en
Feedback
Pomes

Pomes

Open in Telegram

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
7 690
Subscribers
-1324 hours
-137 days
-1330 days
Posts Archive
Pomes
7 690
‼️ህይወቶውን ይቀይሩ🧠🧠 🚘🚘 የታላቁ_ሉሲፈር_የምዝገባ_በኢትዮጵያ 💵💵 "እንዳይሸወዱ በ ኢትዮጵያ ብቸኛ የምዝገባ ማዕከል " *እንኳን ወደ ኢሊሙናትየም የምዝገባ መአከል በደህና መጡ። ☎ +
‼️ህይወቶውን ይቀይሩ🧠🧠 🚘🚘 የታላቁ_ሉሲፈር_የምዝገባ_በኢትዮጵያ 💵💵 "እንዳይሸወዱ በ ኢትዮጵያ ብቸኛ የምዝገባ ማዕከል " *እንኳን ወደ ኢሊሙናትየም የምዝገባ መአከል በደህና መጡ። ☎  +251908282351 📲 0908282351 ተቀላቅላችሁ እንደጨረሳቹህ የሚሰጡ ጥቅሞች 1➡1,000,000 የመጀመሪያ ክፍያ ይከፈልዎታል ETB በየ ስድስት ወሩ 2➡2,000,000 ወርሀዊ ክፍያ ETB 3➡ ተአዋቂ ዝነኛ ዝፍኝ: አልያም አርሱወ የሚፈሉገት የዝና መንደር ይቀላቀላሉ 4➡►ማጂክ ሪንግ ቀለበት 5➡►የእጅ የወርቅ ሰአት 6➡►በመረጠበት ቀን የ 6 ቀን የፓሪስና ግሪክ ጉብኝት 📛►ወደ ቸርቻቺን አባል ያልሆነ ሰው  መምጣት አይቻልም። በዚህ መሥፈርት ተስማመቶ የሚላክለትን ፎርም እንደሞላ የምዝገባ ▬code ይሰጠዋል:: ያንን ቲን ነበር ለመሥዋት አቅራቢዉ በመላክ ክፍያዉን ይከፍላል። ክፍያዉን እንደከፈለም ፎርም በሞላበት የቴሌግራም አካዉንት 1 የባንክ ቡኩን በፎቶ 2 የሂሳብ ቁጥሩን ያንን እንደጨረሰም በ 48 ሰ (2) ቀን ጊዜ ዉስጥ የተመደበለትን የገንዘብ መጠን በ አካዉንቱ ገቢ ይደረጋል። ሌሎች የተቀመጡ ጥቅሞችን በቀጠሮ የሚረከብ ይሆናል። ◆ጥብቅ ማሳሰብያ◆ ▬በየ ሳምንቱ የሚከፈለዉ ገንዘብ የሚጨምረዉ አባሎቺን ወደ ወንድማማቺነቱ ሲቀላቅል ብቻ ይሆናል። # ገቢ የሆነለትን ገንዘብ ከ ባንክ ማውጣትና መጠቀም ይችላል። ከላይ በተጠቀሱት መስፈርቶች የማይስማማ ከሆነ የምዝገባ ፎርሙ አይላክለትም። የሚስማማ ከሆነ ደግሞ የምዝገባ ፎርም በመሙላት ቲን ነበር እስከሚሰጠዉ ይጠብቃል። የታላቁ ሉሲፈር አባል ለመሆን ስለመረጡን እናመሰግናለን። for more info CALL US ፍላጎት ያላችሁ ብቻ ደውሉልን ☎  +251908282351 📲 0908282351📱

Pomes
7 690
አለሁኝ_በደህና (በዕውቀቱ ሥዩም) . አንቺ እንደምን አለሽ … እኔ አለሁ በደህና ይመስገን ዳመና በገበሬው አጥንት – መሬቴን እያረስኩ በገበሬው እንባ – ማሳ እያረሰረስኩ እንጀራ ቢጠፋ – ገበሬ እየጎረስኩ። አለሁኝ በደህና ይመስገን ዳመና . ሰው ሲያፈርስ እያየሁ ሰው ሆኖ ቡልዶዘር አንዱ ጭጋ ነገር ሌላው የብረት ዘር በፈረሰ ሰው ላይ በቆመ ሰገነት ሲዖል አናቱ ላይ በታነፀ ገነት ይኽን ኑሮ ብለው ጥቂቶች ሲኖሩ …ያለምንም ፀፀት …ያለምንም ሃፍረት ይህንን እያየሁ በታላቅ ፅሞና ኣለሁኝ በደህና ይመስገን ዳመና። በምቾት መዲና የነዳያን ትዝብት እንደ ሀሩር ልፎኝ በጠዳ ጎዳና ለማኝ ብላቴና እንደ ጉቶ አንዳቅፎኝ ሃፍረት እንደ ዝናር ከፊት ከኋላ ኣቅፎኝ ልክ እንደ ደባሎች ለመኖር እያቀድሁ በጌቶች መሶብ ላይ እጀን እየሰደድሁ። አለሁኝ በደህና ይመስገን ዳመና . ወይ በሩን አሳዪን ወይ ጠቁሚን መላ መዓበል ሲቃረብ ያመልጣል ሽመላ በነፋስ ገፅ ፊት ይሸሻል ዳመና የኔ ሃዘን ያለበት ያ’ገሬ ሰው ግና በስጋ ደም አጥንት የተሰራ ይመስል እንደ ኮንሶ ሃውልት የመቃብር ምስል አይሸሽ አያባርር ወይ አይተነፍስ ቃል እንጨት ሆኖ ቆሞ ሰደድ ይጠብቃል። . ይህንን እያየሁ ሁኘ በጥሞና አለሁኝ በደህና ይመስገን ዳመና አንቺ ግን አለሽ ወይ እኔ አለሁ በደህና ኣለሁ ግርምት ኖሮኝ ምላሱን በምላጭ እንደተሰለበ ............የማስበው ኖሮኝ .................የምለው ቸግሮኝ @BisotenBepome

Pomes
7 690
:) ለምን ግን ፃፍኩልሽ? ከእጅም አመት ቡኋላ እመጣለው…የዛኔም ግን እንደድሮ ሆኜ አደለም…አንተ ማነህ?…የት ነበርክ?…ትይኝ ይሆናል…እኔም አንገቴን ደፍቼ እምልሽ ነገር ቢኖር…"እያለሁ መች ነበርሽ? ነው። ኖሬ እኮ አውቃለው… አደለም ሰላም እና ደስተኛ ሆኜ አሞኝ እያለም ቢሆን ነበርኩኝ …የት ነሽ?…የት ልምጣ?…ትዝ ብዬሽ አውቃለው? ብዬ ብዙ ጊዜ ጠይቄሽ አውቃለው አደል?…የዛኔ እኮ ዝም ብለሽ ነበር ዝምታሽ ደሞ ያማል… አሁን ላይ ትልቅ ሰው ሆኛለው…በስራዬ ሳይሆን በእድሜ ትልቅ ሰው ሆኛለው…እመጣለው ብዬ ለብዙ ሰው ቀርቻለው…አለሁ እያልኩ ግን እርቄ ነበር…የሰራሁዎቸውን ጥፍቶች እና በደሎች ሳስብ አንገቴን ደፍቼ አምርሬ እራሴን እወቅሳለው…ቢሆንም ግን አሁን ላይ እንደድሮ አደለሁም ለራሴ ራሴ ብቻ ያለሁ ያህል ይስማኛል። ትመጫለሽ ብዬ ብዙ ጊዜ ጠብቄሻለው…ትመጫለሽ ብዬ ያልሆንኩትን ሆኛለው…የእውነት እምትመጪ መስሎኝ ተስፍን ተከትዬ ነበር…ምን ያህል ባንቺ ሰነፍ እንደሆንኩ አንቺ አይገባሽም…ሁሉም ነገር መልካም ይሆናል አደል? እና የእኔ እና የአንቺ ለምን አልሆነም? ወይስ እንዲ መሆኑ ነው መልካም? አሁን እኮ መሽቷል...የጨለመው የእውነት ነው...አሁን እራሴን መፈለግ አለብኝ አንቺን እየፈለገ ልቤ ርቆ ጠፍቶብኛል ውሸታም.፣ሰነፍ፣መጥፎ ሆኜልሻለው... ከመልካም ነገሮች የራቀውን ልቤን መመለስ አለብኝ። ካስደስትኳቸውም ያስከፏሀቸው እጅጉን ይበልጣሉ… (ይቅርታ ጎንበስ ብያለው) እውነት ነው በደሌ ከይቅርታ በላይ ነው …ግን ክርስቶስ የተሰቀለው ለእኛ አይደለ… ፍቅርን እና ይቅርታን ሊያስተምረን …ስለዚህም ይቅርታ… ከበደልሽ በደሌ ይበልጣልና አልወቅስሽም…✨ ☀️መጥፎ ሰዎች የሆነ ቀን ጥሩ ነበሩ…የሆነም ቀን መልሰው ጥሩ ይሆናሉ ! ☀️ ✍🏽 ፊሊሞን የማርያም ልጅ 🌱🍄🌷🎍 @BisotenBepome

Pomes
7 690
ካለፈ በኃሏ ከጊዜው በኃሏ ከረፈደ ወዲህ… እንባ ከደረቀ በዚያው ላይመለስ ፀሀይ ከጠለቀ ካከሸፍኩት ትላንተ በበቀለ ዛሬ አመፃ ነው ማሰብ የሚጣፍጥ ወሬ . . @BisotenBepome

Pomes
7 690
​​..... "ምን ያክል ነው ፍቅርሽ? ብለህ ብጠይቀኝ ❤️❤️ ምን ያክል ልበልህ? ምኑን አውቀዋለሁ፣ እኔ አምላክ አይደለሁ፣ ብቻ ግን... ማንም ጓደኛዋን ከምትወደው በላይ፣ ማንም ፍቅረኛዋን ከምታፈቅረዉ በላይ፣ ውስጤን ገዝተከዋል ቦታ አለህ ልቤ ላይ፡፡ 😍😍😍 ብታምንም ባታምንም፣ እውነቱን ልንገርህ ፍቅሬ አንተን አልዋሽም፣ እስከ ዘላለሙ እኔ አላፈቅርህም፣ እንደ ሞኝ አፍቃሪ የዘላለሜ ነህ ብዬ አልደልልህም፣ ምክንያቱም... ዘላለም የሚኖር ሠው ተፈጥሮ አያውቅም፡፡ አንተም እኔም ሁሉም ማንም ቢሆን ማንም፣ ዘላለም አፍቅሮ ዘላለም አይኖሮም፡፡ ግን... እስከ'ድሜዬ ክልል እስከ ሂወቴ ጫፍ፣ መቼም አይሰለቸኝ አንተና ፍቅርህን አዝያችሁ ብከንፍ፡፡ አፈቅርሃለሁ 💖💖ትላንትም ዛሬም ነገም አስካለው በምድር ፣ከዛም በኋላ ❤️❤️ 👇👇Join👇👇 @BisotenBepome

Pomes
7 690
ቀን 25 አትዋል ከሰው ዋል ከሰው እንዳትለምደው እንዳታጣው እንዳትስመው እንዳትነክሰው @BisotenBepome

Pomes
7 690
​​......ቀድሜክ ከሞትኩኝ...... ውዴ ቃል ልግባልህ፣ በእውነት የማረገው፣ የማስመሰል ሳይሆን፣ ደርሶ የምታየው፣ እኔን ካንተ በፊት፣ ወደሱ ከጠራኝ፡ ውዴ የኔ ፍቅር፣ ቀድሜህ ከሞትኩኝ፣ ሄጄ በሰማዩ፣ ባማረው ስፍራ ላይ፣ በወርቅ ፅፈዋለው፣ ስምክን ኮከብ ላይ፣ ስለምን መሰለክ? ይሄን የማረገው፡ ላንተ ያለኝን ፍቅር፣ መልአክት እንዲያዩ ነው ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ 🌩🌩🌩🌩🌩🌩🌩🌩🌩 @BisotenBepome 😘😘😘😘😘😘😘😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍

Pomes
7 690
‼️ህይወቶውን ይቀይሩ🧠🧠 🚘🚘 የታላቁ_ሉሲፈር_የምዝገባ_በኢትዮጵያ 💵💵 "እንዳይሸወዱ በ ኢትዮጵያ ብቸኛ የምዝገባ ማዕከል " *እንኳን ወደ ኢሊሙናትየም የምዝገባ መአከል በደህና መጡ። ☎ +
‼️ህይወቶውን ይቀይሩ🧠🧠 🚘🚘 የታላቁ_ሉሲፈር_የምዝገባ_በኢትዮጵያ 💵💵 "እንዳይሸወዱ በ ኢትዮጵያ ብቸኛ የምዝገባ ማዕከል " *እንኳን ወደ ኢሊሙናትየም የምዝገባ መአከል በደህና መጡ። ☎  +251908282351 📲 0908282351 ተቀላቅላችሁ እንደጨረሳቹህ የሚሰጡ ጥቅሞች 1➡1,000,000 የመጀመሪያ ክፍያ ይከፈልዎታል ETB በየ ስድስት ወሩ 2➡2,000,000 ወርሀዊ ክፍያ ETB 3➡ ተአዋቂ ዝነኛ ዝፍኝ: አልያም አርሱወ የሚፈሉገት የዝና መንደር ይቀላቀላሉ 4➡►ማጂክ ሪንግ ቀለበት 5➡►የእጅ የወርቅ ሰአት 6➡►በመረጠበት ቀን የ 6 ቀን የፓሪስና ግሪክ ጉብኝት 📛►ወደ ቸርቻቺን አባል ያልሆነ ሰው  መምጣት አይቻልም። በዚህ መሥፈርት ተስማመቶ የሚላክለትን ፎርም እንደሞላ የምዝገባ ▬code ይሰጠዋል:: ያንን ቲን ነበር ለመሥዋት አቅራቢዉ በመላክ ክፍያዉን ይከፍላል። ክፍያዉን እንደከፈለም ፎርም በሞላበት የቴሌግራም አካዉንት 1 የባንክ ቡኩን በፎቶ 2 የሂሳብ ቁጥሩን ያንን እንደጨረሰም በ 48 ሰ (2) ቀን ጊዜ ዉስጥ የተመደበለትን የገንዘብ መጠን በ አካዉንቱ ገቢ ይደረጋል። ሌሎች የተቀመጡ ጥቅሞችን በቀጠሮ የሚረከብ ይሆናል። ◆ጥብቅ ማሳሰብያ◆ ▬በየ ሳምንቱ የሚከፈለዉ ገንዘብ የሚጨምረዉ አባሎቺን ወደ ወንድማማቺነቱ ሲቀላቅል ብቻ ይሆናል። # ገቢ የሆነለትን ገንዘብ ከ ባንክ ማውጣትና መጠቀም ይችላል። ከላይ በተጠቀሱት መስፈርቶች የማይስማማ ከሆነ የምዝገባ ፎርሙ አይላክለትም። የሚስማማ ከሆነ ደግሞ የምዝገባ ፎርም በመሙላት ቲን ነበር እስከሚሰጠዉ ይጠብቃል። የታላቁ ሉሲፈር አባል ለመሆን ስለመረጡን እናመሰግናለን። for more info CALL US ፍላጎት ያላችሁ ብቻ ደውሉልን ☎  +251908282351 📲 0908282351

Pomes
7 690

Pomes
7 690
+1
KUNG FU PANDA~1 0989817531.avi900.18 MB

Pomes
7 690
ዘመም ይላል እንጂ! በእውቀቱ ሥዩም አዳምኤል ( ገፅ 34) ======//====== . እንደ ጊዜው መክፋት እንደ ግፉ መስፋት እንዳገሩ ክስመት እንዳገሬው ጥመት እንደሰው ጭካኔ፤ እንደ ልቡ ፍሬ ታምር ነው መትረፍሽ ፤ ታምር ነው መኖሬ። . የበጎ ሰው ሀሳብ ፤ ሲካድ እለት በለት ጉድጓድ ተምሶለት ሰብእና ሲቀበር፤ በዚህ ምድር መኖር ፤ አያስመኝም ነበር። . ምድሩ ሳር ቅጠሉ፤ በስጋት ተሞልቶ የማለዳው ሰማይ፤ እንዳንቀልባ ቀልቶ ታረደ ነደደ ከዘብጥያ ወጥቶ ዘብጥያ ወረደ የሚል ዜና ብቻ አየሩን ሲሞላው ሰው በገዛ ጥላው በርግጎ ሲሸበር በዚህ ምድር መኖር፤ አያስመኝም ነበር። . አዎ! ለጊዜውም ቢሆን፤ ግፍ ያደነዝዛል በደል ያስተክዛል ጊዜም ጠብን ሽሮ፤ ወደ ፊት ይጓዛል በልብ ሰሌዳ ላይ ፤ ቂም ይደበዝዛል በነገ ያመነ ልጁን ቀብሮ መጥቶ፤ ሚስቱን ያስረግዛል። ይቅርታና ምህረት ፍቅርና ህብረት ከግፍ ጋር ፍልሚያቸው ፤ ቢሆን የሞት ሽረት ዳገት ይወጣሉ ፤ በንጥፍጣፊ አቅም የመኖር ፍላጎት ዘመም ይላል እንጂ፤ ተገርስሶ አይወድቅም።

Pomes
7 690
አይን'ክን ምን ሰበረው? ከጥዋት ፀሀይ ይልቅ ሲያበራ ማደንቀው ከሁሉ አካላትህ አብልጬ ምወደው ታይቼ አይቼው በፍፁም ማልጠግበው ተፈቃሪ ዓይንህን ዛሬስ ምን ሰበረው? ምነው ምን ነካብኝ ብርሃኑ ጨለመ የፍቅር ፍንጣቂው ጨረሩ ለጎመ የመውደድ ስለቱ ጫፉ ዶለዶመ ውዴ ምነው ዓይንህ አንገቱ ተደፋ በድንገት ታውሮ ልሳኑ ተሰፋ ምነው እንደሌባ ዓይንህ ከዓይኔ ራቀ ነጠላ አዘቅዝቆ እቃ እንደጠፋበት መሬቱን ፏቀቀ እንደሁሌ ዓይንህን አተኩሬ ሳየው ከዓይኖቼ ይልቅ መሬቱ እንዴት ሳበው? የምር ጎትቶህ ነው የመሬቱ ስበት ወይስ ከኔው ዓይን ከህሊና ሽሽት? መአዛ ጥበቡ🌓

Pomes
7 690
ጥሬ ጨው (ደበበ ሰይፉ) . መስለውኝ ነበረ የበቁ የነቁ ያወቁ የረቀቁ የሰው ፍጡሮች ለካ እነርሱ ናቸው ጥሬ ጨው...ጥሬ ጨው ጥሬ ጨዋዎች መፈጨት - መሰለቅ - መደለዝ - መወቀጥ መታሸት - መቀየጥ ገና እሚቀራቸው “እኔ የለኹበትም!” ዘወትር ቋንቋቸው።

Pomes
7 690
(ሔለን ፋንታሁን) ... *እልቅስ* ጣሪያ ሽንቁር ሠማይ በጠብታ ልኩ መርጠብን የሚያሳይ በሠማይ ቀዳዳ ያምላክ ዕንባ ሲወርድ እኔ አቅቶኝ ነበር ሰቀቀኑን መልመድ . ስለዚህ ተሸሸኩ ቤቴ ባልኩት መሸኩ ግና ... ያዘልቀኛል ያልኩት ላይከርም አረጀ ሠማይ ያልኩት ጣሪያ ሽንቁሩን አበጀ ጠ ብ . . . ጠብ . . . ጠብ ይላል በሽንቁር ከጣሪያው ሠማይ ስር . ራስ አልኩኝ ዕንባው ተጋባብኝ . እ ል ቅ ስ የተጠማን ላርስ .......//.......

Pomes
7 690
*ምንም አልል * (ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን) እሺ እንግዲህ በዝምታ የልቤን ደም ሥር ትርታ በደቂቃ ዕድሜን ትዝታ ትር ስትል አፍታ ለአፍታ እያዳመጥኩ እያስታመምኩ ጊዜዬን እያሰላሰልኩ ሳልናገር ሳልጋገር፤ እየደገምኩ እያሰለሰልኩ ሰልሰለች እየመላለስኩ .......... እሺ እንግዲህ በጸጥታ የልቤን ደም ሥር ትርታ የእስትንፋሴን ቃል ጉምጉምታ ትር ስትል አፍታ ለአፍታ ሳልሰለቸ እየደጋገምኩ በእግረ ሕልና እያደቀቅኩ እየቋጠርኩ እየቆጠርኩ እሺ እንግዲህ አልናገርም በአንደበቴ አልተነፍስም በልሳኔ አልመሰክርም አልልም፡፡ ምንም አልልም እንዲያው ዝም እንጂ ዝም ዝም ............ የልቤ ደም ሥር ሲያቃጭል ልሳኔን ሲያስነሳ ሲያስጥል ቃላቴን ሲቃኝ ሲያጋግል ትንፋሼን ሲያንር ሲያደውል ክል ሲል ትር ድም ሲል ማዳመጥ ማስታመም እንጅ ፤ ሌላ ምንም ምንም አልል

Pomes
7 690
★★★ነበር★★★ እወድሽ ነበረ? ነበር አትበለኝ በነዚህ ቃላት ዉስጥ ፍቅሬን የሚያሽሙዋጥጥ፣ ተስፋዬን ሚነጥቅ ታሪክ ነዉ ሚታየኝ፡፡ እባክህ አለሜ "ነበር" አትበለኝ በ ነ..በ..ር ቃላት ዉስጥ ፍቅሬን ምትሸሽበት፣ ፍቅርህን ምትክድበት፣ "በ..ር" ነው ሚታየኝ እንዲ ስለምንህ ልመናዬን ትተህ ቃሉን ከቀጠልከው የኔም ቃል ከጊዜያት ኃላ ቀመሩን ይለቃል እወድሀለሁ ቀርቶ እወድህ ነበር በሚለዉ ይተካል ነገር ግን "ነበር" በሚለው ቃል ላንተ ያለኝ ፍቅር ሞቶ ይቀበራል:: ★★★★★★★★★★★★★★ ✍meli

Pomes
7 690
😭በሞቴ በካስከኝ😢 ጥፋልኝ ከህልሜ ደግመህ አትምጣ ባይኔ ውጣ ከህሊናዬ ልረፍ ባንድ ጎኔ ቅርብኝ ልቅርብህ ደግሜ አላስታውስህ ......አልብ...ሰል...ሰል..ልህ እባክህ አስጠላኝ ቋቅ በለኝ አቅረኝ ያለፈውን ልርሳ ምንም ትዝ አትበለኝ መንገዱንም ተወው ላንዴ በጀ በለኝ በጎዳናው አልይህ እባክህ ጥፋብኝ ከአይኔ እራቅብኝ ኮለል ብለህ ጨሰህ ብን ብለህ ጥፋልኝ ብዬ ልል እልና.... መልሼ ፈራለሁ... ደግሞ ብትናፍቀኝ እንዴት እሆናለሁ? ግን ደሞ እጎዳለሁ አሁን በቀደም ለት ቀኑ በመሸበት ፀሀይዋ በቤቷ በጠለቀችበት ብርዱ ጓዙን ይዞ በተሰናዳበት ሰማዩ ተቀዶ ሆዱን ባሳየበት ዶፉ አፋፍሞት ልጁ ውሽንፍርን ባማማጠበት በነጎድጓዱ ድምፅ ጀማው ተርበትብቶ በተሯሯጠበት አኔ ግን ቆሜያለው ህይወት አጥቻለው ልቤ ተሠንጥቆ አቅሌን ስቻለው ደሜ ብቻ አይደለም እኔም ቀዝቅዣለው ለምን እንዳትለኝ አንተን አይቼ ነው የጀማው ጫጫታ የላዩ ብልጭታ ፣የባጃጁ ክላክስ ይህ ሁሉ ምኔም ነው በቃ ደንዝዣለው ምነው ባየህልኝ እነደዚ መሆኔን ወይ ደሞ ባሳዩህ ባንተ መደንዘዜን ላንተ መዋተቴን በየአውራ ጎዳናው አይንህን አንዳየው ደርቄ መቅረቴን አልያም እንዲ አሰብኩ ... ከፊቴ የመጣው የመኪናው ሹፌር በክላክሱ ጩኸት ህዝቡን ከሚያሸብር፣ ምናለ በገጨኝ ደሜን አንቆርቁሮ አጥንቴን በፈጨኝ ምናልባት አይተኸኝ ምነው ባሳዘንኩህ በተቆጨህልኝ ምነው ባስለቀስኩህ የእምባዎቼን ብድር በሞቴ በካስከኝ (ቆሎ በር ያየውህ እለት) ለ Ab ★ ከ ✍የአብሥራ 2012

Pomes
7 690
ያላንቺ ያላንቺ እንዴት ይኖራል አለ ገጣሚው በብዕሩ እየማለ ያላንቺስ እንዴት ይዘለቃል የህይወት ጥዕሟም ያልቃል የአለም ሕዝብ ሁሉ ቢስቅ ያንቺ ሳቅ ግን ከዳመነ ይቺ አለም ምን ሩህ አላት ተስፋዋ ሁሉ መነመነ ስትስቂ ነው የአ'ለም ደስታ አንቺ ካለሽ ነው መኖሯ በምፀት ዐይን እንዲያዩሽ አትፈቅድም ቀየው ከ'አድባሯ ስለዚህ... ስለ....ዚህ እምዬ ደስ ብሎሽ ኑሪ እንደ'ሀሳብሽ ተበሳጭተሽ አታማሪ በኋለኞች ሀሳብ ከኋላ እንዳትቀሪ ‼️ ሁኚ ፊት አውራሪ 👉የስኬት ፣ 👉 የፅናት 👉የነፃነት መሪ 🏃‍♀

Pomes
7 690
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷 😒ጊዜ ነው ጠላቴ😒 ጊዜ ነው ጠላቴ ጊዜ ነው ያስተከዘኝ ከምወደው ሸጋ ጊዜ ነው የነጠለኝ ምን ብዬ ልግለፀው በምን ቃል ጋጋታ ልቤ እንደታመመ አጣሁለት አንድ የቃል ገበታ በሡ ናፍቆት ብቻ አሞኛል ከሡ ጋራ ካልሆንኩ ሞቴ ይናፍቀኛል ካለሡ ለአንድ አፍታ ማሠብ ተስኖኛል የጊዜን እጅ ይዤ ወደ ኋላ ብመልሠው ለሡ ያለኝን ፍቅር በደንብ ቢረዳው ጊዜ የማይሽረው ፍቅር ለሡ ብቻ እንዳለኝ አይን አይኑን እያየው ነግሬው ቢረዳኝ ምናል በሁኔ እንኳን ቀርቶ በህልሜ ባላጣው 💘💘💘💘💘💘💘💘💘💘💘💘 📝@cituye💌 🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋 🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀

Pomes
7 690
😢😢😢😢 ነይ በክረምት ዝናብ ብርድ በበዛበት ነይ የዛኔ ቤቱ በሞላበት ናፍቆት በጫረበት ቶሎ ብለሽ ነይ የኔ አማላይ ግን ... ግንስ ናፍቆትሽን ጥለሽ ሲመጣ በጋው ያኔ ትሄጃለሽ የዛኔ ካንች ምን ፈልጋለሁ አሟቂ እንዳልል ... የፀሃዩ ንዳድ አይሎ አቃጥሎ አንድዶ አማሮ አይደል ያንች ተጨምሮ ... ብቻ እሱን ተይው ነይልኝ ቶሎ ብርዱን እንርሳው እንብላ በቆሎ😂😂😂 ✍ተጻፈ:- ትሁት MAYTES❤️