cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Konjit Teshome

Journalist & Radio Host

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
226
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ትምህርት ሚንስቴር ከክፍያ ነፃ የኦንላይን መማሪያና ላይብረሪ አገልግሎት ይፋ አደረገ ትምህርት ሚኒስቴር የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የኦንላይን መማሪያ ስርዓት እና ዲጂታል ላይብረሪ አገልግሎቶችን በነፃ የሚያቀርብበት መርሃ ግብር ይፋ ማድረጉን አስታወቀ። አካል ጉዳተኞችን እና ወደ ትምህርት ቤት መምጣት የማይችሉ ተማሪዎችን ችግር ያቃልላል የተባለው ድረ ገፅ ባለ ልዪ ተሰጥኦ ተማሪዎች ደግሞ በትምህርት ስርዓቱ ሳይገደቡ መከታተል ያስችላል ተብሏል። የዲጂታል መማሪያ እና ቤተ መፅሀፍት አገልግሎቱ መደበኛና አጋዥ የትምህርት መፅሐፍት እንዲሁም ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ትምህርት ሚኒስቴር ካዘጋጃቸው እና ጠቃሚ ከሆኑ የውጭ ምንጮች የተካተተበት መሆኑ ተገልጿል። አገልግሎቱ በክፍል ደረጃ፣ በትምህርት ዓይነት እና በምዕራፍ ተከፋፍሎ የተዘጋጀበት ሲሆን ግብዓቶቹን በኢንተርኔት አማካይነት በነፃ እንዲሁም በማውረድ መጠቀም የሚያስችል ነው። ተማሪዎች አገልግሎቱን በ https://elearn.moe.gov.et አድራሻ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን የመጀመሪያ ደረጃ እና የቅድመ መደበኛ ተማሪዎች የዲጂታል አገልግሎቱን እንዲጠቀሙ እየተሰራ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
Show all...
MoE E-Learning and Digital Library

ትምህርት ሚኒስቴር: The MoE E-Learning and D-Library provides access to TextBooks, Lecture videos and so on to students and educational staff based on Grade, Course, Units, Sub- Units, etc with multifaceted Search functionality by keywords.

በዩክሬን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከመንቀሳቀሳቸው በፊት ጀርመን ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር እንዲመካከሩ ኤምባሲው አሳሰበ! በጀርመን በርሊን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዩክሬን በትምህርት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ከመንቀሳቀሳቸው በፊት ለኤምባሲው እንዲያሳውቁ አሳሰበ፡፡ ኤምባሲው በሀገሪቱ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ እና ችግር እንደሚረዳና ኢትዮጵያውያን ከመንቀሣቀሣቸው በፊት ለደኅንነታቸው ሲባል በማንኛውም ጊዜ በ+491767269094 የሞባይል ስልክ ቁጥር እና በ [email protected] ኢሜይል አድራሻ በመጠቀም ኤምባሲውን እንዲያገኙ እና እንዲመካከሩ አሳስቧል፡፡
Show all...
በእነ ጌታቸው አሰፋ መዝገብ የተከሰሱ የቀድሞ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ሰራተኞች በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ተወሰነ ****** ዐቤ ህግ በዋስና ሊለቀቁ አገባም በሚል ይግባኝ የጠየቀባቸው በእነ ጌታቸው አሰፋ መዝገብ የተከሰሱ የቀድሞ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ሰራተኞች በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን አንዲከታተሉ ተወሰነ። ለተከሳሾች የስር ፍርድ ቤት የፈቀደላቸውን የዋስትና መብት የሻረው በጠቅላይ ፍርድ ቤት 1ኛ ይግባኝ ሰሚ ችሎት ነው። በቀድሞው የመረጃና ብሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አሰፋ መዝገብ የቀድሞ የብሔራዊ መረጃና ደህንንነት ቢሮ ምክትል ዳሪክተር አቶ ያሬድ ዘሪሁን ጨምሮ የተቋሙ የፀረሽብር ጉዳዮች መምሪያ ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ኡርጌ 22 ተከሳሾች የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ጉዳያቸውን ሲከታተል ለቆየው ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት የዋስትና መብት ጠይቀው በአንድ ዳኛ የድምጽ ተቃውሞ በሁለት ዳኞች አብላጫ ድምጽ ተፈቅዶላቸው ነበር። ተከሳሾቹ ክሳቸውን እንዲከላከሉ በተባለበት በተሻሻለው አንቀጽ 423 እና አንቀጽ 556 መሰረት ሁሉም ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ30 ሺህ ብር ዋስ አስይዘው ከእስር እንዲፈቱና ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ፍርድ ቤቱ ብይን መስጠቱም ይታወሳል። በዚህም መሰረት ዐቃቤ ህግ ተከሳሾች ተደራራቢ ክስ እንዳለባቸው፤ የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት በዋስ ከወጡ በቀጣይ ቀጠሮ ግዴታቸውን አክብረው የማይቀርቡ መሆኑን በመግለጽ የተከሳሾች በዋስትና መፈታት አግባብ አለመሆኑን የያዘ ባለ ዘጠኝ ነጥብ ምክንያቶችን ጠቅሶ በተከሳሾች ዋስትና ላይ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 1ኛ ይግባኝ ሰሚ ችሎት መቃወሚያ አስገብቶ ነበር። የተከሳሽ ጠበቆች ተከሳሾቹ ይከላከሉ የተባሉበት አንቀጽ ዋስትና የማያስከለክል በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቱ ዋስትና መፈቀዱ የህግ አግባብ ያለው በመሆኑ የተፈቀደው የዋስትና መብት ይጽናልን ሲሉ መከራከሪያ ነጥቦችን ጠቅሰው መልስ ሰጥተዋል። መዝገቡን የመረመረው በጠቅላይ ፍርድ ቤት 1ኛ ይግባኝ ሰሚ ችሎቱ በዛሬው ችሎቱ የዋስትና ውሳኔውን በመሻር በሁለት አብላጫ ድምጽ በአንድ ዳኛ ልዩነት ተከሳሾቹ ከነበራቸው ስልጣን አንጻር በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርአት ህግ አንቀጽ 67/ሀ መሰረት የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታን ከግምት በማስገባት ተከሳሾች በዋስ ቢወጡ ግዴታቸውን አክብረው ችሎት ላይቀርቡ ይችላሉ ሲል የዐቃቤ ህግ ይግባኝ ተቀባይነት አግኝቶ ዋስትናውን ሽሮታል። ተከሳሾች ሰዎችን ያለአግባብ በማሰር የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጽመዋል ተብለው ክስ የቀረበባቸው በእነ ጌታቸው አሰፋ መዝገብ የቀድሞው የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ዳይሬክተር ጄነራል አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ በማረሚያ ቤት የሚገኘው ያሬድ ዘሪሁንና ሌሎች 24 ተከሳሾች ላይ እንደየጥፋተቸው በፈፀሙት ወንጀል የጥፋተኝነት ፍርድ መተላለፉ የሚታወስ ነው። በዚህም መሰረት በዛሬው እለት ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤት በተከሳሾች የዋስትና መብታቸውን በተመለከተ የተሰጠውን ውሳኔ የስር ፍርድ ቤቱ የሻረባቸው ተከሳሾች የክስ ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ ትዕዛዝ መስጠቱን ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታውቋል።
Show all...
የ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ተደረገ የ2013 ዓ.ም 12ኛ ክፍል የኢትዮጵያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉን ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ። ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ገብተው ለመማር ብቁ የሚሆኑ ተማሪዎች ለመግቢያነት ከሚያገለግሉ የትምህርት ዓይነቶች በአጠቃላይ አማካይ ነጥብ 50% (ግማሽ) እና ከዚያ በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል ተብሏል። ከ1 ሚልየን በላይ ተማሪዎች በተፈተኑት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና 141 ተማሪዎች የፈተና ደንብ ጥሰት በመፈፀማቸው ከውጤት መሰረዝ ጀምሮ በየደረጃው እርምጃ ተወስዶባቸዋል ሲል ኤጀንሲው ገልጿል። የእያንዳንዱ የትምህርት ዓይነቶች ውጤት በተገመገመበት ሂደት የስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር (ሲቪክስ) ትምህርት በሁሉም ትምህርት ቤቶች በሚባል ደረጃ የውጤት መመሳሰልና ግሽበት የታየበት በመሆኑ ውጤቱ ለዩኒቨርስቲ መግቢያ መወዳደሪያነት እንዳያገለግል ተወስኗል። በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ገብተው ለሚማሩ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲዎችን የመቀበል አቅም በማገናዘብ ዝርዝር የመግቢያ ነጥብ ወደፊት እንደሚገለፅ ኤጄንሲው ገልጿል። ተፈታኝ ተማሪዎችም በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብሳይት (result.neaea.gov.et)፣ በትምህርት ሚኒስቴር ዌብሳይት (result.ethernet.edu.et) እንዲሁም በቴሌግራም ቦት (@moestudentbot) ላይ በመግባት Exam Result የሚለውን በመንካት ውጤት ማየት ይችላሉ ተብሏል። በተጨማሪም በ9444 የአጭር ፅሁፍ መልዕክት መላኪያ ላይ የመለያ ቁጥራቸውን በመላክ ዉጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ ኤጀንሲው አስታውቋል።
Show all...
እነ አቶ አብዲ ኢሌ የስነ-ልቦና ጉዳት ስለደረሰብን ምስክር የመስማት ፍላጎት የለንም ሲሉ ረጅም ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ፍርድ ቤቱን ጠየቁ። ከሌሎች የተለየ ወንጀል ሳንሰራ ሌሎች ዕስረኞች ተፈተው እኛ ፍርድ ቤት የምንቀርብበት ምክንያት የለም በማለት ሁለት ቀጠሮ የቀድሞ የሱማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሀመድ ኡመርን(አብዲ ኢሌን) ጨምሮ 11 ተከሳሾች ችሎት ሳይቀርቡ መቅረታቸው ይታወሳል። ዓቃቢ ህግም ተገደው እንዲቀርቡ አልያም በሌሉበት ጉዳያቸው እንዲታይ ችሎቱን ጠይቆ ነበር። ይሁንና ፍርድ ቤቱ መርምሮ በጉዳዩ ላይ ትእዛዝ ለመስጠት ለዛሬ ቀጥሮ የነበረ ሲሆን ነገር ግን በዛሬው ቀጠሮ ሁሉም ተከሳሾች ፍርድ ቤት ቀርበዋል። የስነልቦና ጉዳት እንደደረሰባቸው እና ባሉበት ሁኔታ ምስክር የመስማት ፍላጎት እንደሌላቸው በመግለጽ እረጅም ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ከሳሽ ዓቃቢህግ በበኩሉ ጥያቄያቸው ከህግ አንጻር አሳማኝ አደለም ሆኖም ዕረጅም ቀጠሮ ቢሰጣቸው እንደማይቃወም አብራርቷል። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የፀረሽብርና ህገመንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በተከሳሾቹ ላይ ቀሪ የአቃቢህግ ምስክሮችን ለመስማት ለመጋቢት 19 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል። ከሳሽ ዓቃቢህግ ከ46 በላይ ምስክሮችን አቅርቦ በተለያዩ ቀናት ማሰማቱ ይታወሳል። Tarike Adugna
Show all...
አሜሪካ የሕወሓት ታጣቂዎች በአማራ ክልል ፈፅመዋል የተባለው ወንጀል አሳስቦኛል አለች የሕወሓት ታጣቂዎች በአማራ ክልል ፆታዊ ጥቃትን ጨምሮ አሰቃቂ ድርጊቶችን መፈጸማቸው መገለጹ በእጅጉ እንዳሳሰባት አሜሪካ ገለጸች። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትላንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጉዳዩን በተመለከተ በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት የሕወሓት ታጣቂዎች በ2013 ዓ.ም ነሐሴ ወር መጨረሻ እና በ2014 ዓ.ም መስከረም መጀመሪያ አካባቢ በአማራ ክልል አሰቃቂ ድርጊቶችን እንደፈፀሙ መግለጹን አስታውሷል። ሁሉም ወገኖች በሰብኣዊነት ላይ የሚፈፀም ጥቃት እና በሲቪሎች ላይ የሚደርሰው በደል እንዲቆም የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ጥሪ አቅርበዋል። ቃል አቀባዩ ግጭቱን ለማስቆም እና ለሁሉም ተበዳዮች ፍትሕን ለማረጋገጥ ጊዜው አሁን ነው ብለዋል።
Show all...
በአዲስ አበባ አውሮፕላን ማረፊያ በጫማ ውስጥ ተደብቆ ወደ ሀገር ሊገባ የነበረ 2 ኪ.ግ ወርቅ ተያዘ ************************** በአዲስ አበባ አውሮፕላን ማረፊያ በገቢ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል በኩል በጫማ ውስጥ ተደብቆ ወደ ሀገር ሊገባ የነበረ 2 ኪ.ግ ወርቅ ተያዘ። ግምታዊ ዋጋው 6.6 ሚሊዮን ብር የሆነው ወርቅ የተያዘው በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የኢንተለጀንስ እና ኮንትሮባንድ ክትትል አባላት ነው። የወንጀሉ ሁኔታ በመጣራት ላይ መሆኑን ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
Show all...
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከሚያዝያ ወር ጀምሮ በ+2517 ኮድ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል! በቀጣይ አሥር ዓመታት በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ1 ነጥብ 5ሚሊየን ሰዎች የሥራ እድል እንደሚፈጥር ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ገለጸ፡፡ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ተቋማት መዕዋለ ንዋያቸውን ያፈሰሱበት በኢትዮጵያ አዲስ ጅማሮ የሆነው የቴሌኮም ዘርፍ ላይ ኢትዮጵያዊያንን የሚመጥን ዘመናዊ የኔትዎርክ ዝርጋታ እንደሚያካሂድ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ጉዳዮች ሃላፊ ማቲው ሀሪሰን ገልፀዋል፡፡ በአዲስ አበባ እና በአዳማ በመቶ ሚሊየን ዶላር ወጪ የዳታ ማዕከል መገንባቱን ያነሱት የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ክፍል ዋና ሃላፊ ፔድሮ ራቫካል በዚህ ዓመት በሁለቱም ከተሞች ሁለት ተጨማሪ የዳታ ማዕከል እንደሚገነቡ ገልጸዋል፡፡በቀጣይ አሥር ዓመታት 8 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር በማፍሰስም የዘርፉን ተጠቃሚነት የማሻሻል ዕቅድ እንዳላቸውም አንስተዋል፡፡የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከሚያዝያ ወር ጀምሮ በ (+2517) ኮድ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ነው የተባለው፡፡ Via FBC
Show all...
የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦችን አስመስለው ሲያትሙ የነበሩ ካሜሮናውያን በቁጥጥር ስር ዋሉ ************************** በቦሌ ክክፍ ከተማ ወረዳ 03 በተለምዶ ፕሬሰዴንሽያል ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ሲታተሙ የነበሩ ልዩ ልዩ ሐሰተኛ የገንዘብ ኖቶች ከተለያዩ የኬሚካል ቁሳቁሶች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል። የአከባቢው ህብረተሰብ ባደረሰው ጥቆማ መሰረት የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አባላት ባደረጉት ክትትል ሐሰተኛ ኖቶቹን ሲያመርቱ የነበሩ ሁለት የካሜሮን ዜግነት ያላቸዉ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውለዋል። ግለሰቦቹ የአሜሪካ ዶላር፣ የሱዳን፣ የቻይና እና የማይናማር እንዲሁም የታንዛኒያ ገንዘቦችን አስመስለው ሲያትሙ በቁጥጥር ስር ውለዋል። ህብረተሰቡ መሰል ተግባር ላይ በመሰማራት የሚያጭበረብሩ ወንጀለኞችን ለፖሊስ በመጠቆም እንዲተባበርም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጥሪ አስተላልፏል።
Show all...
እነ አብዲ ኢሌ አቶ አብዲ ተገደው ችሎት እንዲቀርቡ አልያም በሌሉበት ጉዳያቸው እንዲታይ አቃቤ ህግ ጠየቀ የቀድሞ የሱማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሀመድ ኡመርን (አብዲ ኢሌን) ጨምሮ አጠቃላይ 17 ተከሳሾች በባለፈው ቀጠሮ "በህገ-መንግስቱ የተሰጠን ዕኩል የመታየት መብታችን አልተጠበቀልንም፤ እኛ ከሌሎች የተለየ ወንጀል አልፈጸምንም። ከኛ ጋር ታስረው የነበሩ እስረኞች ተፈተው እኛ ፍርድ ቤት የምንቀርብበት ምክንያት የለም" ሲሉ አቤቱታ ማቅረባቸው ይታወሳል። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የፀረ- ሽብርና ህገ- መንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት አቤቱታቸውን መርምሮ በየካቲት 3 ቀን 2014 ዓ/ም በነበረ ቀጠሮ ጥያቄው መቅረብ ያለበት ክስ ላቋረጠው መንግስታዊ አካል እንጂ ለዚህ ችሎት አደለም አጠቃላይ አቤቱታው የህግ መሰረት የለውም ሲል ጥያቄያቸውን ውድቅ በማድረግ ቀሪ የዓቃቤ ህግ ምስክርን ለመስማት ለዛሬ ቀጠሮ ነበር። በዛሬው ቀጠሮ ግን አቶ አብዲ መሀመድ ኡመርን ጨምሮ 11ተከሳሾች ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀርተዋል። ቀሪዎቹ በተለያዩ ዞን የሚገኙ ስድስት ተከሳሾች ግን በችሎት ተገኝተዋል። የ11 ችሎት ያልቀረቡ ተከሳሾች ጠበቆች በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡ በፍርድ ቤቱ የተጠየቁ ቢሆንሞ ደንበኞቻቸው በሌሉበት አስተያየት መስጠት እንደማይችሉ ምላሽ ሰተዋል። ከሳሽ ዓቃቤ ህግ በበኩሉ ተከሳሾቹ በቀጣይ ቀጠሮ ተገደው እንዲቀርቡ አልያም በሌሉበት ጉዳያቸው እንዲታይ ፍርድ ቤቱን ጠይቋል። ፍርድ ቤቱም መርምሮ ትዛዝ ተመስጠት ለፊታችን ረቡዕ ለየካቲት 16 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። የሱማሌ ክልል የቀድሞ ፕሬዝዳንት አቶ አብዲን ጨምሮ 17 ተከሳሾች ላይ በ2010 ዓ/ም በጂጂጋ ከተማና በተለያዩ ቀበሌና ዞኖች ከተከሰተ የዕርስ በዕርስ ግጭት ጋር ተያይዞ በቀረበባቸው የወንጀል ክስ ዓቃቤ ህግ ከ46 በላይ ምስክሮችን አቅርቦ አሰምቶ እንደነበር ይታወሳል። Via Tarik Adugna
Show all...