cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

እንማር!!

''አገር ያለ አንድነት አእምሮ ያለ ንባብ አይበለጽግም።'' ጃዕፈር መጻሕፍት ስለዚህ እናንብብ እንማር!!

Show more
Advertising posts
225
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
በአዲሱ የትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት የተማሪዎች ምዘና እና የክፍል ክፍል ዝውውር መመሪያ መሠረት፣ 💥ከ1ኛ - 3ኛ ክፍል የተማሪዎች ምዘና እና የክፍል ክፍል ዝውውር ሁኔታ ⚡️ በተከታታይ ምዘና ከሚያዘው 70% እና በትምህርት ዘመኑ ግማሽ ዓመት እና ማጠቃለያ ላይ ከ30% በሚሰጠው ፈተና በአማካይ በሁሉም ትምህርት ዓይነቶች 50% እና በላይ ሲያመጡ ወደ ቀጣዩ ክፍል ይዛወራሉ፤ ⚡️ ከ1ኛ-3ኛ ክፍሎች ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ተማሪዎች ወደ ቀጣዩ ክፍል ለመዘዋወር የሚያስችላቸውን ውጤት ካላገኙ ትምህርት ቤቱ የቀጣዩ ትምህርት ዘመን መጀመሪያ ወር ላይ ተማሪዎች ባላሟሉት ትምህርት ዓይነት ላይ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ በድጋሚ በሚሰጥ ፈተና የሚጠበቅባቸውን ውጤት ማሟላታቸው ሲረጋገጥ ወደ ቀጣዩ የክፍል ደረጃ እንዲዛወሩ ይደረጋል፤ ⚡️ከላይ በተቀመጠው መመሪያ አስፈላጊው ክትትል እና ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደ ቀጣዩ ክፍል መዛወር ያልቻሉ ተማሪዎች #ለአንድ_ጊዜ ብቻ በነበሩበት ክፍል እንዲደግሙ ይደረጋል፤ [ ምስሉን ይመልከቱ ‼️] ➡️መመሪያው ከዚህ ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል የተባለ ሲሆን ትምህርት ሚኒስቴር መመሪያው ተግባራዊ መደረግ የሚጀምርበትን ወር እና ቀን ለጊዜው አልገለፀም። @sketamatemari
Show all...
3👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
በአንድ በህዝብ በተጨናነቀ ባቡር ውስጥ አባት ከ24 አመት ወጣት ልጃቸው ጋር እየተጓዙ ነበር። ✔️ልጅ በጣም ደስተኛ መሆኑን በሚያሳብቅ ሁኔታ የሚያየው ነገር ሁሉ አስገራሚ ሆኖበታል። በየመሃሉ በደስታ ተሞልቶ ወደ አባቱም እየዞረ "አባዬ ዛፎቹን ትተናቸው አለፍን" "አባዬ ደመናው አብሮን እየሄደ ነው እየው " "አባዬ ተራራው ሰማዩን ነክቶታል ተመልከተው" በተደጋጋሚ እንደዚህ ያሉ ነገሮችን በደስታ ተሞልቶ ከፍ ባለ ድምፅ ለአባቱ ይነግራቸው ነበር ፡፡ አባት ልጃቸውን በስስት እያዩ የሚላቸውን ቦታ ሁሉ ይመለከቱ ነበር። አባትም በደስታ ትክክል መሆኑን ያረጋግጡለታል፡፡ በባቡሩ ውስጥ የነበሩት ሌሎች ተሳፋሪዎች በወጣቱና በአባቱ ሁኔታ ግራ እንደመጋባት ብለዋል፡፡የወጣቱን የአይምሮ ጤንነት በፅኑ ተጠራጥረዋል፡፡ የወጣቱ ነገረ ስራ ያበሳጫቸው ጤንነቱንም የተጠራጠሩ ጥንዶች ለአባትየው "ሆስፒታል ብትወስደው የተሻለ ነው። የልጅህ አዕምሮ ጤነኛ አይመስለንም "አሉት:: ⚽️አባትም ጥንዶቹን በአንክሮ እያየ "ከሆስፒታል ነው የምንመጣው፡፡ዛሬ ህክምናውን ጨርሶ ነው የወጣው ፡፡ልጄ ከብዙ አመታት ልፋት በውኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ማየት የቻለበት ቀን ነው። ከተወለደ ጀምሮ ማየት የተሳነው ነበረ"አላቸው። *** ለምን እንፈርዳለን?
Show all...
🔥 4👍 2
ሁላችንም እኩል ራሳችንን ማከም አልተለማመድንም። ለአንድአይነት ስቃይም ተመሳሳይ ምላሽ አልሰጠንም። አንዳንዱ የደረሰበት መከራ ለአለም ያለውን እይታ ጋርዶ ጨለማ ውስጥ ይኖራል። አለ ደሞ የዚህች አይነት ጉድ- የኔዋ ጉድ ልበል እንጂ። እያንዳንዱ rejection ይበልጥ ጥሩ የሚያደርጋት እያንዳንዱ መከራ ይበልጥ ራሷን እንድትጠብቅ የሚያደርጋት። ችግርን እንደችግር ሳይሆን እንደ ማጣፈጫ የምትወስደው ፤ ሳበችኝ እንቢ እንዳልል አድርጋ ምንም የማርያም መንገድ ሳታስተርፍልኝ ወደ ራሷ ሳበቺኝ። "ወደድኩሽ" አልኳት ከስንት ምጥ በኋላ "ለምን አለቺኝ"  " ከማውቃቸው ሁሉ ስለምትሻዪ" አልኳት "ሌላ ሚሻል ስታገኝ መሄድህ አይቀርም" ብላኝ ሄደች። ግራ ገባኝ እንደወደደቺኝ ነበረ የማውቀው፤ ቅሉ አሁንም ከህመሟ አለማገገሟ እንደሆነ ገባኝ። ድጋሜ ላለመሰበር ለራሷ የፈጠረችው፤ ልቧ ዙርያ ያጠረችው አጥር አላሳልፍ አለኝ። ጥሩነቷን አውቃለሁ፥ እንደ ህፃን ልጅ ፍቅር እንደምትሻም እንደዛው። ዳሩ እኔ ከራሷ ላድናት አልችልም። 
Show all...
3👍 2
ትልቅ ህልም አለኝ.pdf 📚ርዕስ:- ትልቅ ሕልም አለኝ 📝ድርሰት:- ዳዊት Dreams 📜ይዘት:-  ስለ ልቦና (psychology) 📆የመጀመሪያ ዕትም:- 📖የገፅ ብዛት:- 376 🔖 **ትልቅ ህልም አለኝ ህልሜ 👉አቅሜን ከመረዳቴ በፊት ፣ ህልሜ የማይቻል እና ከአቅም በላይ ይመስለኝ ነበር። **
Show all...
ትልቅ ህልም አለኝ.pdf78.64 MB
👍 2 1
ወንጀል እና ፍርድ መፅሐፍ ድህነት አሳፋሪ ድክመት አይደለም፡እውነት ነው ሰካራምነትም መልካነት አይደለም፡ልመና ግን ጌታዬ -ልመና ትልቅ ውርድት ነው፡አየህ በድህነት ሳለህ የነፍስህ ልዕልዕናህን ትጠብቃለህ፡ለማኝ ሆነህ ግን ፈፅሞ! ለማኝ ከማህበረሰቡ መካከል የሚባረረው በዱላ አይደለም፡ሀፍረት እንዲሰማው በመጥረጊያ ይጠረጋል እንጅ....!!!      
Show all...
ወንጀል እና ቅጣት @Ethio_books.pdf6.79 MB
2😍 2
📚ርዕስ:- 7ቱ የስኬት ሚስጥራት 📝ደራሲ:- ስቴፈን ኮቪይ 👤ተርጓሚ:- ቢኒያም አለማየሁ 📜ዘውግ:- ራስ አገዝ 📖የገፅ ብዛት:- 430 📌አዘጋጅ:-@Bemnet_Library “The 7 Habits of Highly Effective people” ወይም "7ቱ የውጤታማ ሰዎች ልማዶች or 7ቱ የስኬት ሚስጥራት የተሰኘው መጽሐፍ የተፃፈው ስቴቨን ኮቪይ በሚባል አሜሪካዊ ደራሲ ነው። መጽሐፉ ከ40 ሚሊዮን በላይ ቅጂዎች የተሸጠ፣ከ35 በላይ ቋንቋዎች የተተረጎሞ፣የግል ልህቀት(Personal development) ላይ የሚሰራ ዘመን የማይሽረው ድንቅ መጽሐፍ ነው። አንባቢዎች የህይወትን ውስብስብ ነገሮች ተረድተው፣እንዴት ግባቸውን ማሳካት እንደሚችሉ በዋጋ ሊተመን የማይችል ቴክኒኮችንና ስልቶችን ጣፋጭ በሆነ መልኩ ያቀርባል። 📌ማጋራት አይዘንጋ! @ETHIO_PDF_BOOKS1 @ETHIO_PDF_BOOKS @YETMHRTPDF @BHERE_TREKA
Show all...
7ቱ የስኬት ሚስጥራት @Bemnet_Library.pdf50.24 MB
2🔥 2
Photo unavailableShow in Telegram
❌ አይ እኛ... ❌ "እንቁላሉ ስንት ስንት ነው?" ስትል ጠየቀቻቸው… "አንዱ እንቁላል 4 ብር ነው " ልጄ በማለት መለሱ፣ እማማ… "አምስቱን እንቁላል በ15ብር ልወሰደው?…" ስትል ደግማ ጠየቀቻቸው … "አይጎዳኝም ብለሽ ነው ልጄ?"…በማለት ደከም ባለ ድምፅ መለሱላት… "ከፈለጉ ይሽጡ፣ ካልፈለጉ ግን በቃ መሄዴ ነው…" አለች፣ ጠንከር ባለ ድምፅ… እማማ ትንሽ አሰቡና ቀና ብለው አይተዋት… "እስካሁን ምንም አልሸጥኩም፣ ባያዋጣኝም እንደ መጀመሪያ ገድ ልቁጠረውና ልሽጥልሽ፣ የፈለግሺውን ያህል እንቁላል በፈለግሺው ዋጋ ውሰጂ…" ሲሉ በደከመ ድምፅ ተናገሩ… ዘንቢሏን አውጥታ 5 እንቁላል መርጣ አስገባች፣ ከበርካታ 100 ብሮች መካከል ነጥላ 15 ብር አውጥታ ወርውራላቸው... እየተጣደፈች የሚያምረው ዘመናዊ መኪናዋ ውስጥ ገባች… የአሸናፊነት ስሜት ተሰምቷታል… … ከጓደኛዋ ጋር ወደ አንድ ዘመናዊ ሬስቶራንት ገብተው የሚፈልጉትን አዘዙ…ትንሽ በልተው ብዙ አተረፉ። ተዝናኑ። ሂሳቡ ሲመጣ ቢሉ ላይ 1420 ብር ይላል ። ከቦርሳዋ ውስጥ 1500 ብር አውጥታ ሰጠች ። መልሱን ለሪስቶራንቱ ባለቤት ቲፕ እንዲሆነው ነግራው ወጥተው ሄዱ… … ይህ ድርጊት ለሬስቶራንቱ ባለቤት አዲስ አይደለም፣ ለእንቁላል ሻጯ እናት ግን አስደንጋጭና ልብ ሰባሪ ነው… . . . 👉ከድሆችና ከምስኪኖች የምንፈልገውን ለማገኘት የበላይነታችንን ለማሳየት የምንጥረው ለምንድን ነው? የእኛን እርዳታ ለማይፈልጉትስ ቸር ሆነን ለመታየት ለምን እንፈልጋለን? . . . 💥ለሚገባው እንስጥ🙏
Show all...
5👎 1🤩 1
በህይወት ውስጥ ትልቁ ፈተና የልብህን እውነት ሰዎች እንዲረዱህ ማድረግ ነው። ቤተሰብ፣ ወዳጅ የልቤ የምትለው ጓደኛ ላይረዳህ ሁሉ ይችላል፤ የሚሻለው መተው ነው። እነሱ እንዲረዱህ የምታባክነውን ጉልበትና ልፋት ራስህን ለማሳደግ ብታውለው ብዙ ርቀት ትጓዛለህ። በህይወትህ ላይ ልዩነት የምትፈጥረው ራስህ ላይ ስትሰራ ብቻ ነው! @Futurexethiopia ለውጥ አሁን ይጀምራል!
Show all...
3
ተዓምር ትሰራለህ! አሸናፊ የሆንከው በፈጣሪ መመካት ስትጀምር ነው፤ ስለዚህ ምንም ነገር ብትሞክር ወይ ታሳካዋለህ ወይ የሚገርም የህይወት ትምህርት ትማርበታለህ። ምንም ነገር ለመጀመር አትፍራ! ወዳጄ ህልም ካለህ፣ ጥረት ብትጨምርበት እና የአላማ ፅናት ብታዳብር ካሰብከው በላይ ተዓምር ትሰራለህ! አሸናፊ መሆን የሚፈልግ ሰው ይሄን ማድረግ ነው የሚጠበቅበት። @Futurexthiopia ለውጥ አሁን ይጀምራል!
Show all...
4🤩 3
🛑 እነዚህን 3 ነገሮች ሁሌም አስባቸው 1. አላማ ይኑርህ አለበለዚያ ጊዜው ሲገፋ በዘፈቀደ የሚኖር ከንቱ ሰው እንደሆንክ ማሰብህ አይቀርም፤ 2. ወደ አላማህ አንድ እርምጃም ቢሆን የሚያስጠጋህን ነገር በየቀኑ አድርግ፤ ስለዚህ በየቀኑ አጥና፣ ጥያቄ ስራ። 3. በፈጣሪህ ታመን ከዛ ልበሙሉነት ፀባይህ ይሆናል ግን ሲሳካልህ አመስጋኝ እንጂ ጀብደኛ አትሁን! @Futurexethiopia ለውጥ አሁን ይጀምራል!
Show all...
3👍 2
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.