cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ጠብታ

የጣናም ጠብታ ዓባይን ይሞላል 💧 ☔️

Show more
Advertising posts
235
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ዊንስተን ቸርችል
Show all...
Sheger_FM_Mekoya_Winston_Churchill_መቆያ_ዊንስተን_ቸርችል_የጭንቅ_ቀን_ሰው_በእሸቴ.m4a18.84 MB
የደስተኝነት ምስጢሮች ደስተኝነት እንዲያው በዘፈቀደና እንደ አጋጣሚ ሳይሆን በፍላጎት ወይም ደስተኛ መሆንን በመምረጥ እንዲሁም ደስተኛ ለመሆን በመዘጋጀት ሊገኝ የሚችል በጎ ስሜት ነው፡፡    ደስተኝነትን ለማዳበር የሚረዱ አምስት        ምስጢራት 👉 ተስፈኝነት ፦ ተስፈኛ ሰዎች በብርጭቆ ውስጥ በከፊል የሞላን "ውሀ ግማሽ ሙሉ " ብለው ሲጠሩት ተስፈኛ ያልሆኑት ፀለምተኞች "ግማሽ ጎዶሎ" ይሉታል፡፡ ተስፈኞች ህልማቸው ሊሳካ የሚችለው አዎንታዊውን የአስተሳሰብ መንገድ በመከተል እንደሆነ ያውቃሉ፡፡ ተስፈኝነት የአዎንታዊ አስተሳሰብ ትሩፋት ሲሆን የደስተኝነትም ዋነኛ ግብአት ነው፡፡ 👉  ትህትና ፦ ደስተኛ ሰዎች ለራሳቸውም ሆነ ለሌሎች ትሁትና አዛኝ መሆንን ይመርጣሉ። ራሳቸውንም ሆነ ሌሎችን የሚያስተናግዱበት መንገድ ለሚሰማቸው ስሜትና በአጠቃላይም የማንነታቸው መገለጫ መሰረት እንደሆነ ይገነዘባሉ። 👉 ይቅር ባይነት ፦ ደስተኛ ሰዎች የጎዷቸው ሰዎች ላይ እንኩዋን ቢሆን የቂም እና የበቀል ስሜቶችን በውስጣቸው አምቀው ማቆየት የሚቻላቸው አይደሉም። በሰዎች ማህበራዊ ግንኙነት ውስጥ የሚያበሳጭ ፣ የሚያስቀይም እና የሚያስከፋ ፀባይ ጠፍቶ የማያውቅ ቢሆንም ደስተኞችን ልዩ የሚያደርጋቸው ባህሪይ ግን በእንዲህ ያለው ስብእና መጠለፍ ፈፅሞ የማይፈቅዱ መሆናቸው ነው። ደስተኞች በሌላው ፀባይ ላይ ከመፍረድ ይልቅ ሀዘኔታ የሚሰማቸው ናቸው። 👉 በፀጋ መቀበል ፦ ደስተኛ ሰዎች መቆጣጠር የሚችሉትንና የማይችሉትን ጠንቅቀው ያውቃሉ። ደስተኛ ያልሆኑ ሰዎች ግን ሁሉንም ሰው ወይም ሁኔታ ለመለወጥ ሁልጊዜ ጥረት እንዳደረጉ ናቸው። በዚህ የተነሳ ዘወትር ምቾት የማጣት ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል። ደስተኞች ግን በምንም አይነት ሁኔታ ሁሉንም ነገር መቆጣጠር እንደማይችሉ ፣ እንደማያስፈልጋቸው ጭምር ስለሚረዱ መላ ትኩረታቸውን መቆጣጠር በሚችሉት ነገር ላይ ያሳርፋሉ። 👉 አመስጋኝነት ፦ ደስተኛ ሰዎች የሌሏቸውን ነገሮች በማሰብ ምሬት ውስጥ የሚገቡ ሳይሆኑ ስላላቸው ነገር የሚያመሰግኑ ናቸው። መስማት ፣ መናገር ፣ ማየት ወይም መራመድ ያልታደሉት እንኳን በርካቶቹ ደስተኞች የሚሆኑበት ምስጢር ትኩረታቸውን ባጡት ነገር ላይ ሳይሆን ባሏቸው ነገሮች ላይ ማድረግ መቻላቸው ነው። ምንጭ ፦ ስድስተኛው ስሜት ትርጉም ፦ ፍቅሩ በለጠ #ጠብታ
Show all...
-----ነገም ትላንት ነው------ ተመኘሁ ነገን ፤ትላንትን አልፌ ፤ ዛሬን እየኖርኩኝ ነገን ተመኘሁኝ ትላንትን አልፌ ነገን ተመኘሁኝ! ነገን ተመኘሁኝ! ነገን ተመኘሆት ያቺኛዋ ነገ ፤ዛሬ ተብላ ዛሬ እኖራት ጀመረ ዛሬን አሳልፌ፡፡እንሆ ዛሬ       11/05/2015 ዓ/ም ገጣሚ፡- ....
Show all...
...እችላለው ... አልገባኝም እንጂ ነገር ውሀ ቀጂ እችላለዉ እችላለው ነገዬን በዛሬ አሳምራለው ነገ ላይ ሆኟ ነገ ዛሬ ነው🙄 12/05/2015 ገጣሚ:-ጨለፍ
Show all...
-----ነገም ትላንት ነው------ ተመኘሁ ነገን ፤ትላንትን አልፌ ፤ ዛሬን እየኖርኩኝ ነገን ተመኘሁኝ ትላንትን አልፌ ነገን ተመኘሁኝ! ነገን ተመኘሁኝ! ነገን ተመኘሆት ያቺኛዋ ነገ ፤ዛሬ ተብላ ዛሬ እኖራት ጀመረ ዛሬን አሳልፌ፡፡እንሆ ዛሬ 11/05/2015 ዓ/ም ገጣሚ፡- ....
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
Plss join anda add mameberes
Show all...
Check out afeter you salfe: https://t.me/+Wjnhv2eV1Yo1MzVk
Show all...
afeter you salfe

Ke polatica enda emnate nake wechi y Selamenme aweru tachawetu tasenanu taganaganu Fata balu Afetr you salfe yetachegaruten asebe Ganzabe masetete bachel arife genzaba sete ያንተን ያንቺን የናንተን ያኛን የ ድጋፍ የፈልጋሉና afetr you salfe alahulachu enbalachawe

ዐጼ ዮሀንስ አራተኛ፣ ከንጉሥ ተክለሃይማኖት ጋር ተጣልቶ ጎጃምን በደበደበበት ወቅት ባላገሮች እግዜር በደላቸውን አይቶ እንደሚበቀልላቸው ጠብቀው ነበር። ግን ለጊዜው በንጉሠ ነገሥቱ ላይ የወረደ መብረቅ አልነበረም። አንዲት ተበዳይ ሴት ይህ ጉዳይ የእግዜርን _ ህልውና እንድትጠራጠር ስሳደረጋት እንዲህ ብላ አንጎራጎረች። “ከሀበሻ ወዲህ! ከሀበሻ ወድያ ሰውንም ገረመው፤ እኔንም ገረመኝ ዮሀንስ እግዜርን፤ ገድሎታል መሰለኝ።” “እግዜርን ገድለነዋል” በሚል መርዶው የሚታወቀው ፈላስፋ ፍሬድሪክ ኒቼ ነው። ይህ ሪዛም ጀርመኔ - ሴቶች ከማርገዝና ከመውለድ በቀር የረባ የአእምሮ ፍሬ አያበረክቱም የሚል እምነት ነበረው። እምነቱ የተሳሳተ መሆኑን ለመረዳት እሱ ያነበበውን ያክል ሳታነብ በሦስት ስንኝ መስመር እሱ የደረሰበት ያስተሳሰብ ጥግ ላይ መድረስ የቻለች ይህች ባላገር ሴት ምስክር ናት። ከበእዉቀቱ ሥዩም https://t.me/tebitateb
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ህይወት ያላቸው ሮቦቶች ተሰሩ የሳይንሱ ዓለም በየእለቱ አዳዲስ ግኝቶችን እያሰማን ሲሆን፤ አሁን ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊራቡ የሚችሉ ሕይወት ያላቸው ሮቦቶችን መፍጠር መቻሉን አሰምቶናል። ሊራቡ ይችላሉ የተባሉት ሮቦቶቹ “ዜኖቦትስ” የሚል መጠሪያ ያላቸው ሲሆን፤ ተመራማሪዎች ህይወት ካሏቸው ህዋሶች እንደሰሯቸው ተነግሯል። አዲስ የተሰሩት “ዜኖቦትስ” ሮቦቶች ልክ እንደሌሎች ሮቦቶች የተሰጣቸውን ተልእኮ በአግባቡ የሚፈጽሙ ናቸው የተባለ ሲሆን፤ ከሌሎች ለየት የሚያደርጋቸው ደግሞ መራባት መቻላቸው ነው። ሆኖም ግን “ዜኖቦትስ” ሮቦቶች የሚራቡበት መንገድ ሌሎች ህይወት ያላቸው ፍጥረታት ከሚራቡበት መንገድ የተለየ እንደሆነም ነው ተመራማሪዎች ያስተወቁት። ዜኖቦት ሮቦቶች ጥፍር ካላቸው የአፍሪካ እንቁራሪት ሽሎች የተገኙ የቆዳ ሴሎችንና የልብ ጡንቻ ሴሎች በመቀላቀል እንደተፈጠሩ ተመራማሪዎች አስታውቀዋል። ዕቃዎችን መሸከም እና መግፋት የመሳሰሉ ተግባራትን ያሉ ተግባራትን እንዲከውኑ ታስበው የተሰሩት ሮቦቶቹ በኋላ ላይ ግን ራሳቸውን ማባዛት ሁሉ እንደሚችሉ ለማወቅ ተችሏል። ሮቦቶቹ ራሳቸውን የሚያበዙት ሌሎች ህይወት ያላቸው እንቁራሪቶች በሚራቡበት መንገድ ሳይሆን “ኪነማቲክ” በተባለ የማባዛት ስርዓት እንደሆነም ተመላክቷል። “ኪነማቲክ” በተባለ የማባዛት ስርዓት የሚፈጠሩት ዜኖቦት ሮቦቶች በሕይወት ቆይተው እና አድገው ልክ እንደ ሌሎች ሮቦቶች ስራ እንዲከውን የሚያስችል ምርምር እየተካሄደ መሆኑንም ተመራማሪዎች አስታውቀዋል።
Show all...