ ከሰባት ሚሊየን በላይ በሚሆኑ የአርባ ምንጭና አካባቢዋ ነዋሪዎች ተስፋ የተጣለበት ነው፡፡ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የብሩህ ተስፋ ማዕከል የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
vacancy
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
" የ18 ወራት የዱቲ ክፍያ አልተከፈለንም " - የዲላ ዙሪያ ወረዳ ጤና ባለሙያዎች " መሠረታዊ ችግሩ የበጀት ችግር ነው፤ የካሽ እጥረት ነው ያለው " - የጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ በጌዴኦ ዞን ዲላ ዙሪያ ወረዳ በ6 ጤና ጣቢያዎች የሚገኙ ጤና ባለሙያዎች የ18 ወራት የዱቲ ክፍያ እንዳልተከፈላቸው፣ እንዲከፈላቸው ቢጠይቁም መፍትሄ እንዳላገኙ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። ጤና ባለሙያዎቹ በሰጡት ቃል፣ " እንዲከፈለን ጠይቀን ነበር። ‘#ገንዘብ የለንም እንከፍላለን’ እያሉ ነው የተበጀተ በጀት እያለ ገንዘቡን ለሌላ ጉዳይ እየተጠቀሙ ያቆዩት " ብለዋል። - ጪጩ - አንድዳ - ስሶታ - ወቸማ - ኡዶ - ቱምትቻ በተሰኙ የወረዳው 6 ጤና አጠባበቅ ጣቢያዎች ከ01/06/2015 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 01/09/2016 ዓ/ም ለ18 ወራት የዱቲ ክፍያ አልተከፈለም ነው ያሉት። ያልተከፈላቸውን ገንዘብ መጠን ሲገልጹም አንዷ ቅሬታ አቅራቢ፣ " የእኔ ከ80,000 ብር በላይ ነው። ከእኔ በላይ ደመወዝ እርከን ላላቸው ደግሞ ይጨምራል። የአንድ ሰው ከዚህ በላይ ሲሆን፣ የ6ቱ ጤና ተቋም ብዙ ገንዘብ ነው " ሲሉ አስረድተዋል። ለተነሳው ቅሬታ ምላሽ የጠየቅናቸው የጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አንዱዓለም ማሞ፣ " ጉዳዩ በእርግጥ ያለ ነው። መሠረታዊ ችግሩ የበጀት ችግር ነው፤ የካሽ እጥረት ነው ያለው። ያን ለመፍታት በጋራ እየሰራን ነው " ብለዋል። ባለሙያዎቹ፣ 'የተበጀተ በጀት አለ ግን ለሌላ ጥቅም እያዋሉት ነው ያዘገዩብን' ላሉት ቅሬታ በሰጡት ምላሽ ኃላፊው፣ " እንደዛ አይደለም። በጀቱ ተይዟል እውነት ነው። ነገር ግን የጥሬ ገንዘብ እጥረት እንጂ ወረዳውም ለመክፈል ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቶ አይደለም " ሲሉ ተናግረዋል። የዞኑ የብልጽግና ጽ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ አይደፈር ሽፈራው  በበኩላቸው ፤ ችግሩ የጥሬ ገንዘብ እጥረት መሆኑን ገልጸው፣ ለ3 ዓመታት የዱቲ ክፍያ 6.4 ሚሊዮን ብር  እንደተበጀተ፣ ገንዘቡን ለማፈላግለግ እየተሰራ እንደሆነና ዱቲ የሚከፈላቸው የባለሙያዎች ብዛት መረጃም እየተሰበሰበ መሆኑን አስረድተዋል። via _tikvahethiopia
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
📌 Vacancy announcement 📌የስራ ቦታ ሰሜን ጎንደር ዳንሻ 📌Medical Radiologic Technologist [MRT] 📌only ultrasound 📌 zero year experience 📌 full time 0918706464 0917171781 @loza
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
👉አዲስ ማንኛውም ዓይነት ጤና ተቋም አማራ ክልል ላይ መክፈት ላልተወሰ ጊዜ ታግዷል ብዙዎች እየደወላችሁ እርግጠኛነቱን ትጠይቁናላችሁ👉 አዎ ተከልክሏል አዲስ ነገር ሲኖር እናጋራችሃለን @loza
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
የሚረከብ መድሀኒት 💊መደብር ባህርዳር ቀበሌ 14 አለን 0917171781 0918706464 @loza
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
📌 Vacancy announcement 📌Medical Radiologic Technologist [MRT] 📌only ultrasound 📌 2 year experience 📌 full time 📌 ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጽያ ቴፒ 0918706464 0917171781 @loza
Show all...
Show all...