cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

በሰልጤ ዞን ሚቶ ወረዳ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳይ ጽ/ቤት Mitto Woreda Public Communication

ትክክለኛ መረጃ ለህዝብ ማድረስ ህዝብና መንግስትን ማገናኘት መረጃ አቅም ነው! Information is Power!

Show more
Advertising posts
352
Subscribers
No data24 hours
+57 days
+2130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም ተጠቃሚዎችን ከድህነት እንዲወጡ ለማድረግ በልዩ ሁኔታ መደገፍ እንዳለባቸው የስልጤ ዞን ምግብ ዋስትና ግብረ ሀይል ሰብሳቢ አቶ ሙርሰል አማን ተናገሩ። **** ሚቶ፤ ሚያዝያ 28/2016(ሚቶ ወረዳ መንግስት  ኮሙኒኬሽን)የስልጤ ዞን ምግብ ዋስትና ግብረ ሀይል ሰብሳቢና የዞኑ ግብርና መምርያ ኃላፊ አቶ ሙርሰል አማን በወረዳ በግሪንዚላ ሸፎዴ ቀበሌ በመገኘት በልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም ተጠቃሚ ጓሮ የእንሰት ችግኝ ተከላ ባካሄዱበት ወቅት ባደረጉት ንግግር  የልማታዊ ሴፍትኔት ተጠቃሚዎችን ከድህነት እንዲወጡ ለማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካል በልዩ ሁኔታ መደገፍ እንዳለባቸው ተናግረዋል። በወረዳው ተጠቃሚዎች እራሳቸውን በምግብ እንዲችሉ ለማድረግ የተሰሩ ስራዎችንና የመጡ ለውጦችን አድንቀው እየተከናወኑ ያሉ መልካም ተግባራት በማጎልበት ሁሉም የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎች ከድህነት እንዲወጡ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ እና የምግብ ዋስትና ስትሪንግ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሰበሃዲን ሎባ በፕሮግራሙ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን በቅርብ ክትትል እያደረጉ እንሚገኝ ገልፀው በጓሮ ልማት እየመጣ ያለው ለውጥ አበረታች በመሆኑ በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። የወረዳው ምግብ ዋስትና ግብረ ሀይል ሰብሳቢና የግብርና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ርድዋን ሰይድ በወረዳው በ5 ቀበሌ በ755 አባወራዎች 2906 ቤተሰቦች በል/ሴፍትኔት ፕሮግራም ታቅፈው ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሆነ ገልፀው ለወረዳው የተላለፈውን 208,800 ብር  ካፒታል በጀት የቡናና እንሰት ችግኝ እንዲሁም የፓፓያ ዘር ግዢ በመፈፀም ለተጠቃሚዎች መሰራጨቱን ገልፀው ተግባሩ ውጤታማ በማድረግ ተጠቃሚዎች ከድህነት እንዲወጡ ለማድረግ አበክረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
Show all...
2
የስልጤ ዞን ም/አስተዳዳሪና የግብርና መምርያ ኃላፊ አቶ ሙርሰል አማን እና የሚቶ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰበሃዲን ሎባ በሚቶ ወረዳ ግሪንዚላ ጎጊሎ ቀበሌ ነቃላ ክላስተር ላይ 128 ሄ/ር መሬት የበቆሎ ዘር ማስጀመሪያ መርሃ ግብር አደረጉ። ============ ሚቶ፤ ሚያዝያ 28/2016(ሚቶ ወረዳ መንግስት  ኮሙኒኬሽን)ም/አስተዳዳሪ እና የግብርና መምርያ ኃላፊ አቶ ሙርሰል አማን እና የወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰበሃዲን ሎባ በሚቶ ወረዳ ግሪንዚላ ጎጊሎ ቀበሌ ነቃላ ክላስተር ላይ 128 ሄ/ር መሬት የበልግ በቆሎ ዘር  አስጀምረዋል። የሚቶ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና ግብርና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ርድዋን ሰይድ ባደረጉት ገለጻ በወረዳው  4453 ሄ/ር መሬት በበልግ ሰብል ለማልማት ታቅዶ  እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል። ከሚለማው ሰብል ውስጥ በ32 ክላስተር 3260 ሄ/ር በበቆሎ የሚለማ ሲሆን 3093 ሄ/ር በክላስተር የሚለማ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ ዛሬ በግሪንዝላ ጎጊሎ ቀበሌ በነቃላ ክላስተር የተጀመረው የበልግ በቆሎ ዘር 128 ሄ/ር መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ የክላስተር እርሻ በአርሶ አደሩ ላይ የሚደርሰውን የተናጥል ጫና በማስቀረት በጋራ የመልማት አቅም እንዲጎለብት እንደሚያደርግ ተገልጿል። በዘር ማስጀመርያ መርሃ ግብሩ ላይ የስልጤ ዞን ም/አስተዳዳሪና የግብርና መምርያ ኃላፊ አቶ ሙርሰል አማን፣ የሚቶ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰበሃዲን ሎባ ፣ የሚቶ ወረዳ ብልፅግና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ፎሌ ሞሳ፣ የሚቶ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና ግብርና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ርድዋን ሰይድ፣ የስልጤ ዞን ግብርና መምሪያ የእርሻ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሳዲቅ አህመዲን፣ የስልጤ ዞን አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ወሲላ አሰፋን ጨምሮ የወረዳው አስተባባሪዎች፣ አመራሮች እና የግብርና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
Show all...
👍 1 1
ከሰልን ሲጠቀሙ መወሰድ ያለባቸው ጥንቃቄዎች… ሚያዝያ 26/2016 ሚቶ ወረዳ ኮሙኒኬሽን በተለይም በበዓል እና ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ ሲኖር ከሰልን በአማራጭ የኃይል ምንጭነት መጠቀም የተለመደ ተግባር ነው፡፡ በመሆኑም ከሰልን ሰዎች ለተለያየ አገልግሎት ሲጠቀሙ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡ ምክንያቱም አስፈላጊው ጥንቃቄ ካልተደረገ የከሰሉ ጭስ ሞትን ጨምሮ የዕድሜ ልክ ህመም ለሆኑት የአዕምሮ ጉዳትና የልብ በሽታ ስለሚያጋልጥ ነው ይላሉ፡፡ በጉዳዩ ላይ የተካሄዱ ጥናቶች እንደሚያመላክቱትም÷ የከሰል ጭስ በዓይን የማይታይና ሽታ አልባ መርዛማ ጋዝ አለው፡፡ ይህ ጋዝ የሚፈጠረውም ጋዝ፣ ዘይት፣ ከሰል ወይም እንጨት ሙሉ በሙሉ ተቃጥለው ባለማለቃቸው መሆኑ ይጠቀሳል፡፡ የከሰል ጭስ ባለበት አካባቢ አየር ወደ ውስጥ በሚሳብበት ጊዜ÷ በደም ውስጥ በመግባት የቀይ የደም ኅዋስ አካል የሆነውና ኦክስጅን ተሸክሞ ለተያዩ የሰውነት ክፍሎች ከሚያደርሰው ሂሞግሎቢን ጋር በመቀላቀል ጉዳት ያስከትላል፡፡ ይህን ተከትሎም ደም ኦክስጅን መሸከሙን ያቆማል፤ በዚህ የተነሳ የኅዋሶቹ አነስተኛ ክፍሎች ይጎዳሉ፤ ብሎም ይሞታሉ፡፡ •  በከሰል ጭስ (በካርበን ሞኖክሳይድ) የተጠቃ ሰው የሚያሳያቸው ምልክቶች የራስ ምታት፣ ራስ ማዞርና መታመም፣ የድካም ስሜትና ግራ መጋባት፣ ሚዛንን ለመጠበቅ መቸገር፣ የዕይታና የትውስታ ማጣት፣ ራስን መሳት፣ በአንድ ነገር ላይ አትኩሮት ማጣት፣ የሆድ ህመም እንዲሁም ለመተንፈስ መቸገር ምልክቶች ሊታዩበት እንደሚችሉ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡ •  የከሰል ጭስን እንዴት መከላከል ይቻላል? በከሰል ምግብ ማብሰል ሲያስፈልግ በቂ አየር እንዲያገኝ ከተቻለ ከቤት ውጭ ማብሰል፤ ከቤት ውጭ ማብሰል ካልተቻለ ደግሞ ሙሉ በመሉ ከተቀጣጠለና ጭሱ መጥፋቱ ሲረጋገጥ ወደ ቤት ማስገባት ይመከራል፡፡ በተጨማሪም የከሰል ምድጃ እየተጠቀሙ በር እና መስኮት አለመዝጋት፣ በከሰል ምግብ አብስለው ሲጨርሱ በውኃ ማጥፋትና በርና መስኮት በመክፈት ቤቱን ማናፈስ እንዲሁም ከሰል ቤት ውስጥ አለማቀጣጠልን ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡ ከዚህ ባለፈም ከሰል ቤት ውስጥ አቀጣጥሎ ማሸለብ ወይም መተኛት አደጋው የከፋ በመሆኑ ከእነዚህ ድርጊቶች ይቆጠቡ። (ፋና)
Show all...
Go to the archive of posts